በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ቀዳሚ ገጽ ዜና

የሕንጸተ ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ በዓል ብፁዕነታቸው በተገኙበት በወናጎ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተከበረ!

ኤክቱስ ሰኔ 21/2018 ዓ.ም በዘመነ ሐዋርያት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን የታነጸበት ዓመታዊ በዓል ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት በወናጎ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተከበረ። ለዕለቱ የሚሆን ያሬዳዊ ዝማሬ የደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን ያቀረቡ ሲሆን የዕለቱን ትምህርት መጋቤ ሀዲስ ሔኖክ ፈንቴ በሚገባ አስተምረዋል። በደብሩ ለሚሠሩ የልማት ሥራዎች በሊቀ ልሳናት መምህር ሀብታሙ ተፈራ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ተከናውኗል። በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ያስተላለፉ ሲሆን በንግግራቸው ዕለቱ የቤተ ክርስቲያን በዓል መሆኑንና ቤተ ክርስቲያን ማለት ደግሞ ሕንጻው ብቻ አለመሆኑን በሚገባ አስረድተዋል። በተጨማሪም ብፁዕነታቸው ሰው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደመሆኑ ራሱን ካልተገቡ ልማዶችና ተግባራት እንዲጠብቅ አባታዊ መመሪያ ሰጥተው በጸሎት ፈጽመዋል።

የሕንጸተ ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ በዓል ብፁዕነታቸው በተገኙበት በወናጎ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተከበረ! Read More »

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ከዚህ በታች ባለው ክፍ የሥራ መደብ መስፈርቱን የሚያሟላ ሠራተኛ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል!

ኤክቱስ ሰኔ 18/2018 ዓ.ም

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ከዚህ በታች ባለው ክፍ የሥራ መደብ መስፈርቱን የሚያሟላ ሠራተኛ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል! Read More »

በሀገረ ስብከቱ የሕግ ክፍል ዐቢይ ኮሚቴ ብፁዕነታቸው በተገኙበት ሥልጠና ተሰጠ!

ኤክቱስ ሰኔ 17/2018 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ የሕግ ክፍል ዐቢይ ኮሚቴ አማካኝነት የተዘጋጀ የሕግ ሥልጠና ተሰጥቷል። በዚሁ መርሃግብር ላይ የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች፣ የዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት ሠራተኞች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎችና መላው የአስተዳደር አካላት ተሳትፈዋል። ሥልጠናውን የሰጡት የዲላ ዩኒቨርሲቲ የነጻ ሕግ አገልግሎት ማዕከል አስተባባሪ ወይዘሪት የምስራች ያለው ሲሆኑ በጠዋቱ ክፍለ-ጊዜ ስለ ሕግ ምንነት፣ ስለ ሕጋዊ ሰውነት፣ መብቶችና ስለ ንብረት ሕግ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከሰዓት በኋላ በነበረው መርሃ-ግብር ደግሞ ስለ ግዴታዎች፣ ውሎች እንዲሁም ስለ አሠሪና ሠራተኛ ሕጎች ትኩረት ያደረገ ትምህርት ቀርቧል። ሥልጠናው በአጠቃላይ ተቋማዊ አሠራርን በሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ለመምራትና መብትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ የፍትሐብሔር እና የወንጀል ሕግ መሠረታዊ ነጥቦችን ያካተተ ነበር። በሥልጠናው ወቅት ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከአሰልጣኟ በተጨማሪ የሕግ ክፍል ዐቢይ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዲያቆን መስፍን ተስፋዬ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተውባቸዋል። በማጠቃለያው ላይ ብፁዕነታቸው በተሰጠው ሥልጠና የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው “የቤተ ክርስቲያን ሀብቷ ልጆቿ ናቸው” በማለት በበጎ ፈቃዳቸው አገልግሎት ለሰጡት ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል። አያይዘውም እንዲህ ያሉ ሥልጠናዎች ሁሉም አካል ስለ ሕግ በትክክል እንዲያውቅና ቤተ ክርስቲያንም መብቷን በሕግ አግባብ እንዴት ማስጠበቅ እንዳለባት ለማስገንዘብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ጠቁመው መርሐ-ግብሩን በጸሎት ፈጽመዋል።

በሀገረ ስብከቱ የሕግ ክፍል ዐቢይ ኮሚቴ ብፁዕነታቸው በተገኙበት ሥልጠና ተሰጠ! Read More »

ማስታወቂያለጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የጸሐፊ የሥራ መደብ ውድድር ላይ የነበረውን ውጤት መግለጽን በተመለከተ!

ኤክቱስ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም

ማስታወቂያለጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የጸሐፊ የሥራ መደብ ውድድር ላይ የነበረውን ውጤት መግለጽን በተመለከተ! Read More »

በጉባኤው ለምዕመናን የንሥሐ አባት የማስያዝ መርሃግብር ተከናወነ!

ኤክቱስ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም ​በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በተካሄደው ዐቢይ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ምዕመናን የምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ተካፋይ እንዲሆኑ ለማስቻል የንሥሐ አባት የሌላቸውን ምዕመናን የመመዝገብ ሥራ ተከናውኗል። ይህ ልዩ መርሃ ግብር የጉባኤውን ዋና ዓላማ መነሻ በማድረግ ምዕመናን በንሥሐ ሕይወት ታንጸው ወደ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ እንዲቀርቡ በተግባር ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ​በዚሁ መሠረት በጉባኤው በርካታ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን የንሥሐ አባት እንዲኖራቸው እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን ይህም የሕዝቡን መንፈሳዊ ሕይወት ለመለወጥና ምዕመናንን የምሥጢራት ተካፋይ ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት ይበልጥ እንደሚያጠናክር ተገልጿል።

በጉባኤው ለምዕመናን የንሥሐ አባት የማስያዝ መርሃግብር ተከናወነ! Read More »

በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው ዐቢይ መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ

ኤክቱስ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም የታላቁን መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን ዓመታዊ በዓል በማስመልከት በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ዐቢይ መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቋል። ይህ ታላቅ ጉባኤ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት የተዘጋጀ መሆኑ ነው። የዚህ መንፈሳዊ ጉባኤ ዋና ዓላማ ምዕመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጡ በውጪው ቅጥር ግቢ ብቻ ተመላልሰው የሚመለሱ ሳይሆን በቀጥታ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሥጢራት ተካፋይ መሆን የሚችሉበትን ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑ ተገልጿል። በዚህም መሠረት የሦስቱም ቀናት የትምህርት ትኩረት ምዕመናን በጊዜ መጥተው እንዲያስቀድሱ፣ ንሥሐ እንዲገቡና ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን እንዲቀበሉ (እንዲቆርቡ) ለማነቃቃትና ለማስተማር ያለመ ነበር። በጉባኤው ላይ የተገኙት ከአዲስ አበባ ድረስ የተጋበዙት መምህራን ቀሲስ ደረጀ እና መምህር ብርሃኑ አድማስ ይህንን የጉባኤውን ዓላማ መነሻ በማድረግ የምዕመናንን መንፈሳዊ ሕይወት የሚፈትሹ አስተማሪ ትምህርቶችን በጥልቀት አስተምረዋል። እንዲሁም በዝማሬ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ እና ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን አገልግለዋል። ብፁዕነታቸው በምዕመኑ መንፈሳዊ መነቃቃት እጅግ መርካታቸውን የገለጹ ሲሆን አክለውም ለጉባኤው መሳካት በተለያየ መልኩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ምዕመናንም በንሥሐ ታጥበው የቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ተካፋይ መሆን እንዳለባቸው ባሳሰቡበት አባታዊ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የጉባኤው ፍጻሜ ሆኗል።

በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው ዐቢይ መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ Read More »

​ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ገለጻ አቀረቡ!

ኤክቱስ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለተዘጋጀው ጉባኤ ከአዲስ አበባ ለመጡት መምህራንና ዘማርያን ስለ ሀገረ ስብከቱ አሁናዊ ሁኔታ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የሀገረ ስብከቱ ታሪካዊ ዳራ፣ አጠቃላይ መዋቅራዊ መረጃዎች እንዲሁም በአሁኑ ወቅት እየተሠሩ ያሉ መንፈሳዊና ተቋማዊ ሥራዎች ለእንግዶቹ ቀርበዋል። ​ብፁዕነታቸው ባቀረቡት ገለጻ ሀገረ ስብከቱ በአገልግሎት እንቅስቃሴው ላይ እያጋጠሙት ያሉትን ወቅታዊ ተግዳሮቶች በጥናት ላይ ተመስርተው ያመለከቱ ሲሆን፤ ከችግሮቹ ጎን ለጎንም መፍትሔ ሊሆኑ የሚችሉ ስልታዊ የሃሳብ አማራጮችንና የቀጣይ የተግባር አቅጣጫዎችን በፕረዘንቴሽኑ አካተው አብራርተዋል። ​በተያያዘ ተጋባዥ እንግዶቹ በሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት በሥራ ላይ የሚገኘውን የዶሮ ልማት ፕሮጀክት፣ አዲሱን የመንበረ ጵጵስና ሕንፃ ግንባታ ሂደት እንዲሁም በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እየተከናወኑ ያሉ የግብርና የልማት ሥራዎችን ተገኝተው ጎብኝተዋል። የተደረገው የመስክ ምልከታ የሀገረ ስብከቱን ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ በተግባር ያሳየ እንደነበር ተመልክቷል።

​ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ገለጻ አቀረቡ! Read More »

ታላቅ በዓለ ንግሥና መንፈሳዊ ጉባኤ በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት በወናጎ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከሰኔ 19 – 21/ 2018 ዓ.ም ስለተዘጋጀ ሁላችሁም እንድትሳተፉ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!

ኤክቱስ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም “የእግዚአብሔር ድምጽ ከተማይቱን ይጠራታል”ሚክ ፮፥፱

ታላቅ በዓለ ንግሥና መንፈሳዊ ጉባኤ በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት በወናጎ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከሰኔ 19 – 21/ 2018 ዓ.ም ስለተዘጋጀ ሁላችሁም እንድትሳተፉ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን! Read More »

ሃያ ሁለት አዳዲስ አማንያን በጥምቀት የሥላሴን ልጅነት አገኙ!

ኤክቱስ ሰኔ 13/2018 ዓ.ም በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በኮሬ ዞን ወረዳ ቤተ ክህነት በደርባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በትናንትናው በቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል ዕለት ሃያ ሁለት አዳዲስ አማንያን በጥምቀት የሥላሴ ልጅነትን አግኝተዋል። መረጃው የደብሩ ሕዝብ ግንኙነት ነው።

ሃያ ሁለት አዳዲስ አማንያን በጥምቀት የሥላሴን ልጅነት አገኙ! Read More »

የሰኔ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል ብፁዕነታቸው በተገኙበት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተከበረ!

ኤክቱስ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ተከበረ። በዕለቱ በደብሩ መሠረተ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያም ለዕለቱ የሚስማማ ያሬዳዊ ዝማሬ ያቀረቡ ሲሆን በደብሩ ለሚሠሩ የልማት ሥራዎች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር በሀገረ ስብከቱ የሰበካ ጉባኤና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ክፍል ኃላፊ በመልአከ ብርሃን ዳንኤል ነቢዩ ተከናውኗል። የዕለቱን ትምህርት ብፁዕነታቸው እጅግ በጥልቀት ያስተማሩ ሲሆን ታሪኩን በሰፊው በመዘርዘር ምዕመናን ራሳቸውን እንዴት ከፈተና መጠበቅ እንዳለባቸው እና መንፈሳዊነታቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው አስተምረዋል። በተጨማሪም ብፁዕነታቸው ምዕመናን በቅዳሴ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲሄዱ በአጽንዖት አሳስበው በጸሎት ፈጽመዋል። በመርሃግብሩ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ፣ የሀገረ የመንፈሳዊ ትምህርትና የካህናት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ፣ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጠበብት መሠረት ይልማ፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ካህናትና ምዕመናን ተገኝተዋል።

የሰኔ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል ብፁዕነታቸው በተገኙበት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተከበረ! Read More »

Scroll to Top