በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

Admin

“ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አታሸነፍ” (ሮሜ ፲፪፥፳፩)

“ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አታሸነፍ” (ሮሜ ፲፪፥፳፩) መምህር ሳምሶን ወርቁጥር ፲፯፤ ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት ክፉና በጎ የሰው ልጆች ባሕርያት ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር ለመልካም ነበረ፡፡ (ዘፍ.፩፥፲፪) ምንም እንኳን የፍጥረት አክሊል የሆነው ሰው ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ ከብርሃን ጨለማን፣ ከሕይወት ሞትን፣ ከመታዘዝ አለመታዘዝን ቢመርጥም እግዚአብሔር አምላክ የፈጠረው ስሙን እንዲቀድስ ክብሩን እንዲወርስ ነበረ፡፡ ለዚህም ክፉና ደጉን መለየት ይችል ዘንድ አስቀድሞ የሚያስተውል አእምሮ ሰጥቶት ነበር፡፡ በኅሊናው መመራት ተስኖት የሰው ልጅ ከወደቀ በኋላ ዳግመኛ የተጻፈ ሕግ ሰጥቶታል፡፡ ሰዎች ራሳቸው ላይ የክፉ ብድራት እንዳይደርስባቸው አስበው በባልንጀራቸው ላይ ክፉ እንዳያደርጉ ክፉ ላደረጉ የክፉ ብድራት እንዲከፈላቸው ሙሴ ሕግን ጻፈላቸው፡፡ ክፉ የሚያደርጉ ሁሉ ቅጣት ነበረባቸው፤ “ሕይወት በሕይወት፥ ዓይን በዓይን፥ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር፥መቃጠል በመቃጠል፥ቍስል በቍስል፥ ግርፋት በግርፋት ይከፈል” እንዲል። (ዘፀ.፳፩፥፳፬) በተመሳሳይ ሙሴ ለእስራኤል ሲናገር “ሰውም ባልንጀራውን ቢጐዳ፥እርሱ እንዳደረገ እንዲሁ ይደረግበት። ስብራት በስብራት ፋንታ፥ዓይን በዓይን ፋንታ፥ጥርስ በጥርስ ፋንታ፥ሰውን እንደ ጐዳ እንዲሁ ይደረግበት። እንስሳውንም የሚገድል ካሳ ይተካ፤ ሰውንም የሚገድል ይገደል” በማለት ሕግን አስተምሯል፡፡ (ዘሌ.፳፬፥፲፱) የሕግ መምህር ሐጋጌ ሕግ የሆነው አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመንግሥቱን ወንጌል በመዋዕለ ሥጋዌው ሲያስተምር አስቀድሞ የነበረው በሙሴ የተነገረው እንዳለፈ ሲናገር “ዓይን ለዓይን ጥርስ ለጥርስ እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ እኔ ግን እላችኋለሁ ክፉን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጨህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤ እንዲከስህም እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት፤ ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ፡፡” (ማቴ.፭፥፴፰) ክፉን በክፉ ሳይሆን በበጎነት ማሸነፍ እንደሚገባ ያስተምረናል፡፡ ክፉን በክፉ መመለስ ምን ያስከትላል? ዛሬ ላይ በቤተሰባዊ ሕይወታችን ባል በሚስት፣ ሚስት በባል፣ ወላጆች በወላጆች፣ ልጆች በወላጆች ላይ በክፋት ተነሣስተው አንዱ ሌላው ላይ “እንዲህ አደረጉ ሲባል እንሰማለን፡፡ ለጥፋታቸው እንዲህ አድርጋኝ ነው፤ እንዲህ አድረጎኝ ነው” የሚሉ ምክንያቶችን ሲደረድሩም እንሰማለን፡፡ ክፉን በክፉ መቃወም ሰዎችን የበለጠ እልኸኛ ያደርግ ይሆናል እንጂ ክፉ አድራጊዎችን ከክፋት ለመመለስ አይችልም፡፡ ክፉን በክፉ በመመለስ ሰዎች በመካከላቸው ያለውን ግንኙነትን ማቋረጥ፣ ከዚያም ባለፈ ትልቁን ተቋም ቤተሰብ እስከማፍረስና ልጆች እስከመበተን ያደርሳቸዋል፡፡ ክፉን በክፉ መመለስ ለጊዜው የአሸናፊነት ስሜት በመፍጠር ደስ የሚያሰኝ ቢመስልም ፍጻሜው ጸጸት ነው፡፡ አንዳንዶች ደረሰብኝ ለሚሉት ክፉ ነገር በክፉ መልሰው ከጸጸት ለመሸሽ ሲሉ አደንዛዥ ዕፅንና መጠጥን መደበቂያ የሚያደርጉት ለዚህ ነው፡፡ እንደሀገርም ከገባንበት የፖለቲካ አዙሪት መውጣት የተሳነን ክፉን በክፉ የመመለስ ደዌ ስለተጠናወተን ነው፡፡ ይህ ደግሞ እንደ ሀገር ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን አሳጥቶ ሁለንተናዊ ቀውስ እያስከተለብን ይገኛል፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ ግለሰቦችና ቡድኖች “ደረሰብን ቆመንለታል” በሚሉት ማኅበረሰብ ላይ ደረሰ ለሚሉት ክፉ ነገር አማራጭ መፍትሔ አድርገው የሚያስቡት መልሶ ክፉን በክፉ መመለስ የሆነው ለዚህ ነው፡፡ ክፉን በክፉ መመለስ ለተጠቃው አካል ምን ይጨምርለታል? መቼስ ይህንን ለመረዳት የተለየ ዕውቀት አይጠይቅም፤ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው፡፡ ክርስቲያን መሆን ደግሞ ተጨማሪ ኃላፊነት ነው፡፡ የደረሰብን ክፉ ነገርን በክፉ እንዳንመልስ የወንጌል ሕግ ግድ ይለናል፡፡ “ተወዳጆች ሆይ፥ራሳችሁ አትበቀሉ፥ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፏልና።” (ሮሜ ፲፪፥፲፱) ክፉን በመልካም መመለስ ለጠላት ጊዜያዊ ድል ሊያስገኝ ይችላል! ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ አንጻራዊ ሰላም አግኝታ ይሆናል እንጂ ከክፉዎች ፍላጻ ዕረፍት ያገኘችበት ዘመን አለ ማለት ይቸግራል፡፡ በተለይ አሁን ባለንበት ዘመን የክፉዎች ጥቃት ተቋማዊ ሆኖ አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠል፣ የምእመናን ደም ማፍሰስና ማሳደድ በስፋት እየተመለከትን ነው፡፡ ምንም እንኳ ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ መሥዋዕትነት ሀገርን አጽንታ ብታቆይም መብቷን በድርድር በቸሮታ እንድትቀበል ለማድረግ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ከመሀል ሀገር እስከ ጠረፍ እየተመለከትን ነው፡፡ በጌታችን ሞት እንደተባበሩት እዚህም እዛም ከኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖት በአፍአ ያሉ የእምነት ቡድኖች ተባብረው ቀድሞ የነበረውን ስውር ጦር በግልጽ መወርወር ጀምረዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን በዓላትን በዐደባባይ የምታከብራቸውን ቦታዎች ላይ የይገባኛል ጥያቄ ማንሳት፣ በበዓላት ላይ እንዲህ ዓይነት ቀለም ለበሳችሁ በማለት ምእመናንን ማንገላታት ማስቆጣት፣ ምክንያት እየፈለጉ በኦርቶዶክሳዊ ማንነት ማሸማቀቅ፣ መደብደብ ፣ ማቁሰልና መግደል የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡፡ ይህ ሁሉ ጠላት ለጊዜው ድል ያገኘ እንዲመስለው ያደርግ ይሆናል እንጂ ፍጻሜው ጥፋት ውድቀት ነው፡፡ “የፍጹም ሰው ጽድቁ መንገዱን ያቀናለታል፤ ኃጥእ ግን በኃጥአቱ ይወድቃል” እንዲል፤ (ምሳ.፲፩፥፭) ለጊዜው ከፍ ከፍ ብሎ መታየቱ የውድቀቱ መጀመሪያ እንደሆነ ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡ “ኃጥእን ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት፡፡ ብመለስ ግን አጣሁት ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም” እንዲል፡፡ (መዝ.፴፯፥፴፭) ክፉን በመልካም መመለስ ትዕግሥታችንን ይፈትናል! ባለንበት ዘመን አብያተ ክርስቲያናት እንደ ጣፍ ሲነዱ፣ ንዋየ ቅድሳት እንደ ደረቅ እንጨት ሲማገዱ፣ አገልጋይ ካህናትና ምእመናን እንደ መጻተኛ ሲሳደዱ፣ ይባስ ብሎ እንደ በግ ሲታረዱ፣ ደማቸው ክረምት ከበጋ እንደማይደርቅ ጅረት ሲፈስ እየተመለከተ የማይቀና ኦርቶዶክሳዊ አለ ማለት አይቻልም፡፡ ነገር ግን ቅናታችን እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሊሆን አይገባም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ክፉን በክፉ በመለሰ ጊዜ ጌታችን ገሥጾታል፤ “ስምዖን ጴጥሮስም ሰይፍ ስለ ነበረው መዘዘው፥የሊቀ ካህናቱንም ባሪያ፡መቶ፟ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠ፤ የባሪያውም ስም ማልኮስ ነበረ። ኢየሱስም ጴጥሮስን፦ ሰይፍህን ወደ ሰገባው ክተተው፤ አብ የሰጠኝን ጽዋ አልጠጣትምን አለው።” (ዮሐ. ፲፰፥፲) ክፉን መታገሥ ስሜታችንን የሚፈታተነን ቢሆንም ራሳችንን ገዝተን ክፉን በመልካም በመመለስ ክፉን ማሸነፍ ይገባል እንጂ ክፉን በክፉ በመመለስ በክፉ መሸነፍ አይገባም፡፡ በሰውኛ አስተሳሰብ ክፉን በመልካም መመለስ ከባድ ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን እኛ ፈቃደኝነቱ ካለን እግዚአብሔር ኃይል ብርታት ሆኖ ያስችለናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ በማለት ተናግሯል፤ “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ፡፡” (ፊል.፬፥፲፫) ክፉን በመልካም መመለስ በጠላት ላይ ድል ያስገኛል! ከሰዎች ጋር በሚኖረን ማንኛውም ግንኙነት የሚያጋጥሙንን ክፉ ሐሳቦችን፣ ክፉ ንግግሮችንና ክፉ ድርጊቶችን በበጎ በመመለስ ክፉ አሳቢዎችን፣ ክፉ ተናጋሪዎችንና ክፉ አድራጊዎችን ማስተማርና ወደ መልካም መንገድ መመለስ ከክርስቲያኖች ይጠበቃል፡፡ ምክንያቱም “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ” ተብለናልና ክፉዎች የሠለጠኑበት አልጫው ዓለም የሚጣፍጠው እኛ ጨው ሆነን ስንገኝ እንደሆነ ልንረዳ ይገባል፡፡ (ማቴ.፭፥፲፫) እንዲሁም ክፋት የበረታበት ጨለማው ዓለም በብርሃን የሚመላለሰው በእኛ ክርስቲያኖች ብርሃንነት ነው፡፡ “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፡፡” ስለዚህ ክፉን በመልካም በመመለስ ለአልጫው ዓለም ጨው፤ ለጨለማው ዓለም ብርሃን መሆን የእኛ ድርሻ ነው፡፡ (ማቴ.፭፥፲፬) ክፉን በመልካም መመለስ በጠላት ላይ ድል ያስገኛል፤ ምክንያቱም እኛ ክርስቲያኖች ነን፡፡ ክፉን በመልካም ማሸነፍ የሚቻለው እንዴት ነው? በወንጌል ትርጓሜ ክፉን በበጎ ማሸነፍ እንደሚቻል የሚያስረምር ታሪክ አለ፡፡ ታሪኩ የአንድ ባሕታዊ ሲሆን እርሱ በበዓቱ ሳለ ወንበዴዎች እንግዶች መስለው መጡበት፤ እግራቸውን አጥቦ አብልቶ አሳደራቸው፤ ሌሊት ተነሥተው እርሱን አሥረው መብራት አብርተው ያለ ገንዘቡን ይዘው ሄዱ፡፡ ከሄዱ በኋላ መብራት አብርቶ ቢያይ ሁለት ድሪም የምታወጣ ፀምር አገኘ፡፡ “ይህችም ለአንድ ጉዳይ ትሆናችኋለች” ብሎ ተከትሎ ወስዶ ሰጣቸው፡፡ ይህ ሰው እንዲህ ማድረጉ ከዚህ የበለጠ ዋጋ እንዳለ ቢያውቅ እንጂ ነው ብለው ተመልሰው ንስሓ ገብተው የሚኖሩ ሁነዋል፡፡ ሰዎች የቱንም ያህል ለክፋት ቢሠለጥኑ እግዚአብሔር ኅሊናን የሚያህል ዳኛን ሰጥቷልና የጊዜ የሁኔታ ጉዳይ ይሆናል እንጂ መመለሳቸው አይቀርም፡፡ ክፉ አድራጊዎች ላይ እንኳን ብድር መመለስ ይቅርና መጥላት እንደማይገባ ሲያስተምር እንዲህ ብሏል፡፡ “ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህን ጥላ እንደተባለ ሰምታችኋል፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ በሰማይ ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግማችሁን መርቁ፤ ለሚጠሏችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞች ላይ ዝናብን ያዘንባልና፡፡ የሚወዷችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ፤ ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን፡፡” (ማቴ.፭፥፵፫) ክርስቲያኖች ሰዎች በጠላትነት ተነሥተውባቸው ሲረግሟቸውና ሲያሳድዷቸው ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን ምረረ ገሃነምን ባያውቅ ባታውቅ ነው ብለው መታገሥ እንደሚገባ፣ የሚወዱንን ብቻ ሳይሆን የማይወዱንን በመውደድ ለማያምኑ ሃይማኖታችንን በተግባር በመግለጥ የድኅነት ምክንያት መሆን ከእኛ ከክርስቲያኖች ይጠበቃል፡፡ ክፉን በመልካም ማሸነፍ ማለት ክፉ ግብር ይዘው

“ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አታሸነፍ” (ሮሜ ፲፪፥፳፩) Read More »

ክርስቲያናዊ ህይወት

ክርስትና የሚለው ቃል “XPIETIAVOS” ኽርስቲያኖስ ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም የክርስቶስ መሆን ማለት ነው፡፡ ክርስትና ሰዎች በፍቅረ እግዚአብሔር ተስበው፤ ፈጣሪያቸውን አውቀው፤ እረፍትን ሽተው፤ በህጉና በትእዛዙ ፀንተው፤ ለመኖር ሲሉ ከዓለም ፈቃድ ተለይተው የሚኖሩበት ህይወት ነው፡፡ ይህንንም ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀመዝሙር ዮሐንስ “ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የስጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለገንዘብም መመካት ከዓለም ስለሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ÷ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም፡፡ ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ የእግዚያብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለዐለም ይኖራል” (1ዮሐ 2፡16) በማለት ክርስቲያን ለመሆን በመጀመሪያ ዓለምን መካድ እንዳለብን ያስተምረናል፡፡ በክርስትና ወድቆ (ተረግሞ) የነበረው የሰው ዘር እንደ ተነሳ (እንደ ተፈታ)፤ የታመመው እንደ ተፈወሰ፤ የረከሰው እንደ ተቀደሰ፤ የሞተው እንደተነሳ፤የተሰበረው እንደተጠገነ፤ የሳተው እንደ ተመለሰ ይታመናል፡፡ የክርስትና መስራቹ ራሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ “በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሰራለሁ፡፡ የገሀነም ደጆችም አይችሏት” (ማቴ 16፡18) በማለት ቤተክርስቲያን ሳይሆን ቤተክርስቲያኔን የራሱ እንደሆነች በህያው ቃሉ አረጋግጦልናል፡፡ ክርስቲያኖች ክርስቲያን ከመባላቸው አስቀድሞ ምዕመናን (መዝ 100፡7) ፤ ደቀመዛሙርት (ኢሳ 8፡16) ፤ ወንድሞች (ማቴ 8፡10) የመሳሰሉት በመባል ይጠሩ ነበር፤ ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ ክርስቲያን ተብለው ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰየሙት በአንጾኪያ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት እንደነበር ቅዱስ መጽሀፍ ይነግረናል፡፡ (የሐዋ 11፡26) በምድራችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሃይማኖቶች ይገኛሉ፡፡ የሃይማኖታቸውን መስራች ስናጠና ግን ሰዎች ሆነው እናገኛለን፡፡ ትምህርታቸው ዛሬም በተከታዮቻቸው ይኑር እንጂ እነርሱ ግን በህይወት የሉም፤ የክርስትና ዋና መስራች ግን ትናንት የነበረ ዛሬም ያለ ወደፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ዐልፋና ዖሜጋ ዘዓአለማዊ በመሆኑ ዛሬም ስራውን አላቆመም ማለት ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ህይወት ለመኖር ክርስቲያኖች የሚከተለውን መተግበር እንዳለብን የህይወት ምንጭ የሆነው መጽሀፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ 1.    እግዚያብሔርን ማወቅ መቼም ዓለም አንድ መንደር በሆነችበት ዘመን ስለ እግዚያብሔር ያልሰማ አለ ብሎ ለመናገር ያስቸግራል፡፡ ይሁን እንጂ ከዕውቀት ብዛት እግዚአብሄርን የካዱ (እግዚአብሔር የለም) ያሉ በርካታ ሰዎች በምድራችን መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ ይህም ስንፍና እንጂ እውቀት እንዳልሆነ ልበ አምላከ ቅዱስ ዳዊት ይነግረናል፡፡ “ይበል አብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር” ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል (መዝ 13፡1)፡፡ ፍልስፍና ማለት ጥበብን ማፍቀር ማለት እንጂ እግዚአብሄርን አለማወቅ ወይም መካድ ማለት አይደለም፡፡ አንድ ልጅ አባቱን አላውቅህም አባቴ አይደለህም ስላለው አባቱ አልወለደውም ማለት አይደለም እንዳውም ልጁ ሲጠራ አባቱን የካደ ልጅ ተብሎ ይጠራል፡፡ እግዚአብሄርን ማወቅ፡- ትርጉም ያለው ሕይወት ይሰጣል በምድራችን ትርጉም ያለው ሕይወት ማለት ምን አልባት የሚመስለን ሀብት፤ ንብረት፤ ስልጣን ፤ ጥሩ መልበስ፤ ጥሩ መመገብ ፤ ጥሩ ቤት መኖር ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን ትርጉም ያው ህይወት መኖር የሚቻለው እግዚአብሄርን ሲያውቅ ነው፡፡ በዚህ ዘኪዎስ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል፡፡ ዘኪዎስ ጌታውን ሳያውቅ የኖረበት ዘመን ትርጉም አልባ ህይወት ነበር አምላኩን ሲያውቅ ግን “ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ ማንንም በሃሰት ከስሼ እንደሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው” (ሉቃ 19 ፤9) በማለት አዲሱ ክርስቲያናዊ ህይወት ምን እንደሚመስል ነግሮናል፡፡ ታሪክን ይቀይራል ሰዎች እግዚአብሄሔርን ሲያውቁ ዘማዊ የነበረው ድንግል፤ ዘረኛና ወገንተኛ የነበረው ሁሉን በክርስቶስ አንድ አድርጎ የሚያይ ፍትሃዊ፤ አሳዳጅ የነበረው ስለ ክርስቶስ ተሳደጅ፤ ክፉ የነበረው ደግ፤ ዘፋኝ የነበረው ዘማሪ፤ ነፍሰ ገዳይ የነበረው የሰውን ህይወት የሚያድን ወዘተ ይሆናል፡፡ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ ጥሩ አስረጅ ይሆናል፡፡ 2.    በዕምነት ማደግ ብዙዎች ክርስቲያን ተብለው ይጠራሉ ጥቂቶች ብቻ በእምነት ውስጥ በጥበብ ይኖራሉ፡፡ “ዕምነት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነውና” (ዕብ11፡1) የሰው ልጅ በሃይማኖት ካልኖረ ለምኞቱ ገደብ የለውም፡፡ ያለኝ ይበቃኛል አይልም፡፡ አመንዝራ ሲያይ በፍትወት ስሜት ይቃጠላል፣ የወይን ጠጅ በብርሌ ባማረ መልኩ ባየ ጊዜ መጠጥ ያምረዋል ለዚህ እኮ ጥበበኛው ጠቢቡ ሰለሞን “ከተማን ከመግዛት ራስን መግዛት ይበልጣል ያለው” 3.    በእግዚአብሔር ፍቃድ መኖር እግዚአብሔር ከእኔ ይልቅ ስለ እኔ ያስባል ብሎ ማመን ነው፡፡የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡(የሐ2፡17) የጌታችንም ፈቃድ ሁሉ የእግዚአብሔር እንደሆነ ሲያስተምር “አባት ሆይ ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ ነገር ግን የእኔ ፍቃድ አይሁን የአንተ እንጂ”(ሉቃ22፡42) ምክንያቱም ሀዋርያው እንደተናገረው ”ስለ በጎ ፈቃድ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሰራ እግዚአብሔር ነውና” እንዲል (ፊሊ1፡13) 4.     እግዚአብሔርን መምሰል ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ዓለም ሶስት ዓመት ከሶስት ወራት በአገልግሎት ሲቆይ በርካታ ትምህርቶችን ከማስተማሩም በላይ በሕይወቱ አብነት ለመሆን መልካም ሥራ ካደረገ በኋላ ከመዝ ግበሩ  እናንተም እንዲሁ አድርጉ(ዮሐ13፡14)(ምንም እንኳን መልካምነት የባህርይው ቢሆንም) በማለት ክርስቲያኖች በሕይወት ዘመናቸው ክርስቶስን መምሰል እንዳለባቸው መጽሀፍ ይስተምረናል፡፡ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስም ይህንን ቃል ”እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ”(1ኛቆሮ 11፡1) በማለት ያረጋግጥልናል፡፡በመሆኑም የመንፈስን ፍሬ በማድረግ የስጋን ሥራ በመተው አምላካችንን መምሰል ይገባናል ማለት ነው፡፡(ገላ 5፡18)ይህንን በማድረግ ቅዱሳን ቅድስናን ገንዘብ አድርገዋል፡፡“እግዚአብሔር መምሰል ግን ለአሁኑ እና ለሚመጣው ተስፋ ስላለው ለነገር ሁሉ ይጠቅማል”(2ጢሞ 4፡8) 5.    ፍቅር ሊኖረን ይገባል በክርስትና መጀመሩያውም መጨረሻውም ፍቅር ነው፡፡ ምክንያቱም “ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፡፡እግዚአብሔር ፍቅር ነውና” (1ዮሐ 4፡8) በመሆኑም ያለ ፍቅር ክርስትና የለም፡፡ቢኖር እንኳን ቅ/ጳውሎስ እንደተናገረው ከንቱ ነው “ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ”(1ቆሮ 13፡1) 6.    ከመስቀሉ መካፈል የጠፋውን በግ ፍልጋ ራሱን ባዶ ያደረገው ክርስቶስ (ፊሊ 2፡8) ድሉ በመስቀል ስለ ተጠናቀቀ ክርስቲያኖች በሕይወት ዘመናቸው ከመስቀሉ ተካፋይ መሆን አለባቸው፡፡ ለዚህም ከመስቀሉ ስር የተሰጠችንን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን መውሰድ፤ የተቆረሰውን ቅዱስ ስጋ መብላት፤ የፈሰሰውን ክቡር ደም መጠጣት ይኖርብናል ማለት ነው፡፡ (ዮሐ 19፡27፤ ዮሐ 6፤56) ይህ ሁሉ ሲሆን ለዘለዓለም በሕይወት እንኖራለን ማለት ነው፡፡ ስብሃት ለእግዚያብሔርወለወላዲቱ ድንግልወለ መስቀሉ ክቡርአሜን

ክርስቲያናዊ ህይወት Read More »

ትምህርተ ሃይማኖት

በሊቀ ካህናት ኃይለሥላሴ ዓለማየሁ ወልድ ዋሕድ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና የሌሎች አኃት አብያተ ክርስቲያናት መሠረታዊ እምነት «ተዋሕዶ» ነው። ተዋሕዶን የሚተረጉም ኃይለ ቃልም ፣ «ወልድ ዋሕድ» የሚለው ነው። ወልድ ዋሕድ ለሚለው ሥያሜ መሠረቱ «ቃል ሥጋ ኮነ» የሚለው ቃለ ወንጌል ነው። ዮሐ ፩፥፲፬። ስለሆነም፣ የዚህ ዝግጅት ዐቢይ ርእስ /ዋና ርእስ/ ወልድ ዋሕድ እንዲባል ተመርጦአል።በዚህ ዝግጅት የሚቀርቡ ንኡሳን አርእስተ ትምህርት በየርእሳቸው እየታተቱ የሚቀርቡ ሆኖ ጥናቱ በማስረጃ የተደገፈ እንዲሆን ለማድረግ አዘጋጁ ተገቢውን ጥረት ያደርጋል። ለወጣቱ ግንዛቤ ይሰጣል ተብሎ የሚታመንበት ዝግጅት እንዲሆንም በቀላል አገላለጽ ለማቅረብ ይሞክራል። የትምህርተ ሃይማኖት ምሥጢራዊ ይዘት ከመጽሐፍ ቅዱስና ከአበው ሊቃውንት የትርጉም ዘይቤ እየተገናዘበ ይቀርባል። የዝግጁቱ ዋና ዓላማ፣ ወጣቶች የትምህርተ ሃይማኖት ግንዛቤያቸውን እንዲያሰፉ ማድርግ በመሆኑ፣ የቤተክርስቲያናችንን መሠረተ እምነት ሊያዛቡ ከሚችሉ አዳዲስ አስተሳሰቦችና የግል አስተያየቶች ፍጹም ነፃ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ሆኖ እንዲቀርብ ተገቢው ጥንቃቄ ይደረጋል። ከአንባቢያን ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ሁሉ አስፈላጊው ትኩረት እየተሰጣቸው ተገቢውን መልስ እንዲያገኙ ማድረግ የአዘጋጁ ተቀዳሚ ተግባርና ግዴታ ነው። ይህን ዝግጅት የሚከታተሉ አንባብያንም እያንዳንዱን ኃይለ ቃል፣ በማስተዋል መከታተል፣ ምሥጢሩንና ቁም ነገሩንም በጥንቃቄ መቅሰም ይጠበቅባቸዋል። ጥበብና ማስተዋል የሚገኘው ከእግዚአብሔር ነውና እግዚአብሔር ጥበቡንና ማስተዋሉን ይስጠን። ከእግዚአብሔር አጋዥነትና ረድኤት ውጪ ምንም ምን የሚሆን ነገር ስለሌለ፣ በተለይም ባሕረ ጥበባት የሆነውን ትምህርተ መለኮት ለማቅረብ መሞከር፣ ውቅያኖስን በእንቊላል ቅርፊት… ማለት በመሆኑ፣ የጥበባት አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ጥበቡንና ማስተዋሉን እንዲሰጠን እንለምነዋለን። ትምህርተ ሃይማኖት መለኮታዊ ምሥጢርን የሚያስረዳ እንደመሆኑ ትምህርቱ ጥልቅ፣ ረቂቅና ምጡቅ ነው። ይሁንና በዚህ ዝግጅት ግን እንደ ትምህርቱ ጥልቀትና ምጥቀት ሳይሆን፣ እንደ አዘጋጁ የዕውቀት ውሱንነትና እንደ ተቀባዩ የአእምሮ ስፋት መጠን፣ ግልጽ በሆነ አቀራረብ ባጭር ባጭሩ ይቀርባል። የሃይማኖት ትርጉም  ሃይማኖት ምንድን ነው? ሃይማኖት ወይም እምነት ማለት ማመን፤ መታመን፤ የፈጣሪን ሕልውና ማወቅ፤ ከሃሊነቱን፣ መግቦቱንና ቸርነቱን መረዳት፤ መለኮታዊ እውነታዎችን በትክክል መቀበል፤ በእግዚአብሔር መለኮታዊ ሥራ ፈጽሞ አለመጠራጠር፤ ጥርጥርን ከኅሊና ማስወገድ፤ ስለ ሰማያዊ ሕይወት ጽኑ ተስፋ ማድረግ በሚሉ አገላለጾች ይተረጐማል። ሃይማኖት በረቂቅ ሐሳብ፣ በልብ ሰሌዳነት፣ የሚጻፍ የአእምሮ መጽሔት ነው። ሃይማኖት የኅሊና መሰላል በመሆኑ የዓለምን አስቸጋሪ ዳገት ይወጡበታል። ሃይማኖት የሕይወት መርከብ በመሆኑ ገፊውን ማዕበል ተቋቁመው ባሕሩን ይሻገሩበታል። ንጉሠ ሰማይ ወምድር እግዚአብሔርን ደስ ያሰኙበታል። ዕብ ፲፩፥፮። ልክና መጠን፣ ወሰንና ዳርቻ የሌለው መለኮታዊ ባሕርይ የሚታየው፣ ሕልውናው ከሃሊነቱና መግቦቱ የሚታወቀው በሃይማኖት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ የሃይማኖትን ኃይል ሲተረጉም፦ «እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፣ የማናየውን ነገር የሚያስረዳ ነው።» ይልና በመቀጠልም «ነአምር ከመ ተፈጥረ ዓለም በቃለ እግዚአብሔር። ዓለም በእግዚአብሔር ቃል እንደተፈጠረ እናውቃለን።» ብሎአል። ዕብ ፲፩፥፩-፫። ሃይማኖት ፍጡርን ከፈጣሪው ጋር የሚያገናኝ የኅሊና መሰላል በመሆኑ ፍጡር የሃይማኖት መሰላሉና ድልድዩ ከተሰበረበት ወደ ፈጣሪው መድረስ ይሳነዋል፤ ሌላ መድረሻ ሌላ መንገድ ፈጽሞ የለውም። የሃይማኖት ኃይል ልዩና ዕፁብ ድንቅ የሚያሰኘው፣ ምድራዊ ባለሥልጣን የማይገዛውን የሚገዛ፣ በዓይነ ሥጋ የማይታየውን የሚያሳይ፣ በእጅ የማይዳሰሰውን የሚዳስስ፣ በሥጋዊ ጥበብ የማይመረመረውን የሚመረምር ምሥጢር መሆኑ ነው። ማቴ ፲፮፥፲፯። ልዕልና ነፍስ /የነፍስ ልዕልና/ ክብረ ነፍስ የሚገኘው በሃይማኖት ነው፤ ከሃይማኖት ውጪ የሚሆነው ሁሉ ኃጢአትና በደል ነው። «ወኲሉ ዘይከውን ዘእንበለ አሚን ኃጢአት ወጌጋይ ውእቱ። በእምነት ያልሆነ ሁሉ ኃጢአትም፣ በደልም ነው።» ሮሜ ፲፬፥፳፫። የሚታይና የማይታይ፣ ግዙፍና ረቂቅ፣ ሁሉ ከማይታይ እንደሆነ ማለትም በመለኮታዊ ሥልጣን የተገኘ መሆኑን ያሳውቃል። እግዚአብሔር ለፍጥረቱ ሁሉ መገኘት ምክንያት ሳይሻለት በከሃሊነቱ እምሀበአልቦ ፈጥሮታል። ይህን ማወቅ የሚያስችል ከሃይማኖት ውጪ ሌላ ጥበብ ፈጽሞ የለም። የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወራሽ የመሆን ዕድል የሚያገኘው በሃይማኖት ብቻ ነው። በዓለም ያለውን ሥርዓት በቀላሉ በምሳሌነት ማየት ይቻላል፤ ይኸውም የአንድን ሰው ሃብትና ንብረት ለመውረስ በቀላሉ ባለመብት መሆን የሚቻለው የባለጸጋው ወይም የባለሀብቱ ልጅ ሆኖ መገኘት ሲቻል ነው። በእግዚአብሔር መንግሥትም በሃይማኖት ልጅነትን ካላገኙ የመንግሥቱ ወራሽ መሆን አይቻልም። «እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።» እንዳለ ጌታ በቅዱስ ወንጌል። ዮሐ ፫፥፭። «… ስለዚህ ከእንግዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም። ልጅም ከሆንክ ደግሞ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።» ገላ ፬፥፬-፯።ሃይማኖት በአማኙ ዘንድ ሦስት ነገሮች ተሟልተው እንዲገኙ ግድ ይላል። እነዚህም፦ ፩. ትክክለኛ አረዳድ /እውነት/፪. የልብ ንጽሕና /ቅንነት/፫. መጥዎተ ርእስ፣ ማለትም ጥብዓት፣ ራስን መካድ፣ ራስን አሳልፎ ለሃይማኖት መገዛት ፈቃደ ሥጋን አሸንፎ መስቀልን መሸከም የሚሉ ናቸው። እነዚህ መሠረታዊ ነገሮች ያልተሟሉለት አማኝ ግብዝ ሃይማኖተኛ ይባላል። ማስረጃ «… እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ። አጋንንት ደግሞ ያምናሉ፤ ይንቀጠቀጡማል። …» ያዕ ፪፥፲፬-፳፪። ማር ፭፥፯። ጌታም በቅዱስ ወንጌል እንዲህ ይለናል። «በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።» ማቴ ፯፥፳፩። «ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ፣ እንዲህ አላቸው፤ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፣ ራሱን ይካድ። መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።» ማር ፰፥፴፬። ሉቃ ፱፥፳፫። ማቴ ፲፥፴፰፣ ፲፮፥፳፬። «ወኅሊናሁሰ ለነፍስትነ ሞተ ያመጽእ ላእሌነ፤ ወሕሊናሁሰ ለመንፈስ ሰላመ ወሕይወተ ይሁብነ። የሥጋችን ፈቃድ ሞትን ያመጣብናል /ያስፈርድብናል/ የነፍሳችን ፈቃዱ ግን ሰላምን ከእግዚአብሔር ጋር አንድነትን ድኅነትን ይሰጠናል። እስመ ኅሊናሁ ለነፍስትነ ፀሩ ለእግዚአብሔር ውእቱ። የሥጋችን ፈቃዱ የእግዚአብሔር ጠላቱ ነውና ሞትን ያመጣብናል።» ሮሜ ፰፥፭-፰።የሃይማኖት ዓላማውና ግቡ፣ ሀልዎተ እግዚአብሔርን ማሳወቅና ፍጡር በፈጣሪው ሕግና ትእዛዝ እየተመራ ዘለዓለማዊ ክብር እንዲያገኝ ማድረግ ነው። ማቴ ፳፭፥፴፬። ሀልዎተ እግዚአብሔርን ማወቅ ማለትም ቅድመ ዓለም የነበረ፣ በማዕከለ ዓለም ያለ፣ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር፣ ፈጣሪ፣ መጋቢ ሠራዒ፣ በመለኮታዊ ባሕርዩ ጸንቶ የሚኖር፣ ለመንግሥቱ ሽረት፣ ለሕልውናው ኅልፈት የሌለበት አንድ ፈጣሪ፣ አንድ አምላክ መኖሩን አውቆ ማመን ማለት ነው። «እስራኤል ሆይ ስማ፤ አምላክህ እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው።» ዘዳ ፭፥፬። የማይታይና የማይመረመር፣ የማይገሰስና የማይዳሰስ፣ ሕያወ ባሕርይ እግዚአብሔር በከሃሊነቱ ሁሉን የፈጠረ፣ በመግቦቱ ሁሉን የሚያስተዳድር፣ በቸርነቱ ሁሉን የሚጠብቅ አምላክ በመሆኑ ለፍጥረቱ የሚታወቅበት ገጽታ አንዱ ይኸው ነው። ሁሉን የሚገዛ፣ ሁሉን የሚያስተዳድር በመሆኑ ይቅርታውና መግቦቱ በሁሉም ላይ ነው። «እስመ ቅንየትከ ወምልክናከ ላዕለ ኲሉ፣ ይሬስየከ ትሣሃል ላዕለ ኲሉ። ማለት በሁሉ ላይ ያለ ሥልጣንህና አገዛዝህ ሁሉን ይቅር እንድትል ያደርግሃል።» እንዲል። «… እርሱ በክፉዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።» ማቴ ፭፥፵፭። በከሃሊነቱ ዓለምን የፈጠረ እግዚአብሔር የማይታይ፣ የማይመረመርና የማይዳሰስ፣ እንደሆነ ቢታወቅም፣ ባሕርዩ ከሚገለጽባቸው አያሌ መገለጫዎች ጥቂቶቹን በምሳሌነት መመልከት ይቻላል። እነሱም፦ ፩. ፈጣሪ፪. ከሃሊ፫. ምሉእ፬. ዘለዓለማዊ፭. ቅዱስ፮. ፍጹም፯. ማእምር /አዋቂ/ ጥበበኛ የሚሉ ናቸው። እነዚህን በዝርዝር እንመለከታለን። እግዚአብሔር ፈጣሪ ነው ፈጣሪ ስንል የሌለን ወይም ያልነበረን ነገር በሥልጣኑና በከሃሊነቱ ያስገኘ፣ ዓለምን እምሀበአልቦ /ካለመኖር ወደ መኖር/ የፈጠረ ማለታችን ነው። ዓለምን እምሀበአልቦ ያስገኘ፣ በመለኮታዊ  ሥልጣኑ የሚታየውንና የማይታየውን፣ ግዙፉንና ረቂቁን ፍጥረት ሁሉ የፈጠረ እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ዓለምን /ፍጥረቱን/ ለመፍጠር ምክንያት የሆነው መለኮታዊ ሥልጣኑ ብቻ ነው፤ የፍጥረታት ሁሉ አስገኝ እግዚአብሔር በመሆኑም የፍጥረታት ሁሉ ጌታና ባለቤት እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ዓለምን ፈጥሮ እንዲሁ አልተወውም፤ በመግቦቱ ይጠብቀዋል፤ ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ እግዚአብሔር ብቻ በመሆኑና በመለኮታዊ ሥልጣኑ መሳይ ተወዳዳሪ ስለሌለውም እግዚአብሔር አንድ አምላክ ይባላል። እግዚአብሔር ዓለሙን ሲፈጥር፣ ይሁን ብሎ በቃሉ፣ በመለኮታዊ ሥልጣኑና በከሃሊነቱ ፈጠረው እንጂ ፍጥረታትን ለማስገኘት ሌላ አፍአዊ ምክንያት አላስፈለገውም። እንደዚህ ያለ መለኮታዊ ሥልጣን በሰማይም በምድርም ስለሌለ፣ እግዚአብሔር ብቻ ፈጣሪ እንዲባል ያደርገዋል። «ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቊጥር የሚያወጣ እርሱ ነው። ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል። በኃይሉ ብዛትና በከሃሊነቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።» ይላል የእግዚአብሔር ቃል። ኢሳ ፵፥፳፮። በእግዚአብሔር ረቂቅ ሥልጣንና ከሃሊነት የተፈጠረ ፍጥረት ሁሉ ሥርዓት ተሠርቶለት፤ ወሰን ተበጅቶለት ይኖራል። ከተሠራለት ሥርዓት አይወጣም፤ ከተደነገገለት ወሰን አያልፍም። ለይኩን

ትምህርተ ሃይማኖት Read More »

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነው?

፩. ሥርዓት ቤተ ክርስቲያን  ምንድን ነው? ሥርዓት “ሠርዐ” ሠራ ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ደንብ፣ አሠራር፣ መርሐ ግብር ማለት ነው። ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ስንልም የቤተ ክርስቲያን ዕቅድ፣ የቤተ ክርስቲያን አሠራር መርሐ ግብር ወይንም ደንብ ማለታችን ነው። ሥርዓት የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት፦ ሥራን ወጥ በሆነ መልኩ ለመፈጸም ማንኛውንም ነገር ወጥና ዘላቂ በሆነ መልኩ ለመሥራት ከየት ተጀምሮ በየት በኩል ሄዶ በየት በኩል እንደሚጠናቀቅ ወጥ የሆነ የአሠራር ሥርዓት ይዘጋጅለታል። የአንድ ሥራ አሠራር በትክክል ካልተነደፈና አካሄዱ ካልተስተካከለ፤ ሥራው የተዘበራረቀ ይሆናል ፍጻሜውም አያምርም።ማኅበረ ምዕመናንም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደጻፈው የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ አንድ ዓይነት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያስፈልገናል። ብዙ ስንሆን አንድ ልቡና አንድ ሃሳብ የሚያደርገን ሥርዓት ነውና። /ኤፌ. ፬፥፫፤ የሐዋ. ፬፥፴፪፤ ሮሜ. ፲፭፥፮ የሃይማኖትን ምሥጢራት ለመጠበቅ ሥርዓት የሃይማኖት መገለጫ ነው። ጥምቀት፣ ቁርባን፣ ጾም፣ ጸሎት፣ ሥግደት፣ ወዘተ በማመን ብቻ የሚያበቁ ሳይሆን የአፈጻጸምና አተገባበር መንገድ /ሥርዓት/ ያስፈልጋቸዋል። የእነዚህ ሁሉ ዝርዝር አፈጻጸም በሥርዓት ውስጥ ይካተታል። ስለዚህ በአንዲት ርትዕትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እምነት ሥር ያሉ ሁሉ ያቺን አንዲት እምነት የሚገልጹት አንድ ዓይነት በሆነ ሥርዓት ነው። ሥርዓት በመሠረተ እምነት /ዶግማ/ የምናምናቸውን በተግባር የምንገልጽበትና ተግባራዊ የምናደርግበት መንገድ ስለሆነ ሥርዓቱ ሲሠራና ሲፈጸም ሃይማኖታዊ አንድምታና ነጸብራቅ ይኖረዋል። ፪. ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ማለት ሕንፃው፣ የክርስቲያኖች አንድነት /ጉባኤ/ እና የምዕመኑ ሰውነት በመሆኑ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የምንለውም በእነዚህ በሦስቱ ላይ የተሠራውን ሥርዓት ነው። አንዳንዶቻችን ቤተ ክርስቲያንን ከራሳችን አርቀን ሌላ አካል አድርገን ስለምንመለከት ሥርዓቱ እኛን የሚመለከት አይመስለንም። ሥርዓቱ ግን የተሠራው ለሦስቱም የቤተ ክርስቲያን ትርጓሜዎች መሆኑን ማወቅ ተገቢ ነው። ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንጩ ወይንም መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የቅዱሳን አባቶቻችን ጉባኤያት ውሳኔ /ሲኖዶስ/ እና አባቶቻችን ሊቃውንት በተለያዩ ጊዜ ያደረጓቸው ጉባኤያት ውሳኔዎች ናቸው። ሰንበትን ማክበር፣ በጻድቃን ስም አብያተ ክርስቲያናትን ማነጽ፣ የቁርባን ሥርዓት፣ የመሳሰሉት ከመጽሕፍ ቅዱስ የተገኙ ሥርዓቶች ናቸው። /ዘፍ. ፳፰፥፳-፳፪፤ ዘጸ. ፲፮፥፳፱፤ የሐዋ. ፩፥፲፪/።ወደ ቤተ ክርስቲያን የገባውንና የተቀደሰውን ንዋየ ቅድሳት እንደገና ወደውጭ አውጥቶ ለሥጋዊ ጥቅም ማዋል እንደማይገባ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፩ ረስጣ ፳፰/፣ ጥምቀት በፈሳሽ ውኃ መፈጸም እንዳለበት፣ ወንዶች ሴቶችን ሴቶች ደግሞ ወንዶችን ክርስትና እንዳያነሱ፣ ሥጋ ወደሙ ለመቀበል ፲፰ ሰዓት መጾም እንደሚገባ፣ ሥጋ ወደሙ በምድር ላይ እንዳይወድቅ /እንዳይነጥብ/፣ ያላመኑ ሰዎች ሥጋ ወደሙን መቀበል እንደሌለባቸው፣ ወዘተ ያሉት ደግሞ በሲኖዶስ /የቅዱሳን አባቶቻችን ጉባኤያት/ የተገኙ ሥርዓቶች ናቸው።ከእናቱ፣ ከእህቱ፣ ከአክስቱ ወይንም እንደዚህ ባለ ሁኔታ ከምትታሰብ ሴት ጋር ካልሆነ በቀር አንድ ኤጲስ ቆጶስ፣ አንድ ቄስ፣ አንድ ዲያቆን፣ ወይንም ሌላ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ከማንኛውም ሴት ጋር አብሮ እንዳይኖር፤ ስለ መናፍቃን ጥምቀት፣ ስለ ትንሣኤ በዓል አከባበር፣ ስለ ድንግልና ኑሮ፣ ወዘተ ደግሞ በተለያዩ ጉባኤያት አባቶቻችን ያስተላለፏቸው ውሳኔዎችና ቀኖናዎች የተገኙ ሥርዓቶች ናቸው። የቤተ ክርስቲያን አመሰራረትና የቅዳሴ አገልግሎት ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንጻር መቼም በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን እየሰፋች ከሀገር ቤት አልፋ በውጭ ሀገርም አብያተ ክርስቲያናት እየታነጹ ስለሆነና ሁላችንም የቻልን ዘወትር ቅዳሴ በሚቀደስባቸው ዕለታት፣ ያልቻልን ደግሞ በዕለተ ሰንበት ለቅዳሴ ወደ ቤተ ክርስቲያን ስለምንሄድ ስለ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን አመሠራረት፣ አሠራርና ቡራኬ፣ እንዲሁም ስለ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንጻር እንዴት መሆን እንዳለበት እንገነዘባለን። ለዚህም እንዲረዳን እንደሚከተለው እናያለን። ቤተ ክርስቲያን ሲሠራ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን መሠረተ ቃሉ ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል /ቤቴሰ ቤተጸሎት ትሰመይ/ የሚለው /ኢሳ. ፶፮፥፮-፯፤ ኤር. ፯፥፲፩፤ ማቴ. ፳፩፥፲፫፤ ማር.  ፲፩፥፲፯፤ ሉቃ. ፲፱፥፵፮፤ ዮሐ. ፪፥፲፮-፲፯/ ሲሆን ቤተ ክርስቲያን የዋዛ የፈዛዛ፣ የሳቅ የስላቅ፣ የጨዋታ፣ የመብል፣ የመጠጥ ቤት ሳትሆን፤ ምዕመናን ኃጢአት ቢሠሩ ሰለ ኃጢአታቸው የሚያዝኑባት የሚያለቅሱባት ንጹሕ የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ካህናት የሚያስተምሩባት፣ ምዕመናን የሚማሩባት የግል ጸሎት፣ የማኅበር ጸሎት የሚጸልዩባት፣ በኅብረት የሚያስቀድሱባት ሥጋ  ወደሙ የሚቀበሉባት፣ የኃጢአት ሥርየት የሚያገኙባት፣ ሕፃናት በአርባ ቀንና በሰማንያ ቀን በጥምቀተ ክርስትና አማካኝነት ከሥላሴ የጸጋ ልጅነት የሚቀበሉባት፣ ኢአማንያን የነበሩ በመምህራን ትምህርት አምነው ክርስቲያን የሚሆኑባት፣ ለክህነትም ሆነ ለአባልነት የዘር ሐረግ የማይቆጠርባት ዓለም አቀፋዊት የእግዚአብሔር ቤት ናት፡፡ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ስትመሠረት ጀምሮ ሥርዓት አላት። የምትመሠረተው ባንድ ግለሰብ ስም ሳይሆን በካህናትና በምዕመናን ጥያቄ በሀገረ ስብከቱ ኤጲስ ቆጶስ ፈቃድና ትእዛዝ ነው፤ ካለኤጲስ ቆጶስ ፈቃድ ከመጽሐፉ ትዕዛዝ ወጥቶ አንዱ ቢያቋቁም ወይም ቢሠራ ቤተ ክርስቲያን ናት ብለው ለዘለዓለሙ በዛች ቤተ ክርስቲያን አይቁረቡባት፤ እንደገበያ፣ እንደእንስሳት በረት ፈት ሆና ትኑር ይላል። /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፩-፫/። ቤተክርስቲያን ለመሥራት ፈቃድ ከተገኘ በኋላ ስለ አሠራሯ የሚከተለው ሥርዓት ተሠርቶላታል። ቤተ ክርስቲያኗ ስትሠራ ደጆችና መስኮቶች አውጡላት ዛፍ ቅረጹላት ሐረግ ሳቡላት እንደሚል በተቻለ መጠን ሊያስጌጧት ይገባል የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ናትና።  በሰማይ ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት እንዲያበሩ፣ ሰባቱ ሰማያት ብሩሃን እንዲሆኑ ቤተ ክርስቲያንም ብርህት ትሁን፤ ይልቁንም ክቡራት መጻሕፍት ሐዲሳት፣ የጳውሎስ መልእክታት፣ የሐዋርያት መልእክታት፣ ግብረ ሐዋርያት በሚነበቡበት ጊዜ የበራች ትሁን፣ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ ያለውም ይህንኑ ያመለክታል። /ማቴ. ፭፥፲፬/። ቅዱስ ወንጌል በሚነበብበት ጊዜ ግን ፈጽማ የበራች ትሁን፤ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ያለው ይሻል። /ዮሐ. ፱፥፭/። ቤተ ክርስቲያን ሲባረክ ቤተ ክርስቲያን ሕንፃዋ ተፈጽሞ በምትባረክበትና በምትቀደስበት ጊዜ ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር ሰባት ቀሳውስት አብረውት ሊኖሩ ይገባል፣ ታቦቱም በሚባረክበት እንደዚሁ ሊሆን ይገባል፣ ኤጲስ ቆጶሱ እግዚአብሔር ሰውን የሚያከብርበት ራሱን የሚያስመስልበት ነውና ደስ በሚያሰኝ በቅብዐ ቅዱስ በሜሮን ያክብራት ያትማት፣ ታቦቱንም በመቅደስ ውስጥ በመንበር ያስቀምጡባት ከታቦቱ ጋራ የዮሐንስን ወንጌል ያኑሩ ከደቀ መዛሙርቱም በጌታ ኢየሱስ አጠገብ የሚቀመጥ ጌታ የሚወደው ቅዱስ ዮሐንስን ነበርና። /ዮሐ. ፲፫፥፳፫/ ። ታቦቱም ሲቀረጽ ከላይ አልፋ፣ ቤጣ፣ የውጣ፣ ወኦ/ወዖ/ ይቀረጻል። ቀጥሎ እመቤታችንን፣ ከእመቤታችን ቀጥሎ ዮሐንስን፣ ቀጥሎ ቤተ ክርስቲያኑ የሚተከለው ታቦት መልአክም ቢሆን፣ ሰማዕትም ቢሆን፣ ጻድቅም ቢሆን ይቀረጻል። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ካልተሟሉ ታቦቱን ሊቀድሱበት አይገባም። ከቤተ ክርስቲያን የገባ ዕቃ የወርቅ፣ የብር፣ ፃሕል ጽዋእ እርፈ መስቀል ቢሆን ንዋየ ቅድሳት ነው ተብሎ አቡነ ዘበሰማያት ከተደገመበት በኋላ ከቤታቸው ወስደው በፃሕሉ ፈትፍተው ሊበሉበት በጽዋው ቀድተው ሊጠጡበት አይገባም። ደፍረው ቢያደርጉ ሥርዓት ማፍረስ ነውና ይህን ያደረገ ቢኖር በአንድ ሁለት ተቀጥቶ ንሰሐውን እሰኪፈጽም ከምዕመናን ይለይ። /ዳን. ፭፥፩-፴፩/። በቤተ ክርስቲያንም ኤጲስ ቆጶሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናትና ምዕመናን እንዴት መቆም እንዳለባቸው ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚከተለው ይገልጻል። ኤጲስ ቆጶሳት የቤተ ክርስቲያን አዛዚያን እንደመሆናቸው በታቦቱ ፊት ይቁሙ፣ ቀሳውስትም መምህራን እንደመሆናቸው ከኤጲስ ቆጶሳት ቀጥለው ይቁሙ፣ ሊቀ ዲያቆናትም ከኤጲስ ቆጶስ አጠገብ ይቁሙ፣ ዲያቆናትም አገልጋዮች እንደመሆናቸው ከቀሳውስት ቀጥለው ይቁሙ፣ ከዲያቆናት ቀጥለው ሕዝቡ ሁሉ ባንድ ቦታ ይቁሙ፣ የሚበቃ ቦታ ቢኖር ሕፃናት በአንድ ወገን ለብቻቸው ይቁሙ፣ የሚበቃ ቦታ ከሌለ ግን ከአባቶቻቸው ጋራ ተስገው ይቁሙ፣ እንደዚሁም ሴቶች ባንድ ወገን /ቦታ/ ለብቻቸው ይቁሙ፣ ቦታ ቢገኝ ሕፃናት ሴቶች ባንድ ወገን ለብቻቸው ይቁሙ፣ ቦታ ባይኖር ግን ሕፃናቱ በፊት እናቶች በኋላ ይቁሙ፣ ደናግላን ሴቶችና ባልቴቶች ግን ከሴቶች በላይ ይቀመጡ ። /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፪ ድስቅ ፲፪ ኒቅያ ፷፩/። ሥርዓተ ቅዳሴ በቅዳሴ ጊዜ ስለሚደረጉና ሰለማይደረጉ ነገሮች ደግሞ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚከተለው ያዝዛል፦ በቅዳሴ ጊዜ የሚስቅ ሰው ቅዱስ ባስልዮስ በጻፈው በ፸፪ኛው አንቀጽ ካህን ቢሆን የሚያቀብል ነውና ሥጋ ወደሙን ከተቀበለና ካቀበለ በኋላ ወጥቶ አንድ ሱባዔ ይቀጣ ይጹም ይስገድ፣ የሳቀው ሕዝባዊ ቢሆን ግን ሥጋ ወደሙን ሳይቀበል ያን ጊዜ ፈጥኖ ይውጣ ይላል። ምነው ፍርድ አበላለጠ ካህኑን ተቀብሎ ወጥቶ ይቀጣ አለ፤ ሕዝባዊውን ሳይቀበል ወጥቶ ይሂድ አለ ቢሉ ካህኑ የሚቆመው ከውስጥ ነው ሲስቅ የሚያየው የለም። ካህኑ በቅዳሴ ጊዜ ቅዳሴውን ጥሎ ወጥቶ ሲሄድ ባዩት ጊዜ ቄስ እገሌ አባ እገሌ በመሥዋዕቱ ምን አይተውበታል ብለው መሥዋዕቱን ሳይቀር ይጠራጠሩታል፤ ስለዚህ ነው። ምዕመኑ ግን

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነው? Read More »

ታሪካዊ ቦታዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የእምነት ማዕከል ብቻ ሳትሆን የምጣኔ ሀብታዊ፤ማህበራዊ፤ሥነ ጥበባዊ፤የሥልጣኔ እና የነገሥታት ገድሎች ዜና መዋዕሎች መረጃ ማዕከል ናት፡፡ለምሳሌ ያህል ፡-የአኩሱም፤ላሊበላ፤ደብረ ብርሃን ሥላሴ ፤ጣና ሀይቅ እና  የመሳሉትን ከብዙ በጥቂቱ መጥቀስ ይቻላል፡፡

በአዲስ አበባም ታሪካዊና አስደናቁ የሆኑ ታሪካዊ ቦታዎች በብዛት የገኛሉ ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉም ታሪካዊ ቤተመዛክርት ቢሆኑም ቤተመዘክር ሠርተው በቤተመዘክርነት ደረጃ ከሚያስጎበኙ ገዳማትና አድባራት መካከል፡-

ታሪካዊ ቦታዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን Read More »

Scroll to Top