በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

Public Relation

በብፁዕነታቸው መሪነት ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በሀገረ ስብከቱ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ!

​ኤክቱስ የካቲት 2/2018 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ገሪማ ​የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መሪነት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪና የኢቢሲ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በሀገረ ስብከቱ የሚከናወኑ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። ​በመጀመሪያነት የተጎበኘው በአንዲዳ የሚገኘው የአዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት ሲሆን፤ የመማር ማስተማር ሂደቱ፣ የአብነት ትምህርት ቤቱ ራሱን ለማስቻል ከሚሠሩ የግብርና ሥራዎች መካከል የዶሮ ፕሮጀክት፣ እንዲሁም የመማርያ፣ የመመገቢያ፣ የማደርያ እና የጽሕፈት ቤት ክፍሎች ተጎብኝተዋል። በመቀጠልም በዳማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኘው የእንሰት ልማትና የንብ ማነብ ሥራዎች የተጎበኙ ሲሆን፤ ሀገረ ስብከቱ የሚያስገነባው የመንበረ ጵጵስና ሕንጻ ግንባታም ተመልክተዋል። ​በመጨረሻም በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሚሠሩ የውኃ እና የዶሮ ፕሮጀክቶችን የጎበኙ ሲሆን፤ ክቡር ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ ቤተክርስቲያኗ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግና ራሷን ለመቻል እያከናወነች ያለችውን ዘርፈ ብዙ የልማት እንቅስቃሴ አድንቀዋል።

በብፁዕነታቸው መሪነት ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በሀገረ ስብከቱ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ! Read More »

​H.G. Abune Gerima Receives Muhaze Tibebat Daniel Kibret at His Office!

​Ektus, February 9, 2026 ​His Grace Abune Gerima, Bishop of the Gedeo, Kore, and Burji Diocese and member of the Holy Synod, received Muhaze Tibebat Daniel Kibret, Advisor to the Prime Minister on Social Affairs and Chairperson of the EBC Board, at his office. During the visit, His Grace delivered a detailed presentation regarding the historical background and the current developmental activities of the Diocese. ​In his briefing, His Grace explained that the primary focus and goal of the Diocese is to elevate the Holy Church to a better level. Accordingly, he noted that the Church is currently undertaking various development projects that benefit the community. However, His Grace presented the challenges and resource limitations encountered in these developmental works to the Honorable Minister. ​Following the conclusion of this program, a visit was conducted to the development projects being carried out by the Diocese.

​H.G. Abune Gerima Receives Muhaze Tibebat Daniel Kibret at His Office! Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረትን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ!

ኤክቱስ የካቲት 2/2018 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ገሪማ ​የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የጠቅላይ ሚኒስትር የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪና የኢቢሲ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረትን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። በቆይታቸውም ስለ ሀገረ ስብከቱ ታሪካዊ ዳራና አሁናዊ የልማት እንቅስቃሴ ዝርዝር ገለጻ አቅርበውላቸዋል። ​ብፁዕነታቸው በገለጻቸው ወቅት የሀገረ ስብከቱ ትኩረትና ፍላጎት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ወደተሻለ ደረጃ መሆኑን አብራርተዋል። በዚህም መሠረት ቤተክርስቲያኗ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ የልማት ፕሮጀክቶችን በማከናወን ላይ እንደምትገኝ አስረድተዋል። ​ይሁን እንጂ በእነዚህ የልማት ሥራዎች ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶችንና የግብዓት እጥረቶችን ለክቡር ሚኒስትሩ አቅርበዋል።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረትን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ! Read More »

​Official Sales Announcement

​The modern poultry farming project at Dilla Debre Genet St. Michael Church, under the Gedeo, Kore, and Burji Diocese and the Dilla and Wanago Woreda Bete-Kihnet, is officially presenting its products to the faithful and the local community. ​In line with the Diocese’s initiative to ensure the Holy Church’s self-sufficiency and to serve the public, this project has been realized through the coordination of Laeke Wongel Yared Ademe in partnership with the International Livestock Research Institute (ILRI). We are now offering high-quality, health-compliant, and modernly raised chickens for sale. ​Our products are raised with exceptional care using advanced methods and are supplied directly from the farm to the consumer at highly affordable prices. ​📍 Location: Dilla Debre Genet St. Michael Church Poultry Farm Site ⏰ Sales Dates: February 8–15, 2026 (Yekatit 1–8, 2018 E.C.) during regular working hours. ​“Peace be within thy walls, and prosperity within thy palaces.” (Psalm 122:7)

​Official Sales Announcement Read More »

የሽያጭ ማስታወቂያ

​በጌዴኦ ኮሬና እና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላ እና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት ስር በሚገኘው በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሲከናወን የቆየው የዘመናዊ ዶሮ እርባታ ፕሮጀክት፤ አሁን ላይ ውጤቱን ለምዕመናንና ለአካባቢው ነዋሪዎች ማቅረቡን በደስታ ይገልጻል። ​ይህ የልማት ስራ ሀገረ ስብከቱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን በልማት ራሷን ለማስቻልና ማኅበረሰቡን ለማገልገል በጀመረው እንቅስቃሴ መሠረት፤ ዓለም አቀፉ የእንስሳት ምርምር ተቋም “International Livestock Research Institute (ILRI)” ከላዕከ ወንጌል ያሬድ አደመ ጋር በጋራ በመሆን የተከናወነ ሲሆን ጥራት ያላቸውና ለጤና ተስማሚ የሆኑ የሥጋ ዶሮዎችን ለሽያጭ አቅርቧል። ​ምርቶቻችን በዘመናዊ መልክና በከፍተኛ እንክብካቤ ያደጉ፣ እንዲሁም በቀጥታ ከእርባታ ጣቢያው ለተጠቃሚ የሚቀርቡ በመሆናቸው በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲጠቀሙ ተጋብዘዋል። ​📍 የሽያጭ ቦታ፦ ዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የዶሮ እርባታ ሥፍራ ⏰ የሽያጭ ቀንና ሰዓት፦ ከየካቲት 1 – 8 ቀን 2018 ዓ.ም (ዘወትር በሥራ ሰዓት) ​“በኃይልህ ሰላም ፥ በጌጠኛ ቤትህም ልማት ይሁን” (መዝ 122፥7)

የሽያጭ ማስታወቂያ Read More »

Training on Entrepreneurship and Basic Beekeeping Commences in the Diocese!

​Ecthus: January 26, 2026 (Tir 18, 2018) ​In the Gedeo, Kore, and Burji Diocese, a training program focused on entrepreneurship kicked off today. The initiative aims to empower local churches (Adbarat) to become self-reliant, move away from dependency, and enhance their creative business skills. Scheduled to run for three consecutive days until January 20, the training is part of a strategic plan designed for staff and representatives of churches under the Dilla and Wanago (Episcopal Seat) District Administrations. ​The opening session was attended by high-ranking officials, including Melake Haywot Birhanu Kifle, General Manager of the Diocese; Melake Birhan Atnafu Mamo, General Secretary of the Diocese; various diocesan department heads; the General Manager of the District Administration; and administrators and representatives of several local churches. ​The training is being conducted by ICIPE (International Centre of Insect Physiology and Ecology), a non-governmental international organization renowned for its expertise in beekeeping, sericulture (silk farming), and renewable energy. Leveraging its extensive experience, ICIPE is sharing vital knowledge with church ministers and staff. While today’s session focused on entrepreneurship and skill development, the upcoming days are expected to cover practical, hands-on training in basic beekeeping. ​The primary objective of this training is to enable the Holy Church to become self-sufficient through various developmental sectors. This shift is intended to ensure that the “Mudaye Mitswat” (alms collection) is dedicated solely to its intended charitable and spiritual purposes. Participants have been directed to implement the knowledge gained within their respective local churches and take a leading role in efforts to bolster the institution’s internal revenue.

Training on Entrepreneurship and Basic Beekeeping Commences in the Diocese! Read More »

በሀገረ ስብከቱ የሥራ ፈጠራ ማዳበርና መሠረታዊ የንብ ማነብ ሥልጠና ተጀመረ!

ኤክቱስ በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት፤ አድባራት ከልመና እንዲላቀቁ፣ በገቢ ራሳቸውን እንዲችሉና የሥራ ፈጠራ ችሎታን ለማዳበር በሥራ ፈጠራ ዙሪያ የሚያተኩር ሥልጠና በዛሬው ዕለት ተጀምሯል። እስከ ጥር 20 ቀን ድረስ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው ይህ ሥልጠና፤ በዲላና በወናጎ (በመንበረ ጵጵስና) ወረዳ ቤተ ክህነት ስር ለሚገኙ አድባራት ሠራተኞችና ተወካዮች ታስቦ የተዘጋጀ የዕቅድ አካል ነው። በዛሬው መርሐግብር ላይ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ መልአከ ብርሃን አጥናፉ ማሞ፣ የሀገረ ስብከቱ የክፍል ኃላፊዎች፣ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎችና ተወካዮች ተገኝተዋል። ይህንን ሥልጠና እየሰጠ የሚገኘው በንብ ማነብ፣ በሐር ትል እና በታዳሽ ኃይል ዙሪያ የሚንቀሳቀሰው ICIPE (International Centre of Insect Physiology and Ecology) የተባለ ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው። ድርጅቱ በዘርፉ ያለውን የረዥም ጊዜ ተሞክሮ ለቤተክርስቲያኗ አገልጋዮችና ሠራተኞች እያካፈለ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ውሎ በሥራ ፈጠራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ከዋለ በኋላ በቀጣዮቹ ቀናት ደግሞ በመሠረታዊ የንብ ማነብ ሙያ ላይ ተግባራዊ ትምህርቶች እንደሚሰጡ ይጠበቃል። የዚህ ሥልጠና ዋና ዓላማ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ የልማት መስኮች ተሰማርታ በገቢ ራሷን እንድትችል ማስቻል ነው። ይህም በቤተክርስቲያን የሚሰበሰበው “ሙዳየ ምጽዋት” ለታለመለት ለምጽዋት ተግባር እንዲውል ለማድረግ የሚረዳ መሆኑ ተመልክቷል። ተሳታፊዎችም ከሥልጠናው የሚገኘውን ዕውቀት ወደየአጥቢያቸው በመውሰድ ተግባራዊ እንዲያደርጉና የተቋሙን የውስጥ ገቢ ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆኑ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በሀገረ ስብከቱ የሥራ ፈጠራ ማዳበርና መሠረታዊ የንብ ማነብ ሥልጠና ተጀመረ! Read More »

1,683 New Believers Receive the Grace of Divine Sonship During Epiphany!

​ICTHUS January 21, 2026 (Tir 13, 2018 EC)​ In the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, within the Diocese of Gedeo, Kore, and Burji, 1,683 new believers were baptized and received the Grace of Divine Sonship during the celebrations of the Epiphany (Timket) and Kana Ze Gelila of our Lord and Savior Jesus Christ. ​The distribution of the new converts across the district (Woreda Bete kihnet) is as follows: 408 within the Dilla and Wonago Bete kihnet (the See of the Bishopric), 524 in the Yirgacheffe district, 191 in the Kochore, Gedeb, and Chorso district, 88 in the Bule and Reppe district, 301 in the Kore zone district, and 171 in the Burji zone district. All have received the Sacrament of Baptism and the Grace of Sonship. ​The Diocese is currently undertaking extensive work by assigning gospel preachers who teach in local languages to reach and baptize non-orthodoxy in the region. ICHTHUS GEDEO KORE AND BURJI DIOCESE PUBLIC RELATION DEPARTMENT

1,683 New Believers Receive the Grace of Divine Sonship During Epiphany! Read More »

አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ሦስት አዳዲስ አማንያን በበዓለ ጥምቀት ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አገኙ!

ኤክቱስ ጥር 13/2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በዓላት ላይ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ሦስት አዳዲስ አማንያን ተጠምቀው የሥላሴን አግኝተዋል። በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት 408፣ በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተ ክህነት 524፣ በኮቾሬ ገደብና ጮርሶ ወረዳዎች ቤተ ክህነት 191፣ በቡሌና ረጴ ወረዳዎች ቤተ ክህነት 88፣ በኮሬ ወረዳ ቤተ ክህነት 301፣ በቡርጂ ወረዳ ቤተ ክህነት 171 አዳዲስ አማንያን ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል። ሀገረ ስብከቱ ኢ-አማንያንን ለማስጠመቅ በአከባቢው ቋንቋ የሚያስተምሩ ሰባኪያነ ወንጌል በመመደብ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል።

አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ሦስት አዳዲስ አማንያን በበዓለ ጥምቀት ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አገኙ! Read More »

<<ምልእዎንኬ ለእላ መሣብክት ማየ -ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው >>  ዮሐ 2:7

➠ በወርኃ ጥር ከሚከበሩ ዐበይት በዓላት መካከል ጥር 12 ቀን  የሚከበረው  የገሊላ ክፍል በሆነችው በቃና ሰርግ ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገው ታላቅ ተአምር አንዱ ነው ።<<ነገርን ከስሩ ውኃን ከጥሩ >> እንዲሉ  አበው ነገሩም እንዳህ ነበር  ። አካል ከህልውና ተገልጾለት  የሥላሴን አንድነት ሦስትነት በስፋትና በጥልቀት የተናገረው ነባቤ መለኮት በመባል የሚታወቀው  ባለ ራእዩ ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ   <<በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ >>  በማለት ሙሉ ታሪኩን ይጽፋል  ።➠ ይህም ሰርግ የተደረገው የካቲት 23 /30 ዓ ም ሲሆን የውኃን በዓል ከውኃ በዓል ( የጥምቀትን በዓል የውኃው  ወደ ጠጅነት መለወጥ በዓል ) ጋር እንዲከብር አባቶቻችን ስለ ወሰኑልን  የጥምቀት ማግስት ጥር 12  በቃና ዘገሊላ ኢየሱስ ክርስቶስ በእመቤታችን አማላጅነት ያደረገው ታላቅ ተአምር በደማቅ ሁኔታ ይከበራል  ። አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዕዳ ደብዳቤያችንን ይደመስስልን  ዘንድ ( ቆላ 2:4) ጥር  11 ቀን ዕለተ እሑድ  በእደ ዮሐንስ በማየ ዮርዳኖስ ተጠምቆ ( ማቴ 3:17) ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ ልጅነቱን አስመስክሮ ሳይውል ሳያድር ገዳመ ቆሮንቶስ ሄደ ( ማቴ 4:1) ። በገዳመ ቆሮንቶስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ በሦስቱ አርእስተ ኃጣውእ የመጣውን ሰይጣን ድል ነስቶ የካቲት 20 ቀን በዕለተ ቀዳም ከገዳመ ቆሮንቶስ ወጥቶ ቅዳሜ ለእሑድ  ገሊላ ገብቶ አድሯል ።   የገሊላ ክፍል በሆነችው በቃና  የተደረገውም ሰርግ ጌታ ከገዳም ከወጣ በሦስተኛው ቀን ማለትም  ማክሰኞ   ነበር ።  የዚህ ሰርግ ባለቤት ዶኪማስ ሲሆን በሰርጉ ላይ ይታደሙ ዘንድ ከወንድ እስከ ሴት ከመምህር እስከ ደቀ መዝሙር ያልጠራው አካል ከቶ አልነበረም ። ➠ የሚደንቅ ሰርግ ! ታዋቂ ስዎች ከላይ  ምስኪኖች  ከታች ፤ መምህሩ ከቤት ውጥ ደቀ መዛሙርቱ ከቤት ውጭ ያልታደሙበት ፤ሁሉም አብረው ያከበሩት ሰርግ ነበር ። በአምላካችን የተባረከ ፣  እመቤታችንና ሐዋርያት የተገኙበት ሰርግ ! የሙሽራው የዶኪማስ ልብ እንዴ በደስታ ይመላ ይሆን  ? ትዳሩስ እንዴት ያምር  ? ምንኛ  መመረጥ ምንኛስ መታደል ነው ! የጋብቻን ቅዱስነትና ክቡርነት የተማርነውም በሰርግ ቤት ተገኝቶ   ሰርግን ከባረከው  የቤተ ክርስቲያን ሙሽራዋ ከሆነላት ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።ብዙዎች  ግን ጋብቻን የሚረዱበትና የሚኖሩበት ሕይወት የተስተካከለ ባለመሆኑ መሰላቸትና መናቆር የበዛበት ይሆናል ። በየፍርድ ቤቱ ሳይቀር በስፋት ያለውም ጉዳይ የፍች ጉዳይ ነው ።➠ ### ጋብቻ በባልና ሚስት ፈቃድ ብቻ የሚመሠረት አይደለም ፤ በእግዘብሔር ፈቃድ ጭምር እንጂ ። ጋብቻ ስንፈልግ የምንገባበት ሳንፈልግ ደግሞ የምንወጣበትም አይደለሞ ፤ እስከ መጨረሻ የምንኖርበት እንጂ ። ጋብቻ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የሚፈጸም ፣ ሁለቱም አካላት አንድ የሚሆኑበት ምሥጢርም ነው  ( ሜቴ  19:6) ።   ጋብቻ የተበረከ ስለሆነ  የተበረኩ ልጆችም የሚገኙበት ነው (ዕብ 13:4)  ። የሚገርመው  ሰዎች ራሳቸው ያልፈለጉትን ግን በልጆቻቸው እንዲፈጸሙ የሚፈልጓቸው ሁለት ነገሮች አሉ ።1, የሰርጋቸው ቀን ከቤተ ክርስቲያን ጋር ሳይተዋወቁ የክርስትና  ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጡ ሰዎች ሲሆኑ2, ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ በሆነ ጋብቻ የተጋቡ ሰዎች ልጆቻቸው ሥርዓት ባለመያዛቸው የሚያዝኑ ሰዎች ናቸው ።  ### ልጆች ሥርዓትን ከማን  ይማሩ  ? ማንንስ ይከተሉ ? ተጠያቂውስ ማን ነው ?አሁን በአለንበት ዘመን  በዓለም ላይ ሥርዓት አልባነት ከተስፋፋባቸው መንገዶች መካከል የጋብቻ ሥርዓት መረሳቱና ክቡር በሆነው ጋብቻ የሚወለዱ ልጆች አለመኖራቸው አንዱ ይመስለኛል ። ➠ የእመቤታችን አማለጅነት የሰርጉም ታዳሚዎች ወደ መጡበት ሳይመለሱ ለሰርጉ ይበቃል ተብሎ የታሰበው የወይን ጠጅ ድንገት አለቀ፣ አገልጋዮች የሚያደርጉት አጥተው በጭንቀት ተውጠው ሰማይ ምድሩን ማየት ጀመሩ ፣የአገልጋዮች ፊት ጠቆረ ፣ አንገታቸውንም ደፉ ፤  ማጣት  ክፉ ነውና ያውም በሰርግ ቀን ሰው በተሰበሰበበት  !ነገር ግን ይህን ጭንቀታቸውን ያየችው እመቤታችን ማንም ሳይነግራት  << የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም >>  ስትል ነበር  ወደ ልጇ  የማማለድ ስራዋን ያቀረበችው ።  አምላካችንም የእመቤታችንን ምልጃ ከሰማ በኋላ << አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም >>  አላት ፤ ማለትም አንቺ ያልሽኝን ላለማድረግ ምን ጠብ  አለኝ አደርግልሻለሁ ማለት ነው ። ይህም ሊታወቅ << የሚላችሁን አድርጉ >> ነበር ያለችው ፤ ምልጃዋን እንደ ተቀበላት ታውቅ ነበርና ። የእናት ልመና ፊት አያስመልስ አንገት አያስቀልስ ነውና ነገሩ ።➠  ስለ ምልጃዋ ስለ ርኅራኄዋ  <<ፈጣን ደመና >>  ( ኢሳ 19:1) ብሎ ነቢዩ ኢሳይያስ የገለጣት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዛሬም  ቢሆን በአማላጅነቷ  ትረዳናለች ታግዘናለች ። እኛም  << ወበእንተዝ ንስአል ኀቤሃ  ኵሎ ጊዜ ከመ ታስተሥሪ በእንቲኣነ ኀበ ፍቁር ወለዳ ሔርት ይእቲ በኀበ ኵሎሙ ቅዱሳን – ስለዚህ ሁልጊዜ ወደ እርሷ እንለምን ከተወደደ ልጇ ዘንድ ስለእኛ ይቅር ታስብለን  (ታማልደን) ዘንድ በቅዱሳን ዘንድ ቸር ናት >> እያልን እንደ ቅዱስ ኤፍሬም እንማጸናታለን ።➠ ሌላው አሳብ << ጊዜዬ ገና ነው >> የሚለው ነው ።  ይህም ማለት ብዙ ትርጓሜ ቢኖረውም ዋናው አሳብ ግን ምሳሌው  ወይን የሆነለት ክቡር ደሙን  የዓለምን ኃጢአት ለማስተስረይ በመስቀል የሚያፈስበት ጊዜው  ዕለተ ዐርብ ገና ነው ማለቱ ነበር ። ይህውም አልቀረ ጊዜው ዕለተ ዐርብ ሲደር የዓለም ኃጢአት የሚሰረይበትን ክቡር ደሙን እንኩ ጠጡ ብሎ ሰጠን (ማቴ 26:28) ። በዚህ ክቡር ደም የዓለም ኃጢአት ተወገደ (ዮሐ 1:29) ፣ አነጻን ቀደሰን  << በውኂዘ ደሙ ቅዱስ አንጽሖሙ ለመሀይምናን ወለሕዝብ ንጹሓን >> እንዳለ  ቅዱስ ኤፍሬም  የዶኪማስን ሰርግ የፋሲካ ፤ የወይን ጠጁንም የክቡር ደሙ ምሳሌ አደረገው ።ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ብሉ ጠጡ የሚል ለጋስ ያለ እርሱ ማን አለ ?➠ ይህን ድንቅና ረቂቅ የሆነ ቃል በመናገር ዕለተ ሞቱን ከአስተማረ በኋላ የአገልጋዮቹን ጉድለት ይመላ ዘንድ በሰርግ ቤት የተገኘው አምላካችን  << ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው>> ብሎ አዘዘ ። የእመቤታችንን ምልጃ መቀበሉን የምንረዳውም ጋኖች በውኃ እንዲመሉ በማዘዙና ውኃውን ወደ ጠጅነት  በመለወጡ ነው፤ እመቤታችንም  የሚላችሁን አድርጉ ነበርና ያለችው ።ባዶ የነበሩት  ስድስቱም የድንጋይ ጋኖች በውኃ ከተሞሉ በኋላ በአምላካዊ ሥራው በእመቤታችን አማላጅነት ውኃውን ወደ ወይን ጠጅነት ለወጠው ፤ እግዚአብሔር ሲል ሁሉ ይለወጣልና ። ➠ የሰው ልጅ ጉድለት የሚሞላው በምን  ይሆን  ?የእኛስ ሕይወት የሚለወጠው መቼ ነው ? ከላይ ነጭ ነጠላ ለብሰን እንመላለሳለን ውስጣችን ግን በብዙ ነገሮች ጠቁሯል ፣ ሰብከን ስንጨርስ ቃለ ሕይወት ያሰማልን እንባላለን ሕይወት ግን ከሁላችንም ጠፍቷል ፣ ዘምረን ስንጨርስ ከጣዕሙ ብዛት የተነሣ አጥንትን የሚያለመልም የመላእክትን ዝማሬ ያሰማልን እንላለን  ነገር ግን የለመለመና ጣዕም ያለው ሕይወት የለንም ። ➠ በአምላካዊ ትእዛዝ የተለወጠው የወይን ጠጅ ቀድሞ ከነበረው  እጅጉን ጣፈጭ  መሆኑን የቀመሰው አሳዳሪውም   ሙሽራውን  ጠርቶ   << ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል ከሰከሩም በኋላ መናኛውን ፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል >> በማለት በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የተለወጠውን ወይን  ማድነቅ ጀመረ  ። በእርግጥ እግዚአብሔር ያደረገው ነገር በሙሉ ከሁሉ በላይ ነውና   መርምረንና ተናግረን ስለማንጨርሰው  << ናርምም እስመ ኢንክል ፈጽሞ ጥንቁቀ ነጊረ በእንተ ዕበዩ  >>   እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም ሁሉን ቻይ መሆኑን  አድንቀን ዝም እንላለን ። ➠ ይህም ሰርግ የሰርግ ሥርዓት ብቻ የተፈጸመበት አልነበረም ውኃውን ከውኃነት ወደ ወይን ጠጅነት በመለወጡ ምሥጢረ ሥጋዌን በሥራ ገልጦ ያሳየበት ዕለትም ጭምር  እንጂ ፤ በኋላም በኬልቄዶን ጉባኤ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ  የልዮናውያንን አስተምህሮ ማለትም ሁለት ባሕርይ የሚለውን ትምህርት ሲቃወም መልስ የሰጠበት ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነበር ።<< ወደ ሰርግ ቤት የተጠራ  ውኃውን ጠጅ ያደረገ  ማን ነው  ?>>  ብሎ ጠየቀ ። ሥጋ ካላችሁ የሥጋ ወደ ሠርግ ቤት መጠራት አያስደንቅም ፤ ብቻውንም ሥጋ ውኃውን ጠጅ ማድረግ አይችልም ፣ መለኮት ካላችሁ ውኃውን ጠጅ መድረግ ቢችልም ወደ ሰርግ ቤት መጠራት ግን አይችልም ብሎ እረቶበታል

<>  ዮሐ 2:7 Read More »

Scroll to Top