በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መልዕክት

A message transmitted by Hisgrace Abune Gerima Bishop

​A message transmitted by His Eminence Abune Gerima, bishop of the Gedeo, Kore, and Burji Diocese and Member of the Holy Synod, regarding the 2018 E.C. Nativity of Our Lord and Savior Jesus Christ, addressed to his spiritual children within the Gedeo, Kore, and Burji Diocese, across the nation, and in various parts of the world. ​Ichthus: Tahsas 28, 2018 E.C.

A message transmitted by Hisgrace Abune Gerima Bishop Read More »

Eebbisemeek Abune Geriima Gede’o Koorenna Burjixxe Hagere Sibkete Phaaphaasichchi Qullitte Sinoodeesexxi una 2018 G.W Goottanna Qorsa Iyyesuusi Kiristoosika ilenshatika ayyaana uuddaaxxin Qullichchi manfasixxe ila insa’nexxee Gede’uffat Laagadinni Sa’issineexxa erga.

Ekituus Arfaasa 28/2018 G.W

Eebbisemeek Abune Geriima Gede’o Koorenna Burjixxe Hagere Sibkete Phaaphaasichchi Qullitte Sinoodeesexxi una 2018 G.W Goottanna Qorsa Iyyesuusi Kiristoosika ilenshatika ayyaana uuddaaxxin Qullichchi manfasixxe ila insa’nexxee Gede’uffat Laagadinni Sa’issineexxa erga. Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የ2018 ዓ.ም የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በተመለከተ በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት፣ በሀገር ውስጥና በተለያዩ ክፍላተ ዓለም ለሚገኙ ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ያስተላለፉት መልእክት።

ኤክቱስ ታኅሣሥ 28/2018 ዓ.ም

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የ2018 ዓ.ም የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በተመለከተ በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት፣ በሀገር ውስጥና በተለያዩ ክፍላተ ዓለም ለሚገኙ ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ያስተላለፉት መልእክት። Read More »

“የሚመለከታቸው አካላት የዜጎችን ደኅንነት እንዲያስጠብቁ እና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ሊሠሩ እንደሚገባ በአጽንዖት እናሳስባለን”ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በደረሰው ጥቃት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለጹ። የብፁዕነታቸው ሙሉ መልእክት እንደሚከተለው ነው። “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ነገር ግን አይዟችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ”ዮሐ 16፥33 በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ላይ በደረሰው አሳዛኝ ጥቃት ሕይወታቸውን ባጡ እና በተጎዱ ወገኖቻችን ከልባችን አዝነናል። በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተደጋገመው በዚህ ድርጊት ቤተ ክርስቲያናችንን ከልብ የሚያሳዝን እና የሀገራችንን ዘላቂ ሰላም ጥያቄ ውስጥ የሚከት በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት የዜጎችን ደኅንነት እንዲያስጠብቁ እና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ሊሰሩ እንደሚገባ በአጽንዖት ለማሳሰብ እንወዳለን።መአቱን በምሕረቱ ቁጣውን በትግዕስቱ ይመልስልን ዘንድ ሁልጊዜም ምላሽ ወደሚሰጠን አምላክ በጸሎት መጠየቅ ይገባናል። የልጆቻችንን ነፍስ ከቅዱሳን ማኅበር እንዲደምርልን፣ ያዘኑ የተከዙ ወገኖቻችንን ከሀዘናቸው እንዲያጽናናልን ጸሎታችን ነው። እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ!አባ ገሪማየጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስየቅዱስ ሲኖዶስ አባል

“የሚመለከታቸው አካላት የዜጎችን ደኅንነት እንዲያስጠብቁ እና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ሊሠሩ እንደሚገባ በአጽንዖት እናሳስባለን”ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኘው የአረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለጹ!!

“ይቤዙ እግዚአብሔር ነፍሰ አግብርቲሁ ወኢይኔስሑ ኩሎሙ እለ ይትዌከሉ ቦቱ – የባርያዎቹን ነፍስ እግዚአብሔር ይቤዣል በርሱም የሚያምኑ ሁሉ አይጸጸቱም”መዝ 33፥22 በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ሥር በሚገኘው አረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም በሕንጻ ግንባታ ምክንያት ለፊኒሽንግ ሥራ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ እስካሁን በሚያሳዝን ሁኔታ በውል ያልታወቁ ወገኖቻችን ሕይወታቸው ማለፉን ከሀገረ ስብከቱ ሚዲያ ስንሰማ እጅግ ከልባችን አዝነናል። ለሞቱት ወገኖቻችን እግዚአብሔር አምላካችን ሀገረ ሕይወትን መንግስተ ሰማያትን እንዲያወርስልን ከቅዱሳን ማኅበር እንዲደምርልን፤ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንዲልክን ጸሎታችን ነው። እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ! አባ ገሪማየጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባልመስከረም 21/2018 ዓ.ም

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኘው የአረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለጹ!! Read More »

ቃለ በረከት ዘብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ዘተናገሮ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወሰመንቱ ዓመተ ምሕረት

ቃለ በረከት ዘብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ዘተናገሮ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወሰመንቱ ዓመተ ምሕረት

ኤክቱስ ጳጉሜን 5/2017 ዓ.ም

ቃለ በረከት ዘብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ዘተናገሮ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወሰመንቱ ዓመተ ምሕረት Read More »

የአባ ገሪማ መልዕክት  

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን! በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት፤ በሀገር ውስጥና በመላው ክፍላተ ዓለም የምትገኙ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምዕመናን ወምዕመናት በቸርነቱ እና በረድዔቱ ብዛት በዕድሜያችን ላይ ይህችን ዓመት ጨምሮ ለ2017 ዓ.ም ለጾመ ማርያም እንኳን በሰላም አደረሳችሁ! ጾመ ፍልሰታ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከ፯ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ ነው። ቅዱሳን ሐዋርያት ከእመቤታችን መለየታቸው እጅግ አሳዝኗቸው በነበረበት ጊዜ የጾሙት ጾም ነው። በጾማቸው እመቤታችንን አግኝተውበታል። ውድ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ጾመ ፍልሰታ ሕጻኑም አረጋዊውም ጠንካራውም ደካማውም ወንዱም ሴቱም ሁሉም የሚጾሙት ጾም እንደሆነና ከሌላው ጊዜ በተለየ የሱባኤ ወቅት መሆኑ ይታወቃል። ይኸውም ምዕመናን በጾሙ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድዔት በረከት እንደሚገኝበት እመቤታችን የልባችንን መሻት እንድትፈጽምልን የምንማጸንበት ወቅት መሆኑን በመረዳት ነው። “ጾም ቅድስት ትሜህሮሙ ለወራዙት ጽሙና ዛቲ ጾም ቅድስት ወበይእቲ ጾም ተመጠወ ሙሴ ሕገ እግዚአብሔር ጾም ቅድስት ወበይእቲ ጾም ኤልያስ ዓርገ ውስተ ሰማያት ጾም ቅድስት ወበይእቲ ጾም ዳንኤል ድኅነ እምአፈ አናብስት ጾም ቅድስት ሶስና ድኅነት እምዕደ ረበናት ጾም ቅድስት ዓቀመ ኢያሱ ፀሐየ በገባዖን ጾም ቅድስት ጳውሉስኒ ይቤ ትግሁ እንከ አኃውየ በጾም ወበጸሎት ዛቲ ጾም ቅድስት ወበይእቲ ጾም ጾም ቅድስት ትሚህሮሙ ለወራዙት ጽሙና። ቅድስት ጾም ለወጣቶች እርጋታ ዝምታን ታስተምራቸዋለች፡፡ ጾም የተለየችና የተቀደሰች ናት በዚህች የተቀደሰችዋ ጾም ሙሴ የአምላኩን ሕግ ተቀበለባት፤ ጾም የተለየችና የተቀደሰች ናት:  በዚህች ቅድስት ጾም ኤልያስ ወደ ሰማይ ዐረገባት በዚህች ቅድስት ጾም ዳንኤል ከአንበሶች አፍ ዳነባት፣ ጾም የተለየችና የተቀደሰች ናት:: በዚህች ቅድስት ጾም ሶስና ከመምህራኑ ክስ ተርፋለች፣ በዚህች ቅድስት ጾም ኢያሱ በገባዖን ፀሐይን አቆመ ። ጾም የተለየችና የተቀደሰች ናት! ጳውሎስ እንዲህ አለ “እንግዲህ ወንደረሞቼ በጾምና በጸሎት ትጉ”፣ ጾም የተለየችና የተቀደሰች ናት። በዚህች በተቀደሰችዋ ጾም … ቅድስት ጾም ለወጣቶች እርጋታ ዝምታን ታስተምራቸዋለች” እንዳለ ቅዱስ ያሬድ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ፍትሐ ነገስት በአንቀጽ 15፣598 ላይ “ወአኮ ጾም እምኀብስት ወማይ አላ ጾምሰ ዘውኩፍ ቅድመ እግዚአብሔር ንጽሐ ልብ – ጾም ከእህል ከውሃ መከልከል ብቻ አይደለም እግዚአብሔር የሚቀበለው ጾም የልብ ንጸሕና ናት” እንደሚለን እኛም ይህንን ጾም ጾመን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድዔት በረከት ለማግኘት የልብ ንጽህናን ገንዘብ ማድረግ ዋናው ቅድመ ሁኔታ ነው። በዚህ ጾም በቤተ ክርስቲያናችን በተለየ መልኩ ሶርያዊ ለብሐዊ የተባለ ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰው የእመቤታችን ውዳሴዋ (ውዳሴ ማርያም) እንዲሁም የብሕንሳው ኤጴስ ቆፅስ አባ ሕርያቆስ የደረሰው የእመቤታችን ቅዳሴ (ቅዳሴ ማርያም) ይተረጎማል። በዚህ ጊዜ እንዲሁም በሌሎቹም በቤተ ክርስቲያን በሚሰጡ መንፈሳዊ አገልግሉቶች በሰዓታት፤ በኪዳን፤ በቅዳሴ፤- በሚሰጠው  የስብከተ- ወንጌል አገልግሎት ላይ እየተገኘን አገልግሎቱን እየተሳተፍን ቸሩ አምላካችን ለሀገራችን ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ ፍጹም ሰላምን እንዲሰጣት እና ከእመቤታችን በረከት ረድዔት እንዲያሳትፈን ልንጸልይ ይገባል እያልን አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን። በመጨረሻም በቅድስና በንጽሕና በተሰበረ ልብ ሆነን ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት፤ የልቡናችን መልካም መሻት የሚፈጸምበት፤ ኃይለ አጋንንት ወድቆልን ኃይለ መንፈስ ቅዱስ የሚቀርብን የበረከት ጾም ያድርግልን። ጾሙን የሰላም የፍቅር የበረከት ጾም አምሳካችን ልዑል እግዚአብሔር ያድርግልን። እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክልን!!! አባ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ

የአባ ገሪማ መልዕክት   Read More »

የአባ ገሪማ መልዕክት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሃገረ ስብከት ለምትገኙየመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ! እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ። የሰው ልጅ በኀጢአተኛዎች እጅ ዐልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው። (ሉቃ 24፡6-7) የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውሃ ፈሳሽ ሳይሆንአስቀድሞ በነቢያት የተነገረ በተለይም በዳዊት “እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ” (መዝ 77፡68) ተብሎ እንደሚነሣ በእርግጠኛነት የተነገረለት፤ በሆሴዕ ከሲኦል እጅ እታደጋቸዋለሁ ሞት ሆይቸነፈርህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ ማጥፋትህ ወዴት አለ? (ሆሴ 13፡14) ተብሎ ለአምስት ሺህ አምስትመቶ ዘመን እንደ መዥገር በሰው ልጅ ተጣብቆ የኖረውን የሞት ኃይል አድቅቆ በታላቅ ኃይልና ሥልጣንእንደሚነሣ ያለጥርጥር የተነገረና እውነት የሆነ ትንቢት ነበር። ዮናስ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በከርሰአንበሪ ማደሩ (ት ዮናስ 2፡1) ክርስቶስ በመቃብር ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት አድሮ በኃይልእንደሚነሣ በምሳሌ የተነገረና በሙሉ ተስፋ ሲጠበቅ የኖረ ትንሣኤ ነው። ትንቢቱን አውቆ ያናገረምሳሌውንም እንዲሁ አውቆ ያስመሰለ ጌታ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር በምድር ላይ ዞሮ ባስተማረበትወቅት ከመሞቱ አስቀድሞ ገና በገሊላ ሳለ “የሰው ልጅ በኀጢአተኛዎች እጅ ዐልፎ ሊሰጥና ሊሰቀልበሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው” (ሉቃ 24፡67፤ ማቴ. 12፡40) ተብሎ የተነገረው ትንቢትናየተመሰለው ምሣሌ እሙን ሊሆን መቅረቡን በአንደበቱ አበክሮ ለደቀ መዛሙርቱ ሲያሳስባቸውናሲያስታውሳቸው የነበረ የድል አድራጊነት ትንሣኤ ነው። በመሆኑም ዕለቲቱና ሰዐቲቱ በደረሰች ጊዜ በጥቂት ጥቅመኛ ነገረ ሰሪዎች ከውጭ በነ ሃናና ቀያፍ ከውስጥደግሞ በነ ይሁዳ አማካኝነት ለሞት ተላልፎ ተሰጠ። በዕለተ ሆሣዕና “ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት” ሲልየነበረው ሕዝብ ይሰቀል ይሰቀል እያለ እንዲጮኽ የሀሰት ወሬ በከተማው ሁሉ ተነዛ። ጲላጦስም ምንምየሰራው ወንጀል እንደሌለ እያወቀ ከሥልጣኑ እንዳይሻር በመስጋት የሕዝቡን ጩኸት ፈርቶ እንዲሞትፈረደበት። በአይሁድ ዘንድ እንደወንጀለኛ መቆጠሩና በነሱ እጅ መሞቱ ግን በነቢዩ በኢሳይያስ “ስለመተላለፋችን ቈሰለ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በርሱ ላይ ነበረ በርሱ ቊስል እኛተፈወስን” (ኢሳ 53፡5) ተብሎ የተጻፈው ይፈጸም ዘንድ ነው። ዓርብ በዘጠኝ ሰዐት ራሱን ዘንበል አድርጎነፍሱን በገዛ ፈቃዱ ሰጠ። ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። የሃናና ቀያፋ ሴራ ግን በመግደል ብቻ አላበቃም ትንሣኤውን ለመከልከል ካልሆነም እነሣለሁ ብሎየተናገረው እውነት ሆኖ ከተነሣ እኛ ተኝተን ሣለን ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሰርቀው ወሰዱ የሚለውንየተለመደ የሽብርና የሀሰት ወሬ ለመንዛት እንዲመቻችው መቃብሩን በወታደር አስጠበቁ። የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ! የኛ ጌታ ግን ሀሰተኞችንና የሀሰት አባቷ የሆነውን ዲያብሎስን ለማሳፈር፣ የሞትን ኃይል ባዶ ለማድረግናነቢያት ስለ ትንሣኤው አስረግጠው የተናገሩትንና እርሱም እንደሚነሣ ከሞቱ አስቀድሞ ስለራሱየተናገረው የትንሣኤውን እውነት ለዓለም ሁሉ ይገልጽ ዘንድ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይልበታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን መካከል ተለይቶ በክብር ተነሣ። መቃብሩም ባዶ ሆነ። እንኳን ደስአላችሁ። እንኳን ደስ አለን። ምንም እንኳን የመቃብሩ ጠባቂዎች ጥቂት መደለያ (እጅ መንሻ ተቀብለው ደቀ መዛሙርቱ ሰርቀውወሰዱት ብለው እንዲያወሩ ተደርገው ወሬው ከተማውን ሁሉ ቢያጥለቀልቀውም በኩረ ትንሣኤ ከርስቶስግን ከተነሣ በኋላ ትንሣኤው እሙን መሆኑን ለነ ማርያም መግደላዊት በመታየት፣ ለሐዋርያት በተለያየጊዜ ለኬፋም ለዐሥራ ሁለቱም፣ ከዐምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች ባንድ ጊዜ በመታየት የአይሁድንሴራ መና እንዳስቀረ ሐዋርያው ጳውሎስ በስፋት ጽፎልናል። (ቆሮ 15፡58)። በተዘጋ ቤት ገብቶ ሰላምለናንተ ይሁን ብሎ ሰላምን ሰብኮላቸዋል። ምትሀት አለመሆኑን ለመግለጽ የተቸነከረበትን እጁን እግሩን፣በጦር የተወጋውን ጎኑን አሣይቷቸዋል። በመቃብሩ ቦታ የተገኙ መላእከትም ሕያውን ከሙታን መካከልስለ ምን ትፈልጋላችሁ ተነሥቷል እንጂ በዚህ የለም (ሉቃ 24፡5) ሲሉ የትንሣኤውን ኃይል ገልጸዋል።የትንሣኤው ችቦ በሐዋርያት እየተቀጣጠለ ለዓለም ሁሉ በማብራቱ የአይሁድ ሀሰት ተጋለጠ። የክርስቶስትንሣኤ ለኛ ትንሣኤም በኩር በመሆኑ እስከምጻት ሲነገርና ሲታመን ይኖራል። እኛም ዛሬ የሐዋርያትንጆሮ ጆሮ አድርገን ዐይኖቻቸውንም ዐይኖቻችን አድርገን ትንሣኤውን በደስታ እያከበርን እንገኛለን። በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ። ውድ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ ይህ በዓል መንፈሳዊ በዓል እንደመሆኑ ከአልባሌ ነግር ርቀን አብዝቶ ከመብላትና ከመጠጣት ተቆጥበንምንም የሌላችውን፣ አባት እናት የሞቱባቸውን፣ በተለያዩ ደዌ ተይዘው በየሆስፒታሉ፣ በየጸበል ቦታውናበየቤታቸው ሆነው በዓሉን እንደኛ ማክበር የተሳናቸውን፣ በሕግ ጥላ ሥር ሆነው በማረሚያ ቤት ያሉትንበመጎብኘትና ካለን ላይ ከፍለን በማብላት ልናከብረው ይገባል፡፡ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም። አባ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ

የአባ ገሪማ መልዕክት Read More »

Scroll to Top