በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ሥር በምትገኘው በጌ/ሰ/ባዕታ ለማርያም ቤተክርስቲያን በሰንበት ት/ቤት አገልጋይነት እንዲሁም በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት በዝማሬ የሚያገለግለው ዘማሪ አዲስ ነጋሽ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ እና የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች በተገኙበት ካህናት የዲላ ምዕመናን በተገኙበት በዲላ ዋለሜ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን አዳራሽ በብፁዕ አቡነ ገሪማ የዘማሪ አዲስ ነጋሽ የዝማሬ አልበም በብፁዕነታቸው ተመርቋል።
በዕለቱም በተለያዩ ዘማሪያን ዝማሬ ፣በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ትምህርተ ወንጌል ፣የዝማሬ አልበሙ ምርቃት ፣ስጦታና ጨረታ ተከናውኖ በመርሐ ግብሩ በጸሎት ተዘግቷል ።






ኤክቱስ ሐምሌ 6/2017 ዓ.ም