በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ቀዳሚ ገጽ ዜና

ለስምንት ወራት የተማሩ ደቀመዛሙርት በብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ተመረቁ!!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በሀገረ ስብከቱ በተቋቋመው በአንዲዳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የተማሩ የአብነት እና የተለያዩ መሠረታዊ ትምህርትና ሥልጠና የወሰዱ ከ5ት ወረዳ ቤተክህነት የተወጣጡ 5ት ደቀመዛሙርት በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተመረቁ። በምርቃ መርሐ ግብር ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ደቀመዛሙርት የተሸለሙ ሲሆን የተለያዩ መጻሕፍት ከማህበረ ቅዱሳን ተሰጥቷቸዋል።በተጨማሪ ያለ ምንም ክፍያ ለስምንት ወራት ያስተማሩ መምህራን በብፁዕነታቸው ተመስግነዋል ሽልማት ተሰጥቷቸዋል። የደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት መዘምራን መዝሙር ያቀረቡ ሲሆን ተመራቂ ደቀመዛሙርትም ያሬዳዊ ወረብና ግጥም አቅርበዋል ። ስለ ተመራቂ ደቀመዛሙርት አጠቃላይ ቆይታ በቀሲስ ጤናው እንዳለማው ቀርቧል። አጠቃላይ አጭር ስለ አብነት ት/ቤቱ ሪፖርት በመልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ የሀገረ ስብከቱ የትምህርትና የካህናት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ ገልጸዋል ። በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ቃለምዕዳን ያስተላለፉ ሲሆን ደቀመዛሙርት የተሰጣቸውን ተልዕኮ መወጣት ማስተማር እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

ለስምንት ወራት የተማሩ ደቀመዛሙርት በብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ተመረቁ!! Read More »

ሊቀ ስዩማን ቀሲስ ምህረቴ ገ/ሥላሴ የሻራ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ እንዲሆኑ በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተሹመዋል።

በዕለቱም የማስተዋወቅ መርሐ ግብሩን ያከናወኑት የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ በሆኑት በመልአከ ብርሃን ቀሲስ አጥናፉ ማሞ የማስተዋወቅ ሥራ ተከናውኗል። በመጨረሻም በሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ በመልአከ ብርሃን አጥናፉ ማሞ መልካም የሥራና የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላቸው በመመኘት በጸሎት ተፈጽሟል።

ሊቀ ስዩማን ቀሲስ ምህረቴ ገ/ሥላሴ የሻራ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ እንዲሆኑ በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተሹመዋል። Read More »

በግንባታ ላይ የሚገኘው የመንበረ ጵጵስና ሕንጻ ጉብኝት ተደረገ!!

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የሀገረ ስብከት አቀፍ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች አዲስ ሀገረ ስብከቱ በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚያስገነባውን የመንበረ ጵጵስና ሕንጻ ጉብኝት አደረጉ። በጉብኝቱ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ መልአከ ብርሃን አጥናፉ ማሞ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ፣ የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች፣ የወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች እና ጸሐፊዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች በጠቅላላ ጉባኤው የተገኙ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። በጉብኝት ስለሕንጻው አሁናዊ ሁኔታ ገለጻ የሰጡት ኢንጅነር አማኑኤል ሲሆኑ ሕንጻው በደረሰበት ደረጃ መደነቃቸውን ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል። በተጨማሪ በቅጥር ግቢ ውስጥ እየተሰሩ የሚገኙት የግብርና የልማት ሥራዎች የተጎበኙ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ወደፊት ስለሚሰሩ ሥራዎች ገለጻ አድርገው እንዲሁም ለመጎብኘት ለመጡት እንግዶች ምስጋና አቅርበው ፍጻሜ ሆኗል።

በግንባታ ላይ የሚገኘው የመንበረ ጵጵስና ሕንጻ ጉብኝት ተደረገ!! Read More »

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ ላይ ይገኛል!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የሀገረ ስብከት አቀፍ ፪ኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤ በደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን በማካሄድ ላይ ይገኛል። በመርሃግብሩ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ መልአከ ብርሃን አጥናፉ ማሞ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ፣ የሀገረ ስብከቱ የየሥራ ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ የወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች እና ጸሐፊዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎች፣ ምክትል ሊቀመንበር፣ ሒሳብ ሹም፣ የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት ተወካዮች፣ የመንበረ ጵጵስና የልማት ኮሚቴዎች እና የምዕመናን ተወካዮች ተገኝተዋል። መርሃግብሩን ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ጸሎተ ወንጌል፣ ኪዳን በማድረስ በጸሎት የከፈቱ ሲሆን ቀጥለውም የመርሃ ግብሩን መጀመር በይፋ አብስረዋል። በመርሃግብሩ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ የአንድ ዓመት የሥራ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርታቸው በሀገረ ስብከቱ በአገልጋይ እጥረት ምክንያት የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎት በማይሰጥባቸው አብያተ ክርስቲያናት ከምእመናን በተሰበሰበ 1,116,000 ገንዘብና እርዳታ ለአንድ ዓመት ለ፮ ካህናት ደሞዛቸውን ችሎ አብያተ ክርስቲያናቱ የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ እንዲሁም በስድስቱ ወረዳ ቤተ ክህነት በቋንቋ ተዘዋውረው የሚሰብኩ ለአንድ ዓመት 21 ደቀመዛሙርት ለ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት እንዲሰማሩ ምልመላ ተደርጎ የስምሪት ስልጠና ወስደው ወደ አገልግሎት መግባታቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ሥልጣነ ክህነትን በተመለከተ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለ90 ደቀመዛሙርት የዲቁና 16 በአጠቃላይ 106 ሥልጣነ ክህነት መሰጠቱን እንዲሁም በርካታ ኢ-አማንያን በጥምቀት የሥላሴን ልጅነት ማግኘታቸውን ገልጸዋል። በመርሃግብሩ የወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች የየወረዳ ቤተ ክህነቱን ዓመታዊ የ፩ ዓመት ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርታቸው በሁሉም ወረዳ ቤተ ክህነት 3372 ኢ-አማንያን መጠመቃቸውን ገልጸዋል። የመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት በበጀት ዓመቱ 822 ኢ-አማንያን መጠመቃቸውን ገልጸው የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን በተመለከተ፣ መልካም አስተዳደርን፣ ሁለገብ ልማትን፣ የአብነት ትምህርት ቤት እና ዘመናዊ ትምህርት ቤትን፣ ሰንበት ትምህርት ቤትን በተመለከተ (የአንድነት ሰንበት ትምህርት ቤት)፣ የአደባባይ ክብረ በዓላት አከባበርን፣ የቤተ ክርስቲያን ምረቃ፣ የመሰረት ድንጋይ መቀመጥ፣ የጠበል አገልግሎት፣ የማረምያ ቤት፣ የፋይናንስ አያያዝ አስተዳደር፣ ፐርሰንት ክፍያ በተመለከተ እንዲሁም የተሀድሶን ሴራ ስለማጋለጥ የተሰሩ ሥራዎችን ገልጸዋል። የይርጋጨፌ ወረዳ ቤተ ክህነት 823 ኢ-አማንያን ማስጠመቃቸውን ገልጸው የብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ሐዋርያዊ አገልግሎት፣ ከአድባራት አስረዳዳሪዎች ጋር የተደረጉ ውይይቶችን፣ ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት የተሰሩ ሥራዎችን፣ በአድባራቱ የተሰሩ ልማቶችን እንደአብነት የግብርና የልማት ሥራዎችን፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት እንዲከተሉ ለማድረግ የተሰሩ ሥራዎችን በሰፊው ገልጸዋል። በኮቾሬና ገደብ ወረዳዎች ቤተ ክህነት 273 ኢ-አማንያን መጠመቃቸውን ገልጸው በዕቅድ ዙርያ የተደረገ ውይይት፣ የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን ለማስከፈት የተሰሩ ሥራዎችን፣ የክህነት አሰጣጥን በተመለከተ፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ለማቋቋም የተሰሩ ሥራዎችን፣ የስብከት ኬላ ማቋቋምን፣ የአቅም ማጎልመቻ ሥልጠናዎችን በተመለከተ፣ የተቸገሩ አብያተ ክርስቲያናትን መለየትና ማቋቋምን በተመለከተ፣ የንግስ በዓላትን መምህራንን መመደብ መቆጣጠር የመሳሰሉትን ሥራዎች አቅርበዋል። የቡሌና ረጴ ወረዳ ቤተ ክህነት 127 ኢ-አማንያንን ማስጠመቃቸውን ገልጸው በስብከተ ወንጌል፣ ሁለንተናዊ የልማት ሥራዎችን፣ በሰንበት ትምህርት ቤት የተሰሩ ሥራዎችን፣ በፐርሰንት የተሰሩ ሥራዎችን፣ በአብነት ተማሪዎች ዙርያ የተሰሩ ሥራዎችን ገልጸዋል። የኮሬ ወረዳ ቤተ ክህነት 594 ኢ-አማንያንን ማስጠመቃቸውን ገልጸው የብፁዕ አባታችንን ሐዋርያዊ አገልግሎት፣ የአገልጋይ እጥረት ያለባቸውን አብያተ ክርስቲያናትን አገልጋይ በመመደብ እንዲሁም ንዋየ ቅድሳትን ሟሟላት፣ ስብከተ ወንጌል አገልግሎትን ለማስፋፋት የተሰሩ ሥራዎችን ገልጸዋል። የቡርጂ ወረዳ ቤተ ክህነት 733 ኢ-አማንያንን ማስጠመቃቸውን ገልጸው የብፁዕ ሊቀጳጳሱን ሐዋርያዊ አገልግሎት፣ ስብከተ ወንጌልን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር የተሰሩ ሥራዎች፣ ሥራዎችን ከማዘመን አንጻር የተሰሩ ሥራዎችን ሪፖርት አድርገዋል።

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ ላይ ይገኛል!! Read More »

የቅዱስ ዑራኤል ዓመታዊ በዓል በዲላ ዋለሜ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ በተገኙበት ተከበረ!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ሐምሌ ሃያ ሁለት ቀን የሚከበረው የመልአኩ የቅዱስ ዑራኤል በዓለ ንግሥ በዲላ ዋለሜ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል። መርሃግብሩ በሀገረ ስብከቱ ትምህርት እና ካህናት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ በመልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ የተመራ ሲሆን በደብሩ የሰንበት ትምህርት ቤት ዘምርያን ያሬዳዊ ዝማሬ ከቀረበ በኋላ ለዕለቱ የሚስማማ ትምህርት በደብሩ ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ የሆኑት ሊቀ ማእምራን መምህር ሰሎሞን ፈጠነ ተሰጥቷል። የደብሩ የግብርና የልማት ሥራ እንዲጠናከር ትልቅ ሥራ ላደረጉ ለአባ ገብረ አረጋዊ ረታ እና ለዲያቆን አምራች ገብረ ሥላሴ የምስጋና ስጦታ እና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል። በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የደብሩ የልማት ሥራ እንዲፋጠን የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ላደረጉ ሰዎች ምስጋና ካቀረቡ በኋላ ሁሉም አድባራት የተለያዩ የግብርና ሥራዎችን በመስራት ላይ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይ አብያተ ክርስቲያናቱ ወደ አምራችነት ለማሳደግ እየተሰራ ያለውን ሥራ ገልጸው እንዲሁም በዓለ ንግሡን በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ በመስጠት መርሃግብሩን በጸሎት ፈጽመዋል።

የቅዱስ ዑራኤል ዓመታዊ በዓል በዲላ ዋለሜ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ በተገኙበት ተከበረ!! Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ከኮምፒተር ባለሙያዎች ጋር ተወያዩ!!

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ከዲላ ዩኒቨርስቲ የኮምፒውተር ባለሙያዎች ጋር ተወያዩ። የውይይቱ መሠረታዊ ዓላማ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ከመስጠትና ከመቀበል አንጻር የኮምፒውተር መሠረታዊ እውቀት መኖር አስፈላጊ መሆኑ ይታወቃል ። ይኸም በሀገረ ስብከቱ ዘመናዊ አገልግሎት ከመስጠት አንጻር ያለውን ክፍተት ለመቅረፍ በቀጣይም ዘመናዊ አሰራር ለመዘርጋት ይቻል ዘንድ የውይይቱ አካል ነበር። ዘመናዊ የኮምፒውተር እውቀት ወረቀት አልባ አገልግሎት እንዲኖር ከማድረጉ በተጨማሪ የኢንተርኔት አገልግሎትን በሚገባ ከተጠቀሙ የመረጃ ልውውጥ የሚያፋጥን መሆኑ እሙን ነው።ይኸንም በቀጣይ የተሻለ አሰራር ለመተግበር የሚያስችል መሆኑ ተመልክቷል ።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ከኮምፒተር ባለሙያዎች ጋር ተወያዩ!! Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ከቂሻ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ጋር ተወያሀዩ!!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በጮርሶ ወረዳ አዲስ ለሚሰራው በቅርቡም መንፈሳዊ የእግር ጉዞ ተደርጎበት ውጤታማ ሥራ ለተሰራበት የቂሻ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን ህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ጋር በቀጣይ በህንጻው ሥራና ጉዳይ ላይ ከብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ጋር ውይይት አደረጉ። በውይይቱም በቀጣይ በህንጻው ሥራ ላይ እስከ አሁን ከምዕመናን የተሰበሰበ ገንዘብ በማቴሪያል ቃል የተገባውን ምዕመናን ገንዘብ ለመስጠት ቃል ገብተው እስከ አሁን ያላስገቡ በቀጣይ በቤተክርስቲያኑ ሕጋዊ አካውንት ማስገባት እንዳለባቸው ትኩረት ተሰጥቶ ውይይት ተደርጓል። የህንጻ ቤተክርስቲያን ተጀምሮ ለማጠናቀቅ በቀጣይ ምዕመናን በቤተክርስቲያኑ ሕጋዊ አካውንት ገንዘብ በማስገባት ድጋፋቸውን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል በሌላ በአይነትም ድጋፋቸውን መቀጠል እንዳለበት አጽንኦት ተሰጥቶበታል። ለቂሻ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000705214647 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማለት ቃል የገባችሁትን እንድታስገቡልን በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ስም እንጠይቃለን ።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ከቂሻ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ጋር ተወያሀዩ!! Read More »

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ከአዲስአበባና ከሀዋሳ የመጡ የቤተክርስቲያን ልጆች ጋር በሀገረ ስብከቱ አጠቃላይ ጉዳዮች ጋር ውይይት አደረጉ !!

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ከአዲስአበባና ከሀዋሳ የመጡ የቤተክርስቲያን ልጆች ጋር በሀገረ ስብከቱ አጠቃላይ ጉዳዮች ጋር ውይይት አደረጉ ብፁዕነታቸዉ በሀገረ ስብከቱ ላለፉት ሁለት አመታት ታቅደው እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እንዲሁም በቀጣይ የሚተገበሩ ስራዎችን ለታዳሚዉ ገለፃ አድርገዋል ። ተሳታፊዎችም ከተደረገዉ ገለጻ በመነሳት በብፁዕ አቡነ ገሪማ ገለፃ በመደረጉ መገረማቸዉን እና አብሪዉ የሚችሉትን ሁሉ ለማገዝ እንደሚፈልጉ ቃል ገብተዋል። በመጨረሻም በግንባታ ላይ የሚገኝዉን መንበረ ጵጵስና የተጎበኝ ሲሆን በነበረው ቆይታ ደስተኛ እንደሆኑ በመግለጽ ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ብር በላይ (1,200.000…) ቃል ገብተዋል። #ብፁዕነታቸዉም ድጋፍ ያደረጉትን አመስግነዉ በቀጣይም ከሀገረ ስብከቱ ጎን በመቆም በሀሳብም በገንዘብም አቅም በፈቀደ ሁሉ አብረዉ እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዉ በፀሎት ተፈፅሟል።

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ከአዲስአበባና ከሀዋሳ የመጡ የቤተክርስቲያን ልጆች ጋር በሀገረ ስብከቱ አጠቃላይ ጉዳዮች ጋር ውይይት አደረጉ !! Read More »

በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ብፁዕ አቡነ ገሪማ በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከበረ!

በጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስ ዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ሥር የሚገኘው በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ መልአከ ብርሃን አጥናፉ ማሞ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ፣ የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች ፣ የወረዳ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀጠበብት መሪጌታ መሠረት እና ዋና ጸሐፊ ሊቀ ኅሩያን እሸቱ ዋለ ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ኃይል መሪጌታ ሀብቴ ፣የየአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ሊቀውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤት አባላት፣ ቁጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የተገኙ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ክብር ተከብሯል ። #በዕለቱም በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ለድቁና የሚያበቃቸውን ትምህርት ለተማሩ ለ44 ደቀመዛሙርት ማዕረገ ድቁና የሰጡ ሲሆን ለቅስና የሚያበቃቸውን ትምህርት ለተማሩ ለ10ት ዲያቆናት ማዕረገ ቅስና ሰጥተዋል። #ታቦቱ ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ ዑደት ካደረገ በኋላ የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ያሬዳዊ መዝሙር አቅርበዋል። #በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ አስተዳደር የዲላ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር መስፍን ደምሴ በክብረ በዓሉ ላይ በመገኘት የመልካም ምኞትና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። #ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በክብር እንግድነት የተገኙትን የዲላ ከተማ ከንቲባንና የሥራ ባልደረቦቻቸውን አመስግነዋል። የዕለቱን ትምህርት ብፁዕ አቡነ ገሪማ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዓሉን የተ92መለከተ ስለ ቅዱሳን መላእክት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል በመላእክትና በሰው መካከል ያለውን ግንኙነት የቅዱስ ጳውሎስን መልዕክት መነሻ በማድረግ የመላእክት እርዳታ አስፈላጊነት ገልጸዋል። የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነትና ጥበቃ ቅድስት ኢየሉጣና ቅዱስ ቂርቆስ ቅዱስ ገብርኤል እንደረዳቸውን በሰፊው ትምህርት ሰጥተዋል። በመጨረሻም ጸሎት በመድረግ የበዓሉ ፍጻሜ ሲሆን ጸሎተ ቅዳሴው በብፁዓን አባቶች ተመርቷል።

በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ብፁዕ አቡነ ገሪማ በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከበረ! Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ለ54 ደቀመዛሙርት ሥልጣነ ክህነት ሰጡ!!

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ በሚከበረው በቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል ላይ በመገኘት በሀገረ ስብከቱ ለሚገኙ መንፈሳዊ ትምህርታቸው ሲከታተሉ ለነበሩ ለ44 ደቀመዛሙርት የዲቁና እንዲሁም ለ 10 ዲያቆናት የቅስና ሥልጣነ ክህነት ክህነት ሰጥተዋል። ብፁዕነታቸው መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግሉ በንጽህናና በቅድስና ማገልገል እንዳለባቸው፣ በማይመጥናቸው ቦታ መገኘት እንደሌለባቸው እና የተቀበሉትን ትልቅ ኃላፊነት በትጋት መጠበቅ እንዳለባቸው መልእክታቸውን ከአደራ ጭምር አስተላልፈዋል።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ለ54 ደቀመዛሙርት ሥልጣነ ክህነት ሰጡ!! Read More »

Scroll to Top