በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የልማት እንቅስቃሴዎች

የዶሮ ልማት ፕሮጀክትን አስመልክቶ የውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃግብር ተካሄደ!

ኤክቱስ ታኅሣሥ 17/2018 ዓ.ም በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የተጀመረው የዶሮ ልማት ፕሮጀክት ውጤታማ እንዲሆን የደብሩ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስተዳደርና የልማት ኮሚቴ አባላት ለሥራው ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃግብር ተካሄደ። ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃግብር የተካሄደው የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅና የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነው። ​የመርሃግብሩ ዋና ዓላማ የደብሩ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስተዳደርና የልማት ኮሚቴው ለፕሮጀክቱ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉና ለሥራው መፋጠን በትጋት እንዲነሳሱ ግንዛቤ መፍጠር ነው። በውይይቱ ወቅት የልማት ኮሚቴውና የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት በፕሮጀክቱ አፈጻጸም፣ በሚጠበቁ ውጤቶችና ሊያጋጥሙ በሚችሉ ተግዳሮቶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ የበኩላቸውን ገንቢ ሃሳቦችን አቅርበዋል። የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ ከብፁዕነታቸው በሚሰጣቸው አባታዊ መመሪያ መሰረት በፕሮጀክቱ ዙርያ ሰፊ ሥራ እንደተሠራ እንዲሁም ከዚህም በኋላ በርካታ ሥራዎችን ለመሥራት ቅድመ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል። ​ብፁዕነታቸው የቀረቡትን ሃሳቦች መነሻ በማድረግ በሰጡት አባታዊ ግንዛቤ ማስጨበጫ ንግግር፤ ቤተ ክርስቲያን ያሏትን ሀብቶች ተጠቅማ ሙዳየ ምጽዋትን ለዓላማው ማዋልና ራሷን በኢኮኖሚ መቻል እንዳለባት አስገንዝበዋል። የዶሮ ልማት ፕሮጀክቱ የደብሩን ገቢ ከማሳደግ ባለፈ፣ ለሌሎች አድባራትና ገዳማት ተምሳሌት የሚሆን ሥራ መሆኑን ገልጸው፤ የሰበካ ጉባኤውና የልማት ኮሚቴው በኃላፊነት ስሜትና በቁርጠኝነት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ መመሪያ ሰጥተው በጸሎት ፈጽመዋል።

የዶሮ ልማት ፕሮጀክትን አስመልክቶ የውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃግብር ተካሄደ! Read More »

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት መንፈሳዊ አገልግሎትን ከልማት ጋር የሚያቀናጅ የዶሮ እርባታ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ!!!

ኤክቱስ ታኅሣሥ 11/2018 ዓ.ም በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል እና በአንዲዳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያናት ገቢን ለማጠናከርና የአብነት ተማሪዎችን በቋሚነት ለመርዳት የታለመ የዶሮ እርባታ ፕሮጀክት በይፋ ተጀምሯል። ይህ ተስፋ ሰጪ የልማት ሥራ በዶ/ር ሙሉእመቤት ወርቁ አነሳሽነት እንዲሁም በላዕከ ወንጌል ያሬድ አደመ እና በወ/ሪት ሰላም አያሌው አስተባባሪነት የተጀመረ ነው። በመጀመሪያው ዙር በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን 250 የሥጋ ዶሮዎች እንዲሁም በአንዲዳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን 100 የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች እንዲገቡ ተደርጓል። ለሥራው ስኬታማነትም የዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ተቋም (ILRI) ሰራተኛና ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ወንድሜነህ እሳቱ፣ ዶ/ር አሉላ አለማየሁ እና ዶ/ር መኮንን ግርማ ዶሮዎችን ከአዲስ አበባ በማምጣት፣ በማስገባትና የማስጀመር ሥራውን በማከናወን ሙያዊ ፣ የቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። ከዲላ መንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት ከሚገኙ 13 አብያተ ክርስቲያናት ለተውጣጡ 24 ሰልጣኞች በዘርፉ ባለሙያዎች ስለ ዶሮ እርባታ ጥልቅ ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናውም፦•  ጥምር ጠቀሜታ ያላቸው ዶሮዎች እርባታ፤•  የዶሮ መኖ አዘገጃጀት፤•  ሳይንሳዊ የዶሮ እንክብካቤና ጤና አጠባበቅ እና•  የዶሮ እርባታ ትርፋማነት ላይ ያተኮረ ነበር። ሰልጣኞቹ በሰጡት አስተያየትም “ይህ ስልጠና ቤተ ክርስቲያናችን ያላትን ሰፊ መሬትና የሰው ኃይል በመጠቀም እንዴት ውጤታማ መሆን እንደምትችል ዓይን ከፋች ሆኖልናል፤ ወደ ተግባር ለመግባትም ተዘጋጅተናል” ብለዋል። የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ በዕለቱ ተገኝተው  ይህ ፕሮጀክት እውን እንዲሆን ያስተባበሩትን፣ ድጋፍ ያደረጉትንና ስልጠና የሰጡ ባለሙያዎችን አመስግነው ሀገረ ስብከቱ የፕሮጀክቱ ባለቤት በመሆን ወደ ትግበራ እንደተገባና ወደፊትም አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ በመግለጽ አባታዊ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል። ብፁዕነታቸው በመልእክታቸውም “ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎቷን በስፋት ለማከናወን ራሷን በኢኮኖሚ መደገፍ ይኖርባታል። ይህ የዶሮ እርባታ ፕሮጀክት የአካባቢውን ምዕመናንና ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ የሚችልና የአብነት ተማሪዎቻችንን ለመመገብና የቤተ ክርስቲያንን ገቢ ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ አለው” በማለት አሳስበዋል። በዕለቱ እንግዶች በአንዲዳ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ የአብነት ተማሪዎችን በመጎብኘት የትምህርት ሂደታቸውን ተመልክተዋል።

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት መንፈሳዊ አገልግሎትን ከልማት ጋር የሚያቀናጅ የዶሮ እርባታ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ!!! Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ በዲላ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ያደረጉት የመስክ ጉብኝት!!

በባለፈው ዓመት ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እያንዳንዱ መሬት ጾም ማደር እንደሌለበት ባስተላለፉት መመሪያ መሰረት በሀገረ ስብከቱ ባሉ አጥብያ አቢያተ ክርስቲያናት የተሰሩ በርካታ የግብርና የልማት ሥራዎት እየተጎበኙ ይገኛሉ። በዚሁ መሰረት የዲላ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን አንድ ሄክታር በላይ በሚሆን መሬት ላይ ፓፓያ ፣ ማንጎ፣ የጓሮ አትክልት ፣ ብርቱካን፣ ሸንኮራ እና የንብ እርባታ ተጎብኝቷል። ኤክቱስ ሐምሌ 04/2017

ብፁዕ አቡነ ገሪማ በዲላ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ያደረጉት የመስክ ጉብኝት!! Read More »

የልማት እንቅስቃሴዎች

የልማት እንቅስቃሴዎች November 27, 2012 ልማት በቤተክርስቲያን እንደ ተጀመረ ሥነ ፍጥረት በሰፊው ያስረዳል በመሆኑም ሥራ/ልማት የተጀመረውና የተገኘው ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሔር ነው፡፡ በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ከዚያም በቅደም ተከተል 22ቱን ፍጥረታት ከእሁድ እስከ ዓርብ በ6 ቀናት ፈጥሯል /ዘፍ 1፡1/ በአጠቃላይ ሥራ /ልማት ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን እንደ እግዚአብሔር ትዕዛዝ ሠርታ ሕብረተሰቡን የማሠራትና የማስተማር ተቀዳሚ ዓላማዋ ነው፡፡ ሥራን የማይወድ ሰው ሃይማኖት አለኝ እግዚአብሔርን አምናለሁ ብሎ መናገር ፈፅሞ አይቻለውም ይኸውም እንደ ቅዱሳት መፃህፍት አስተምሮ ሃይማኖት የሚገለፀው በሥራ ነው ሥራም የሚታወቀው በሃይማኖት ነው፡፡ በአጭሩ በሥራ ያልተገለጸ ሃይማኖት ዋጋ የለውም ማለት ነው፡፡ ከዚህም በመነሳነት በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በገጠርና በከተማ ባሉ ገዳማትና አድባራት ከጥንት     ጀምሮ ስለሆነም ሀገረ ስብከቱ፡- ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሀገረ ስብከቱ ከእቅድና ከልማት ክፍሉ ጋር በመሆን ልማት ነክና ከሕንፃ ግንባታ ጋር ተያዥነት ያላቸው ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

የልማት እንቅስቃሴዎች Read More »

Scroll to Top