በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

Public Relation

ከአራቱ ወረዳ ለተውጣጡ ከቋንቋ ሰባኪያነ ወንጌል ጋር ውይይት ተደረገ!!

ከአራቱ ወረዳ ለተውጣጡ ከቋንቋ ሰባኪያነ ወንጌል ጋር ውይይት ተደረገ!! በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ከአራት ወረዳ ቤተክህነት ማለትም ከመንበረ ጵጵስናና ወናጎ፣ ከይርጋጨፌ፣ከኮቸሬና ገደብ ፣ከቡሌና ረጴ ወረዳዎች ከተውጣጡ በጌዴኡፋ ቋንቋ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ከሚሰጡ ሰባኪያነ ወንጌል ጋር ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ጋር ውይይት ተደረገ። ውይይቱ ከቤተክርስቲያን ካህናት ማሰልጠኛ ተመርቀው ወጥተው ምን አከናወኑ፣የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሲሰጡ የገጠማቸው ተግዳድሮት ነበረ፣ለገጠማቸው ችግር የወሰዱት የመፍትሔ ሃሳብ ምን ነበር፣በአገልግሎት የተገኘው ውጤት ምን ነበር፣ያሉትን ለማጽናት የጠፉትን ለመመለስ አዳዲስ ኢአማንያንን ለማምጣት ምን አከናወኑ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን። ሰባኪያነ ወንጌሉ በአገልግሎት ላይ የገጠማቸውን ችግር ያነሱ ሲሆን መስዋዕትነት እስኪከፍሉ ድረስ ዋጋ መክፈላቸው ሰንበት ት/ቤት ማደራጀት ባዕድ አምልኮ ማጥፋት ብዙ ኢአማኒያን ማስጠመቅ ኮርስ መስጠት በማኀበራዊ ሕይወት መሳተፍ በሀዘንና በደስታ ስብከተ ወንጌል መስጠት የሚሉ የአገልግሎት ተግባራትን የዘረዘሩ ሲሆን። በቀጣይ ከተከናወነው ያልተሰራው ስለሚበዛ በቁጭት በቋንቋ ለማስተማር ቃል ገብተዋል። የሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሀብታሙ አበበ በሰጡት አስተያየት ለተጠራንበት አገልግሎት ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባ ከጠባቂነት መውጣትና በዕቅድና በዓላማ ማገልገል አገልግሎታቸው ሁሉ በውጤት የታጀበ መሆን እንዳለት በተለይ ያሉትን በማጽናትና መጠበቅ የጠፉትን ማምጣት አዳዲስ አማኒያንን ወደ ክርስትና በማምጣት ላይ አገልግሎታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አንስተዋል። በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በማጠቃለያው የስብከተ ወንጌል በሚገባ አገልግሎት አልተፈጸም የቤተክርስቲያንን ተልዕኮ በአግባቡ አውቆ ያለመፈጸም ሰባኪ ከጠባቂነት መውጣት ለዚህ አገልግሎት የተጠራን ባለዕዳዎች መሆንናችንን አንስተው የማሳመኑን የማስተማሩን ሥራ በአግባቡ መወጣት አለብን ብለዋል። በየመንደሩ የስብከተ ወንጌል ኬላ ማቋቋምና አገልግሎትን መፈጸም በማኀበራዊ ሁነቶች ላይ መሳተፍ በቁርጠኝነት ወንጌልን ማገልገል እንደሚያስፈልግ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት መክፈል እንደሚገባ አሳስበው በቀጣይ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ፕሮጀክት የተወጋጀና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሥምሪት እንደሚሰጥ በማሳሰብ ውይይቱ ተጠናቋል ።

ከአራቱ ወረዳ ለተውጣጡ ከቋንቋ ሰባኪያነ ወንጌል ጋር ውይይት ተደረገ!! Read More »

በዲላ መዝገበ ምሕረት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው ሁለተኛ ቀን መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ።

በዲላ መዝገበ ምሕረት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው ሁለተኛ ቀን መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ። በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት በመዝገበ ምሕረት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ጽንሰት በማስመልከት የተዘጋጀው መንፈሳዊ ጉባኤ ሁለተኛ ቀን ተጠናቋል። በጉባኤው የሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ሊቀ ትጉሃን ሀብታሙ አበበ፣ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጠበብት መሪጌታ መሰረት ይልማ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ምሕረት ቀሲስ ሰናይ፣ ሰባኪያነ ወንጌል እና ዘማሪያን፣ የደብሩ ካህናትና ዲያቆናት፣ በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል። በጉባኤው የበገና ዝማሬ፣ ትምህርተ ወንጌል በተጋባዥ መምህራን፣ ዝማሬ የተሰጠ ሲሆን ጉባኤው ዛሬም እንደሚቀጥል ተገልጾ የመርሃግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።

በዲላ መዝገበ ምሕረት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው ሁለተኛ ቀን መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ። Read More »

በሐሩ እግዚአብሔር ወልድ ቤተክርስቲያን በዓለ ጽንሰት በመንፈሳዊ ክብር ተከበረ።

በሐሩ እግዚአብሔር ወልድ ቤተክርስቲያን በዓለ ጽንሰት በመንፈሳዊ ክብር ተከበረ። በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተክህነት ሥር የሚገኘው በሐሩ እግዚአብሔር ወልድ ቤተክርስቲያን የጽንሰት በዓል የይርጋጨፌ ወረዳ ቤተክህነት ዋና ፀሐፊ መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ብዙአየሁ ዳመና የደብሩ አስተዳዳሪ ካህናትና የሐሩና የአካባቢው ምዕመናንን በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ክብር ተከበረ። በዕለቱም ይርጋጨፌ ወረዳ ቤተክህነት ዋና ፀሐፊ መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ብዙአየሁ ዳመና ለዕለቱ የሚስማማ የጌታን ዓለምን ለማዳን ከቅድስት ድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ግብር በቅዱስ ገብርኤል ብስራት መጸነሱን ዓለምን ለማዳን የተጠቀመውን የፍቅር ጥበብ በሰፊው በመግለጽ አስተምረዋል። በመጨረሻም ለቤተክርስቲያኑ የልማት ሥራ የገቢ ማስገኛ ሥራ ምዕመናንን በማስተባበር ከተከናወነ በኋላ ጸሎትና ቡራኬ ተሰጥቶ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

በሐሩ እግዚአብሔር ወልድ ቤተክርስቲያን በዓለ ጽንሰት በመንፈሳዊ ክብር ተከበረ። Read More »

ለሁለት ቀን የሚቆይ ሥልጠና ተጀመረ!!

ለሁለት ቀን የሚቆይ ሥልጠና ተጀመረ!! በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ለሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች ከሀገረ ስብከቱ ከሁሉም ወረዳ ቤተክህነት እንዲሁም አድባራት ለተወከሉ ሥራአስኪያጅና አስተዳዳሪዎች ካህናት የአስተዳደር ሠራተኞች ለሁለት ቀን የሚቆይ ሥልጠና በሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ በተገኙበት በዲላ ዋለሜ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን አዳራሽ በጸሎት ተጀመረ። ሥልጠናውን የሚሰጡት የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳት ፕሮፌሰር አባ ኃይለ ገብርኤል ሲሆኑ ሥልጠናውን ሰልጣኞች በቡድን ውይይት እንዲሳተፉና የውይይቱን ውጤት ለተሳታፊ እንዲያቀርቡ በማድረግ በርዕሰ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በመስጠት ነው። #ሥልጠናው በኦርቶዶክሳዊ አገልግሎት ዙሪያ የተሰጠ ሲሆን ልዩ ልዩ አስረጂዎችን ከቡሉይ እና ሀዲስ ኪዳን በማቅረብ የቅዱሳን አባቶችን መጽሐፍት በዋቢነት በማቅረብ አካባቢን በማየት ከሚታወቀው ነገር በመነሳት ግልጽና አሳታፊ በሆነ አቀራረብ ጥልቅ ምሥጢራትን በመግለጽና በማሳየት እየቀረበ ያለ ሥልጠና ነው። ሁሉም ሠልጣኝ በመመልስ ፣በመጠየቅና በንቃት በመከታተል ሥልጠናውን እየተሳተፈ ይገኛል። #የመጀመሪያው ቀን ሥልጠና የተጠናቀቀ ሲሆን ነገም እንደሚቀጥል የወጣው መርሐ ግብር ያመለክታል።

ለሁለት ቀን የሚቆይ ሥልጠና ተጀመረ!! Read More »

Scroll to Top