በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ቀዳሚ ገጽ ዜና

በቡርጂ ወረዳ ቤተክህነት ሀረወንጄ ቅ/ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን የንዋየ ቅድሳት ድጋፍ ተደረገ!!

ኤክቱስ ሐምሌ 17/2017 ዓ.ምበጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በቡርጃ ወረዳ ቤተክህነት ሥር ለምትገኘው ሀረወንጄ ቅ/ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ቅዱሳት መጽሐፍት ፣ንዋየ ቅድሳት ልብሰ ተክህኖ ጽና ፣መስቀል ፣አውድ እና ሌሎች ንዋየ ቅድሳትን ከብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የሲኖዶስ አባል እጅ የቤተክርስቲያኑ ተወካይ ተቀብለዋል።

በቡርጂ ወረዳ ቤተክህነት ሀረወንጄ ቅ/ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን የንዋየ ቅድሳት ድጋፍ ተደረገ!! Read More »

በጨለለቅቱ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከሐምሌ11-13/2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ !!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በኮቸሬ ገደብና ጮርሶ ወረዳ ቤተክህነት በጨለለቅቱ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከሐምሌ 11-13/2017 ዓ.ም ሲካሄድ የነበረው ጉባኤ በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ጸሎት ሰጥተው ምስጋና ለሚገባቸው ምስጋና አቅርበው ተጠናቋል ። በጉባኤው፦ #ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ደሳለኝ #መጋቤ ሠናያት መ/ር አብይ #መጋቤ ሀዲስ ግሩም #ዘማሪ መ/ሰ/እንግዳወርቅ በቀለ #ዘማሪት መቅደስ መኮንን #ዘማሪ ዕዝራ ኃ/ሚካኤል #የዜማ መሣሪያ ተጨዋቾች #ከጉባኤ መጀመሪያ እስከ ፍጻሜ ድረስ የወረዳ ቤተክህነት የሥራ ኃላፊዎች የደብሩ አስተዳደሪና ካህናት እና የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ በጉባኤው ተገኝተዋል። በጉባኤው የእግዚአብሔር ቃል የተሰበከበት ፣ልዩ ልዩ ጣዕመ ዝማሬ መንፈሳዊ ዝማሬ የቀረበበት እንዲሁም የምክረ አበው መርሐ ግብር የተከናወነበት ነው ።

በጨለለቅቱ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከሐምሌ11-13/2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ !! Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ከተለያዩ የቤተክርስቲያን ልጆች ጋር ተወያዩ !!

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በሀገረ ስብከቱ እየተከናወኑ ባሉ ስራዎችና በቀጣይ በሚተገበሩ ሥራዎች ዙሪያ ውይይት አደረጉ ። ውይይቱ ከተደረገ በኋላም በአንዲዳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የሚገኘውን አብነት ት/ቤት ፣አዲስ እየተገነባ የሚገኘዉን መንበረ ጵጵስናና በውስጡ እየለማ የሚገኘውን የጎሮ አትክልትና የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት ተጎብኝቷል።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ከተለያዩ የቤተክርስቲያን ልጆች ጋር ተወያዩ !! Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ከጌዴኦ የባህል አባቶች አባ ገዳ ቢፎም ዋቆ እና ካብኔዎቻቸው ጋር በጽ/ቤታቸዉ ተወያዩ ።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ከጌዴኦ የባህል አባቶች አባ ገዳ ቢፎም ዋቆ እና ካብኔዎቻቸው ጋር በጽ/ቤታቸዉ ተወያዩ ። Read More »

የጎላ ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን የጸበል ሥፍራ በብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ተባረከ!!

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በጎላ ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን በሚገኘው የጸበል ሥፍራ ላይ በመገኘት ጸሎተ ወንጌል፣ ኪዳን አድርሰው የጸበል ሥፍራውን ባርከዋል። በመርሃግብሩ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ መልአከ ብርሃን ቀሲስ አጥናፉ ማሞ ፣ የመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጠበብት መሪጌታ መሰረት፣ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ እሸቱ ዋለ፣ ቀሲስ ሄኖክ የቤተ ክርስቲያኑ የሰበካ ጉባኤ ሊቀ መንበር፣ የደብሩ ካህናትና ዲያቆናት፣ የደብሩ የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያንና ምዕመናን ተገኝተዋል። ብፁዕነታቸው በመርሃግብሩ ትምህርት የሰጡ ሲሆን በትምህርታቸው የእግዚአብሔር መልአክ በሚያናውጸው ውሃ ብዙዎች ከደዌ ሥጋ ይፈወሱ እንደነበር፣ ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌው ምራቁን በአፈር እንትፍ ብሎ ተአምራትን እንዳደረገ አንስተው ዛሬም በዘመናችን እግዚአብሔር የሰጠንን ይህንን ጸበል አክብረን ብንይዘው እና በእምነት ብንጠቀመው ብዙ ተአምራትን እንደሚያደርግ በሰፊው ገልጸው መርሃግብሩን በጸሎት ፈጽመዋል።

የጎላ ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን የጸበል ሥፍራ በብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ተባረከ!! Read More »

#ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንኳን ለ፪ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ በሰላምና በጤና አደረስዎ !!

ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን በሙሉ ለብፁዕ አባታችን አቡነ ገሪማ ጳጳስ የ፪ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በዓል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን። በኢትዮጵያ ኦርቶዶከክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የብፁዕ አቡነ ገሪማ የ፪ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም በታላቅ ድምቀት የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅና የየክፍል ኃላፊዎች የወረዳ ቤተክህነት ኃላፊዎች እና የአድባራት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት ይከበራል። ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በሀገረ ስብከት ከተመደቡበት ጊዜ ጀምሮ ሐዋርያዊ ጉዞ በማድረግ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ከ 70 በላይ አብያተክርስቲያናት የጎበኙ፣ አባታዊ ምክርና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት የሰጡና ከዚህ በፊት በጳጳሳት ያልተጎበኙና ያልተባረኩ ምዕመናን በመጎብኘታቸው ልዩ አባት ያደርጋቸዋል። ብፁዕ አቡነ ገሪማ የስብከተ ወንጌልን አገልግሎት እንዲስፋፋ፣ ለሰበካ ጉባኤ አባላት ስልጠና በመስጠት አዳዲስ አማኒያንን በማጥመቅ የሀገረ ስብከቱን የ፲ ዓመት መሪ ዕቅ እንዲዘጋጅ በማድረግ ፣የመንበረ ጵጵስና መኖሪያ ግንባታ እንዲጀመር በማድረግ ፣ አዲስ የተሠሩ አብያተክርስቲያናትን ባርከው ለአገልግሎት እንዲበቁ፣በሀገረ ስብከቱ ዘመናዊ አሠራርን በመዘርጋት፣ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት፣ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ሁሉም አብያተክርስቲያናት በይዞታቸው አቅደው ተገቢውን ልማት እንዲያለሙ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጥናት እንዲያደርግ መመሪያ በመስጠት የመጎብኘትና የማበረታታት ተግባርን አከናውነዋል። በገጠሪቱ አብያተክርስቲያናት የእግር ጉዞ በማድረግ ወንጌል ሰብከዋል። በታላላቅ በዓላት በመገኘት ቀድሶ በማቁረብ ወንጌልን በማስተማር በሀገረ ስብከቱ በሚነገሩ ቋንቋዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ያደረጉ እንዲገለገልበት መመሪያን የሰጡ ፣የገጠሪቷ ቤተክርስቲያን የጎበኙ ፤ ሀገረ ስብከቱ ዘመኑን ያማከለ ዘመናዊ አሰራርን እንዲያከናውን ያደረጉ፤ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ጥያቄዎች አፋጣኝ መልስ የሚሰጡ፤ወደ ገጠር ቤተክርስቲያን የእግር ጉዞ እንዲደረግ በማድረግ አብያተክርስቲያናት እንዲረዱና እንዲተዋወቁ አድርገዋል። በተለይ በቅርቡ አዲስ ቤተክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠለትን የቂሻ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ጉዞ እንዲደረግ በማድረግ ሕዝበ ክርስቲያኑ ለቤተክርስቲያን መታነጽ ከፍተኛ ገቢ እንዲገባ ተደርጓል ። በጸሎታቸው በመንፈሳዊ አገልግሎታቸው የመልካም አሰተዳደርና የልማት አባት መሆናቸውን በተግባር ያሳዩ ፤ሐዋርያዊ አባትነታቸው ዘወትር የሚነገርላቸው ፤ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ከሠራተኞች ጀምሮ ካህናት ዲያቆናት በሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በምዕመናን ከልብ የሚወደዱ አባት ናቸው። ለሀገራችንና ለሕዝቦቿ ፍቅር ፣ሰላም ፣አንድነት እንዲኖር አብዝተው የሚጸልዩ አባታችን፤ እንኳን ለ ፪ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ በሰላምና በጤና አደረስዎ ! ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ዲላ ኢትዮጵያ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ብፁዕነትዎ ለረጅም ዘመናት በሰላምና በጤና በሀገረ ስብከትዎ ያቆይልን !!!! #የብፁዕነታቸው_ቡራኬ_አይለየን!!

#ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንኳን ለ፪ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ በሰላምና በጤና አደረስዎ !! Read More »

ለገጠር አብያተክርስቲያናት የሚሆን የቅዱሳት መጽሐፍት ድጋፍ ተደረገ !!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት የማይሰጡ አብያተክርስቲያናት ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ለማድረግ አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ ይታወቃል ።ከዚህም በንዋየ ቅድሳት ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ ድጋፎች እየተደረጉ ይገኛል ። ከእነዚህም የቅዱሳት መጽሐፍት እጥረቱ ላለባቸው አብያተክርስቲያናት የሚሆን መጽሐፍትን መ/ርት አልማዝ ለብፁዕ አቡነ ገሪማ ለሀገረ ስብከቱ ጳጳስ አስረክበዋል። ብፁዕነታቸውም ስለተሰጠው ስጦታ ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም አብያተክርስቲያናቱ ተከፍተው መንፈሳዊ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ሁሉም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሀገር የሚገኙ የቤተክርስቲያን ልጆች የአቅማቸውን ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል። ንዋየቅዱሳት ፣ ቅዱስት መጽሐፍትን ፣ልብሰ ተክህኖ አልባሳትን የካህናት ደመወዝን በመቻል የተዘጉ አብያተክርስቲያናት ማስፈከትና በረከት መቀበል አለብን እያልን መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ለገጠር አብያተክርስቲያናት የሚሆን የቅዱሳት መጽሐፍት ድጋፍ ተደረገ !! Read More »

19 ነፍሳት የሥላሴን ልጅነት አገኙ!!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በኮሬ ወረዳ ቤተክህነት ሥር በሚገኘው በኬረዳ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሐምሌ7/2017 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ 19 ኢአማንያን ተጠምቀው የሥላሴ ልጅነትን አግኝተዋል ። ኤክቱስ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም

19 ነፍሳት የሥላሴን ልጅነት አገኙ!! Read More »

የቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በዲላ መካነ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀትና ክብር ተከበረ!!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ሥር በሚገኘው በዲላ መካነ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት ተከበረ። በዕለቱም የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ሊቀትጉሃን ቀሲስ ሀብታሙ አበበ ፣የመንበረ ጵጵስና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ሊቀጠበብት መሪጌታ መሠረት ይልማ፣የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም አምሳሉ ሣለ ፣ለመንፈሳዊ ጉባኤ የተጋበዙ ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ፣መጋቤ ሐዲስ አድነው ወንድሙ ፣ዘማሪያን፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የዲላና አካባቢው ምዕመናን በተገኙበት ተከብሯል። መርሐ ግብሩ በሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል የተመራ ሲሆን የመጀመሪያውን ክፍለ ጊዜ ያስተማሩት መጋቤ ሐዲስ አድነው ወንድሙ ሲሆኑ ታቦቱ ከመንበረ ክብሩ ከወጣ በኋላ በደብሩ ፍሬ ተዋህዶ ሰንበት ት/ቤት መዘምራን ወረብ ከቀረበ በኋላ ሁለተኛውን ትምህርት የሰጡት ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ሲሆኑ በመቀጠል ለቤተክርስቲያኑ የልማት ሥራ የማስተባበር በመጋቤ ሐዲስ አድነው ወንድሙ ተከናውኗል ። በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ቃለ ምዕዳንና ጸሎት ተደርጎ በዓሉ ፍጻሜውን አግኝቷል ። ኤክቱስ ሐምሌ 7/2017 ዓ.ም

የቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በዲላ መካነ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀትና ክብር ተከበረ!! Read More »

የዘማሪ አዲስ ነጋሽ ቁጥር አንድ የዝማሬ አልበም ተመረቀ!!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ሥር በምትገኘው በጌ/ሰ/ባዕታ ለማርያም ቤተክርስቲያን በሰንበት ት/ቤት አገልጋይነት እንዲሁም በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት በዝማሬ የሚያገለግለው ዘማሪ አዲስ ነጋሽ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ እና የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች በተገኙበት ካህናት የዲላ ምዕመናን በተገኙበት በዲላ ዋለሜ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን አዳራሽ በብፁዕ አቡነ ገሪማ የዘማሪ አዲስ ነጋሽ የዝማሬ አልበም በብፁዕነታቸው ተመርቋል። በዕለቱም በተለያዩ ዘማሪያን ዝማሬ ፣በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ትምህርተ ወንጌል ፣የዝማሬ አልበሙ ምርቃት ፣ስጦታና ጨረታ ተከናውኖ በመርሐ ግብሩ በጸሎት ተዘግቷል ። ኤክቱስ ሐምሌ 6/2017 ዓ.ም

የዘማሪ አዲስ ነጋሽ ቁጥር አንድ የዝማሬ አልበም ተመረቀ!! Read More »

Scroll to Top