በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

Public Relation

የመንበረ ጵጵስና ገቢ ማስገኛ ዕጣ ይፋ ሆነ!

ኤክቱስ የካቲት 16/2018 ዓ.ም የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ለሚያስገነባው የመንበረ ጵጵስና ግንባታ ገቢ ማስገኛ ሎተሪ በዛሬው ዕለት በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በይርጋጨፌ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በዐውደ ምሕረት ይፋ ሆኗል። 1ኛ ዕጣ ሞተር ሳይክል ………180252ኛ ዕጣ ፍሪጅ………………….128753ኛ ቴሌቭዥን…………………..120414ኛ ምስለ ፍቁር ወልዳ…………125215ኛ መጽሐፍ ቅዱስ……………0041406ኛ መዝገበ ጸሎት…………006147 ነው። ዕጣው የደረሳችሁ በሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት በአካል በመቅረብ መውሰድ እንደምትችሉ ተገልጿል።

የመንበረ ጵጵስና ገቢ ማስገኛ ዕጣ ይፋ ሆነ! Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ለአምስት ደቀ መዛሙርት ማዕረገ ዲቁና ሰጡ!

ኤክቱስ የካቲት 16/2018 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተ ክህነት በይርጋጨፌ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርታቸው ሲከታተሉ ለቆዩ ለአምስት ደቀ መዛሙርት ማዕረገ ክህነት ሰጥተዋል። በተጨማሪም ለአንድ እናት ሥርዓተ ምንኩስናን ፈጽመዋል። ብፁዕነታቸው ዲያቆናቱ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት ጠብቀው በትጋት ማገልገል እንዳለባቸው አባታዊ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ለአምስት ደቀ መዛሙርት ማዕረገ ዲቁና ሰጡ! Read More »

ወደ ኦቲልቾ የስብከተ ወንጌል ኬላ በሚደረገው የእግር ጉዞ ላይ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ውይይት ተደረገ!

ኤክቱስ የካቲት 15/2018 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መሪነት በዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት ወደ ኦቲልቾ የስብከተ ወንጌል ኬላ በተዘጋጀው የእግር ጉዞ ላይ ተጓዦች በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ በአምስት ምድብ ማለትም የቅዱስ ማቴዎስ፣ የቅዱስ ማርቆስ፣ የቅዱስ ሉቃስ፣ የቅዱስ ዮሐንስና የቅዱስ እስጢፋኖስ ምድብ ተከፋፍሎ ውይይት ተደርጓል። የመጀመርያው ርእሰ ጉዳይ በገጠር አብያተ ክርስቲያናት የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን ለማጠናከር ምን እንደሚጠበቅ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በከተማ የሚገኙ ምዕመናን ወደ ገጠሪቱ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ የአገልግሎቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምን ማድረግ እንደሚገባ በተጨማሪም ምዕመናንን መንፈሳዊ ዕውቀት እንዳይኖራቸው የሚያደርጋቸው ተግዳሮቶች ምን እንደሆኑ በሰፊው በመወያየት የተለያዩ ምክረ ሃሳቦች ቀርበዋል።

ወደ ኦቲልቾ የስብከተ ወንጌል ኬላ በሚደረገው የእግር ጉዞ ላይ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ውይይት ተደረገ! Read More »

ልዩ መንፈሳዊ የእግር ጉዞ

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር በሚገኘው የኦቲልቾ የስብከተ ወንጌል ኬላ በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መሪነት የካቲት 15/2018 ዓ.ም ስለተዘጋጀ ሁላችሁም ምዕመናን በቦታው ተገኝታችሁ የጉዞው ተሳታፊ እንድትሆኑ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም መንፈሳዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን! የጉዞ ቀን- የካቲት 15/2018 ዓ.ም ዕለተ ሰንበትየጉዞው ሰዓት – ከጠዋቱ 1:00 ሰዓትመነሻ ቦታ – የአንዲዳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያንመድረሻ ቦታ – የኦቲልቾ የስብከተ ወንጌል ኬላ

ልዩ መንፈሳዊ የእግር ጉዞ Read More »

​Clarification Regarding the Job Vacancy Announcement

​Regarding the inquiries raised concerning the “fully healthy” criterion and the registration procedures in our Diocese’s recent job vacancy announcement, we hereby provide the following clarification: ​First and foremost, the term “fully healthy” is intended to ensure that applicants possess the physical and mental well-being necessary to perform their assigned duties effectively. Accordingly, as long as an applicant has the capacity to competently perform the essential functions of the accounting position—such as meticulously verifying documents and performing computer-based financial tasks—any physical condition shall not be considered a disqualifying criterion. ​Furthermore, we wish to clarify that the requirement for medical evidence is solely to verify that the applicant is in a state of health that enables them to fulfill the responsibilities of the position and to ensure overall professional fitness; it is not intended to facilitate any form of discrimination. ​Finally, for applicants who are in remote locations and are unable to register in person, we announce that you may register online by submitting all necessary and complete supporting documents, as specified in the announcement, via the official Diocese email address: Office@eotc-gkb.org. ​Public Relations DepartmentGedeo, Kore, and Burji Diocese

​Clarification Regarding the Job Vacancy Announcement Read More »

ስለ ሥራ ማስታወቂያው የተሰጠ ማብራሪያ

​በሀገረ ስብከታችን በወጣው የሥራ ማስታወቂያ ላይ “ሙሉ ጤነኛ” ለሚለው መስፈርት ለተፈጠረው ጥያቄና ስለምዝገባው ሁኔታ የሚከተለውን ማብራሪያ እንሰጣለን። ​በመጀመሪያ ደረጃ “ሙሉ ጤነኛ” የሚለው አገላለጽ የተፈለገው አመልካቾች የተሰጣቸውን የሥራ ኃላፊነት ያለ ጤና እክል በብቃት መወጣት የሚችሉ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው። በመሆኑም አንድ አመልካች ለሂሳብ ሥራ መደቡ የሚያስፈልጉትን መሠረታዊ ተግባራት (ለምሳሌ የሰነዶችን ትክክለኛነት በጥንቃቄ ማረጋገጥ እና የኮምፒውተር ላይ የሂሳብ ሥራዎችን ማከናወን) በብቃት ለመወጣት የሚያስችል አቅም እስካለው ድረስ፣ ማንኛውም አካላዊ ሁኔታ እንደ መከልከያ መስፈርት አይቆጠርም። ​በተጨማሪም የሚጠየቀው የሕክምና ማስረጃ ዓላማው አመልካቹ የተመደበበትን የሥራ ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችልና ለሥራው አስፈላጊ የሆነው የተሟላ የጤና ቁመና ላይ መሆኑን ለማረጋገጥ እንጂ ማንኛውንም ዓይነት መድልዎ ለመፈጸም እንዳልሆነ እንገልጻለን። ​በመጨረሻም በርቀት የምትገኙና በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የማትችሉ አመልካቾች በማስታወቂያው ላይ የተጠቀሱትን አስፈላጊና የተሟሉ ማስረጃዎች በሙሉ በሀገረ ስብከቱ ይፋዊ የኢሜል አድራሻ Office@eotc-gkb.org በመላክ በኦንላይን መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። ​የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል​

ስለ ሥራ ማስታወቂያው የተሰጠ ማብራሪያ Read More »

ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተ ክህነት በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መሪነት አዲስ ወደሚገነባው ወደ ጨልባ ቅዱስ መርቆርዮስ ቤተ ክርስቲያን የካቲት 29/2018 ዓ.ም ጉዞ ስለተዘጋጀ ሁላችሁም እንድትሳተፉ መልእክታችንን እናስተላልፋለን!

ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ Read More »

​🔔 የዕጣ ማውጫ ቀን ማሳሰቢያ!

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ​የመንበረ ጵጵስና ሕንጻ ግንባታ ዕጣ የካቲት 16 በይርጋጨፌ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በሕዝብ ፊት በይፋ ይወጣል። በዕለቱ ዕጣ የማውጣት ሥነ ሥርዓቱን በገጻችን በቀጥታ ሥርጭት (Live) የምናስተላልፍ መሆኑን እየገለጽን ሁላችሁም እንድትከታተሉን እናሳውቃለን።

​🔔 የዕጣ ማውጫ ቀን ማሳሰቢያ! Read More »

ልዩ መንፈሳዊ የእግር ጉዞ ጥቂት ምዕመናን ብቻ ወደሚገኙበት ወደ ኦቲልቾ የስብከተ ወንጌል ኬላ

በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መሪነት በቀን 15/6/2018 ዓ/ም በዕለተ እሁድ የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ ስለሚካሄድ ሁላችሁም በዕለቱ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን! የጉዞ መነሻ አንዲዳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን

ልዩ መንፈሳዊ የእግር ጉዞ ጥቂት ምዕመናን ብቻ ወደሚገኙበት ወደ ኦቲልቾ የስብከተ ወንጌል ኬላ Read More »

Scroll to Top