ኤክቱስ ሰኔ 7/2018 ዓ.ም
በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተ ክህነት የይርጋጨፌ ደብረ ታቦር አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ከማኅበረ ቅዱሳን ይርጋጨፌ ወረዳ ማዕከል ጋር በመሆን ከሦስት ወር በላይ የቅድመ ጥምቀት ትምህርት ሲማሩ የቆዩ ሰባ ሁለት አዳዲስ አማንያን በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል።
ከተጠማቂያኑ መካከል ሠላሳ ስድስት ሴቶች ሠላሳ ስድስት ወንዶች ይገኙበታል።
