በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ቀዳሚ ገጽ ዜና

ሦስተኛው ዙር ወርሃዊ የወንጌል ጉባኤ በዲላ ደ/ገ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተደረገ!!

ሦስተኛው ዙር ወርሃዊ የወንጌል ጉባኤ በዲላ ደ/ገ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተደረገ!! ለጥምቀት በዓል መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጡ ጥምቀትን በዲላ በሚል መጠሪያ ስም የተመሠረቱ የወጣቶች መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኀበር በብፁዕ አባታችን አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መልካም ፈቃድ በወር መጨረሻ እሁድ የሚደረገው የወንጌል አገልግሎት የሦስተኛ ወሩን አገልግሎት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተካሄደ። በዕለቱ ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመጽሐፍ መምህር ትምህርተ ወንጌል የሰጡ ሲሆን የሀገረ ስብከቱ የትምህርትና የካህናት አስተዳደር ክፍል ኃላፊ የሆኑት መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ጉባኤው በሚቀጥለው ወር በመጨረሻ እሁድ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በስልክ በዚያ ለተሰበሰቡ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው በአገልግሎት ምክንያት በመርሃግብሩ መገኘት እንዳልቻሉ ገልጸው ቃለ ምህዳን እና ቡራኬ ሰጥተው መርሃግብሩ በጸሎት ተፈጽሟል።

ሦስተኛው ዙር ወርሃዊ የወንጌል ጉባኤ በዲላ ደ/ገ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተደረገ!! Read More »

ለብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ የትንሣኤን በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር ተከናወነ!!

ለብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ የትንሣኤን በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር ተከናወነ!! ለብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣኤ በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረስዎ መርሐግብር ተናውኗል። በዕለቱ የሃገረ ስብከቱ የሥራ ሃላፊዎች፣ የመንበረ ጵጵስና እና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና ጸሐፊ፣ የአድባራቱ አስተዳዳሪዎች፣ የካህናት ተወካዮች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና የምዕመናን ተወካዮች በተገኙበት ተከናውኗል። በዕለቱ መርሐ ግብሩ በሀገረ ስብከቱ ጳጳስ የተመራ ጸሎተ ወንጌል የተጀመረ ሲሆን የአድባራቱ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ዝማሬ ካቀረቡ በኋላ ያሬዳዊ ዝማሬ ከአድባራቱ በተውጣጡ ሊቃውንት ቀርቧል። በመቀጠልም ከጪጩ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንና እና የበዓታ ዳግማዊት ጌቴሴማኒ ቤተክርስቲያን የመጽሐፈ ሐዲሳት መምህራን ቅኔ የቀረበ ሲሆን ከመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች ሃሳብና አስተያየት ተሰጥቷል። በመጨረሻም የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ቃለ ምህዳንና ቡራኬ ሰጥተው መርሐግብሩ በጸሎት ተፈጽሟል።

ለብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ የትንሣኤን በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር ተከናወነ!! Read More »

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜዎች

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜዎች ከትንሣኤ ሌሊት ፩ ሰዓት ጀምሮ እስከ ዳግም ትንሣኤ ያለው ሳምንት የፉሲካ ምሥጢር የተገለጠበት፤ ከግብፅ ወደ ምድረርስት ከሲኦል ወደ ገነት መሻገርን የሚያመላክት ሳምንት ነው። ለፉሲካ የሚታረደውም በግ ፉሲካ ይባላል (ዘዳ. ፲፮÷፪:፭÷፮)፤ ፉሲካ ማለት ደግሞ ማለፍ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትም ሳምንት የፉሲካ ሳምንት ነበር፤ (ሉቃ. ፳፪፥፲፬-፲፮፤ ዮሐ. ፲፰፥፴፰-፵)። እርሱም ንጹሕ የእግዚአብሔር በግ ሆኖ ደሙን ስላፈሰሰልን ፉሲካችን ክርስቶስ ተባለ፤ ብሉይ ደግሞ የሐዲስ አምሳል ነው። ይኸውም ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ ባሕረ ኤርትራን ካሻገራቸው በኋላ ወደ ምድረ ርስት፤ ነፍሳት ደግሞ በክርስቶስ መሪነት ከሲኦል ወደ ገነት መግባታቸውን የሚገልጽ ነው፡፡ ዕለቱም ሙሴ የወልደ እግዚአብሔር፤ በትረ ሙሴ የመስቀል ምሳሌ፤ግብፅ የሲኦል፤ የገሃነመ እሳት፤ የፈርዖን የዲያብሎስ፤ ሠራዊቱ የሠራዊተ ዲያብሎስ፤ እስራኤል የምእመናንና ባሕረ ኤርትራ የባሕረ ሲኦል ምሳሌ ነው፡፡ ሰኞ– ማዕዶት (ፀአተ ሲኦል) ማዕዶት የቃሉ ትርጓሜ መሻገር ሲሆን፤ በዚህ ቀን ቤተ ክርስቲያን ነፍሳት በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ከሞት ወደ ሕይወት፤ ከሐሳር ወደ ክብር፤ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሲኦል ወደ ገነት መሻገራቸውንና ፉሲካችን ክርስቶስ መሆኑን ታስባለች። ማክሰኞ– ቶማስ ቅዱስ ቶማስ በጦር የተወጋ ጎኑን፤ በቀኖት የተቸነከረው እጁንና እግሩን ካላየሁ አላምንም በማለቱ ክርስቶስም «ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤እጅህንም አምጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን» ብሎታል። ቶማስም «ጌታዬ አምላኬም»፤ ብሎ በመለሰ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስም «ስለ አየኸኝ አመንህን? ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓንስ ናቸው» አለው (ዮሐ ፳፥፳፯-፳፱)፤ ቶማስ የጌታን ፍቅር ተገንዝቦ ትንሣኤውን ስላመነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዕለቱን ቶማስ ብላ ታስበዋለች። ዲዲሞስ የተባለ ከአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙር አንዱ ቶማስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዝግ ቤት ገብቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ባላቸው ጊዜ ከእርሳቸው ጋራ አልነበረም»። ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ (ማቴ. ፲፥፪-፫) ቶማስ በአራማይክ ዲዲሞስ በግሪክ መንታ ማለት ነው፤ (ዮሐ. ፳፥፳፬)፡፡ ቶማስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በፋርስና በሕንድ ወንጌልን እንዳስተማረ ይነገራል። ለቶማስ ጎኑን እንዲዳስስ የፈቀደው ለሌሎችም ቅዱሳን ሐዋርያት የተቸነከረውን እጅና እግሩን ያሳየው ካህናት ሥጋውና ደሙን እንዲፈትቱ ነው፤ ዮሐንስም በእጃችን ዳሰስነው ብሏል፤ (ሉቃ. ፳፬፥፴፱)፡፡ ለማርያም መግደላዊት ግን የተነሣ ዕለት አትንኪኝ ማለቱ ለሴቶች ሥጋውን ደሙን መፈተት አልተፈቀደም ሲል ነው ብለው ሊቃውንት ያትታሉ፤ «አትንኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሂጅና፡- ወደ አባቴ÷ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ÷ ወደ አምላካችሁም አርጋለሁ አለ ብለሽ ንገሪአቸው» አላት፤ (ዮሐ. ፳፥፲፯)። ገቦ መለኮቱን የዳሰሰች እጁ በሕይወት ትኖራለች፤ በሕንድ ሀገር ከታቦት ጋር በመንበር ላይ ትኖራለች። በየዓመቱ በእመቤታችን በዓል በአስተርእዮ ሊያጥኑ ሲገቡ የሚሾመውን ወጥታ ቀኝ እጁን ትይዘዋለች፤ ዓመት አገልግሎ ያርፋል። ረቡዕ –አልዓዛር አልዓዛር ክርስቶስ ያስነሣው የማርያምና የማርታ ወንድም ነው፤ የስሙም ትርጓሜ እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው፤ (ዮሐ. ፲፩፥፯-፵፰)፤ አልዓዛር የሞተው መጋቢት ፲፯ ነበር፡፡ እህቶቹም ክርስቶስ እንዲመጣ መልእክት ልከውበት ነበር፤ ክርስቶስ ግን በ፬ኛው ቀን ማለትም መጋቢት ፳ መጥቶ ከሞት አስነሥቶታል፤(ዮሐ.፲፩፥፵፬)፡፡ ፋሲካውንም በወዳጁ በአልዓዛር ቤት ያከብር ዘንድ ከቀደ መዛሙርቱ ጴጥሮስንና ዮሐንስን አስቀድሞ ላከ፤ ከዚያም በአልዓዛር ቤት ሆኖ የሐዲስ ኪዳንን ሥርዓት ምሥጢረ ቁርባንን ሰርቶ ለደቀ መዛሙርቱ አሳያቸው፤ አልዓዛር ከተነሣ በኋላ በሐዋርያት ኤጲስ ቆጶስነት ተሸሞ ፵ ዓመት አገልግሎ ግንቦት ፳፯ ቀን ዐርፏል (ስንክሳር ግንቦት ፳፯)፡፡ አዳም ሐሙስ አዳም የመጀመሪያ ሰውና የሰው ሁሉ አባት ነው፤ በ፮ኛው ቀን የተፈጠረ የሰው ሁሉ ምንጭ ስለሆነ የሰው ዘር ሁሉ ከእርሱ ተገኝቷል፡፡ በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው የተስፋ ቃል ስለመፈጸሙ፤ (ዘፍ. ፫÷፲፭) አዳም ከነልጆቹ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻ ስለመውጣቱ ይታሰብበታል፡፡ ክርስቶስ በተነሳበት በአምስተኛው ቀን ሐሙስ አዳም ይባላል፤ ጌታችን አዳምን ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ብሎ ቃል ገብቶለት እንደነበር በቀሌምንጦስ ተጽፏል፡፡ አዳምና ሔዋን በገነት ፯ ዓመት ከቆዩ በኋላ ትእዛዙን በመተላለፋቸው ከኤደን ገነት አስወጣቸው (ኩፋ.፬፥፲፮፤ዘፍ.፫፥፳፫) «ብዙ ተባዙ» ያለው ቃል እንዳይቀር በምድር ላይ ወርደው ልጆችን ወለዱ ይላል፡፡ የተወለዱትም ልጆችም በቁጥር ፷ እንደሆኑ (፩መቃ. ፳፰፥፮) የተወለዱት ልጆች ደጎችና ክፉዎች እንደ ነበሩ በአቤልና በቃየል ታውቋል፤ (ዘፍ. ፬፥፰)፤ አዳም በዚህ ዓለም ፱፻፴ ዓመት ኑሮ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ፵፻፭፻፸ ሚያዚያ ፮ ዐርፏል፡፡ ዐርብ– ቤተ ክርስቲያን ዐርብ የእግዚአብሔር ቅድስት ማደሪያ በሆነችው ቤተ ክርስቲያን ተሰይማለች፤ ይህም ሁሉም ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመባት ዕለት በመሆኗ ነው፤ ዕለተ ዐርብ፤ የሥራ መከተቻ፤ ምዕራብና መግቢያ በሚሉት ስያሜዎችም ትጠራለች፡፡ በዕለቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ያደረገውን ተአምር በመስቀሉ ድኅነትን እንዳሳየ፤ በቀራንዮ የሕንጻዋ መሠረት እንደተተከለላትና ሥጋ መለኮት እንደተቆረሰላት፤ ልጆቿን ከማሕፀነ ዮርዳኖስና ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ የምትወልድበት ማየ ገቦ እንደፈሰሰላት ተገልጾባታል፤(ኤፍ.፪፥፲፱፤ራዕ.፩፥፮-፰)፡፡ ቅዳሜ– ቅዱሳት አንስት ቅዳሜ ቅዱሳት አንስት ተብሎ ይጠራል፤ ይህም ስያሜ በስቅለት ዕለት በልቅሶና በዋይታ የሸኙትን፤(ሉቃ. ፳፫፥፳፯) በዕለተ ትንሣኤ ሽቱና አበባ ይዘው ወደ መቃብር የገሰገሱትን፤ ከሁሉም ቀድሞ ጌታችን በዕለተ ሰንበት ተነሥቶ ለተገለጸላቸው ማርያም መግደላዊት፤ የታናሹ ያዕቆብ እና የዮሳ እናት ማርያም፤ የዘብዴዎስም የልጆቹ እናት ሰሎሜንም መታሰቢያ ለማድረግ ነው፤«ከሳንምንቱ በመጀመሪያዩቱ ቀን ያዘጋጁትን ሽቶ ይዘው እጅግ ማልደው ወደ መቃብሩ ሄዱ፤ሌሎች ሴቶችም አብረዋቸው ነበሩ (ሉቃ. ፳፬ ፥ ፩ )፡፡ እሑድ– ዳግም ትንሣኤ «ያም ከሳምንቱ የመጀመሪያው ቀን በመሸ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን ስለ ፈሩ ተሰብስበው የነበሩት ቤት ደጁ ተቆልፎ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ መጥቶ በመካከላቸው ቆመና÷«ሰላም ለእናንተ ይሁን» አላቸው፤ ማቴ.፳፥፲፱፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ተሰውሮ ከሰነበተ በኋላ በዕለተ እሑድ በዝግ ቤት እንዳሉ ዳግም ተገለጸላቸው፤ስለዚህም ዳግም ትንሣኤ ተባለ፡፡ (ምንጭ:-መዝሙረ ማኅሌት ወቅዳሴ፤ ሥርዓተ አምልኮ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፤ የዮሐንስ ወንጌል አንድምታ፤ ምዕ. ፳፥፳፬)

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜዎች Read More »

ከአራቱ ወረዳ ለተውጣጡ ከቋንቋ ሰባኪያነ ወንጌል ጋር ውይይት ተደረገ!!

ከአራቱ ወረዳ ለተውጣጡ ከቋንቋ ሰባኪያነ ወንጌል ጋር ውይይት ተደረገ!! በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ከአራት ወረዳ ቤተክህነት ማለትም ከመንበረ ጵጵስናና ወናጎ፣ ከይርጋጨፌ፣ከኮቸሬና ገደብ ፣ከቡሌና ረጴ ወረዳዎች ከተውጣጡ በጌዴኡፋ ቋንቋ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ከሚሰጡ ሰባኪያነ ወንጌል ጋር ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ጋር ውይይት ተደረገ። ውይይቱ ከቤተክርስቲያን ካህናት ማሰልጠኛ ተመርቀው ወጥተው ምን አከናወኑ፣የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሲሰጡ የገጠማቸው ተግዳድሮት ነበረ፣ለገጠማቸው ችግር የወሰዱት የመፍትሔ ሃሳብ ምን ነበር፣በአገልግሎት የተገኘው ውጤት ምን ነበር፣ያሉትን ለማጽናት የጠፉትን ለመመለስ አዳዲስ ኢአማንያንን ለማምጣት ምን አከናወኑ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን። ሰባኪያነ ወንጌሉ በአገልግሎት ላይ የገጠማቸውን ችግር ያነሱ ሲሆን መስዋዕትነት እስኪከፍሉ ድረስ ዋጋ መክፈላቸው ሰንበት ት/ቤት ማደራጀት ባዕድ አምልኮ ማጥፋት ብዙ ኢአማኒያን ማስጠመቅ ኮርስ መስጠት በማኀበራዊ ሕይወት መሳተፍ በሀዘንና በደስታ ስብከተ ወንጌል መስጠት የሚሉ የአገልግሎት ተግባራትን የዘረዘሩ ሲሆን። በቀጣይ ከተከናወነው ያልተሰራው ስለሚበዛ በቁጭት በቋንቋ ለማስተማር ቃል ገብተዋል። የሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሀብታሙ አበበ በሰጡት አስተያየት ለተጠራንበት አገልግሎት ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባ ከጠባቂነት መውጣትና በዕቅድና በዓላማ ማገልገል አገልግሎታቸው ሁሉ በውጤት የታጀበ መሆን እንዳለት በተለይ ያሉትን በማጽናትና መጠበቅ የጠፉትን ማምጣት አዳዲስ አማኒያንን ወደ ክርስትና በማምጣት ላይ አገልግሎታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አንስተዋል። በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በማጠቃለያው የስብከተ ወንጌል በሚገባ አገልግሎት አልተፈጸም የቤተክርስቲያንን ተልዕኮ በአግባቡ አውቆ ያለመፈጸም ሰባኪ ከጠባቂነት መውጣት ለዚህ አገልግሎት የተጠራን ባለዕዳዎች መሆንናችንን አንስተው የማሳመኑን የማስተማሩን ሥራ በአግባቡ መወጣት አለብን ብለዋል። በየመንደሩ የስብከተ ወንጌል ኬላ ማቋቋምና አገልግሎትን መፈጸም በማኀበራዊ ሁነቶች ላይ መሳተፍ በቁርጠኝነት ወንጌልን ማገልገል እንደሚያስፈልግ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት መክፈል እንደሚገባ አሳስበው በቀጣይ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ፕሮጀክት የተወጋጀና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሥምሪት እንደሚሰጥ በማሳሰብ ውይይቱ ተጠናቋል ።

ከአራቱ ወረዳ ለተውጣጡ ከቋንቋ ሰባኪያነ ወንጌል ጋር ውይይት ተደረገ!! Read More »

በመምህር ያሬድ አደመ እና በወዳጆቹ ለዳኖ ቡልቶ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የንዋየ ቅድሳት ድጋፍ ተደረገ!!

በመምህር ያሬድ አደመ እና በወዳጆቹ ለዳኖ ቡልቶ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የንዋየ ቅድሳት ድጋፍ ተደረገ!! በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በኮሬ ወረዳ ቤተክህነት ሥር ለሚገኘው ለዳኖ ቡልቶ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በመምህር ያሬድ እና በወዳጆቹ ለአንድ ሰሞነኛ የሚሆን ሙሉ መቀደሻ አልባሳ፣ የተለያዩ መጽሐፍትና መጽሐፈ ድጓ ሳይቀር ለአብነት ተማሪዎች ጫማ የተደረገውን ድጋፍ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የተረከቡ ሲሆን ድጋፉን ያደረጉትን ሁሉ አመስግነው ድጋፉ ቅድስት ቤተክርስቲያን አገልግሎቷን በተሟላ መልኩ እንድትሰጥ የሚያደርግ በመሆኑ ለሌላው አርአያ መሆኑም ተገልጿል ።

በመምህር ያሬድ አደመ እና በወዳጆቹ ለዳኖ ቡልቶ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የንዋየ ቅድሳት ድጋፍ ተደረገ!! Read More »

ከአራቱ ወረዳ ለተውጣጡ ከቋንቋ ሰባኪያነ ወንጌል ጋር ውይይት ተደረገ!!

ከአራቱ ወረዳ ለተውጣጡ ከቋንቋ ሰባኪያነ ወንጌል ጋር ውይይት ተደረገ!! በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ከአራት ወረዳ ቤተክህነት ማለትም ከመንበረ ጵጵስናና ወናጎ፣ ከይርጋጨፌ፣ከኮቸሬና ገደብ ፣ከቡሌና ረጴ ወረዳዎች ከተውጣጡ በጌዴኡፋ ቋንቋ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ከሚሰጡ ሰባኪያነ ወንጌል ጋር ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ጋር ውይይት ተደረገ። ውይይቱ ከቤተክርስቲያን ካህናት ማሰልጠኛ ተመርቀው ወጥተው ምን አከናወኑ፣የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሲሰጡ የገጠማቸው ተግዳድሮት ነበረ፣ለገጠማቸው ችግር የወሰዱት የመፍትሔ ሃሳብ ምን ነበር፣በአገልግሎት የተገኘው ውጤት ምን ነበር፣ያሉትን ለማጽናት የጠፉትን ለመመለስ አዳዲስ ኢአማንያንን ለማምጣት ምን አከናወኑ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን። ሰባኪያነ ወንጌሉ በአገልግሎት ላይ የገጠማቸውን ችግር ያነሱ ሲሆን መስዋዕትነት እስኪከፍሉ ድረስ ዋጋ መክፈላቸው ሰንበት ት/ቤት ማደራጀት ባዕድ አምልኮ ማጥፋት ብዙ ኢአማኒያን ማስጠመቅ ኮርስ መስጠት በማኀበራዊ ሕይወት መሳተፍ በሀዘንና በደስታ ስብከተ ወንጌል መስጠት የሚሉ የአገልግሎት ተግባራትን የዘረዘሩ ሲሆን። በቀጣይ ከተከናወነው ያልተሰራው ስለሚበዛ በቁጭት በቋንቋ ለማስተማር ቃል ገብተዋል። የሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሀብታሙ አበበ በሰጡት አስተያየት ለተጠራንበት አገልግሎት ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባ ከጠባቂነት መውጣትና በዕቅድና በዓላማ ማገልገል አገልግሎታቸው ሁሉ በውጤት የታጀበ መሆን እንዳለት በተለይ ያሉትን በማጽናትና መጠበቅ የጠፉትን ማምጣት አዳዲስ አማኒያንን ወደ ክርስትና በማምጣት ላይ አገልግሎታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አንስተዋል። በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በማጠቃለያው የስብከተ ወንጌል በሚገባ አገልግሎት አልተፈጸም የቤተክርስቲያንን ተልዕኮ በአግባቡ አውቆ ያለመፈጸም ሰባኪ ከጠባቂነት መውጣት ለዚህ አገልግሎት የተጠራን ባለዕዳዎች መሆንናችንን አንስተው የማሳመኑን የማስተማሩን ሥራ በአግባቡ መወጣት አለብን ብለዋል። በየመንደሩ የስብከተ ወንጌል ኬላ ማቋቋምና አገልግሎትን መፈጸም በማኀበራዊ ሁነቶች ላይ መሳተፍ በቁርጠኝነት ወንጌልን ማገልገል እንደሚያስፈልግ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት መክፈል እንደሚገባ አሳስበው በቀጣይ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ፕሮጀክት የተወጋጀና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሥምሪት እንደሚሰጥ በማሳሰብ ውይይቱ ተጠናቋል ።

ከአራቱ ወረዳ ለተውጣጡ ከቋንቋ ሰባኪያነ ወንጌል ጋር ውይይት ተደረገ!! Read More »

በዲላ መዝገበ ምሕረት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው ሁለተኛ ቀን መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ።

በዲላ መዝገበ ምሕረት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው ሁለተኛ ቀን መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ። በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት በመዝገበ ምሕረት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ጽንሰት በማስመልከት የተዘጋጀው መንፈሳዊ ጉባኤ ሁለተኛ ቀን ተጠናቋል። በጉባኤው የሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ሊቀ ትጉሃን ሀብታሙ አበበ፣ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጠበብት መሪጌታ መሰረት ይልማ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ምሕረት ቀሲስ ሰናይ፣ ሰባኪያነ ወንጌል እና ዘማሪያን፣ የደብሩ ካህናትና ዲያቆናት፣ በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል። በጉባኤው የበገና ዝማሬ፣ ትምህርተ ወንጌል በተጋባዥ መምህራን፣ ዝማሬ የተሰጠ ሲሆን ጉባኤው ዛሬም እንደሚቀጥል ተገልጾ የመርሃግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።

በዲላ መዝገበ ምሕረት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው ሁለተኛ ቀን መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ። Read More »

በሐሩ እግዚአብሔር ወልድ ቤተክርስቲያን በዓለ ጽንሰት በመንፈሳዊ ክብር ተከበረ።

በሐሩ እግዚአብሔር ወልድ ቤተክርስቲያን በዓለ ጽንሰት በመንፈሳዊ ክብር ተከበረ። በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተክህነት ሥር የሚገኘው በሐሩ እግዚአብሔር ወልድ ቤተክርስቲያን የጽንሰት በዓል የይርጋጨፌ ወረዳ ቤተክህነት ዋና ፀሐፊ መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ብዙአየሁ ዳመና የደብሩ አስተዳዳሪ ካህናትና የሐሩና የአካባቢው ምዕመናንን በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ክብር ተከበረ። በዕለቱም ይርጋጨፌ ወረዳ ቤተክህነት ዋና ፀሐፊ መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ብዙአየሁ ዳመና ለዕለቱ የሚስማማ የጌታን ዓለምን ለማዳን ከቅድስት ድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ግብር በቅዱስ ገብርኤል ብስራት መጸነሱን ዓለምን ለማዳን የተጠቀመውን የፍቅር ጥበብ በሰፊው በመግለጽ አስተምረዋል። በመጨረሻም ለቤተክርስቲያኑ የልማት ሥራ የገቢ ማስገኛ ሥራ ምዕመናንን በማስተባበር ከተከናወነ በኋላ ጸሎትና ቡራኬ ተሰጥቶ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

በሐሩ እግዚአብሔር ወልድ ቤተክርስቲያን በዓለ ጽንሰት በመንፈሳዊ ክብር ተከበረ። Read More »

ለሁለት ቀን የሚቆይ ሥልጠና ተጀመረ!!

ለሁለት ቀን የሚቆይ ሥልጠና ተጀመረ!! በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ለሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች ከሀገረ ስብከቱ ከሁሉም ወረዳ ቤተክህነት እንዲሁም አድባራት ለተወከሉ ሥራአስኪያጅና አስተዳዳሪዎች ካህናት የአስተዳደር ሠራተኞች ለሁለት ቀን የሚቆይ ሥልጠና በሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ በተገኙበት በዲላ ዋለሜ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን አዳራሽ በጸሎት ተጀመረ። ሥልጠናውን የሚሰጡት የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳት ፕሮፌሰር አባ ኃይለ ገብርኤል ሲሆኑ ሥልጠናውን ሰልጣኞች በቡድን ውይይት እንዲሳተፉና የውይይቱን ውጤት ለተሳታፊ እንዲያቀርቡ በማድረግ በርዕሰ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በመስጠት ነው። #ሥልጠናው በኦርቶዶክሳዊ አገልግሎት ዙሪያ የተሰጠ ሲሆን ልዩ ልዩ አስረጂዎችን ከቡሉይ እና ሀዲስ ኪዳን በማቅረብ የቅዱሳን አባቶችን መጽሐፍት በዋቢነት በማቅረብ አካባቢን በማየት ከሚታወቀው ነገር በመነሳት ግልጽና አሳታፊ በሆነ አቀራረብ ጥልቅ ምሥጢራትን በመግለጽና በማሳየት እየቀረበ ያለ ሥልጠና ነው። ሁሉም ሠልጣኝ በመመልስ ፣በመጠየቅና በንቃት በመከታተል ሥልጠናውን እየተሳተፈ ይገኛል። #የመጀመሪያው ቀን ሥልጠና የተጠናቀቀ ሲሆን ነገም እንደሚቀጥል የወጣው መርሐ ግብር ያመለክታል።

ለሁለት ቀን የሚቆይ ሥልጠና ተጀመረ!! Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጅ ሀገረ ስብከት ጳጳስ በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፍ ተሰማርተው በአዲስ አበባ ከሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ጋር በሀገረ ስብከቱ በሚከናወኑ ዕቅዶች ዙሪያ ውይይት አደረጉ።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ በሀገረ ስብከቱ እየተከናወኑና ወደፊት ሊተገበሩ በታቀዱ ዕቅዶች ዙሪያ በአዲስአበባ ከተማ ከሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ጋር በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የነገረ መለኮት መማሪያ ክፍል የጋራ ውይይትና ምክክር አደረጉ። ለምክክሩ መነሻ የሚሆን ሰነድ የቀረበ ሲሆን በሰነዱ በሀገረ ስብከቱ ታሪካዊ ጉዞ፣ አሁናዊ ሀገረ ስብከቱ ያለበት ነባራዊ እውነታና ተግዳሮት፣ ወደፊት በሀገረ ስብከቱና በምእመናን መሥራት ያለበትን ተግባራት፣ የተሳታፊዎች ድርሻና አስተዋጽኦ ዙሪያ ሰፋ ያለ ሰነድ በፓወር ፖይንት ቀርቧል። ብፁዕነታቸው እስካሁን የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማዕከል ከተማ ተኮር በመሆኑ የተነሳ በገጠር ያለው ብዙ ቁጥር ያለው ምእመናን ካህን፣ መምህርና ሰባኬ ወንጌል ባለመኖሩ በትምህርት እና ጠባቂ በማጣት ወደ ተለያዩ ቤተ እምነት እንዲሄዱ ምክንያት የሆነና ሂደቱም እየቀጠለ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ከተመሠረተ ጥቂት ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን በተለይ በሀገረ ስብከት ደረጃ የ10 ዓመት ስልታዊ ዕቅድ ታቅዶ ወደ ተግባራዊ ሂደት መግባቱ አንዱ ማሳያ በመሆኑ ይህን ሀሳብ ለመላው ማህበረሰብ መድረስ እንዳለበት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል። እንደ ሀገረ ስብከት የቀረበው ጥናቱ ችግሮቹን በሙሉ የለየ ከመሆኑ በተጨማሪ የመፍትሔ ሃሳብ የተቀመጠ በመሆኑ ወደ ሥራ መግባት ያስፈልጋል ብለዋል ። በአዲስአበባ የሚኖሩ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆችም በቀረበው የውይይት ሰነድ መነሻነት ሃሳብ የሰጡ ሲሆን በቀጣይ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት በሃሳብ ፣በገንዘብ ፣በእውቀት እንዲሁም ሌሎችንም በማስተባበር ጭምር እገዛ ለማድረግ ቃል ገብተዋል። ይህ መድረክ ቀጣይነት ያለው ሲሆን ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በገንዘባቸው በእውቀታቸው በሙያቸው ሀገረ ስብከቱን እንዲደግፉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን በመጨረሻም በጉባኤው ማጠቃለያ ሶስት አባላት ያሉት አስተባባሪ ኮሚቴ በማቋቋም በብፁዕነታቸው ጸሎትና ቡራኬ ተጠናቋል።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጅ ሀገረ ስብከት ጳጳስ በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፍ ተሰማርተው በአዲስ አበባ ከሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ጋር በሀገረ ስብከቱ በሚከናወኑ ዕቅዶች ዙሪያ ውይይት አደረጉ። Read More »

Scroll to Top