ሊቀ ትጉሃን ሀብታሙ አበበ – የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ
ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሀብታሙ አበበ የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ
ሊቀ ትጉሃን ሀብታሙ አበበ – የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ Read More »
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት
ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሀብታሙ አበበ የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ
ሊቀ ትጉሃን ሀብታሙ አበበ – የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ Read More »
መንፈሳዊ ጉባኤ ከህዳር 12 እስከ ህዳር 15፣ 2017 ዓ.ም
መንፈሳዊ ጉባኤ ከህዳር 12 እስከ ህዳር 15፣ 2017 ዓ.ም Read More »
መንፈሳዊ ጉባኤ ጥቅምት 26 እና 27፣ 2017 ዓ.ም
መንፈሳዊ ጉባኤ ጥቅምት 26 እና 27፣ 2017 ዓ.ም Read More »
መልአከ ኃይል ጌታሁን ገሰሰ – የሀገረ ስብከቱ ዕቅድና ልማት ክፍል ኃላፊ
መልአከ ኃይል ጌታሁን ገሰሰ – የሀገረ ስብከቱ ዕቅድና ልማት ክፍል ኃላፊ Read More »
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና ( 1ቆሮ 1 ÷ 17 ፡ 18 )
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና ( 1ቆሮ 1 ÷ 17 ፡ 18 ) Read More »
ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ በሀገረ ስብከቱ እየተከናወኑና ወደፊት ሊተገበሩ በታቀዱ ዕቅዶች ዙሪያ በአዲስአበባ ከተማ ከሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ጋር በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የነገረ መለኮት መማሪያ ክፍል የጋራ ውይይትና ምክክር አደረጉ። ለምክክሩ መነሻ የሚሆን ሰነድ የቀረበ ሲሆን በሰነዱ በሀገረ ስብከቱ ታሪካዊ ጉዞ፣ አሁናዊ ሀገረ ስብከቱ ያለበት ነባራዊ እውነታና ተግዳሮት፣ ወደፊት በሀገረ ስብከቱና በምእመናን መሥራት ያለበትን ተግባራት፣ የተሳታፊዎች ድርሻና አስተዋጽኦ ዙሪያ ሰፋ ያለ ሰነድ በፓወር ፖይንት ቀርቧል። ብፁዕነታቸው እስካሁን የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማዕከል ከተማ ተኮር በመሆኑ የተነሳ በገጠር ያለው ብዙ ቁጥር ያለው ምእመናን ካህን፣ መምህርና ሰባኬ ወንጌል ባለመኖሩ በትምህርት እና ጠባቂ በማጣት ወደ ተለያዩ ቤተ እምነት እንዲሄዱ ምክንያት የሆነና ሂደቱም እየቀጠለ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ከተመሠረተ ጥቂት ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን በተለይ በሀገረ ስብከት ደረጃ የ10 ዓመት ስልታዊ ዕቅድ ታቅዶ ወደ ተግባራዊ ሂደት መግባቱ አንዱ ማሳያ በመሆኑ ይህን ሀሳብ ለመላው ማህበረሰብ መድረስ እንዳለበት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል። እንደ ሀገረ ስብከት የቀረበው ጥናቱ ችግሮቹን በሙሉ የለየ ከመሆኑ በተጨማሪ የመፍትሔ ሃሳብ የተቀመጠ በመሆኑ ወደ ሥራ መግባት ያስፈልጋል ብለዋል ። በአዲስአበባ የሚኖሩ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆችም በቀረበው የውይይት ሰነድ መነሻነት ሃሳብ የሰጡ ሲሆን በቀጣይ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት በሃሳብ ፣በገንዘብ ፣በእውቀት እንዲሁም ሌሎችንም በማስተባበር ጭምር እገዛ ለማድረግ ቃል ገብተዋል። ይህ መድረክ ቀጣይነት ያለው ሲሆን ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በገንዘባቸው በእውቀታቸው በሙያቸው ሀገረ ስብከቱን እንዲደግፉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን በመጨረሻም በጉባኤው ማጠቃለያ ሶስት አባላት ያሉት አስተባባሪ ኮሚቴ በማቋቋም በብፁዕነታቸው ጸሎትና ቡራኬ ተጠናቋል።
የልማት እንቅስቃሴዎች November 27, 2012 ልማት በቤተክርስቲያን እንደ ተጀመረ ሥነ ፍጥረት በሰፊው ያስረዳል በመሆኑም ሥራ/ልማት የተጀመረውና የተገኘው ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሔር ነው፡፡ በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ከዚያም በቅደም ተከተል 22ቱን ፍጥረታት ከእሁድ እስከ ዓርብ በ6 ቀናት ፈጥሯል /ዘፍ 1፡1/ በአጠቃላይ ሥራ /ልማት ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን እንደ እግዚአብሔር ትዕዛዝ ሠርታ ሕብረተሰቡን የማሠራትና የማስተማር ተቀዳሚ ዓላማዋ ነው፡፡ ሥራን የማይወድ ሰው ሃይማኖት አለኝ እግዚአብሔርን አምናለሁ ብሎ መናገር ፈፅሞ አይቻለውም ይኸውም እንደ ቅዱሳት መፃህፍት አስተምሮ ሃይማኖት የሚገለፀው በሥራ ነው ሥራም የሚታወቀው በሃይማኖት ነው፡፡ በአጭሩ በሥራ ያልተገለጸ ሃይማኖት ዋጋ የለውም ማለት ነው፡፡ ከዚህም በመነሳነት በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በገጠርና በከተማ ባሉ ገዳማትና አድባራት ከጥንት ጀምሮ ስለሆነም ሀገረ ስብከቱ፡- ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሀገረ ስብከቱ ከእቅድና ከልማት ክፍሉ ጋር በመሆን ልማት ነክና ከሕንፃ ግንባታ ጋር ተያዥነት ያላቸው ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡
የሀገረ ስብከት ቅድመ ታሪክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቃለ ዐዋዲ ምዕራፍ ስድስት፣ ዐንቀጽ ሠላሳ ስምንት እስከ አርባ አምስት ድረስ በተዘረዘረው መሠረት ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠቅላይ ጽ/ቤት ቀጥሎ በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር መሠረት የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት መሥርቶ እና አጠናክሮ መሥራቱ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት አስፈላጊ እና ወሳኝ ነው፡፡በቃለ ዐዋዲው ዐንቀጽ አርባ ሦስት ቁጥር አንድ ላይ እንደ ተገለጠው «የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሀገረ ስብከቱ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ገዳማት፣ አድባራት እና የገጠር አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም በየደረጃው ለተቋቋሙት ሰበካ መንፈሳውያን ጉባኤያትና ለወረዳ ቤተ ክህነት የሥራ አመራርና ከፍተኛ የአስተዳደር ኃላፊነት ያለው መሥሪያ ቤት ነው» በእንግሊዝኛው «ዳዮሰስ» የሚለው ቃል dioikesis ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ነው፡፡ በመሆኑም ሀገረ ስብከት ማለት በአንድ ሊቀ ጳጳስ የሚመራ አንድ አካባቢ ማለት ነው፡፡ሀገረ ስብከት ለመጀመርያ ጊዜ በሥራ ላይ የዋለው ቅዱሳን ሐዋርያት የጌታችንን ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ ዓለምን ዕጣ በዕጣ ተከፋፍለው ለማስተማር በወጡ ጊዜ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ይመቻል፣ አይመችም ሳይሉ በተሠማሩበት ሀገረ ስብከት ገብተው አብያተ ክርስቲያናትን በመትከል፣ ምእመናንን አስተምረው በማጥመቅ፣ ካህናትን እና ዲያቆናትን በመሾም የወንጌልን ቃል ለዓለም አዳርሰዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም ሀገረ ስብከቱ፣ ዮሐንስ ወንጌላዊው በታናሽ እስያ ሀገረ ስብከቱ፣ ቶማስ በሕንድ ሀገረ ስብከቱ፣ማርቆስም በእስክንድርያ የሠሩት ሥራ ለዚህ ማስረጃችን ነው፡፡ በኢትዮጵያውያን ነገሥታት እና ሕዝብ በጎ ፈቃድ እና አርቆ አስተዋይነት ወደ እስክንድርያ ተልእኮ ለጵጵስና የበቃው የመጀመርያው ጳጳስ ፍሬምናጦስ ሀገረ ስብከት «ጳጳስ ዘአኩስም ወዘኩላ ኢትዮጵያ» የሚል ነበር፡፡ ከእርሱ በኋላ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር እንደ አንድ ሀገረ ስብከት ሆና ከአንድ ሺ ዓመታት በላይ ቆይታለች፡፡የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል በተለያዩ ጊዜያት ከአንድ በላይ ሊቃነ ጳጳሳት ተሾመው መጥተው ስለነበር ከአንድ በላይ አህጉረ ስብከት እንደነበራት ይጠቁማል፡፡ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት በ1438 ዓም ሁለት ሊቃነ ጳጳሳት ከግብጹ ፓትርያርክ ዮሐንስ 14ኛ ተሾመው መጥተው ነበር፡፡ እነዚህ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ለአምሐራ፣ አቡነ ገብርኤልም ለሸዋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ሆነው ተመደቡ፡፡ ይህም በወቅቱ የነበረውን የሀገረ ስብከት አደረጃጀት ያመለክታል፡፡ በዐፄ ዮሐንስ ጊዜም በ1874 ዓ.ም አራት ጳጳሳት ከግብጽ መጥተው አቡነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ፣ አቡነ ማቴዎስ የሸዋ ጳጳስ፣ አቡነ ሉቃስ የጎጃም፣ አቡነ ማርቆስ የበጌምድር ሀገረ ስብከት ጳጳስ ሆነው ተሾመዋል፡፡ እነዚህ አበው በውል የተለየ ቦታ ተከልሎ ተሰጥቷቸው እንደነበር ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ በጻፉት «ታሪከ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ» በተባለው መጽሐፋቸው የአቡነ ማቴዎስን ሀገረ ስብከት ሲዘረዝሩ «ሸዋን ከበሽሎ ወዲህ መደብ አድርገው የጁን፣ ዋድላን፣ ደላንታን፣ ዳውንትን፣ ግራ መቄትን፣ ከበጌምድር መጃን፣ ስዲን፣ ፎገራን፣ ጭህራን፣ደምቢያን፣ አርማጭሆን፣ መረባን፣ ጃን ፈቀራን፣ ጃንዋራን፣ ቆላ ወገራን፣ ጠገዴን፣ ወልቃይትን» እያለ ይዘረዝራል፡፡ በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመርያዎቹን ጳጳሳት ስታገኝ የታወጀው ዐዋጅ ዐንቀጽ አንድ «የኢትዮጵያ የመላው ሊቀ ጳጳሳት በአቡነ ቄርሎስ ሆኖ ደቡቡ ለአቡነ ሳዊሮስ፣ ምዕራቡ ለአቡነ አብርሃም፣ ምሥራቁ ለአቡነ ጴጥሮስ፣ አዜቡ ለአቡነ ሚካኤል፣ ሰሜኑ ለአቡነ ይስሐቅ ይሁን» ይላል፡፡ ይኼው ዐዋጅ የየአንዳንዱን ጳጳስ የሀገረ ስብከት ክልል ዝርዝር እና የመንበረ ጵጵስናውን ማረፊያ ከተማ ይተነትናል፡፡ በጣልያን ዘመን ግብፃዊው አቡነ ቄርሎስ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት እና ጳጳሳት ተሰባስበው ብጹዕ አቡነ አብርሃምን ሊቀ ጳጳስ አድርገው አምስት ጳጳሳትን ሲሾሙ አዳዲስ አህጉረ ስብከት ተመሠረቱ፡፡ አቡነ ዮሐንስ የሸዋ፣ አቡነ ማርቆስ የኤርትራ፣ አቡነ ማቴዎስ የወሎ፣ አቡነ ገብርኤል የጎንደር እንዲሁም አቡነ ሉቃስ የወለጋ አህጉረ ስብከት ጳጳሳት ሆነው ተሾመዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የራስዋን አህጉረ ስብከት መመሥረት የጀመረችው ከራስዋ ልጆች መካከል ፓትርያርክ ባገኘች ጊዜ ነበር፡፡ በ1943 ዓም የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ ሆነው የተሾሙት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ አቡነ ታዴዎስን ለጎሬ፣ አቡነ ገብርኤልን ለወሎ፣ አቡነ ማርቆስን ለኤርትራ፣ አቡነ ፊልጶስን ለኢየሩሳሌም፣ አቡነ ጎርጎርዮስን ለከፋ ጳጳሳት አድርገው ሾመው ነበር፡፡ ይህም አዳዲስ አህጉረ ስብከት መመሥረታቸውን ያመለክታል፡፡ በ1948 ዓ.ም ትግራይ በሀገረ ስብከትነት ተቋቁሞ ብጹዕ አቡነ ዮሐንስ ተሾመውበታል፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የአህጉረ ስብከት ቁጥር በየጊዜው እያደገ መጥቶ፣ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ «የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ» በተሰኘው መጽሐፋቸው እንደገለጡት፣ በ1974 ዓ.ም የአህጉረ ስብከቱ ዕድገት ወደ አሥራ ዘጠኋ ያህል ደርሶ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ «የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ እስከ 2000 ዓ.ም» የተሰኘው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት መጽሐፍ እንደሚገልጠው አርባ በሀገር ውስጥ፣ ስምንት ከሀገር ውጭ፤ በድምሩ አርባ ስምንት አህጉረ ስብከት ይገኛሉ፡፡ ሀገረ ስብከት ሀገረ ስብከት ቤተ ክህነቱን ወክሎ የሚሠራ ተቋም ሲሆን፣ ሃይማኖቱን እና ቀኖናውን ለመጠበቅ እና ለማስጠበቅ፣ ከክርስቶስ ጀምሮ የመጣውን ሀብተ ክህነት ለመጠበቅ እና ለማስተላለፍ፣ ስብከተ ወንጌል እንዲስፋፋ፣ ገዳማት እና አድባራት እንዲረዱ፣ አብያተ ክርስቲያናት እንዲተከሉ፣ ምእመናን ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መብት እንዲከበር፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት ወጥ እና ሥርዓቱን የጠበቀ እንዲሆን፣ የካህናት አስተዳደር እና አገልግሎት በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ መሠረት እንዲሆን፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብት እና ንብረት በሕግ እና በሥርዓት መሠረት እንዲጠበቅ፣ ምእመናን በቤተ ክርስቲያኒቱ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ እና እንዲሰጡ ማድረግ ዋና ዋናዎቹ ተግባሮቹ ናቸው፡፡
የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት መልዕክት ለሀገራችን ኢትዮጵያ ጥንታዊት ታሪካዊትና ብሔራዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በረዥም ዘመንጉዞዋ ያበረከተችው እሴት ለአፍሪካዊያን መኩሪያና ለመላው ዓለም በታሪክ መዝገብ ከፍተኛሥፍራየሚሰጣት ቤተክርስቲያን ናት፡፡በሀገራችን የሚገኙት ጥንታውያን ገዳማትና አድባራት ከመንፈሳዊ አገልግሎታቸው ባሻገር ለሀገሪቱ ማንነት የስኬት ውጤትዋና መሠረቶች ናቸው፡፡ የተወደዳችሁ ምዕመናን!የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እንደ አንድ ትልቅ ሃይማኖታዊ ተቋምነቷ ለሀገሪቱ ሰፊ ሥራን አበርክታለች፣ እያበረከተችም ነው፡፡ ታሪካዊዋንና ጥንታዊትዋን ቤተክርስቲያን የበለጠ ለማወቅ የተዘጋጀው ይህ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ድረ ገጽ ለአብያተ ክርስቲያናት ጠቃሚ መረጃ ከመስጠት ባሻገር ለሀገር ውስጥና ለውጪ ሀገር ጎብኚዎች መረጃን በመስጠት ጠቀሜታው እጅግ በጣም የላቀነው ብለን እናምናለን፡፡ በመሆኑም ቤተክርስቲያችን ብዙ ዘመናትን ተሻግራ አሁን የደረስንበት ደረጃ ላይ የደረሰች ሲሆን በዚህ በተጓዘችባቸው ጉዞዎች አባቶቻችን ሃለፊያትንና መፃዕያትን በመገንዘብ አስቀድመው ከትውልድ ሃሳብ ቀድመውና ከትውልድ እኩል እየተጓዙ ክርስትናን አቆይተው ለእኛ አስረክበውልናል፡፡ እኛም ከአባቶቻችን የተረከብነውን ሃይማኖት ለትውልዱ ዘመኑ በሚፈቅደው መሳሪያ በመገልገል ሐዋሪያዊ መልዕክት ማስተላለፍ አስፈላጊነው ፡፡ የሰው ልጅ ሲፈጠር በቦታ የሚወሰንና የሚገደብ ሆኖ በመፈጠሩ በአንድ ሥፍራ ሆኖ በሌላ ስፍራ ያለውን ነገር በራሱ ለማወቅ አይችልም፡፡ይህንን ማድረግ የሚቻለው እንደ ቅዱሳኑ በሕይወቱ ሳለ በቅቶ ሲገኝ ብቻ ነው አለ በለዚያ በሀገር ርቀት ምክንያት ሰዎች ከሰዎች ጋር ለመገናኘት ሌሎች መንገዶችን መጠቀም ስለነበረበት ከእግዚአብሔር በተሰጠው አዕምሮ በመጠቀም የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን ሰርቷል፡፡ ከእነዚህም መካከል አሁን በዚህ ዘመን የተጀመረው የመረጃ መረብ ቴክኖሎጅ አንዱነው፡፡ይህም ቴክኖሎጂ ትውልዱ ሲጠቀምበት በዓለማዊ ትምህርት ብቻ እንዳይዋጥ መንፈሳዊ ትምህርትንም ለማስታላለፍ ጥሩ አማራጭ መንገድ ነው። ቤተክርስቲያንም በዘመኑ ያሉትን በዕውቀቱ የተካኑትን ልጆቿን በመጠቀም ዘመኑ ባስገኘው መሳሪያ ትምህርት እንዲስተላለፍ መደረጉ አግባብ ነው፡፡ አባቶቻችን ሐዋሪያት በቁጥር ጥቂቶች ሲሆኑ የተሰጣቸውን የወንጌል ቃል እስከ ምድር ዳርቻ ምስክሮች በመሆን በልዩ ልዩ ቋንቋ ፣ የወንጌሉን ቃል ለዓለም ሁሉ አዳርሰዋል፡፡በዚህ ዘመን ደግሞ ይህንን ዓለም አቀፍ ሐዋሪያዊ ተልዕኮ ለመፈጸም ቴክኖሎጂውን መጠቀም ጥሩ አማራጭ ነው፡፡ በመሆኑም በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ሰዎችን በቀላሉ ስለ ሀገረ ስብከታችን ሁለንተናዊ የሥራ እንቅስቀሴም ይሁን ትምህርታዊ የሆኑ ጽሁፎችን በማዘጋጀት በዌብሳይቱ ብዙ ሰዎችን በቀላሉ ማስተማር ይቻላል፡፡ የተወደዳችሁ ምዕመናን ሀገረስብከቱ የሚጠበቅበት ድርሻውን ለማበርከት ለሚያደርገውን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ከጎኑ ሆናችሁ የሚጠበቅባችሁን ማንኛውንም የቤተክርስቲያን አገልግሎት ተሳታፊ እንድትሆኑ ሀገረ ስብከቱ መልእክቱን ያስተላልፋል፡፡ ጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት
የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት መልዕክት Read More »
ማኀበራዊ ጉዳይ የኢትዮጵያ ቤት ክርስቲያን ማኅበራዊ አስተዋጽኦ የሚመነጨው ከዐሥርቱ ሕግጋት እና ከስድሰተቱ ቃላተ ወንጌል ነው፡፡ ዐሠርቱ ቃላተ ኦሪት እና ስድስቱ ቃላተ ወንጌል በመተባበር ማኅበራዊ ሕግጋትን ያስተምራሉ፡፡ ማኅበራዊ ሕጎች በአንድ የኅብረተሰብ ክፍል ውስጥ የእረስ በእርስ ትስስር እና መተሳስብን ፍቅርንና አብሮ በሰላም የሚኖርበት አንድነትን የሚያጠብቁ መሠረቶች ናቸው፡፡ በመልካም መሠረት ላይ የሚኖር የኅብረተሰብ ክፍል ደግሞ በጊዜ ሂደት የራሱ የሆነ ባህል ይፈጥራል፡፡ ባህል ደግሞ የማንነቱ መገለጫ ከሌላ የኅብረተሰብ ክፍል የሚለይበት ኦርቶዶክሳዊ ማንነቱ የሚታወቅበት አንዱ መንገድ ነው፡፡ በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሚከተሉትን ማኅበራዊ አሰተዋጽኦዎች አድርጋለች እያደረገችም ነው፡፡ ማኅበራዊ አስተዋጽ ፩∙ በበጎ አድራጎት አገልግሎት መሳተፍ የበጎ አድራጎት መነሻው ቅድሳት መጻሕፍት ሲሆኑ በኅብረተሰብ መካከል መተሳሰብን እና ሰብአዊ ርህራሄን ከማጎልበት ባሻገር ለነፍስ ዋጋ የሚያሰጡ ትምህርቶችንም የያዙ ናቸው፡፡ስለሆነም የመንፈስዊ አገልግሎት ዋጋ ከመስጠቱም ባሻገር በህብረተሰቡ ዘንድ የመተሳሰብና የሰብአዊ ርኅራኄ መንፈስ ለማዳበር እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ የህንንም ለማድረግ ጠቃሚ የሆኑት ስልቶች ሕዝቡን ማስተማር፤ ማደራጀት፤ ማስተባበር እና ተቋማትን መክፈት ናቸው፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መነሻውም ሃይማኖት ነው፡፡ እግዚአብሔር ራሱ ያለምንም ከፍያ /በጸጋ/ ፍጥረትን ሁሉ መልካም መሆናቸውን እያረጋገጠ ከመፍጠር የዕለት ተዕለት ፈላጎታቸውን እሰከ መስጠት ድረስ መሠረት ሆአኖል፡፡ አምላካቸውን የተከተሉ ሰዎችም ከአምላካቸው ተምረው ይህንኑ የበጎ ፋቃድ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡ አበ ብዙኀን አብርሃም ያለምንም ክፍያ መንገደኞችን ማብላቱንና ማጠጣቱ ዋና ማስረጃ ነው፡፡በመጽሐፍ ቅድስ ውስጥ የተዘረዘሩ ብዙ አገልግሎቶች በበጎ ፈቃድ የተከናወኑ ናቸው፡፡ ሰው የተቸገረ ወገኑን እንዲሁም እንግዶችን እየተቀበለ በገንዘብ፣ በእውቀት፣ በጉልበት ያለውን ለሌለው መርዳትና ማገዝ ይጠበቅበታል፡፡ ደጉ ሳምራዊ ተጎድቶ፣ ቆስሎ ያየውን ሰው፤ ማንም ሳያስገድደው በፈቃዱ አንስቶ፤ ቁስሉን በዘይት ቀብቶ፤ ለሚረዱት ሌሎች ሰዎች ገንዘብ ሰጥቶ፤ ተመልሶ እንደሚረዳው ቃል ገብቶ መሄዱ የሚታወስ የቤተ ክርስቲያን ተግባር ነው፡፡ አሁንም በቤተ ክርስቲያን ካህናት፤ ዲያቆናት፤ ምእመናን ብዙ ነገሮችን በበጎ ፈቃድ የሠራሉ፡፡የሕፃናት ማሳደጊያ እና የአረጋውያን መጦሪያ ተቋማት መከፈት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲየን ድሆችን የመርዳት የቆየ ባህል አላት፡፡ ምጽዋት ከመሥዋዕት ይበልጣል እንዲል፡፡ /ማቴ ፱፥፲፩፤ሆሴ ፮፥፮፤ አረጋዊ መንፈሳዊ/፡፡ ብራብ አበልችሁኝ፤ ብጠማ አጠጣችሁኝ፤ ብታረዝ አለበሳችሁኝ፤ የሚለው የምጽዋት ዋጋ በቅዱስ መጽሐፍ፣ በብዙ ገድላትና ድርሳናት ጎልቶ ስለተሰበከ ምጽዋትን ለተቸገሩ መስጠት በጠቅላላ የኢትዮጵያውያን ታላቅ መንፈሳዊ እሴት ነው፡፡ ትናንትም ሆነ ዛሬ የማኅበረሰባችን ማኅበራዊ ዋስትና ይኸው ክርስቲያናዊ ባህላችን ነው፡፡ የቀድሞው፣ የዛሬውም የቆሎ ተማሪ የተማረው እና እየተማረ ያለው ቤተ ክርስቲያን በዘረጋችውና በሺሕ በሚቆጠሩ ዓመታት በዘለቀው በዚሁ ተቋም አካል ጽኑ ሃይማኖታዊ ባህል እንጂ በመንግሥት ወይም በሌሎች ድጋፍ አይደለም፡፡ በአጠቃለይ ቤተ ክርስቲያን ለተራቡት ቀለብ፣ ለታረዙት ልብስ፣ ለሕሙማን ፈውስ፣ ለአረጋውያን መጦሪያና ለእጓለምውታን ማሳደጊያ የሆነ ማኅበራዊ ዋስትና ለማረጋጥ በማስተባበር የተቻላትን ሁሉ ስታደርግ ቆይታለች፡፡እነዚህ መኅበራዊ ተቋማት እንደዘመናችን ዓይነት መዋቅር ባይኖራቸውም በስንበቴና በጡት ልጅ እና በመሳሰሉት ማኅበራዊ መጠሪያዎች የሚታወቁ ማኅበራዊ ዋስትናዎች ነበሩ፡፡ ዘመናዊ የማኀበራዊ ዋስትና በኢትዮጵያ እሰከሚጀመርበት ድረስ ጧሪ የሌላቸው ሰዎች እና አሳዳጊ ያጡ ሕፃናት በዚህ መንገድ ሲረዱ ኑረዋል፡፡እነዚህ ተቋማት ከተመሠረቱም በኋላ ቤተ ክትስቲያን አዲሶቹን ተቋማት መሥርታ የማኅበራዊ ዋስትና አገልግሎቷን አጠናክራ ቀጥላለች፡፡በድርቅ ጊዜ ርዳታን በማስተባበር ስደተኞችን መርዳትቤተ ክርስቲያን የተቸገሩትን መርዳት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተግባሯ በመሆኑ ተግባሩን ስታከናውነው ኖራለች፡፡ ዛሬም በዘመናዊ መልክ ልማትና ተራድኦ ኮሚሽን በማቋቋም ድንገተኛ አደጋ ሲከሰት እህል ዘይት እና ሌሎች ምግቦችን በማቅረብ የሰብአዊ እርዳታና መልሶ ማቋቋም ተግባር አከናውናለች እያከናወነችም ትገኛለች፡፡መንፈሳዊ ማኀበራትን መደራጀትለበጎ ፈቃድ አገልግሎት ምሳሌ የሚሆኑ ዝክሮች፣ ሰንበቴዎችና ማኅበሮች ወዘተ በስፋት ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የተቀደሱና ጠናካራ ትውፊቶች የበጎ አገልግሎት ለመሰጠት አመቺ ናቸው፡፡ በገጠሩ አካባቢ በስፋት ይጠቀሙባቸዋል፡፡ በድንገት ሀብት ንብረቱ ቢቃጠልበት ርዳታ ያደርጉለታል፡፡ እንዲሁም ጧሪ ዘመድ ሳይኖረውና የሚሠራ ጉልበቱ ሲደክም ከቤታቸው በማስቀመጥ ተፈራርቀው የጦሩታል፡፡ ይህም ተግባር መጽሐፍ ቅድሳዊ ተግባር በመሆኑ በሕዝቡ አኗኗር ላይ በጎ ተጽዕኖ በማሳደሩ ለዚህ ድርጊት የቤተ ክርስቲያን አስተዋጽኦ ክፍተኛ ነው :: ፪ መልካም ዜጋን በማፍራት ሰው ሁሉ ለሚኖርባት ዓለም ነጻና ክቡር ዜጋ ነው፡፡ዜግነት የተፈጥሮ ሲሆን መልካም ዜግት ግን የመልም ጠባይና ምግባር ውጤት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛና ቅድስት በመሆኗ ዜጎች ሁሉ በሃይማኖትና በምግባር ለሀገራቸውና ለሰማያዊት ርስታቸው መልካምና ታማኝ እንዲሆኑ ከማስተማርና ከመምከር የተቆጠበችበት አፍታ ጊዜ የለም፡፡ ምንም እንኳን በሥልጣኔ ስም የሚመጡ ጉዳዮች የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ ቢፈታተኑትም ቤተክርስቲያን ግን ከጥንት ጀምሮ ልጆቿ በሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባቸው የሀገርና የወገን አለኝታዎች እንዲሆኑ የተለያዩ ሥራዎችን ሠርታለች፡፡ ፫ የሥራ ባህልን በማዳበር ሥራ የኑሮ መሠረት መሆኑን ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡የምትመራባቸው ቅዱሳት መጻሕፍትም የሥራን ጠቃሚነት በስፋት የሚተነትኑና የሥራን ባህል የሚያዳብሩ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለአባታችን አዳም ገነትን ያበጃት ይጠብቃትም ዘንድ ሓላፊነትን ሰጥቶት ነበር፡፡ አዳም ከተሳሳተም በኋላ ጥሮ ግሮ በወዙ እንዲበላ፣ በስንፍና ተዘልሎ እንዳየቀመጥ፣ በወገኖቹ ላይ ጥገኛ ሆኖ እንዳይከብድባቸው ይልቁንም የድካሙን ፍሬ ቢመገብ መልካም እንደሚሆንለት ተነግሮታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት መሠረት በማድረግ ልጆቿ ዘወትር በሥራ የተጠመዱ እንዲሆኑ ይህ ካልሆነ ግን አእምሮአቸው የዲያብሎስ ተገዥ እንደሚሆን ታሰተምራለች፡፡ ከዚህ አኳያ ቤተ ክርስቲያን የሕዝቡን ሁለንተናዊ እድገት በማጽናት ለኢኮኖሚ ጤናማ እድገት፣ ለሕዝቡ ልማትና ደኅንነት መጠበቅ የበኩሏን ድረሻ እየተወጣች ነው፡፡ ፬∙ሥነምግባርን በማሰተማር ሥነምግባር የሚለው ቃል በሥራ ማማር፣ የሥራ መልካምነት ማለት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ክርሰቲያኖች በጎ ሥራን እንዲሠሩ፣ ሰዎችን ያለምንም ልዩነት እንዲወዱ፣ የራስን ሰውነት ሕይወትና ክብር ከሚጎዱ ዲርጊቶች እንዲረቁ ሕይወታቸውን በቅድስና መንፈሳቸውን በንጽሕና እዲያዙ ታሰተምራለች፡፡ ከዚህም ትምህርቷ የተነሣ ምእመኖቿ በጎ ሕሊና እንዲኖራቸው፣ ከአንደበታቸው መልካም ቃል እንዲወጣ ንግግራቸው ሁሉ ከቁጣና ከትዕቢት የራቀ ጠብን ከመጫር ይልቅ ሰላምና እርቅ አንድነት እንዲያወርድ ወደ እግዚአብሔር መቅረብና ከእርሱ ጋር ሊያኖር የሚችል መልካም ሥራን መሥራትን የሚፈልጉ እንዲሆኑ አድረጋለች፤ እያደረገችም ነው፡፡ በማኅበራዊ ሕይወትም የሌላውን ድካምና ስሕተት ለቅመው ከመክሰስና ከመተቸት ይልቅ ባለማወቅ ያጠፋነውን ወደ ማወቅ አድርሰው ያርሙታል፣ የደከመውን ያበረቱታል፡፡ ክፉውን ወደ መልካም ይለውጡታል፡፡ ሕይወታቸው በእግዚአብሔር ፊት ብቻ ሳይሆን በሰውም ፊት የተገለጠ ሰለሆነ በኅብረተሰቡም ፊት መልካም የሆነውን የፈጽማሉ፡፡ ‘’ስለምናገለግለው ስለዚህ ለጋስ ስጦታው ማነም እንዳይነቅፈን እንጠነቀቃለን በጌታ ፊት ብቻ ያይደለ ነገር ግን በሰው ፊት ደግሞ መልካም የሆነውን እናስባለንና’’ ፡፡ በአጠቃለይ ቤተ ክርስቲያን ባላት የሥነ ምግባር ትምህርቷ ኅብረተሰቡ ለእግዚአብሔር እንዲሁም ለሀገሩና ለባልንጀራው ታማኝ እንዲሆንና ሓላፊነቱን፤ ተጠያቂነቱን በአግባቡ እንዲወጣ፤ ያለ እድልዎ ሥራን እንዲያከናውን በማሰተማር ሙስናን በመከላል ለሀገር ዕድገት አስተዋጽኦ ስታበረክት ቆይታለች እያበረከተችም ትገኛለች፡፡ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን ፤ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ፤መፈራት ለሚገባው መፈራትን፣ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ፡፡ በሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያ መሠረት ቤተ ክርስቲያን የእንግዚአብሔር የሆነውን አሥራት በኩራት ለቤተክርሰቲያን ግብርን ደግሞ ለመንግሥት በወቅቱ እንዲከፍሉ ለማድረግ የማይናቅ ድርሻ ተወጥታለች፡፡ ይህን ማለት የሚያሰደፍረውም፡- በተለይም በዚህ በዘመነ ሉላዊነት /Globalization/ በተለያየ መልኩ የሥነ ምብናር ችግር እየገጠመው ያለውን ትውልድ፣ በተሻለ መለኩ ለመቅረጽ መንግሥት በኮሚሽን ደረጃ አቋቁም የሚታገልበትን ሙስና ከሥሩ የሚነቅል ሥራ ለመሥራት ቤት ክርስቲያን ካለባት ሓላፊነት አኳያ እያደረገችው ያለው ትውልድን በሥነ ምብባር የማነጽ ሥራ የሃይማኖቱ ግዴታ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ ፭∙ በጤና ጥበቃ ዘርፍ በመሳተፍ ጤና ማለት የበሽታ አለመኖር ብቻ ሳይሆን የአንድ ሰው /ማኅበረሰብ/፣ አካላዊ /physical/፣ ሥነ ልቡናዊ /psychological/ ማኀበረሰባዊ /social/ አእምሮአዊ /mental/ እና ሃይማኖታዊ ደኅንነት / Spritual wellbeing / ነው፡፡ አስከፊ በሆነ ድህነትና ችግር ውስጥ ላለ ኅብረተሰብ የጤና ችግር ትልቁን ቦታ የሚይዝ ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ከሥጋ ሕመም ባሻገር የሚፈጥረው የአእምሮ ጭንቀት የአንድ ኀብረተሰብ ክፍልን ምርታማነትና ውጤታማነት እጅጉን ይጎዳል፡፡ ቤተ ክፍስቲያን የጤናውን ችግር ለመቅረፍ ያላትን አስተዋጽኦ የሚከተሉትን መዘርዘር/መጥቀስ ይቻላል፡፡ ፮∙ በትምህርት ዘርፍ ባለአእምሮ ሰው በደማዊነት አእምሮው እያዘገመ እንዳይኖር በትምህርት ድንቁርናን አርቆ፣ ክፉና ደጉን ለይቶ በዕውቀት ዓለም እንዲኖር ልቡናን