በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ቀዳሚ ገጽ ዜና

እንኳን ደስ አላችሁ!የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ በከፍተኛ የሥራ አፈጻጸም ከምድብ ስድስት በአንደኛ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ!!

ኤክቱስ ጥቅምት 08/2018 ዓ.ም በ44ተኛው ዓለም አቀፍ ጠቅላላ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በከፍተኛ የሥራ አፈጻጸም ማለትም በመልካም አስተዳደር፣ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት፣ ሰበካ ጉባኤን በማጠናከር፣ ሰንበት ትምህርት ቤትን በማደራጀት፣ ራስ አገዝ ልማትን በማስፋፋት፣ በገንዘብ ንብረትና አጠባበቅ፣ በቅርሳቅርስ ጥበቃ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትንና የተለያዩ ኅትመቶችን በማሰራጨት፣ በምግባረ ሠናይ ሥራ ባሳየው ከፍተኛ አፈጻጸም በምድብ 6 ከተካተቱት አህጉረ ስብከቶች መካከል አንደኛ በመውጣት የምስክር ወረቀትና የመቶ ሃምሳ ሲሲ ባለ ሁለት እግር የሞተር ሳይክል ተሸላሚ ሆነ።

እንኳን ደስ አላችሁ!የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ በከፍተኛ የሥራ አፈጻጸም ከምድብ ስድስት በአንደኛ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ!! Read More »

3372 አዳዲስ አማንያንን ማስጠመቁን የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ገለጸ!!

ኤክቱስ ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ከተጀመረ ሁለተኛ ቀኑን በያዘው ፵፬ተኛው ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በ2017 በጀት ዓመት ያሳካውን የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ሪፖርት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ አቅርበዋል። በሪፖርቱ እንደተገለጸው ሀገረ ስብከቱ በበጀት ዓመቱ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የቤተ ክርስቲያንን ልጆች በማስተባበር የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን እንዳስከፈቱ የተገለጸ ሲሆን በሁሉም ወረዳ ቤተ ክርስቲነት በመዘዋወር ሀዋርያዊ አገልግሎታቸውን መፈጸማቸውም ተገልጿል። የአብነት ትምህርት ቤትን በተመለከተ በአንዲዳ ለመጀመርያ ዙር የአብነት ተማሪዎች የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በሟሟላት እና የቅዳሴ መምህር በመቅጠር ትምህርት እንዲሰጥ እንደተደረገ ተገልጿል። በተጨማሪም በሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት ከ20 በላይ በተመረጡ አብያተ ክርስቲያናት ሕዝባዊ መንፈሳዊ ጉባኤያት የተደረገ ሲሆን በስድስቱም ወረዳ ቤተ ክህነቶች ካለፈው ዓመት በተሻለ መልኩ 3372 አዳዲስ አማንያን መጠመቃቸውን ገልጸዋል።

3372 አዳዲስ አማንያንን ማስጠመቁን የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ገለጸ!! Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኘው የአረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለጹ!!

“ይቤዙ እግዚአብሔር ነፍሰ አግብርቲሁ ወኢይኔስሑ ኩሎሙ እለ ይትዌከሉ ቦቱ – የባርያዎቹን ነፍስ እግዚአብሔር ይቤዣል በርሱም የሚያምኑ ሁሉ አይጸጸቱም”መዝ 33፥22 በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ሥር በሚገኘው አረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም በሕንጻ ግንባታ ምክንያት ለፊኒሽንግ ሥራ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ እስካሁን በሚያሳዝን ሁኔታ በውል ያልታወቁ ወገኖቻችን ሕይወታቸው ማለፉን ከሀገረ ስብከቱ ሚዲያ ስንሰማ እጅግ ከልባችን አዝነናል። ለሞቱት ወገኖቻችን እግዚአብሔር አምላካችን ሀገረ ሕይወትን መንግስተ ሰማያትን እንዲያወርስልን ከቅዱሳን ማኅበር እንዲደምርልን፤ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንዲልክን ጸሎታችን ነው። እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ! አባ ገሪማየጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባልመስከረም 21/2018 ዓ.ም

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኘው የአረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለጹ!! Read More »

‎ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለ2018 አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር ለሚገኙ፣ የሀገሪቱን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ ለቆሙ፤ በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ለሚገኙ ብሎም የሕግ ታራሚዎች ሆነው በየማረሚያ ቤቱ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት፤ “እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ስምንት ዓመተ ምህረት የርእሰ ዐውደ ዓመት በዓል አደረሳችሁ!” ሲሉ የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።‎‎ቅዱስነታቸው በአባታዊ መክልዕታቸው፤ “የሰው ልጅ ከፍጥረታት ሁሉ የተለየ ክብርና ደረጃ እንዳለው በቅዱስ መጽሐፍ በተደጋጋሚ ተገልጾአል፣ ልዩ የሚያደርገውም ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ነው፣ ሰው ልዩ ፍጡር መሆኑን ከሚገለጽባቸው መካከል እግዚአብሔር በሦስትነቱ “ሰውን በአርአያችንና በአምሳላችን እንፍጠር በሚል ልዩ አገላለጽ መፈጠሩ፣ አፈጣጠሩም በእግዚአሔር መልክና አምሳል መሆኑ፣ በእግዚአብሔር እፍታ ሕያው ነፍስ እንዲኖረው መደረጉ፤ በሥልጣንም የፍጥረታት ሁሉ የበላይ ሆኖ መሾሙ ከሌሎች ፍጥረታት ልዩ ያደርገዋል” ብለዋል፡፡‎‎”እኛ ሰዎች የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ ሆነን እንድንኖር በእግዚአብሔር ስንፈጠር በሕይወት እንድንኖር ነው፣ እግዚአብሔር በምድር ላይ በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ሰውን ከአንድ ፈጠረ የሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮም ይህንን ያመለክታል” ሲሉም ተናግረዋል፡፡ አክለውም “ሰዎች በምድር ላይ በሕይወት እንዲኖሩ የተፈጠሩ ሆነው እያለ በሕይወት እንዳይኖሩ ማድረግ ከፈቃደ እግዚአብሔር ጋር መጋጨትን ያስከትላል በዘመናችን ዓለማችንን እየፈተነ ያለው ተቀዳሚ ፈተና ሰዎች በሕይወት እንዳይኖሩ የማድረግ ዝንባሌ ነው” ብለዋል።‎‎”እንደዚህ ዓይነቱ ዝንባሌ በዓለም ባይኖር ኖሮ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ድሆች ባሉበት ዓለም ለሰው ልጅ ሕይወት ማጥፊያ የሚሆን መሳሪያ ለማምረት ቁጥር ስፍር የሌለው ገንዘብ አይወጣም ነበር” በማለትም ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።‎‎ስለሆነም በሕይወት እንዲኖር የተፈጠረውን ሰው በሕይወት የመኖር መብቱን ከመንፈግ መቆጠብ የአዲሱ ዓመት ትልቁ አጀንዳ አድርገን ብንወስድ ለሁላችንም ይበጀናል በማለት አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።‎‎ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አክለውም፤ “ለኑሯአችን የሚያስፈልገንን ፍጆታ በበቂ ሁኔታ እንድናገኝ ላባችንን አንጠፍጥፈን መስራት ይገባናል፣ ይህም ከሠራን ያለጥርጥር የምናገኘው ነው፤ ሁለቱም የጎደሉብን በኛ አስተሳሰብ፣ አሠራርና አጠቃቀም እንጂ እግዚአብሔር ሳይፈቅድልን ቀርቶ ወይም ነፍጎን አይደለም”ብለዋል።‎‎ነገር ግን እኛ በምንራመድበት በእግራችን ሥር ያለውን ሀብት ትተን በሩቅ ያለውን ስንመለከት ሁሉን ያጣን ሆነን በችግር ወድቀን እንገኛለን፤ በተለይም እኛ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ጊዜ እየተፈታተነን ያለው ይኸው የተሳሳተ እሳቤ ነው ብለዋል።‎‎”ኢትዮጵያ የሁላችንም ኢትዮጵያውያን አድርገን በማመን በእኩልነት፣ በአንድነትና በስምምነት ከመጠቀም ይልቅ ያ የኔ ነው ያም የኔ ነው በሚል አባባል ምን ያህል ዋጋ እየተከፈለ እንደሆነ እያየን ነው፣ ይህ ግለኝነት ያየለበት አስተሳሰብ ገታ አድርገን በእኩልነትና በአብሮነት የሚያሳድገንን አስተሳሰብ የተሻለ መግባቢያ ሊሆን ይችላል፣ አዲሱ ዓመት በአዲስ እሳቤ ካላጀብነው አዲስ ሊሆን አይችልም” በማለት ገልጸዋል።‎‎ስለሆነም “አዲሱን ዓመት መልካም በሆነ አዲስ ሀሳብ ፣እግዚአብሔርንና ሰውን በሚያገናኝ ቅዱስ ተግባር፣ በልማት፣ በሰላም፣ በፍቅር፣ በዕርቅና በስምምነት እንድንቀበለው” ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፏል።‎‎አዲሱ ዓመት ለሀገር ሰላምና ልማት፤ ለሕዝቦች አንድነትና ስምምነት እንደዚሁም አለመግባባትን በፍትሕና በዕርቅ ለመፍታት ከልብ የምንተጋበት መልካም የስኬት ዘመን እንዲሆንልን እንጸልይ በማለት ለመላ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ©መረጃው የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ነው የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችንን ይወዳጁ! Facebook https://www.facebook.com/Ge7de12o Telegram https://t.me/Gedeokoreburji Tiktok Tiktok.com/@gedeokoreburji Instagram https://www.instagram.com/gedeokoreburji?igsh=azJrOGdpbDN4cG4= Youtube Website – Eotc-gkb.org

‎ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለ2018 አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ! Read More »

ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት የንዋየ ቅድሳት ድጋፍ ተደረገ!!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ የንዋየ ቅድሳት እጥረት ላለባቸው የገጠር አብያተክርስቲያናት የንዋየ ቅድሳት ድጋፍ ተደረገ። ድጋፉ በመምህር ያሬድ አደመ በኩል የተደረገ ሲሆን ልብሰ ተክኅኖ፣ ጧፍ፣ እጣን፣ ዘቢብ፣ መጾርና መባረኪያ መስቀሎች፣ በርካታ የቤተ መቅደስ መጻሕፍት፣ የሥጋ ወደሙ ማክበሪያ አጎበር፣ ጸናጽል፣ ማዕፈድ የመሳሰሉ ንዋየ ቅድሳት ድጋፍ ተደርገዋል። ድጋፉን ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የተረከቡ ሲሆን ድጋፉን ላደረጉ ምዕመናን ምሥጋና አቅርበዋል።

ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት የንዋየ ቅድሳት ድጋፍ ተደረገ!! Read More »

የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በቆቲ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በታላቅ መንፈሳዊ ክብር ተከበረ !!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ሥር በሚገኘው በቆቲ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ። መርሐ ግብሩን የመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ዋና ጸሐፊ ሊቀኀሩያን እሸቱ ዋለ የመሩት ሲሆን ትምህርተ ወንጌል የሰጡትና ለቤተክርስቲያን የልማት ሥራ ያስተባበሩት የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ሊቀትጉሃን ቀሲስ ሀብታሙ አበበ ሲሆኑ በትምህርታቸውም ሩፋኤል ማለት እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው ማለት መሆኑን የገለጹ ሲሆን ሩፋኤል ማለት ፈታሄ ማኅፀን ማለት ነው ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ጸሎት ተደርጎ የበዓሉ ፍጻሜ ይሆናል ።

የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በቆቲ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በታላቅ መንፈሳዊ ክብር ተከበረ !! Read More »

ጾመ ፍልሰታ/ጾመ ማርያም/

ፍልሰታ ማለት ፈለሰ፤ተሰደደ፤ተጓዘ፤ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ «ፈለሰት ማርያም እምዘይበሊ ኀበኢይበሊ፤ ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት፣ ተሻገረች» በማለት ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጓሜ አመሥጥሮ ገልጾታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የዕረፍት ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እመቤታችን በዚህ ዓለም ፷፬ ዓመታትን በሕይወተ ሥጋ ከቆየች በኋላ ጌታችን የእናቱን ተድላ ነፍሷን እንጂ ተድላ ሥጋዋን አይወድምና ጥር ፳፩ ቀን ፵፱ ዓመተ ምሕርት አረፈች፡፡ ዕረፍቷም እንደሌላው ሰው በሕማምና በድካም አይደለም፡፡ በገነት ዕፀዋት መዓዛ ተመስጣ ቅድስት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታለች፡፡ ታሪኩ በነገረ ማርያም እንደተጻፈው ሐዋርያት እመቤታችንን በአጎበር አድርገው አክብረው ወደጌቴሴማኒ መካነ መቃብር ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉም ነበርና ቀድሞ ልጇን ተነሣ ዐረገ እያሉ ሲያውኩ ኖረዋል፤ እርሷን ደግሞ ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነውና «ኑ የማርያምን ሥጋ በእሳት እናቃጥለው» ብለው በምቀኝነት ተነሱ፡፡ ከመካከላቸው አንድ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ ዘሎ ሄዶ የአልጋውን ሸንኮር ሲይዝ የታዘዘ መልአክ በረቂቅ ሰይፉ እጆቹን ቆረጠው፡፡ እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ የምሕረት እናት የሆነችው ድንግል ማርያም ቅዱስ ጴጥሮስ ጸልዮ እጆቹን እንዲመልስለት ነግራው እንደነበረ አድርጎለታል፡፡ የእመቤታችን ሥጋዋን መላእክት ከዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ወስደው አስቀምጠውታል፡፡ ሥጋዋ ያለበትን ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እነርሱ ባለማየታቸው እመቤታችን ባረፈች በ፮ኛው ወር ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ፲፬ ቀን ድረስ ከጾሙ በኋላ በ፲፬ኛው ቀን ሥጋዋን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በጌቴሴማኒ ባለው መቃብር ቀብረውታል፡፡ ከዚህ በኋላ እንደ ልጇ በ፫ኛው ቀን ተነሥታ መላእክት እየዘመሩላት ወደሰማያት ስታርግ፤ ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሰ ዕርገቷን በማየቱ መላእክት «እመቤትህ እርሷ ናት፤ስገድላት» አሉት፤ እርሱም «ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይላል፤ከደመናው ሊወድቅ ወደደ» ምክንያቱም ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ፤ዛሬ ደግሞ የእርሷን ትንሣኤ ለማየት ብሎ ነው፡፡ እመቤታችንም «ትንሣኤየን ያየህ አንተ ነህ ሌሎቹ አላዩም» ብላ ሐዋርያት ገንዘው የቀበሩበትን የሐር ግምጃ ሰጥታ አጽናንታ ሰደደችው፡፡ ቅዱስ ቶማስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ ብሎ ጠየቃቸው፤እነርሱም አግኝተው እንደቀበሯት ነገሩት፤ እርሱም ያየውን ምሥጢር በልቡ ይዞ «ሞት በጥር፤ በነሐሴ መቃብር፤ ለሰሚውም አያምር፤ይህ እንዴት ይሆናል?»፤ ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ «ድሮም አንተ ተጠራጣሪ ነህ፤ማን ያርዳ የቀበረ፤ ማን ይናገር የነበረ እንዲሉ፤ ገንዘን የቀበረን እኛ እያለን እንዴት ትጠራጠራለህ» ብለው ወደ መቃብሯ ሄደው መቃብሯን ቢከፍቱት ባዶ ሆኖ አገኙት፡፡ በዚህ ተደናግጠው ተያዩ፤ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቶማስ «አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነሣች፤ዐረገች፤ ይኸው ምልክቱ» ብሎ ገንዘው የቀበሩበትን ሰበን አሳያቸው፤እነርሱም አምነው ሰበኗን ለበረከት ተካፈሉት፡፡ በዓመቱ ነሐሴ ፩ ቀን ሐዋርያት በመንፈሰዊ ቅናት ተነሳስተው «ቶማስ ትንሣኤዋን አይቶ እኛ ሳናይ እንዴት ይቀርብናል» በማለት ነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ ጀምረው በ፲፮ኛው ቀን የሐዋርያትን ሱባኤ ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር ጴጥሮስን ተራዳኢ፣ ካህን እስጢፋኖስን ሠራዔ ዲያቆን አድርጉ ቀድሶ አቅርቧቸዋል፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላም ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፭ ቀን ጾመ ፍልሰታ ተብሎ ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ይጾመዋል፡፡ የጾሙና የትንሣኤዋ በረከት ተካፋይ ያድረገን፤አሜን።

ጾመ ፍልሰታ/ጾመ ማርያም/ Read More »

ለገጠር አብያተክርስቲያናት የንዋየ ቅድሳት ድጋፍ ተደረገ!!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ለሚገኙ፦ #ለቡርጂ ወረዳ ቤተክህነት #ለኮሬ ወረዳ ቤተክህነት #ለቡሌና ረጴ ወረዳ ቤተክህነት #ለይርጋጨፌ ወረዳ ቤተክህነት ለሚገኙ ገጠር አብያተክርስቲያናት የሚሆን የተለያዩ ንዋየ ቅድሳት መቀደሻ አልባሳት፣ ዣንጥላ፣ ዕጣን፣ ጧፍ ፣ቅዱሳት መጽሐፍት፣ መጎናጸፊያ ፣መጋረጃ፣ ጽና፣ መስቀል ፣ጽዋ ለአራቱም ወረዳ ቤተክህነት ኃላፊዎች ከሀገረ ስብከቱ የሰበካ ጉባኤና የሰ/ት/ቤት ማደራጃ ክፍል ኃላፊ ከመልአከ ብርሃን ዳንኤል ነቢዩ ተረክበዋል። የየወረዳ ኃላፊዎችም የተረከቡትን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አብያተክርስቲያናት የሚያደርሱ ይሆናል። በቀጣይም በሀገረ ስብከቱ ለሚገኙ ገጠር አብያተክርስቲያናት የሚያስፈልጉ ንዋየ ቅድሳትን ለማሟላት ድጋፋችሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንጠይቃለን ።

ለገጠር አብያተክርስቲያናት የንዋየ ቅድሳት ድጋፍ ተደረገ!! Read More »

ስድስተኛው ዙር የወጣቶች መርሃግብር ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ በተገኙበት ተካሄደ!!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላ ከተማ በብፁዕ አቡነ ገሪማ በሀገረ ስብከቱ ጳጳስና በቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሚመራው ወርሃዊው የወጣቶች መርሃግብር ስድስተኛ ዙር ብፁዕነታቸው በተገኙበት ተካሂዷል። መርሃግብሩ የተመራው መምህር በላይ ሁንደራ ሲሆን ዝማሬ በዘማሪት ሰላም ዘሪሁን እና በዘማሪት ሰላም ሀብታሙ ቀርቧል። እንዲሁም በወጣት ኪሩቤል አሰፋ እና በወጣት እርቅይሁን ደመላሽ ግጥም ቀርቧል። መጋቤ ሀዲስ መልአክ አማረ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል የመጻሕፍት መምህር ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለልጁ ለጢሞቴዎስ በጻፈው በሁለተኛው መልእክቱ ፪ኛ ጢሞ ፫፥፲፬ ላይ የሚገኘውን “አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር ከማን እንደተማርኸው ታውቃለህና” የሚለውን ኃይለ ቃል መነሻ በማድረግ ወጣቶች ውሏቸውን ማስተካከል እንዳለባቸው፣ በቤተ ክርስቲያን በተማሩበት ትምህርት በአሚነ ሥላሴ ጸንተው መኖር እንዳለባቸው በሰፊው አስተምረዋል። በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ወጣቶቹ ወደዚህ መርሃግብር (ወደ ቤተ ክርስቲያን) ሲመጡ ሌሎቹንም በመጋበዝ፣ ወጣቶች በማይመጥናቸው በአልባሌ ሥፍራ ላይ መገኘት እንደሌለባቸው እንዲሁም ራሳቸውን ከሱስ መጠበቅ እንዳለባቸው ገልጸው ስለሱስ አስከፊነት በሰፊው ተናግረው በቀጣይ ሊሰሩ ስለሚገባቸው ጉዳዮች አባታዊ መመሪያ ሰጥተው መርሃግብሩን በጸሎት ፈጽመዋል። የሚቀጥለው ወር የሚውለው ነሐሴ 25/2017 ዓ.ም ነው።

ስድስተኛው ዙር የወጣቶች መርሃግብር ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ በተገኙበት ተካሄደ!! Read More »

Scroll to Top