በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ብፁዕ አቡነ ገሪማ በዲላ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ያደረጉት የመስክ ጉብኝት!!

በባለፈው ዓመት ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እያንዳንዱ መሬት ጾም ማደር እንደሌለበት ባስተላለፉት መመሪያ መሰረት በሀገረ ስብከቱ ባሉ አጥብያ አቢያተ ክርስቲያናት የተሰሩ በርካታ የግብርና የልማት ሥራዎት እየተጎበኙ ይገኛሉ።

በዚሁ መሰረት የዲላ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን አንድ ሄክታር በላይ በሚሆን መሬት ላይ ፓፓያ ፣ ማንጎ፣ የጓሮ አትክልት ፣ ብርቱካን፣ ሸንኮራ እና የንብ እርባታ ተጎብኝቷል።

ኤክቱስ ሐምሌ 04/2017

Scroll to Top