በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ቀዳሚ ገጽ ዜና

የቅዱስ መስቀል የደመራ በዓል በዲላ ከተማ ብፁዕነታቸው በተገኙበት ተከበረ!

ኤክቱስ መስከረም 16/2019 ዓ.ም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜም በየዓመቱ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የቅዱስ መስቀል የደመራ በዓል በዲላ ከተማ በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በዲላ ከተማ ሻላይቱ ስቴዲየም በታላቅ ድምቀት ተከብሯል። በብፁዕነታቸው መሪነት መርሃግብሩ በጸሎተ አኮቴት፣ ጸሎተ ምህላ እና ምልጣን የተጀመረ ሲሆን በመቀጠልም በከተማው በሚገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ያሬዳዊ ዝማሬ የቀረበ ሲሆን የሀገረ ስብከቱ የጌዴኡፋ ቋንቋ ትርጉም ክፍል ኃላፊ ቀሲስ ሀብታሙ ሮቤ ለዕለቱ የሚስማማ የጌዴኡፋ ቋንቋ ዝማሬ አቅርበዋል። በበዓሉ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ዝናቡ ወልዴ የመስቀል በዓል በአንድነትና በጋራ የሚከበር ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓል በመሆኑ ሁሉም በአንድነት ሊያከብረው እንደሚገባ ገልጸዋል። አክለውም በዓሉ የምስጋናና የአብሮነት መገለጫ በመሆኑ ከደመራው የሚገኘውን የአንድነት እሴት በመውሰድ ለዞኑ ልማት በጋራ መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል። የዲላ ከተማ ምክትል ከንቲባና የሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታሪኩ በየነ በበኩላቸው ደመራው ፍቅርና አንድነት የሚያንጸባርቅ እሴት ለዲላ ከተማ ልማትና ሰላም ማዋል እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በመልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ ጋባዥነት ብፁዕ አቡነ ገሪማ አባታዊ ቃለ በረከት አስተላላፈዋል። ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት መልእክት በዩኔስኮ የተመዘገበው በዓለ መስቀል በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት በተመዘገበው የጌዴኦ ባህላዊ መልክአ ምድር ላይ መከበሩ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው ገልጸው ይህም መንፈሳዊና ባህላዊ ቅርሳችንን አስተሳስሮ ለዓለም የሚያስተዋውቅ እንዲሁም ወጣቱ ትውልድ ሃይማኖቱን፣ ማንነቱንና ተፈጥሮውን አክብሮ እንዲጠብቅ የሚያነቃቃ ሀብት መሆኑን ተናግረዋል። አክለውም ምዕመናን እርስ በእርስ በመደጋገፍ ፍቅርን በማብዛትና የቤተ ክርስቲያናቸውን ክብር በመጠበቅ የመስቀሉ ሥራ ምስክሮች መሆናቸውን በሥራ ሊያሳዩ እንደሚገባ አባታዊ አደራቸውን ጥለዋል። በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ጸሎት አድርገው በጋራ የተዘጋጀውን ደመራ ለኩሰው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

የቅዱስ መስቀል የደመራ በዓል በዲላ ከተማ ብፁዕነታቸው በተገኙበት ተከበረ! Read More »

Anninke summin Beltinke summin Qullichcha Manfasike summin mitte Mageno Ameen.Ulfaatendineek Hagere sibketetik Huje me’isalliUlfaatendineexxi mootumate’n lumoke baalloma’n hexxineekUlfaatendineexxi Hagere sibiketetikinna roginxe Bete-kinetek hujaluwwiUlfaatendineexxi Beete kiristaanet dhotuwwi, Kahinaate nna Wongeeletixxi barsiisano

Konnee ayyaana ulfeesatee birii’ninna bayyii’n bukkitineexi no’oxxi keessumma duuchchinxi Baga lame kumanna tommenna sallane Gattowaalitixxe Woggake Qullitte fannoke baabbet ayyaani’a nage’ikinna fayyuntet geltineen gennenen. “ወአልቦ ኅቡዕ ዘኢይትከበት ወአልቦ ክዱን ዘኢይትከሠትማር ፬-፳፪“Leellitabaashsha shoondeexxi hexxebaan ifa fuldo’a malee buqendeexxi hexxebaan.”Marqoos 4:22 Gootti nna qorsi no’ok Iyyesuusi Kiristoosi dada duuchchixe fayya’a hiyyeexxi haqichchinxe fanno’n fanniseme’e fayyiseechchi uduma qullitte fanno hara lumolla manbe’a hujjaa’na uudemmak Ayihudoot gaabbet ke’neen. Goottinxi fanno lumolla Manbe’a hujjaa’na uundeemmaxxee isexxa baada balleessatee welenxe lame fannon welti Iyyerusaalemi’n afendaaxxe lumoxxe bale’n moongeen. Loolink mani duuchchi tenne bale’n kora tuullaashsha ajanjeen. Sase dhibba wogga’ana kora tuullammale kooba kadeen. Kaddomalee Mageninik ulfinni heenooke mannixxe fuggonni shoome gato’a dande’ebaan. Sase dhibba wogga uduma Mootitte Illeeni ke’isseen. Qulliyye ke’isseexxi Gedaametiba,Tolcheme manna ke’isseexxi munde dunnaashsha,Hawwaariyaate ke’isseexxi butta duuchcha doone barsiinsaasha asseek Mageni Mootitte Illeeni ke’ise’e qeerraake bari’a shoonde hexxeemmaxa goottinxa fanno fulchito’a qalbe isexxa kekke’issammale Iyyerusaalemi’a marteen. Okkoonna marteexxi geechcho Kiraakoosi hiyyemaaka qorte’e isi hiyyeeshsha assiteexxi baabbe otte’e ixaana wiliilchiteexxi ixaaniinxi wiliille iimi’a mete wirrite higher dagge sagaddeexxi qullitte fanno moogendeexxa bakka kuldeen. Tenne hundaayye’n bakka ettenee birra’a tommenna torbaaneke’n sanfee qonteexxi caansa tommeke’n galatikina faarot gonshe fulchineen. Ulfaatendineexxi manfasi qullichchinxi Ila Gootti nna qorsi Iyyesuusi Kiristoosixxi qullitte fanno manjinxe nna Mageninxe oddo’n hedhemmaki loli diiggeme Mageninxi fayyisatixxi huje ifa fuldeeke ayyaanan. Telcho konne loola’n baabbe onte xassa xassine ayyaana ulfeessinano wodda Magenokenaa’n eebba alfinona sa’esanenaa’n caalsine ulfeesa hasissaan. Fanno no’oxxe Betekirstaaneke beesisa no’anna Kiristaanake beesisa kaddeemmaxxe goobake’n usidhine qalbete’n maxxanse’neenen. Kaddemmaxxe qalbe no’oxxenaa’n lolinka yaada balleessine qullitte fanno xurrite hujenni welt moongeennexxa goshiyyo hasisaan. Gootti no’ok fannote’n hedhe “አባ ኅድግ ወስረይ ሎሙ እስመ በዘኢየአምሩ ይገብሩ” hiyyat cubbo gattowwal hiyyaak cubbo baada balleessaak aadde aaggo eeyyaake kadeexxa ifa leellisheen. Tinni baabbe xassa haqqe gubbe balleessitammashshann no’onna qalbete’n hexxeexxa fuggonna gargarunte gattowwaalit gunbe no’oxxe oddonaa’n balleessat jaalala kaasa hasissaan. Giddii’nin no’oxxe Hagere Sibikete’n afendinaak Magenink Ilaali konnee lumoka ayyaana Yuunesko butta duuchchixxe tare assexxe borreessexxeeka Yuuneskote’n borreessemeeke Gede’inke boga’n ulfeessa gargar assitaaxxen. Konne ba’la raaga afeeka fannot ayyaana dargaggeeyye adde,ayyunte nna dada ulfeesendeexxi hexxaashsha assitaaxxe adde asse’na’n Kunni fannotik ayyaani qullitte no’oxxe Beete kiristaane’a, boga no’okee nna arda duuchchi’a Nage’inke,jaalalatike nna eebbatike kaddaashsha Mageninxe eeyyante kaddowwaal! Mageni boga no’oka eebbisowwaal! Birra’a 16/2019 G.WAbba Geriima Gede’o Koorenna Burjixxe Hagere Sibikete Phaphaasichcho

Anninke summin Beltinke summin Qullichcha Manfasike summin mitte Mageno Ameen.Ulfaatendineek Hagere sibketetik Huje me’isalliUlfaatendineexxi mootumate’n lumoke baalloma’n hexxineekUlfaatendineexxi Hagere sibiketetikinna roginxe Bete-kinetek hujaluwwiUlfaatendineexxi Beete kiristaanet dhotuwwi, Kahinaate nna Wongeeletixxi barsiisano Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በሁለት ሺህ አሥራ ዘጠኝ ዓመተ ምሕረት በቅዱስ መስቀል የደመራ በዓል ያስተላለፉት ቃለ በረከት!

ኤክቱስ መስከረም 16/2019 ዓ.ም በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን! – የተከበሩ የሀገረ ስብከታችን ዋና ሥራ አስኪያጅ – የተከበራችሁ የመንግሥት ባለሥልጣናት – የተከበራችሁ የሀገረ ስብከታችን፣ የወረዳ ቤተ ክህነት ኃላፊዎች እና ሠራተኞች – ክቡራን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ካህናትና መምህራን – ይህንን በዓል ለማክበር ከሩቅም ከቅርብም የተገኛችሁ እንግዶቻችንን ሁላችሁም ክቡራንና ክቡራት እንኳን ለሁለት ሺህ አሥራ ዘጠኝ ዓመተ ምሕረት ለቅዱስ መስቀል የደመራ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ! “ወአልቦ ኅቡዕ ዘኢይትከበት ወአልቦ ክዱን ዘኢይትከሠት – እንዲገለጥ ባይሆን የተሰወረ የለምና ወደ ግልጥ እንዲመጣ እንጂ የተሸሸገ የለም።” ማር ፬-፳፪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለድኅነተ ዓለም ሲል በዕፀ መስቀል ተሰቅሎ ዓለምን ካዳነ በኋላ፤ ቅዱስ መስቀሉ እጅግ ድንቅ ድንቅ ገቢረ ተአምራት ሲያደርግ ያዩት አይሁድ በምቀኝነት ተነሡ። የጌታ መስቀል እጅግ ብዙ ተአምራትን ማድረግ እንደሚችል ስላወቁና ይህንን ትምህርት ለማጥፋት ስለፈለጉ ቅዱስ መስቀሉን ከሁለት መስቀል ጋር በመውሰድ በኢየሩሳሌም በሚገኝ አንድ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ቀበሩት፤ በላዩም ላይ የከተማው ሕዝብ ቆሻሻ እንዲጥልበት አዘዙ። ለሦስት መቶ ዓመታትም ያኽል የከተማው ጥራጊና ቆሻሻ በላዩ ላይ ሲጣልበት በመቆየቱ ሥፍራው ትልቅ የቆሻሻ ተራራ ወይም ኮረብታ ሆነ። ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ክብር በጥቂት ሰዎች ተንኮል ምክንያት ተሸሽጎ ሊቀር አልቻለም። ከሦስት መቶ ዓመታት በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ንግሥት ዕሌኒን አስነሣ። ጻድቃንን አነሳስቶ ወደገዳም፣ ሰማዕታትን አነሳስቶ ወደ ደም፣ ሐዋርያትን አነሳስቶ ወደ ዓለም ጫፎች የሚሰድ አምላክ ንግሥት ዕሌኒ የጠፋውንና ለዘመናት በተራራ ሥር ተሰውሮ የኖረውን የጌታን ቅዱስ መስቀል ፈልጋ እንድታወጣ ታላቅ መንፈሳዊ ፍላጎት አሳደረባት፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ተጓዘች። በዚያም አረጋዊውን ኪራኮስን አግኝታ በሚሰጣት መመሪያ መሠረት ደመራ አስደምራ ከንጹሕ ዕጣን ጋራ ጸሎት አደረገች። የዕጣኑ ጢስ ወደ ሰማይ ወጥቶ ቁልቁል ሰግዶ ቅዱስ መስቀሉ የተቀበረበትን ትክክለኛ ሥፍራ አመላከተ። በዚህም መሪነት ንግሥት ዕሌኒና ሕዝቡ መስከረም ፲፯ ቀን ቁፋሮውን በመጀመር፣ የቆሻሻውን ተራራ አስነስተው መጋቢት ፲ ቀን የጌታን ቅዱስ መስቀል በይባቤና በአኮቴት ቆፍረው አወጡት። የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀል በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው የጥል ግድግዳ ተሰብሮ የአምላካችን የማዳን ሥራ በግልጽ የታየበት ትልቅ በዓላችን ነው። ዛሬ በዚህ ስፍራ የደመራው እሳት ተለኩሶ በዓሉን ስናከብር ከእግዚአብሔር ረድኤት እና በረከት እንድናገኝ ከአምናውና ካለፈው በተሻለ በንጽሐ ልብ ሆነን ልናከብር ይገባናል። መስቀል የቤተ ክርስቲያናችን አርማ የእኛም የክርስቲያኖች መለያችን ነው፤ በአንገታችንም አስረነዋል። በልባችንም ስለነዋል። በመሆኑም በልባችን ያለውን የጥላቻ አስተሳሰብ በንስሐ አስወግደን፣ ቅዱስ መስቀሉን ከተቀበረበት ከቆሸሸ ተግባራችን ሥር ልናወጣው እና “ብርሃኑም በሰዎች ሁሉ ፊት እንዲያበራ” ልናደርገው ይገባል። ጌታችን በመስቀል ላይ ሆኖ “አባ ኅድግ ወስረይ ሎሙ እስመ በዘኢየአምሩ ይገብሩ” በማለት ኃጢአትን ይቅር የሚል፣ በደልን የሚደመስስና መፍቀሬ ንስሐ መሆኑን በገሃድ አሳይቶናል። ይህ ከፊታችን ያለው የደመራው እሳት እንጨቱን አቃጥሎ እንደሚያጠፋው ሁሉ እኛም በልባችን ያለውን ቅሬታና ልዩነት በፍጹም ይቅርታ አቃጥለን በመካከላችን ፍቅርን ልንዘራ ይገባናል። የቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ክብሯ በልጆቿ አንድነት ውስጥ ጎልቶ ይታያልና። በተለይም በሀገረ ስብከታችን የምትኖሩ ውድ ልጆቻችን፤ ይህንን ታላቅ በዓል እያከበርን የምንገኘው  በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት በተመዘገበው የጌዴኦ ባህላዊ መልክአ ምድር ላይ መሆኑ የራሱ የሆነ ዘርፈ ብዙ የሆነ ትልቅ ፋይዳ አለው። በዩኔስኮ ከተመዘገበው ታሪካዊው የመስቀል በዓላችን ጋር ተያይዞ የተገኘው ይህ ልዩ አጋጣሚ መንፈሳዊ እሴታችንንና ባህላዊ ቅርሳችንን አስተሳስሮ ለዓለም የሚያስተዋውቅ እንዲሁም የአካባቢያችንን ገጽታ የሚያጎላና ወጣቱ ትውልድ ኃይማኖቱን፣ ማንነቱንና ተፈጥሮውን አክብሮ እንዲጠብቅ የሚያነቃቃ ትልቅ ሀብታችን ነው። በመሆኑም እርስ በእርስ በመደጋገፍ፣ ፍቅርን በማብዛትና የቤተ ክርስቲያናችንን ክብር በመጠበቅ የመስቀሉ ሥራ ምስክሮች መሆናችሁን በሥራ ልታሳዩ ይገባል። ይህ የደመራና የመስቀል በዓል ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን፣ ለሀገራችንና ለሕዝቦቿ ሁሉ የሰላም፣ የፍቅርና የበረከት በዓል ዘመኑም የተባረከ ዘመን እንዲሆንልን አምላካችንን ይፍቀድልን። እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ! መስከረም 16/2019 ዓ.ምዲላ፤ ኢትዮጵያ

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በሁለት ሺህ አሥራ ዘጠኝ ዓመተ ምሕረት በቅዱስ መስቀል የደመራ በዓል ያስተላለፉት ቃለ በረከት! Read More »

በዲላ ከተማ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ በሚገኘው በቅዱስ መስቀል የደመራ በዓል ላይ በዲላ ከተማ በሚገኙ ሊቃውንት በኋላም በሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የቀረበ ያሬዳዊ ዝማሬ በፎቶ!

ኤክቱስ መስከረም 16/2019 ዓ.ም

በዲላ ከተማ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ በሚገኘው በቅዱስ መስቀል የደመራ በዓል ላይ በዲላ ከተማ በሚገኙ ሊቃውንት በኋላም በሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የቀረበ ያሬዳዊ ዝማሬ በፎቶ! Read More »

የቅዱስ መስቀል የደመራ በዓል በዲላ ከተማ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በብፁዕነታቸው መሪነት ጸሎተ አኮቴት፣ ጸሎተ ምህላ እና ምልጣን በፎቶ!

ኤክቱስ መስከረም 16/2019 ዓ.ም

የቅዱስ መስቀል የደመራ በዓል በዲላ ከተማ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በብፁዕነታቸው መሪነት ጸሎተ አኮቴት፣ ጸሎተ ምህላ እና ምልጣን በፎቶ! Read More »

የቅዱስ መስቀል የደመራን በዓል ለማክበር ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበይ በዲላ ከተማ የሚገኙ አድባራት ወደ ዲላ ከተማ ሻላይቱ ስቴዲየም ጉዞ እያደረጉ ይገኛሉ!

ኤክቱስ መስከረም 16/2019 ዓ.ም

የቅዱስ መስቀል የደመራን በዓል ለማክበር ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበይ በዲላ ከተማ የሚገኙ አድባራት ወደ ዲላ ከተማ ሻላይቱ ስቴዲየም ጉዞ እያደረጉ ይገኛሉ! Read More »

Eebbisemeek Abune Geriima Gede’o Koorenna Burjixxe Hagere Sibikete Phaaphaasichchi Qullitte Sinoodoosexi una 2019 G.W haaroxxe woggake ayyani’a baga geltineen hiyyat sa’issineexxa annuntetixxa erga!

Ekitusi Qoodama 5/2018 G.W Anninke summin beltinke summin Qullichcha hafuurike summin mitte Mageno Ameen! እግዚኦ ባርክ ፍሬሃ ለምድር መሐሪ ወጻድቅ መኑ ከማከ ዘታርኁ ክረምተ በጸጋከ ነፍስ ድኅንት ወነፍስ ርህብት እንተ ጸግበት ተአኩተከ“Buttatixxa sanne eebbisi atixxe uwwann haarso hiisite idagattokee atishsha hedheek qullichchinna maraak ayyete  hedhe dhibendeexxi hedho fayyiteexxa yanna solo’week godob goddeexxa yanna galateefataak atee callan.” (Barook 2:6)No’oxxe Hagere Sibikete’nna kadi boga duuchcha’n afendinaak manfasi qullichchinxi ila Duchchingena’n arji Mageni eeti isixxin dullachcha Marqoosike barinaa’n haarooke Luqaasike baro 2019 G.W fooseexxe summi isik lummedheeke kadowwaal! Haarooxxi wogga daggaa wodda bari calli jijjiiremaa’na no’o jijjiiremmabe’nok heddi bari no’o’n sa’een. Assichchik,haaso’ikinna gargarike orinn Mageno yaadinsa’n turreennen.Saxxeexxa wogga aadde aagot muunxennexxi haarooxxa wogga jaalalat,nage’ikinna eloxxe hujenni safa gonphaannole barinxi jijjiirra calli la’o affebaan. Ulfesendineek Magenink ardi No’o Kiristoosin Kiristaana kandeennek Kiristoosi barsiisebaaxxa halo,gosunte ifixxe asse’ne he’naannole Qullichi Phawuloosi “no’o seerinke hadinanan” hiyya’n seera heqqabaaka Ayihudoota “Magenink summi ha’nooxxe buutonn Ahizaabete’n yowwemeen.” Hiyye ifisemmashshann No’onna weli’a weli gattowwaalitinna mittuntet hedhat Kiristoosixa jaalala hedho no’oxxin ifisa gonphonnole tinni erga telchonna no’aten. Ulfaatineek Magenink ardı No’oxxe Hagere Sibikete’anna Bette-kirstaaneke nage’a heqqendaaxxa duuchcha assitinaashsha maganne hinannen. Konne Luqaasike baro’n no’oxxe Hagere Sibikete’n Mageni minixxa ergachcho ba’lisatee,hadi giddixxa Betekirstaane kiphatee,Abinetetika barachchot mine ba’lisatee ,dargaggeeyye addetinna eloke adabinn nossatee ittann rakkateeka nna baala gopheeka gargaaratee safendeexxa manfasinxa ergachcho jabeessine me’atee konne eloke yaadi’a bogi giddonna kadi gadho hexxineek Magenink ardi asitinammaka kipha uurrisinabaashsha hinaannen. 2019 Haarooxxi wogga Tophakeenna bogi duuchchi’a nage’inxe,jaalalatixe,fayyuntetixenna suginxe kaddaashsha Mageno kadhantannon. Oriitetike bari muuxam haarooxe kakok safi cuuphat Kahine kadeek, buttatixxa cubbo gattowwaal hiyyaak ani uduma dagaan hiyyeexxe Wabeeko hiyyemeek Kiristoosi summi’a tolchemeexe Sema’ite kadeeke Qullichcha Yohaaanisixi eebba no’anna geltowwal. Mageni boga no’oka eebbisowwaal! Abba GeriimaGede’o Koorenna Burjixxe Hagere Sibikete Phaphaasichcho

Eebbisemeek Abune Geriima Gede’o Koorenna Burjixxe Hagere Sibikete Phaaphaasichchi Qullitte Sinoodoosexi una 2019 G.W haaroxxe woggake ayyani’a baga geltineen hiyyat sa’issineexxa annuntetixxa erga! Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አዲሱን ዓመት የሁለት ሺህ አሥራ ዘጠኝ ዓመተ ምሕረት ዘመነ ሉቃስን በማስመልከት የሰጡት የእንኳን አደረሳችሁ አባታዊ መልእክት!

ኤክቱስ ጳጉሜን 5/2018 ዓ.ም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። “እግዚኦ ባርክ ፍሬሃ ለምድር መሐሪ ወጻድቅ መኑ ከማከ ዘታርኁ ክረምተ በጸጋከ ነፍስ ድኅንት ወነፍስ ርህብት እንተ ጸግበት ተአኩተከ – አቤቱ የምድርን ፍሬ ባርክ በሥጦታህ ክረምትን መልሰህ የምታመጣው ሆይ! እንደ አንተ ጻድቅና ርኅሩኅ አምላክ ማን ነው የታመመች ሰውነት በተፈወሰች ጊዜ የተራበች ሰውነት በጠገበች ጊዜ ታመሰግንሃለች” ባሮክ ፪ ፥ ፮ በሀገረ ስብከታችን፣ በሀገር ውስጥና በመላው ክፍላተ ዓለም የምትገኙ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምዕመናንና ምዕመናት በሙሉ፤ ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር እንደርሱ ፈቃድና ቸርነት አሮጌውን ዓመት ዘመነ ማርቆስን አሳልፈን ወደ አዲሱ ዘመነ ሉቃስ የ2019 ዓመተ ምሕረት ስለሸጋገረን ዘለዓለማዊ ስሙ የከበረና የተመሰገነ ይሁን። እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! እንደሚታወቀው አዲስ ዓመት ሲመጣ የጊዜያት መለወጥና የዘመን መፈራረቅ ብቻ ሆኖ እኛ የሕይወት መታደስ ሳይኖረው እጅግ ብዙ ዓመታትን አሳልፈናል። በሥራችን፣ በመውጣታችን፣ በመግባታችን፣ በንግግራችን፣ በሀሳባችን…. አምላካችን እግዚአብሔርን ስናሳዝን ቆይተናል። ያለፈውን ዓመት በንስሐ፣ በኃዳጌ በቀል ልብና በይቅርታ ቋጭተን አዲሱን ምዕራፍ በፍቅር፣ በሰላም፣ በበጎ ሥራ ሁሉ ልንጀምረው ካልቻልን የዘመን መፈራረቅ በራሱ ዋጋ ያለው ነገር ሆኖ ብቻውን ሊቆም እንደማይችል ግልጽ ነው። የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምዕመናን እና ምዕመናት እኛ ክርስቲያኖች ተብለን በክርስቶስ ስም እየተጠራን ነገር ግን ክርስቶስ ያላስተማረንን ቂም፣ በቀል እና ዘረኝነትን ገንዘብ አድርገን የምንኖር ከሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “የሕግ ባለቤት ነን” እያሉ ነገር ግን ሕጉን የማይጠብቁትንና በግብዝነት የሚኖሩትን አይሁድን በሮሜ መልእክቱ “የእግዚአብሔር ስም በእናንተ ምክንያት በአህዛብ መካከል ይሰደባልና” ብሎ እንደገሰጸ እኛም እርስ በእርሳችን በይቅርታና በአንድነት በመቆም የክርስቶስን ፍቅርና ቸርነት በሕይወታችንና በሥራችን መግለጽ ካልቻልን ዛሬም ይህ መልእክት ለእኛ ነው። ውድ ምእመናን ለሀገረ ስብከታችን፣ ለቤተክርስቲያናችንና ለሀገራችን ሰላም፣ ዕርቅና አንድነት የበኩላችንን ክርስቲያናዊ ኃላፊነት እንድንወጣ አደራ እንላለን። በአዲሱ ዘመነ ሉቃስ ሀገረ ስብከታችን የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ከዚህ በላይ ተዳራሽነቱን ይበልጥ ለማስፋት፣ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን ለመደገፍ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችን ለማስፋፋት፣ ወጣቶችን በሃይማኖትና በበጎ ምግባር ለማነጽ፣ እንዲሁም የተቸገሩትንና ደካሞችን በመደገፍ ረገድ የተጀመሩ ዐበይት መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሥራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል። ለዚህም ቅዱስ ዓላማ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የምትገኙ ምዕመናን የምታደርጉትን ያልተገደበ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ድጋፍ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። አዲሱ የ2019 ዓመተ ምሕረት ለሀገራችን ኢትዮጵያና ለመላው ዓለም የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና እና የበረከት ዓመት እንዲሆንልን ወደ እግዚአብሔር አምላካችን እንጸልያለን። የዘመነ ኦሪት መጨረሻ፣ የዘመነ ሐዲስ መነሻ፣ በአጥማቂነቱ ካህን፣ የዓለምን ኃጢአት ይቅር የሚል ከእኔ በኋላ ይመጣል በማለቱ ነቢይ እና ስለክርስቶስ ሕይወቱን በመስጠቱ ሰማዕት ከሆነው ከቅዱስ ዮሐንስ ረድኤት በረከት ያድለን። እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ!አባ ገሪማየጌዴኦ ኮሬ እና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል                    ዲላ/ኢትዮጵያ

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አዲሱን ዓመት የሁለት ሺህ አሥራ ዘጠኝ ዓመተ ምሕረት ዘመነ ሉቃስን በማስመልከት የሰጡት የእንኳን አደረሳችሁ አባታዊ መልእክት! Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አዲሱን ዓመት የሁለት ሺህ አሥራ ዘጠኝ ዓመተ ምሕረት ዘመነ ሉቃስን በማስመልከት የሰጡት የእንኳን አደረሳችሁ አባታዊ መልእክት!

ኤክቱስ ጳጉሜን 5/2018 ዓ.ም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። “እግዚኦ ባርክ ፍሬሃ ለምድር መሐሪ ወጻድቅ መኑ ከማከ ዘታርኁ ክረምተ በጸጋከ ነፍስ ድኅንት ወነፍስ ርህብት እንተ ጸግበት ተአኩተከ – አቤቱ የምድርን ፍሬ ባርክ በሥጦታህ ክረምትን መልሰህ የምታመጣው ሆይ! እንደ አንተ ጻድቅና ርኅሩኅ አምላክ ማን ነው የታመመች ሰውነት በተፈወሰች ጊዜ የተራበች ሰውነት በጠገበች ጊዜ ታመሰግንሃለች” ባሮክ ፪ ፥ ፮ በሀገረ ስብከታችን፣ በሀገር ውስጥና በመላው ክፍላተ ዓለም የምትገኙ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምዕመናንና ምዕመናት በሙሉ፤ ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር እንደርሱ ፈቃድና ቸርነት አሮጌውን ዓመት ዘመነ ማርቆስን አሳልፈን ወደ አዲሱ ዘመነ ሉቃስ የ2019 ዓመተ ምሕረት ስለሸጋገረን ዘለዓለማዊ ስሙ የከበረና የተመሰገነ ይሁን። እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! እንደሚታወቀው አዲስ ዓመት ሲመጣ የጊዜያት መለወጥና የዘመን መፈራረቅ ብቻ ሆኖ እኛ የሕይወት መታደስ ሳይኖረው እጅግ ብዙ ዓመታትን አሳልፈናል። በሥራችን፣ በመውጣታችን፣ በመግባታችን፣ በንግግራችን፣ በሀሳባችን…. አምላካችን እግዚአብሔርን ስናሳዝን ቆይተናል። ያለፈውን ዓመት በንስሐ፣ በኃዳጌ በቀል ልብና በይቅርታ ቋጭተን አዲሱን ምዕራፍ በፍቅር፣ በሰላም፣ በበጎ ሥራ ሁሉ ልንጀምረው ካልቻልን የዘመን መፈራረቅ በራሱ ዋጋ ያለው ነገር ሆኖ ብቻውን ሊቆም እንደማይችል ግልጽ ነው። የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምዕመናን እና ምዕመናት እኛ ክርስቲያኖች ተብለን በክርስቶስ ስም እየተጠራን ነገር ግን ክርስቶስ ያላስተማረንን ቂም፣ በቀል እና ዘረኝነትን ገንዘብ አድርገን የምንኖር ከሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “የሕግ ባለቤት ነን” እያሉ ነገር ግን ሕጉን የማይጠብቁትንና በግብዝነት የሚኖሩትን አይሁድን በሮሜ መልእክቱ “የእግዚአብሔር ስም በእናንተ ምክንያት በአህዛብ መካከል ይሰደባልና” ብሎ እንደገሰጸ እኛም እርስ በእርሳችን በይቅርታና በአንድነት በመቆም የክርስቶስን ፍቅርና ቸርነት በሕይወታችንና በሥራችን መግለጽ ካልቻልን ዛሬም ይህ መልእክት ለእኛ ነው። ውድ ምእመናን ለሀገረ ስብከታችን፣ ለቤተክርስቲያናችንና ለሀገራችን ሰላም፣ ዕርቅና አንድነት የበኩላችንን ክርስቲያናዊ ኃላፊነት እንድንወጣ አደራ እንላለን። በአዲሱ ዘመነ ሉቃስ ሀገረ ስብከታችን የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ከዚህ በላይ ተዳራሽነቱን ይበልጥ ለማስፋት፣ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን ለመደገፍ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችን ለማስፋፋት፣ ወጣቶችን በሃይማኖትና በበጎ ምግባር ለማነጽ፣ እንዲሁም የተቸገሩትንና ደካሞችን በመደገፍ ረገድ የተጀመሩ ዐበይት መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሥራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል። ለዚህም ቅዱስ ዓላማ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የምትገኙ ምዕመናን የምታደርጉትን ያልተገደበ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ድጋፍ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። አዲሱ የ2019 ዓመተ ምሕረት ለሀገራችን ኢትዮጵያና ለመላው ዓለም የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና እና የበረከት ዓመት እንዲሆንልን ወደ እግዚአብሔር አምላካችን እንጸልያለን። የዘመነ ኦሪት መጨረሻ፣ የዘመነ ሐዲስ መነሻ፣ በአጥማቂነቱ ካህን፣ የዓለምን ኃጢአት ይቅር የሚል ከእኔ በኋላ ይመጣል በማለቱ ነቢይ እና ስለክርስቶስ ሕይወቱን በመስጠቱ ሰማዕት ከሆነው ከቅዱስ ዮሐንስ ረድኤት በረከት ያድለን። እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ!አባ ገሪማየጌዴኦ ኮሬ እና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል                    ዲላ/ኢትዮጵያ

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አዲሱን ዓመት የሁለት ሺህ አሥራ ዘጠኝ ዓመተ ምሕረት ዘመነ ሉቃስን በማስመልከት የሰጡት የእንኳን አደረሳችሁ አባታዊ መልእክት! Read More »

Scroll to Top