በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

Public Relation

አንድ መቶ ሃያ አዳዲስ አማንያን በብፁዕ አቡነ ገሪማ ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አገኙ!

ኤክቱስ ጥር 11/2018 ዓ.ም በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት በዲላ ከተማ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል ዕለት አንድ መቶ ሃያ አዳዲስ አማንያን በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል። በዕለቱ ከአንድ መቶ ሃያ ተጠማቂያን መካከል አንድ መቶ አስሩ ኢ-አማንያን ሲሆኑ አስሩ ደግሞ ሕጻናት መሆናቸው ተገልጿል።

አንድ መቶ ሃያ አዳዲስ አማንያን በብፁዕ አቡነ ገሪማ ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አገኙ! Read More »

ታቦታት ከባሕረ ጥምቀት ወደ አብያተ ክርስቲያናት ጉዞ አደረጉ!

አክቱስ ጥር 11/2018 ዓ.ም በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት በዲላ ከተማ የጥምቀት በዓል አራት አብያተ ክርስቲያናት ማለትም የመዝገበ ምሕረት ቅድስት ልደታ ለማርያም፣ የዳግማዊት ጌቴሴማኒ በዓታ ለማርያም፣ ጎላ ቅዱስ ራጉኤል እና የዲላ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል አብያተ ክርስቲያናት ታቦታት ከባሕረ ጥምቀት ወደ አብያተ ክርስቲያናት ጉዞ አድርገዋል።

ታቦታት ከባሕረ ጥምቀት ወደ አብያተ ክርስቲያናት ጉዞ አደረጉ! Read More »

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበት ዓመታዊ የጥምቀት በዓል በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላ ከተማ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል!

ኤክቱስ ጥር 11/2018 ዓ.ም

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበት ዓመታዊ የጥምቀት በዓል በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላ ከተማ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል! Read More »

ተጠምቀ ሰማያዊ በዕደ መሬታዊጥምቀት ከሰባቱ  ምሥጢራተ  ቤተክርስቲያን  አንዱ ነው፡፡

  የምሥጢረ ጥምቀት መሥራች ራሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ሲሆን በአገልጋዩ በቅዱስ ዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ በፍጹም ትህትና ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ይህንንም ያደረገልን አብነት ሊሆነን ነው። ምክንያቱም ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን “መጥተህ አጥምቀኝ” ብሎት ቢሆን ኖሮ ነገ ነገሥታቱና መኳንንቱ ካህናቱን “መጥታችሁ አጥምቁን” ባሉ ነበር። ስለዚህ እንዲህ እንዳይሆን ነው ጌታችን “ጌታ” ሲሆን በባሪያዬ እጅ እንደተጠመቅሁ እናንተም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዳችሁ በካህናት እጅ ተጠመቁ ሲል ነው።  ቅደስ ዮሐንስ ጌታችን በእርሱ እጅ ለመጠመቅ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ “እኔ ባሪያህ በአንተ በጌታዬ እጅ ልጠመቅ ያስፈልገኛል እንጂ አንተ በእኔ በባሪያህ እጅ ትጠመቅ ዘንድ እንዴት ወደ እኔ ትመጣለህ?” አለው። ጌታችንም መልሶ “አሁንስ ፍቀድልኝ፣ እንግዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና /ትንቢተ ነቢያትን እንዲህ ልንፈጽም ያስፈልጋል/” አለው። በዚህን ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን አጠመቀው። በዚህም “መጥምቀ መለኮት” ተብሎ የቅዱስ ዮሐንስ ገናንነቱ ይነገራል፣ ጌታችንም በባሪያው እጅ በመጠመቁ ፍጹም ትህትናው ይነገርለታል።መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በኃጢአት የተዳደፉት ሁሉ ንስሐ ገብተው የተዘጋጀላቸውን መንግሥት ወራሾች ይሆኑ ዘንድ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” እያለ ሲሰብክ ነበር። ይህ “መንግሥተ ሰማያት በልጅነት፤ ልጅነት ደግሞ በሃይማኖት ልትሰጥ ቀርባለችና ከኃጢአት ተለይታችሁ፣ ከበደል ርቃችሁ ቅረቡ” ማለት ነው። በነቢያት እንደተነገረውም “ የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ፣ ጥርጊያውንም አቅኑ” እያለ ድምጹን አሰምቶ ሰብኳል። ምሥጢሩንም በመጣ ጊዜ ተራራውና ኮረበታው ተንዶ፣ ጎድጓዳው ተመልቶ፣ ሥሩ ተነቅሎ፣ ደንጊያው ተለቅሞ ለፈረስ ለሰረገላ እንዲመች ተደልድሎ እንደሚቆይ ሁሉ እናንተም የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ሰውነታችሁን ከኃጢአታችሁ ንጹሕ አድርጋችሁ ጠብቁ ማለት ነው።  ቅዱስ ዮሐንስ ከንስሐው ስብከት በተጨማሪም ዘመን የማይቆጠርለት ሲሆን ሥጋን በመለበሱ ዘመን ተቆጥሮለት ከእርሱ በኋላ ስድስት ወር ዘግይቶ ስለሚመጣው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነትም ሰብኳል፦ “እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል። እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤ መንሹም በእጁ ነው። አውድማውንም ስንዴውንም በጎተረው ይከታል፤ ፈጽሞ ያጠራል፤ ሰንዴወንም በጎተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል። /ማቴ 3፡11፤ ዮሐ 1፡26/ ጥምቀት በምሥጢረ ሥላሴና በምሥጢረ ሥጋዌ አምኖ ለሚፈጽመው ሰው ሁሉ ለኃጢአት መደምሰሻ ከሥላሴ የጸጋ ልጅነት ለመቀበልና የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ የተሰጠ ልዩ የሕይወት መንገድ ነው፡፡ ጥምቀት በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋኒያ በግእዝ አስተርዮ በአማርኛ መገለጥ ይባላል፡፡ ቃሉ በቀጥታ ሲተረጎም በውኃ ውስጥ ገብቶ መውጣት፣ መነከር፣ መዘፈቅ፣ መጥለቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ለምን ተጠመቀ? የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ አዳምና ሔዋን ፍዳው በፀናባቸው መከራው በበዛባቸው ጊዜ የሚያቃልልላቸው መስሏቸው ዲያብሎሰ ስመ ግብርናችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ ባላቸው ጊዜ አዳም ገብሩ ለዲያቢሎስ (አዳም የዲያብሎስ የወንድ አገልጋይ) ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ (ሔዋን የዲያብሎስ ሴት አገልጋይ) ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ዲያብሎስም ይህንን ደብዳቤ አንዱን በሲኦል አንዱን በዮርዳኖስ አስቀመጠው፡፡ በዮርዳኖስ ያስቀመጠውን ጌታችን ሲጠመቅ እንደሰውነቱ ረግጦ ደምስሶታል፡፡ ይህንን ጽሕፈት ለመደምሰስ ነው ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው” ያለው /ቆላ 2፥14/፡፡ ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ የላይኛው ሸሽቶ ወደ ላይ ተመልሶ ሽቅብ ፈሷል፡፡ የታቹም ወደ ታች ሸሽቷል፡፡ የላይኛው ፈሳሽ ተቋርጦ እንደ ክምር ተቆልሎ ቀርቷል።ቅዱስ ዳዊት የተመለከተውም ይህንኑ ነው። ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ቤዛነት ተቋርጦ ፤ የታቹም ፈጽሞ መድረቁ ኃጢአተ አዳም የመጥፋቱ ምሳሌ ነው፡፡ እስራኤል ፈለገ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ኢያሪኮ መሔዳቸው ምእመናን በጥምቀት ከኃጢአት ቍራኝነት ተላቀው እግራቸውን ወደ ልምላሜ ገነት ወደ ዕረፍት መንግሥተ ሰማያት አቅንተው ለመሔዳቸው ምሳሌ ነው፡፡ ኢያሱ የጌታ፣ እስራኤል የምእመናን፣ ዮርዳኖስ የጥምቀት፣ ምድረ ርስት የገነት መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው፡፡ ምስጢረ ሥላሴን ለመግለጥ ጌታችን በፈለገ ዮርዳኖስ ሲጠመቅ ምስጢረ ሥላሴ ግልጽ ሆኗል፡፡ አብ በደመና “የምወደው የምወልደው ልጄ ይህ ነው” በማለቱ አብ የወልድ አባት መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ ሕይወቱ መሆኑን ሲያስረዳ በአምሳለ ርግብ በራሱ ላይ ተቀመጠ ወልድም በተለየ አካሉ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ ታየ፡፡ ስለዚህ ምሥጢርን ለመግለጥ ስንል የአንድነት የሦስትነት ምስጢር በጐላ ሁኔታ እንዲታወቅ ተጠመቀ ማለት ነው፡፡ /ማቴ. 3፥16/ ትንቢቱን ለመፈጸምአቤቱ ውሆች አዩህ፣ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ ውሆችም ጮኹ፡፡” ተብሎ በቅዱስ ዳዊት የተነገረውን ትንቢት ለመፈጸም ተጠመቀ /መዝ 77፥16/፡፡              ወስብሐት ለእግዚአብሔር           ሊቀትጉሃን ቀሲስ ሀብታሙ አበበ      የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ

ተጠምቀ ሰማያዊ በዕደ መሬታዊጥምቀት ከሰባቱ  ምሥጢራተ  ቤተክርስቲያን  አንዱ ነው፡፡ Read More »

የበዓለ ጥምቀት የከተራ በዓል በዲላ ከተማ ብፁዕነታቸው በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ!!

ኤክቱስ ጥር 10/2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያ ሁልጊዜ ከበዓለ ጥምቀት አንድ ቀን አስቀድሞ የሚከበረው እና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መውረዱ የሚያሰስብበት በዓል በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት በዲላ ከተማ በታላቅ ድምቀት ተከብሯል። በዕለቱ ታቦታቱ ከአድባራቱ ተነስተው በካህናትና በበርካታ ምዕመናን ታጅበው ወደ ጥምቀተ ባሕር ጉዞ አድርገዋል። በበዓሉ የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በዶክተር መስፍን ደምሴ ጋባዥነት የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ዝናቡ ወልዴ በበዓሉ ተገኝተው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ንግግር ያደረጉ ሲሆን በዕለቱ በዓሉ በልዩ ሁኔታ እንዲከበር አስተዋጽዖ ላደረጉ አካላትና በዓሉን ከሚመሩት ሕዝብ ጋር በጋራ ለማክበር ለመጡ የመንግሥት አካላት ምሥጋና አቅርበው በጸሎት ፈጽመዋል። በዕለቱ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ፣ የጌዴኦ ዞን እና የዲላ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣ የወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጠበብት መሪጌታ መሰረት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በርካታ ካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን ተገኝተዋል። “ወአሜሃ መጽአ እግዚእ ኢየሱስ እምገሊላ ውስተ ዮርዳኖስ ከመ ይጠመቅ እምዮሐንስ – ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ” ማቴ ፫፥፲፫

የበዓለ ጥምቀት የከተራ በዓል በዲላ ከተማ ብፁዕነታቸው በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ!! Read More »

In the Name of the Father, and of the Son, and of the Holy Spirit, One God. Amen.

To our beloved children in the Holy Spirit, the faithful throughout our Diocese, across our nation, and in the Diaspora;May the peace of the Lord be with you as we celebrate the Glorious Feast of the Epiphany. We congratulate you on reaching this great public festival, commemorating the baptism of our Lord and Savior Jesus Christ in the River Jordan by the hand of John, for the sake of the salvation of the entire world. “ርእዩከ ማያት እግዚኦ ርእዩከ ማያት ወፈርሁ ደንገፁ ቀላያተ ማያት ወድምጸ ማያቲሆሙ”“The waters saw Thee, O Lord, the waters saw Thee and were afraid; the depths also were troubled. The waters poured out a sound.” (Psalm 77:16 / 76:16) This prophetic utterance of the Holy Prophet David describes the awe of creation as it recognized its Creator. When our Lord and Savior stood in the Jordan to be baptized, the inanimate elements manifested their fear and reverence for Him who became man through the Mystery of the Incarnation (ተዋሕዶ). Our Lord did not approach the Jordan because He was in need of purification; rather, as the “Source of Life” from whom “አፍላገ ማየ ሕይወት ዘይውኅዝ እምከርሡ”—”rivers of living water flow” (John 7:38) — He went down into the waters to sanctify them, transforming them into a womb of spiritual rebirth and divine adoption for us.On that day, the Jordan recoiled and the depths trembled, acknowledging the Divine Nature of the Christ standing in their midst. As the Holy Scripture bears witness: “ባሕርኒ ርእየት ወጎየት ወዮርዳኖስኒ ገብአ ድኅሬሁ” — “The sea saw it and fled; Jordan was driven back” (Psalm 114:3). This marks the great day of triumph where the debt of human sin was annulled, and humanity was led from the shadows of darkness into the marvelous light of grace.Beloved children in the Holy Spirit;The baptism of our Lord in the Jordan was intended to pave the way for our salvation and to grant us new life by washing away our transgressions. Therefore, as we celebrate this sublime feast, we must reflect deeply on the price Christ paid for our redemption. Our celebration should be marked by Christian conduct that honors the dignity of the sonship we received through Holy Baptism.We must refrain from worldly excesses and secular behaviors that obscure the spiritual depth of this mystery or deviate from the ancient traditions of the Church (ጥንታዊ ሥርዓት). Instead, let us observe the feast through liturgy (ሥርዓተ አምልኮ), fervent prayer, and acts of charity.In conclusion, may our Lord and Savior Jesus Christ, through the grace of His baptism, strengthen us to live in faith and righteousness throughout this year. May He, who stood in the midst of the Jordan, grant enduring peace to our nation and bestow health and divine blessings upon all our people. May God Bless Ethiopia! Abba GerimaBishop of the Diocese of Gedeo, Kore, and BurjiMember of the Holy Synod

In the Name of the Father, and of the Son, and of the Holy Spirit, One God. Amen. Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት!

ኤክቱስ ጥር 10/2018 ዓ.ም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። በሀገረ ስብከታችን፣ በሀገር ውስጥና በሌሎች ክፍላተ ዓለም የምትገኙ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናን ወምእመናት፤ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ድኅነተ ዓለም ሲል በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ለተጠመቀበት፣ ለታላቁ የአደባባይ በዓላችን ለብርሃነ ጥምቀቱ እንኳን በሰላም አደረሳችሁ! “ርእዩከ ማያት እግዚኦ ርእዩከ ማያት ወፈርሁ  ደንገፁ ቀላያተ ማያት ወድምጸ ማያቲሆሙ – አቤቱ ውኃዎች አዩህ ውኃዎችም አዩህና ፈሩ ጥልቆችም ተነዋወጡ ውኃዎችም ጮሁ።” መዝ. ፸፮፥፲፮ ይህ የቅዱስ ዳዊት ቃለ ትንቢት ባሕርየ ሰብእን ለማዳን በተዋሕዶ ሰው የሆነው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ ሊጠመቅ በቆመ ጊዜ ግዑዛን ፍጥረታት ፈጣሪያቸውን አውቀው ያሳዩትን ድንጋጤ የሚገልጽ ነው። ጌታችን ወደ ዮርዳኖስ ለመጠመቅ የሄደው መጠመቅ የሚገባው ሆኖ ሳይሆን፣ እርሱ ማየ ሕይወት በመሆኑ “አፍላገ ማየ ሕይወት ዘይውኅዝ እምከርሡ – ከሆዱ የሕይወት ውኃ ወንዝ ይፈስሳል” (ዮሐ. ፯፥፴፰) ተብሎ እንደተጻፈ፤ ውኃውን ቀድሶ ለእኛ የልጅነት መገኛ እንዲሆንልን ነው። በዚያን ዕለት ዮርዳኖስ ወደ ኋላ የሸሸውና ጥልቆች የተነዋወጡት፣ በማዕከለ ዮርዳኖስ የቆመውን የጌታችንን የባሕርይ አምላክነት ተረድተው ነው። ይህ ምስጢርም “ባሕርኒ ርእየት ወጎየት ወዮርዳኖስኒ ገብአ ድኅሬሁ – ባሕር አየችና ሸሸች፤ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ” (መዝ. ፻፲፫፥፫) ተብሎ በቅዱስ መጽሐፍ እንደተመሰከረ፣ የሰው ልጅ የኃጢአት ዕዳ ተደምስሶ ከጨለማ ወደ ብርሃን የተሸጋገረበት ታላቅ የድል ቀን ነው። የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን፤ ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው ለእኛ የድኅነትን መንገድ ሊከፍትልንና በጥምቀቱ የኃጢአት ዕዳችንን ደምስሶ አዲስ ሕይወትን ሊሰጠን ነው። በመሆኑም ይህን ታላቅ የድኅነት በዓል ስናከብር ክርስቶስ የከፈለንን ዋጋ እያሰብንና በጥምቀት ካገኘነው ልጅነት ጋር በሚስማማ ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር ሊሆን ይገባል። በጥምቀት ያገኘነውን ልጅነት ከሚጋርዱ፣ ከቤተ ክርስቲያን ጥንታዊ ሥርዓት ውጭ ከሆኑና የምስጢረ ጥምቀቱን ረቂቅነት ከሚያደበዝዙ ሥጋዊ ድርጊቶች ተቆጥበን፤ በዓሉን በሥርዓተ አምልኮ፣ በጸሎት እና መልካም ሥራዎችን በመሥራት  ልናከብረው ይገባል።  በመጨረሻም፣ ይህ የ፳፻፲፰ ዓመተ ምሕረት የጥምቀት በዓል አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ የሰጠንን የልጅነት ጸጋ በሃይማኖትና በምግባር አጽንተን እንድንኖር ይርዳን። በማዕከለ ዮርዳኖስ የቆመው የባሕርይ አምላክ ለሀገራችን ሰላምን፣ ለሕዝባችንም ጤናንና በረከትን ያድልልን። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ! አባ ገሪማየጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት! Read More »

“ወነሥኡ ካህናት  ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር ወሖሩ ቅድመ ሕዝብ” (የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዘው በሕዝቡ ፊት አለፉ) ኢያ 3፥6‎

‎ታቦቱ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን  ታቦት በመባል ይጠራል፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ታቦት አሁን ካለው የተለየ ነው፡፡ የብሉይ ኪዳኑን ታቦት የሚሸከሙት አራት ሰዎች ሆነው ነው፡፡ የአሁኑ ታቦት ምሥዋዕ በመባል ይጠራል፡፡ ለሥጋ ወደሙ መፈተቻነት የሚያገለግል ነው፡፡‎‎እስራኤላውያን ከግብፅ ወጥተው ወደ አገራቸው በሚያደርጉት ጉዞ የዮርዳኖስ ወንዝ ፊታቸው ተደንቅሮ አላሳልፍ አላቸው፡፡ ታቦቱ በአንድ ሰው ብቻ ሊሸከሙት የማይቻል ነበርና ታቦቱን  የተሸከሙ ካህናት እግር ጫማ በዮርዳኖስ ወንዝ ውኃ ውስጥ ሲቆም እንደ ክምር ሆኖ ቆመ፡፡  ለእነርሱ ሲል ውኃው ሲቆም ሲያዩ ምንኛ ይደነቁ! ቆሞ አሳለፋቸው ፡፡ ሕዝቡ ተሻግረው ሲያበቁ ካህናቱ ከውኃው ወጥተው እግራቸው ደረቅ መሬት መርገጥ ሲጀምር ውኃው መልሶ መፍሰስ ጀመረ፡፡ ውኃው ቆሞ እንዳሳለፋቸው ፣ ከወጡ በኋላ ደግሞ መፍሰስ ሲጀምር መልሰው እንዴት ነው የማይደነቁት ትላላችሁ?‎‎ከወንዙም ውስጥ ያወጡአቸውን 12 ድንጋዮች ካህናቱ እግራቸው ቆሞ በነበረበት በወንዙ ውስጥም እንዲሁም ከወንዙ ውጭም ተተከሉ፡፡ የሚመጣ ትውልድ እግዚእብሔር ያደረገውን ተአምር እንዲሰማ ታስቦ ነው፡፡‎‎እግዚእብሔር ከግብፅ ያወጣውን ሕዝብ ሊያውም እጅግ ባለመታዘዝ ያስቸገሩትን በእንዲህ መልኩ ነበር ደንቅን እያሳያቸው የመራቸው፡፡ ቸርነቱ እንዴት ብዙ ነው!‎‎በዚህ ክፍል ግን የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት ወደ ጥምቀተ ባሕር የሚወርድበትን የከተራ በዓል ታሪክና ምሥጢር ነው የምንመለከተው ።‎‎”ከተራ”‎ተራ ምንድን ነው?‎   “ከተራ” በመባል የሚታወቀው “የጥምቀት ዋዜማው” ነው፡፡ “ከተራ” የሚለው ቃል “ከተረ ከበበ ካለው የግዕዝ ግስ የወጣ ነው፡፡ ከተራ ፍቺውም ውኃ መከተር፣ ወይም መገደብ ማለት ነው፡፡” ደስታ ተከለ ወልድ /1962፣ 694/ ደግሞ  የጥምቀት ዋዜማ፣ ጥር ፲ የጠራ ወራጅ ውኃ የሚከተርበት ታቦትና ሰው ወደ ዠማ ወንዝ የሚወርዱበት ጊዜ” ነው በማለት ይፈቱታል፡፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም /1948፣ 555/ ከተረ የሚለውን ቃል በቁሙ፣ “ዘጋ፣ አቆመ፣ አገደ፣ ከለከለ” ማለት ነው ብለው ይፈቱታል፡፡ በየዓመቱ ጥር ፲ ቀን የምእመናኑ አብዛኛው ሥራ ውኃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላል፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥል ይውላል፡፡ የምንጮች ውኃ ደካማ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከተራል ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሔድ ይገደባል፡፡ ውኃው የሚከተረው በማግሥቱ ጥር ፲፩ ቀን የጥምቀት በዓል ስለሚከበር ለሕዝቡ መጠመቂያ እንዲሆን ነው፡፡‎   ‎ ባሕረ ጥምቀት፣ የታቦት ማደሪያ‎በየሰበካው ቦታ ተለይቶና ተከልሎ ታቦታቱ በዳስ ወይም በድንኳን የሚያድሩበት፣ የተለያዩ የውኃ አካላት ተጠርገው የሚከተሩበት ወይም ሰው ሠራሽ የግድብ ውኃ የሚበጅበት ስፍራ “ባሕረ ጥምቀት”፣ “የታቦት ማደርያ” እየተባለ ይጠራል፡፡‎‎የከተራ በዓል በኢትዮጵያ‎‎ከዐፄ ገብረ መስቀል ጀምሮ የአደባባይ በዓል የሆነው የጥምቀት በዓል በ፲፭ኛው ክ/ዘመን በኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ /1426-1460 ዓ.ም/ አማካኝነት ታቦታቱ ወደ ወንዝ ወርደው ዕለቱን እንዳይመለሱ፣ በዚያ ፈንታ በጥምቀት ዋዜማ ጥር ፲ ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርደው እንዲያድሩ፣ አገሩን በኪደተ እግር ይባርኩም ዘንድ በሔዱበት መንገድ እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ፡፡ ይህን ታሪክ በመከተል ዐፄ ናዖድ /1486-1500 ዓ.ም/ ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመን ታቦተ ሕጉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በሚወርድበት እና ከባሕረ ጥምቀቱ ወደ ቤተ መቅደሱ በሚመለስበት ጊዜ አጅቦ አውርዶ፣ አጅቦ መመለስ እንዳለበት በዐዋጅ አስነግረው ነበር፡፡ ሕዝቡም ታቦታተ ሕጉን በሆታና በእልልታ ከቤተ መቅደስ አጅቦ ከአወጣ በኋላ በባሕረ ጥምቀት ከትሞ ማደር ጀመረ። /ሐመር ጥር/የካቲት 1998 ዓ.ም/‎‎ከቤተመቅደስ ወደ ባሕረ ጥምቀት‎     የከተራ ዕለት ጥር ፲ ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ የሔደበትን ለማዘከር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ኃዳፌ ነፍስ ለጻድቃን የሚለውን ዋዜማ ይቆማሉ፡፡  የዋዜማው ቀለም  ከቀኑ በአራት ሰዓት በመላው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ይጀመራል ከዚያም የዋዜማው ሥርዐት ቅዱስ ተብሎ እስከ ሰላም ያለው ቀለም ይደርሳል፡፡ በዕለቱም ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ ታቦተ ሕጉን የሚያነሡት ሰሞነኛ ካህን ከምግበ ሥጋ ተከልክለው ለዕለቱ የሚገባውን ጸሎት ያደርሳሉ፡፡ በከተራው ዕለት ድንኳን ተተክሎ፣ ዳሱ ተጥሎና ውኃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ ታቦተ ሕጉ የሚንቀሳቀስበት ሰዓት ሲደርስ የየቤተ መቅደሱ ታቦታት  በወርቅና በብር መጎናጸፊያ እየተሸፈኑ በተለያየ ኅብር በተሸለሙ የክህነት አልባሳት በደመቁ ካህናትና የመጾር መስቀል በያዙ ዲያቆናት ከብረው፣ ከቤተ መቅደስ ወደ አብሕርት /ምጥማቃት/ ለመሔድ ሲነሡ መላው አብያተ ክርስቲያናት የደወል ድምፅ ያሰማሉ፡፡ ምእመናን ከልጅ እስከ ዐዋቂ በዐጸደ ቤተ ክርስቲንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች “ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ …’’ እንደሚባለው ያማረ ልብሳቸውን ለብሰው በዓሉን ያደምቃሉ፡፡‎        ታቦቱ ከመንበረ ክብሩ ሲነሡ “ዮም ፍስሀ ኮነ” ተብሎ ከተጸነጸለ በኋላ ታቦቱ ወጥቶ ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት የሚለው ሰላም በሊቃውንቱ  ይዘመራል፣ ይጸነጸላል፣ ይመላለሳል፡፡ የወርቅ ካባና ላንቃ የለበሱ ቀሳውስት፣ መነኮሳት ጥላ የያዙት ከታቦቱ ጎን መስቀልና ጽና የያዙት ከታቦቱ ፊት ይሔዳሉ፡፡ እንደ ቀሳውስቱ ተመሳሳይ ልብሰ ተክህኖ የለበሱት ዲያቆናት ጥላ፣ መስቀልና ቃጭል ይዘው እያቃጨሉ ከቀሳውስቱ ፊት በመሆን ያጅቧቸዋል፡፡ ከነዚህም ሌላ ካባ፣ ላንቃ ጥንግ ድርብ የለበሱ መዘምራን የብር፣ የነሐስ መቋሚያና ጸናጽል ይዘው “ወረደ ወልድ”  የሚለውን አመላለስ እያሸበሸቡ ዲያቆናቱን ቀድመው ይሄዳሉ፡፡ የደብር አለቆችና አበው ካህናት ታቦቱን ተከትለው ይጓዛሉ፡፡ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎችም በተለያዩ ቀለማት ባሸበረቁ አልባሳት ተውበው ትርዒት እያሳዩ “ወረደ ወልድ፣ እግዚኡ መርሐ፣ ሆረ ኢየሱስ” እና ሌሎችንም የአማርኛ መዝሙራትን እየዘመሩ፣ እናቶች “ነይ ነይ እምዬ ማርያም” እያሉ ሌሎችም ምስጋናዎችም እየቀረቡ ጉዞ በዝግታ ወደ ጥምቀተ ባሕር ይሆናል፡፡‎‎የከተራ በዓል ማክበሪያ ቦታ እንደደረሱ ታቦታቱ በድንኳኑ አጠገብ ቆመው “ወረደ ወልድ”  የሚለው ሰላም ተመርቶ በአግባቡ ከተለዘበ በኋላ ጸሎት ተደርጎ የዕለቱ ትምህርተ ወንጌልና ዝማሬ  ከቀረበ በኋላ ውዳሴ ማርያም፣መልክዐ ኢየሱስ ተደግሞ  ታቦቱ ሕጉ  ወደ ተዘጋጀላቸው ድንኳን ይገባሉ /ሥርግው፤1981፣9/፡፡ በሁለተኛ የአገልግሎት ክፍል  ካህናቱ ስብሐተ እግዚአብሔር ሲያደርሱ ያድራሉ፡፡ በመንፈቀ ሌሊትም ሥርዐተ ቅዳሴው ተጀምሮ ከሌሊቱ በ9፡00 ሠርሆተ ሕዝብ ይሆናል፡፡‎የከተራ ምሳሌነት ‎‎በበዓለ ጥምቀት ዋዜማ የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድና የባሕረ ጥምቀቱ መዘጋጀት  ሃይማኖታዊ ታሪክና ምሳሌ አለው፡፡ እስራኤል ዘሥጋ ወደ ምድረ ርስት ለመግባት የዮርዳኖስን ወንዝ ሲሻገሩ፡- ድንኳን ጥለው የቃል ኪዳኑን ታቦት በድንኳን ውስጥ አድርገው ሌዋውያኑ በዙሪያው፣ ካህናቱ ደግሞ በውስጥ ኾነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አድረው በማለዳ ተሻግረዋል /ኢያሱ.፫፥፰-፱/፡፡  ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት አክብረው  የወንዙን ዳርቻ በረገጡት ጊዜ እንደ ክረምት ማዕበል ይወርድ የነበረው ውኃ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ወደ ላይ ቆሟል፡፡ ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ታቦተ ጽዮንን ያከበሩት  ካህናት ከወንዙ መሀል ይቆሙ ነበር፡፡ በዚህ መሠረት  “የካህናት እግሮቻቸው የዮርዳኖስን ውኃ በመርገጣቸው እንደ ጥምቀት ሆናቸው” በሐዲስ ኪዳነ ጌታችን ለመሠረተው ሥርዐተ ጥምቀት ምሳሌ ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የጥምቀትን ዋዜማ ከተራ ብላ የጠራችው ከዚህ በመነሣት ነው፡፡‎‎ጌታችን በተጠመቀ  ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ የላይኛው ሸሽቶ ወደ ላይ ተመልሶ ሽቅብ ፈሷል፡፡ የታቹም ወደ ታች ሸሽቷል፡፡ የላይኛው ፈሳሽ ተቋርጦ እንደ ክምር ተቆልሎ ቀርቷል። ቅዱስ ዳዊት የተመለከተውም ይህንኑ ነው። ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ቤዛነት ተቋርጦ፤ የታቹም ፈጽሞ መድረቁ ኃጢአተ አዳም የመጥፋቱ ምሳሌ ነው፡፡ እስራኤል ፈለገ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ኢያሪኮ  መሔዳቸው ምእመናን በጥምቀት ከኃጢአት ቍራኝነት ተላቀው እግራቸውን ወደ ልምላሜ ገነት ወደ ዕረፍት መንግሥተ ሰማያት አቅንተው ለመሔዳቸው ምሳሌ ነው፡፡  ኢያሱ የጌታ፣ እስራኤል  የምእመናን፣ ዮርዳኖስ የጥምቀት፣ ምድረ ርስት የገነት መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው፡፡‎       ታቦቱን አክብሮ  የሚሔደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ፣ ታቦቱ የጌታችን፣ ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ፣ ታቦታቱን አጅበው የሚሔዱትና በዓሉን የሚያከብሩት ምእመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩት ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ታቦታቱ በጥምቀት ዋዜማ ከመንበራቸው ወደ ጥምቀተ ባሕር መውረዳቸውና በዚያ ማደራቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከማታው ጀምሮ መውረዱንና ተሰልፎ ተራውን ሲጠብቅ ማደሩን ያጠይቃል፡፡  በመኾኑም ከዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ሁሉ በዮርዳኖስ ዙሪያ ድንኳናቸውን ተክለው ያርፉ ነበር፡፡ በዚህ አንጻር ዛሬም በባሕረ ጥምቀት ዙሪያ ድንኳኖች ዳሶች ይጣላሉ፡፡ የከተራ በዓል ታሪካዊ፣

“ወነሥኡ ካህናት  ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር ወሖሩ ቅድመ ሕዝብ” (የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዘው በሕዝቡ ፊት አለፉ) ኢያ 3፥6‎ Read More »

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በሀገረ ስብከቱ የሚሠሩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ!

ኤክቱስ ጥር 6/2018 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የሚሠሩ በርካታ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ሀገረ ስብከቱ በዲላ ከተማ የሚያስገነባው የመንበረ ጵጵስና ግንባታ፣ በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሚሠራው የውኃ እና የዶሮ ልማቶች ተጎብኝተዋል። በተጨማሪም በአንዲዳ የሚገኘው የአዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት መደበኛ የመማር የማስተማር ሂደት፣ አዲስ ለመገንባት የታሰበበት ቦታ፣ የተማሪዎች የማደርያና የመመገቢያ ክፍላት እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት ተጎብኝቷል። ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ በአጠቃላይ ስለሚሠሩ የልማት ሥራዎች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ብፁዕነታቸው በሀገረ ስብከቱ የተሠሩ ሥራዎችን እና ደቀ መዛሙርቱን በመጎብኘታቸው እና ቡራኬ በመስጠታቸው እጅግ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሊቀ ጳጳስ በተመለከቱት ሥራዎች ፍጥነት መገረማቸውን የገለጹ ሲሆን ሁሉም አካል ከብፁዕነታቸው አጠገብ ከሆነ ከዚህ በላይ በርካታ ሥራዎችን በሀገረ ስብከታቸው እንደሚሠሩና ገና ብዙ ያልተጠቀምንባቸው አባት መሆናቸውን ገልጸው እግዚአብሔር ሀገረ ስብከቱን በፍጹም ሰላም እንዲጠብቅ በመማጸን ጉብኝታቸውን በጸሎት ፈጽመዋል። በመርሃግብሩ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌን ጨምሮ የክፍል ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በሀገረ ስብከቱ የሚሠሩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ! Read More »

Scroll to Top