በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ቀዳሚ ገጽ ዜና

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ለ፭ ዲያቆናት ማዕረገ ቅስና ሰጡ!

ኤክቱስ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዛሬው ዕለት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለቅስና የሚያበቃ መንፈሳዊ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ ለ፭ ዲያቆናት የቅስና ማዕረግ ሰጥተዋል። በዛሬው ዕለት ማዕረገ ቅስናን ከተቀበሉት ፭ ዲያቆናት መካከል ፬ቱ በአንዲዳ የአዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት መንፈሳዊ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው። ብፁዕነታቸው በመጨረሻም የተቀበሉትን አደራ በሥነ-ምግባር ጠብቀው እንዲኖሩ እና ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ አባታዊ ምክራቸውን ለግሰዋል።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ለ፭ ዲያቆናት ማዕረገ ቅስና ሰጡ! Read More »

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ለጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ወቅዱስ ፊልጶስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ለጸሐፊ መደብ ሠራተኛ ለመቅጠር ባወጣው ማስታወቂያ የተመዘገባችሁ ሰኞ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በማስታወቂያው መሠረት የተሟላ ዶክመንት ያስገባችሁ ብቻ በሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት ለፈተና እንድትቀርቡ ስንል እናስታውቃለን!

ኤክቱስ ሰኔ 11/2018 ዓ.ም

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ለጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ወቅዱስ ፊልጶስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ለጸሐፊ መደብ ሠራተኛ ለመቅጠር ባወጣው ማስታወቂያ የተመዘገባችሁ ሰኞ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በማስታወቂያው መሠረት የተሟላ ዶክመንት ያስገባችሁ ብቻ በሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት ለፈተና እንድትቀርቡ ስንል እናስታውቃለን! Read More »

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የሰኔ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል የሚከበርባቸው አብያተ ክርስቲያናት!

ኤክቱስ ሰኔ 11/2018 ዓ.ም በዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት 1. ዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን2. በንቆ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ይርጋጨፌ ወረዳ ቤተ ክህነት 3. ይርጋጨፌ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በኮቾሬ ገደብና ጮርሶ ወረዳዎች ቤተ ክህነት 4. ፍሥሓ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን 5. በንቆ ጎቲቲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በቡሌና ረጴ ወረዳዎች ቤተ ክህነት 6. ቡላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን 7. መንዶ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ኮሬ ወረዳ ቤተ ክህነት 8. ቡኒቲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን 9. ደርባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ቡርጂ ወረዳ ቤተ ክህነት 10. ላድሼ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን “በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል” ዳን ፲፪፥፩

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የሰኔ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል የሚከበርባቸው አብያተ ክርስቲያናት! Read More »

በዛሬው ዕለት የተጠመቃችሁ ልጆቻችን ከዛሬ ጀምሮ በቤቱ ያላችሁ የክርስቶስ ሙሽራዎች ናችሁ!ብፁዕ አቡነ ገሪማ

ኤክቱስ ሰኔ 7/2018 ዓ.ም በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተ ክህነት የይርጋጨፌ ደብረ ታቦር አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን በነበረው የሰንበት መርሃግብር ጉባኤ ላይ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ዋና ጸሐፊ መጋቤ ኃይማኖት ብዙአየሁ ዳመነ የዕለቱን ትምህርት በጌዴኡፋ ቋንቋ ያስተማሩ ሲሆን፣ በመቀጠል በማኅበረ ቅዱሳን ዲላ ማዕከል የስብከተ ወንጌልና ዜማ አገልግሎት ክፍል ኃላፊ በመምህር መልአኩ ጌታቸው የማኅበሩ መግለጫ ተነቧል። እንዲሁም በደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት፣ በነባር አባላትና በማኅበረ ቅዱሳን ይርጋጨፌ ወረዳ ማዕከል የመዝሙር ክፍል አባላት ዝማሬ ቀርቧል። በመጨረሻም በሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ በመልአከ ብርሃን አጥናፉ ማሞ ጋባዥነት ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተለያዩ ቋንቋዎች መዝሙር በመዘመርና የዕለቱን ወንጌል በማንሳት በአማርኛ፣ በጌዴኡፋ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች አስተምረዋል። ብፁዕነታቸው በንግግራቸው መካከል “በዛሬው ዕለት ቤተ ክርስቲያናችን አዳዲስ ምዕመናንን አግኝታለች፤ ይህ በሰማያት በቅዱሳን በመላእክት ዘንድም ትልቅ የምስራች ነው። በዛሬው ዕለት የመጣችሁ ልጆቻችን እንኳን የክርስቶስ ልጆች ለመሆን አበቃችሁ! ከዛሬ ጀምሮ በቤቱ ያላችሁ የክርስቶስ ሙሽራዎች ናችሁ” በማለት አባታዊ ምክራቸውን አስተላልፈው መርሃ ግብሩን በጸሎት ፈጽመዋል።

በዛሬው ዕለት የተጠመቃችሁ ልጆቻችን ከዛሬ ጀምሮ በቤቱ ያላችሁ የክርስቶስ ሙሽራዎች ናችሁ!ብፁዕ አቡነ ገሪማ Read More »

ሰባ ሁለት አዳዲስ አማንያን በብፁዕ አቡነ ገሪማ ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል!

ኤክቱስ ሰኔ 7/2018 ዓ.ም በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተ ክህነት የይርጋጨፌ ደብረ ታቦር አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ከማኅበረ ቅዱሳን ይርጋጨፌ ወረዳ ማዕከል ጋር በመሆን ከሦስት ወር በላይ የቅድመ ጥምቀት ትምህርት ሲማሩ የቆዩ ሰባ ሁለት አዳዲስ አማንያን በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል። ከተጠማቂያኑ መካከል ሠላሳ ስድስት ሴቶች ሠላሳ ስድስት ወንዶች ይገኙበታል።

ሰባ ሁለት አዳዲስ አማንያን በብፁዕ አቡነ ገሪማ ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል! Read More »

Poultry Development Project Officially Launched at the Diocesan Office!Ektus, June 13, 2026 (Sene 6, 2018 E.C.)Building on the experiences successfully implemented previously at the Dilla Debre Genet Holy Michael Church and the Andida Boarding Traditional Church School (Abinet School), the Diocese of Gedeo, Kore, and Burji has today purchased broiler chicks to launch the project within the diocesan office compound. This initiative strengthens the Church’s efforts to become self-reliant alongside its spiritual services.In order to manage this development work with quality and success, the Diocese has spent the past few days constructing modern poultry housing based on specialized studies. It was stated that this preparation was undertaken to ensure the safety (welfare) of the chickens and to guarantee their productivity.In the presence of His Grace Abune Gerima, Bishop of the Gedeo, Kore, and Burji Diocese and Member of the Holy Synod, the Diocese purchased nine hundred and five (905) chickens for the prepared modern shelter.The primary objective of this project is to inspire and encourage all parishes under the Diocese to actively participate in various development activities in their respective areas, using the Diocese’s exemplary approach, operational methods, and study experiences as a reference. Furthermore, it aims to enable them to break away from reliance on alms (offering box/charity) and become self-sufficient in income.

Poultry Development Project Officially Launched at the Diocesan Office!Ektus, June 13, 2026 (Sene 6, 2018 E.C.)Building on the experiences successfully implemented previously at the Dilla Debre Genet Holy Michael Church and the Andida Boarding Traditional Church School (Abinet School), the Diocese of Gedeo, Kore, and Burji has today purchased broiler chicks to launch the project within the diocesan office compound. This initiative strengthens the Church’s efforts to become self-reliant alongside its spiritual services.In order to manage this development work with quality and success, the Diocese has spent the past few days constructing modern poultry housing based on specialized studies. It was stated that this preparation was undertaken to ensure the safety (welfare) of the chickens and to guarantee their productivity.In the presence of His Grace Abune Gerima, Bishop of the Gedeo, Kore, and Burji Diocese and Member of the Holy Synod, the Diocese purchased nine hundred and five (905) chickens for the prepared modern shelter.The primary objective of this project is to inspire and encourage all parishes under the Diocese to actively participate in various development activities in their respective areas, using the Diocese’s exemplary approach, operational methods, and study experiences as a reference. Furthermore, it aims to enable them to break away from reliance on alms (offering box/charity) and become self-sufficient in income. Read More »

በሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት የዶሮ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ!

ኤክቱስ ሰኔ 6/2018 ዓ.ም የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ቀደም ሲል በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እና በአንዲዳ የአዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ የተደረጉትን ተሞክሮዎች መሠረት በማድረግ በዛሬው ዕለት በሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ ፕሮጀክቱን ለመጀመር የሥጋ ዶሮዎች ጫጩቶችን ግዢ ፈጽሟል። ይህ እንቅስቃሴ ቤተ ክርስቲያን ከመንፈሳዊ አገልግሎቷ ጎን ለጎን ራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት የሚያጠናክር ነው። ይህንኑ የልማት ሥራ በጥራትና በስኬት ለመምራት እንዲቻል ሀገረ ስብከቱ ላለፉት ዕለታት ለዶሮዎቹ መኖሪያ የሚሆኑ ዘመናዊ ቤቶችን በጥናት ላይ በተመሠረተ መልኩ በሥራ ላይ ሲገነባ ያሳለፈ ሲሆን ይህ ቅድመ-ዝግጅት የዶሮዎቹን ደህንነት ለመጠበቅና ምርታማነታቸውን አስተማማኝ ለማድረግ ታስቦ የተከናወነ ተግባር መሆኑ ተገልጿል። ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበትም ሀገረ ስብከቱ ለተዘጋጀው ዘመናዊ መጠለያ የሚሆኑ ዘጠኝ መቶ አምስት (905) ዶሮዎችን ግዢ አከናውኗል። የዚህ ፕሮጀክት ዋና ዓላማ በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙ አድባራት ሁሉ የሀገረ ስብከቱን አርአያነት፣ አሠራርና የጥናት ተሞክሮ ዋቢ በማድረግ በየአካባቢያቸው በተለያዩ የልማት ሥራዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ማነቃቃትና ማበረታታት እንዲሁም ከሙዳየ ምጽዋት በመላቀቅ በገቢ ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ መሆኑ ተገልጿል።

በሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት የዶሮ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ! Read More »

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ከዚህ በታች ባለው ክፍት የሥራ መደብ መስፈርቱን የሚያሟላ ሠራተኛ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

ኤክቱስ ግንቦት 28/2018 ዓ.ም

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ከዚህ በታች ባለው ክፍት የሥራ መደብ መስፈርቱን የሚያሟላ ሠራተኛ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። Read More »

​“How long, O Lord, holy and true, until You judge and avenge our blood on those who dwell on the earth?” (Rev. 6:10)

​The killings committed against innocent believers (faithful / parishioners), the displacement of people, as well as the complete destruction by fire of the Tselata Chefa St. Gabriel Church—which has stood for over a century—and the looting of the Medhane Alem (Savior of the World) Church, occurring since May 31, 2026 (Ginbot 23, 2018 E.C.) in the Tseko and Shirka districts (woredas) of the East Arsi Diocese, have plunged our Church into deep mourning (grief). The repeated occurrence of similar security problems in the area and the subjection of innocent citizens, mothers, and children to severe mistreatment (hardship / harassment) and displacement (exile) is a matter that must be corrected and has deeply concerned us all. ​Therefore, we urgently call upon (remind / urge) the government and security forces to immediately fulfill their responsibility to maintain law and order and to protect the safety of citizens. We firmly demand that those involved in the attack be brought to justice, that the necessary support and rehabilitation (resettlement) be provided to our displaced and sheltered compatriots, and that reliable protection be ensured for the churches and the believers. ​We pray that God grants comfort (solace) to all the families of the deceased and displaced believers who are going through this difficult trial. May the Lord God grant comfort to those who are affected (harmed / injured); may He protect our country and our Orthodox Church.                 ​Abba GerimaBishop of the Gedeo, Kore, and Burji Diocese, and Member of the Holy Synod

​“How long, O Lord, holy and true, until You judge and avenge our blood on those who dwell on the earth?” (Rev. 6:10) Read More »

“Ee Mageno qullichchinna dhugaati gootti haani qico’n murte uwwa gophphaatte?  no’oxxe munde’a buttate’n hedhaake’n mayee halo fula gophphete?” (Yohanisixxa ra’iy 6:10)

Boroxxe Arsiixe Hageresibikete’n Asikonna Beshirka roga’n Ella 23/2018 G.W saffe mitte balleessa afebaake Magenin arda’n gelteexxi reyo nna manninxi godaana ittann Mitte dhibba wogga bari iima turteexxi Xellata Cefa qullichcha Gabreelinx Betekirstaanexx giirat gubemanna Medaanealemixxi betekirsataane’n geyeek moori haranga yaadiseeken. Okkone loola’n tenne fakkaataaxi bala higge-higgeen   kadda’na qullichchi manni,amuwwa,annoole fuggoxxe geebensha’n nna boga waale godaanaashsha assiteemmaxxee toggiyyo hasisaaxxe nna duuchchinga yaadiseexxe yaanen.Mootummanna nage’a heqisaalli seera heqisat ardinxa fayyunte heqqatixxa hurrine fullaashsha ege’ninshaannen. Tenne balleessa’n anga uggeeka manna seeri hunda geessisat,baqate godaaneexxi qubataaba gopheeke ardi’a hasisaak kiphinna hinge ofolaaka gara giissa;ittann Betekirstaanetenna ardi addachchisaake garin heqqemaashsha haranga jabaqicin qorraanen.tenne jabaxxe rakko  giddo hexxineeke reyeke mannike hadi’anna baqateeke ardi’a Mageni jajjabeenna uwwaashsha kadhantaannen.Mageni miidhemeeka jajjabeessowwaal, boga no’okanna Ortodokisetixxa adde heqqowwaal! Abba GeriimaGede’o Korenna Burji Hageresi kete Phaphasiichcho

“Ee Mageno qullichchinna dhugaati gootti haani qico’n murte uwwa gophphaatte?  no’oxxe munde’a buttate’n hedhaake’n mayee halo fula gophphete?” (Yohanisixxa ra’iy 6:10) Read More »

Scroll to Top