በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

Admin

ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕላ ጸሎት አስመልክቶ ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕላ ጸሎት አስመልክቶ ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ‹‹ተማሕለሉ ወሰአሉ ኃበ አቡክሙ ሰማያዊ እስመ አብ ይሁበክሙ ኵሎ ዘሰአልክሙ…አባታችሁ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋልና ወደ ሰማይ አባታችሁ ለምኑ፣ ምሕላንም አውጁ›› ኢዩኤል 1፤14 ቅዱስ ያሬድበሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን፣ምሕላን በማወጅ ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ ወደሚችለው አምላካችን አግዚአብሔር ምልጃን ማቅረብ የሚያስፈልግ መሆኑን ከሀገራችን ሊቃውንት መካከል የመጀመሪያ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ከሰማያውያን ዐውደ ማህሌት ሰምቶ በቀሰመው ጣዕመ ዜማ አበክሮ ይነግረናል፡፡ በመሆኑም ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷልና በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በሁሉም የሀገራችን ክፍልና በሌሎችም አህጉራተ ዓለም የምትገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብላችሁ የምሕላ ጸሎት እንድታደርሱ፣ በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀር እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንድትይዙ፣ ቋሚ ሲኖዶስ በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ከአደራ ጋር ያሳስባል፡፡ ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትንና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ››ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም.አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕላ ጸሎት አስመልክቶ ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ Read More »

የአባ ገሪማ መልዕክት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሃገረ ስብከት ለምትገኙየመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ! እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ። የሰው ልጅ በኀጢአተኛዎች እጅ ዐልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው። (ሉቃ 24፡6-7) የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውሃ ፈሳሽ ሳይሆንአስቀድሞ በነቢያት የተነገረ በተለይም በዳዊት “እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ” (መዝ 77፡68) ተብሎ እንደሚነሣ በእርግጠኛነት የተነገረለት፤ በሆሴዕ ከሲኦል እጅ እታደጋቸዋለሁ ሞት ሆይቸነፈርህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ ማጥፋትህ ወዴት አለ? (ሆሴ 13፡14) ተብሎ ለአምስት ሺህ አምስትመቶ ዘመን እንደ መዥገር በሰው ልጅ ተጣብቆ የኖረውን የሞት ኃይል አድቅቆ በታላቅ ኃይልና ሥልጣንእንደሚነሣ ያለጥርጥር የተነገረና እውነት የሆነ ትንቢት ነበር። ዮናስ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በከርሰአንበሪ ማደሩ (ት ዮናስ 2፡1) ክርስቶስ በመቃብር ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት አድሮ በኃይልእንደሚነሣ በምሳሌ የተነገረና በሙሉ ተስፋ ሲጠበቅ የኖረ ትንሣኤ ነው። ትንቢቱን አውቆ ያናገረምሳሌውንም እንዲሁ አውቆ ያስመሰለ ጌታ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር በምድር ላይ ዞሮ ባስተማረበትወቅት ከመሞቱ አስቀድሞ ገና በገሊላ ሳለ “የሰው ልጅ በኀጢአተኛዎች እጅ ዐልፎ ሊሰጥና ሊሰቀልበሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው” (ሉቃ 24፡67፤ ማቴ. 12፡40) ተብሎ የተነገረው ትንቢትናየተመሰለው ምሣሌ እሙን ሊሆን መቅረቡን በአንደበቱ አበክሮ ለደቀ መዛሙርቱ ሲያሳስባቸውናሲያስታውሳቸው የነበረ የድል አድራጊነት ትንሣኤ ነው። በመሆኑም ዕለቲቱና ሰዐቲቱ በደረሰች ጊዜ በጥቂት ጥቅመኛ ነገረ ሰሪዎች ከውጭ በነ ሃናና ቀያፍ ከውስጥደግሞ በነ ይሁዳ አማካኝነት ለሞት ተላልፎ ተሰጠ። በዕለተ ሆሣዕና “ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት” ሲልየነበረው ሕዝብ ይሰቀል ይሰቀል እያለ እንዲጮኽ የሀሰት ወሬ በከተማው ሁሉ ተነዛ። ጲላጦስም ምንምየሰራው ወንጀል እንደሌለ እያወቀ ከሥልጣኑ እንዳይሻር በመስጋት የሕዝቡን ጩኸት ፈርቶ እንዲሞትፈረደበት። በአይሁድ ዘንድ እንደወንጀለኛ መቆጠሩና በነሱ እጅ መሞቱ ግን በነቢዩ በኢሳይያስ “ስለመተላለፋችን ቈሰለ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በርሱ ላይ ነበረ በርሱ ቊስል እኛተፈወስን” (ኢሳ 53፡5) ተብሎ የተጻፈው ይፈጸም ዘንድ ነው። ዓርብ በዘጠኝ ሰዐት ራሱን ዘንበል አድርጎነፍሱን በገዛ ፈቃዱ ሰጠ። ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። የሃናና ቀያፋ ሴራ ግን በመግደል ብቻ አላበቃም ትንሣኤውን ለመከልከል ካልሆነም እነሣለሁ ብሎየተናገረው እውነት ሆኖ ከተነሣ እኛ ተኝተን ሣለን ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሰርቀው ወሰዱ የሚለውንየተለመደ የሽብርና የሀሰት ወሬ ለመንዛት እንዲመቻችው መቃብሩን በወታደር አስጠበቁ። የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ! የኛ ጌታ ግን ሀሰተኞችንና የሀሰት አባቷ የሆነውን ዲያብሎስን ለማሳፈር፣ የሞትን ኃይል ባዶ ለማድረግናነቢያት ስለ ትንሣኤው አስረግጠው የተናገሩትንና እርሱም እንደሚነሣ ከሞቱ አስቀድሞ ስለራሱየተናገረው የትንሣኤውን እውነት ለዓለም ሁሉ ይገልጽ ዘንድ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይልበታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን መካከል ተለይቶ በክብር ተነሣ። መቃብሩም ባዶ ሆነ። እንኳን ደስአላችሁ። እንኳን ደስ አለን። ምንም እንኳን የመቃብሩ ጠባቂዎች ጥቂት መደለያ (እጅ መንሻ ተቀብለው ደቀ መዛሙርቱ ሰርቀውወሰዱት ብለው እንዲያወሩ ተደርገው ወሬው ከተማውን ሁሉ ቢያጥለቀልቀውም በኩረ ትንሣኤ ከርስቶስግን ከተነሣ በኋላ ትንሣኤው እሙን መሆኑን ለነ ማርያም መግደላዊት በመታየት፣ ለሐዋርያት በተለያየጊዜ ለኬፋም ለዐሥራ ሁለቱም፣ ከዐምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች ባንድ ጊዜ በመታየት የአይሁድንሴራ መና እንዳስቀረ ሐዋርያው ጳውሎስ በስፋት ጽፎልናል። (ቆሮ 15፡58)። በተዘጋ ቤት ገብቶ ሰላምለናንተ ይሁን ብሎ ሰላምን ሰብኮላቸዋል። ምትሀት አለመሆኑን ለመግለጽ የተቸነከረበትን እጁን እግሩን፣በጦር የተወጋውን ጎኑን አሣይቷቸዋል። በመቃብሩ ቦታ የተገኙ መላእከትም ሕያውን ከሙታን መካከልስለ ምን ትፈልጋላችሁ ተነሥቷል እንጂ በዚህ የለም (ሉቃ 24፡5) ሲሉ የትንሣኤውን ኃይል ገልጸዋል።የትንሣኤው ችቦ በሐዋርያት እየተቀጣጠለ ለዓለም ሁሉ በማብራቱ የአይሁድ ሀሰት ተጋለጠ። የክርስቶስትንሣኤ ለኛ ትንሣኤም በኩር በመሆኑ እስከምጻት ሲነገርና ሲታመን ይኖራል። እኛም ዛሬ የሐዋርያትንጆሮ ጆሮ አድርገን ዐይኖቻቸውንም ዐይኖቻችን አድርገን ትንሣኤውን በደስታ እያከበርን እንገኛለን። በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ። ውድ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ ይህ በዓል መንፈሳዊ በዓል እንደመሆኑ ከአልባሌ ነግር ርቀን አብዝቶ ከመብላትና ከመጠጣት ተቆጥበንምንም የሌላችውን፣ አባት እናት የሞቱባቸውን፣ በተለያዩ ደዌ ተይዘው በየሆስፒታሉ፣ በየጸበል ቦታውናበየቤታቸው ሆነው በዓሉን እንደኛ ማክበር የተሳናቸውን፣ በሕግ ጥላ ሥር ሆነው በማረሚያ ቤት ያሉትንበመጎብኘትና ካለን ላይ ከፍለን በማብላት ልናከብረው ይገባል፡፡ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም። አባ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ

የአባ ገሪማ መልዕክት Read More »

መልአከ ብርሃን ቀሲስ ዳንኤል ነቢዩ የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤቶችና የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ክፍል ኃላፊ

መልአከ ብርሃን ቀሲስ ዳንኤል ነቢዩ የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤቶችና የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ክፍል ኃላፊ

መልአከ ብርሃን ቀሲስ ዳንኤል ነቢዩ የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤቶችና የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ክፍል ኃላፊ Read More »

መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ የሀገረ ስብከቱ የመንፈሳዊ ትምህርትና የካህናት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ

መልአከ ሰላም አባ ዮሐንስ ምህረቱ

መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ የሀገረ ስብከቱ የመንፈሳዊ ትምህርትና የካህናት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ Read More »

Scroll to Top