በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

Admin

የሀገረ  ስብከቱ  የገንዘብ  ቤት  ሥራና  ኃላፊነት

    የሀገረ  ስብከቱ  የገንዘብ  ቤት  ሥራና  ኃላፊነት ፩.ገንዘብን በህጋዊ ደረሰኝ (ካርኒ) ይቀበላል፡፡ ፪.ለማንኛውም የገንዘብ ወጪ ህጋዊ ትዕዛዝ ሲደርሰው ብቻ ክፍያ ይፈጽማል፡፡ ፫.ገቢና ወጪውን በተለየ በተዘጋጀ የገቢና የወጪ መዛግብት ላይ ይመዘግባል እንዲሁም ሂሳቡን በጥንቃቄ መዝግቦ ይይዛል፡፡ ፬.በየወሩ መጨረሻ በጠቅላላ የገባውና የወጣውን ገንዘብ ልክ ከወጪ ቀሪውን ከሂሳብ ክፍሉ መዛግባት ጋር ያመሳክራል፡፡

የሀገረ  ስብከቱ  የገንዘብ  ቤት  ሥራና  ኃላፊነት Read More »

የሀገረ ስብከቱ የቁጥጥር ክፍል ሥራና ኀላፊነት

የሀገረ ስብከቱ የቁጥጥር ክፍል ሥራና ኀላፊነት ፩.ልዩ ልዩ ገቢና ወጪ የተደረገባቸውን ካርኒዎችና ሰነዶች ህጋዊ መሆናቸውን ይመረምራል እንዲሁም ገንዘቡ በትክክል ተቆጥሮ በባንክ መቀመጡን ያረጋግጣል ፡፡ ፪.የሒሳቡ አያያዝ አጠባበቅ ትክክል መሆኑንና አለመሆኑን በዝርዝር መዝግቦ በየሦስት ወር  ለአስተዳደር ጉባኤ ሪፖርት ያቀርባል፡፡ ፫. ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር የሀገረ ስብከቱን ንብረት በየዓመቱ ኦዲት ያደርጋል፡፡ ፬. በሀገረ ስብከቱ ለዓመት ከተመደበው በጀት በላይ ወጪ እንዳይሆን ይቆጣጠራል፡፡

የሀገረ ስብከቱ የቁጥጥር ክፍል ሥራና ኀላፊነት Read More »

የሀገረ ስብከቱ የመንፈሳዊ ትምህርት ክፍል ሥራና ኀላፊነት

የሀገረ ስብከቱ የመንፈሳዊ ትምህርት ክፍል ሥራና ኀላፊነት ፩.በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መንፈሳዊና ዘመናዊ ት/ቤት እንዲቋቋም ያደርጋል እንዲሁም ለተማሪዎችም የሚያስፈልገውን በጀት እንዲመደብ የሚመለከታቸውን ሁሉ ያስተባብራል፡፡ ፪.የትምህርት መስጫ ቦታዎች አመቺ እንዲሆኑና መምህራን ጉባኤያቸውን ሳይፈቱ እንዲያስተምሩ ያደርጋል፡፡ ፫. ቤተ መጻሕፍት እንዲያቋቁሙና ካህናት ዲያቆናት የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ተገኝተው እንዲያነቡ አስፈላጊው ሁሉ እንዲፈጸም ያደርጋል፡፡ ፬. ህጻናት በሥነ ምግባርና በሃይማኖት ተኮትኩተው እንዲያድጉ ያደርጋል፡፡ ፭. የመማር የማስተማር ሂደት በተሳለጠ መልኩ በቅርበት ሆኖ ይቆጣጠራል፡፡

የሀገረ ስብከቱ የመንፈሳዊ ትምህርት ክፍል ሥራና ኀላፊነት Read More »

የሀገረ  ስብከቱ  የንብረት የንዋየ ቅድሳትና የቅርሳ ቅርስ ክፍል ሥራና ኀላፊነት

የሀገረ  ስብከቱ  የንብረት የንዋየ ቅድሳትና የቅርሳ ቅርስ ክፍል ሥራና ኀላፊነት ፩.የሀገረ ስብከቱ አላቂና ቋሚ ዕቃዎችን የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን በየአይነታቸው ለይቶ መዝግቦ ይይዛል ፡፡ ወጪ ሆነው ለሥራ የሚሰጡትን ዕቃዎችና ንብረቶች በህጋዊ ሰነድ ያስረክባል፣ወጪ የተደረጉ ንብረቶችን ሥራ ላይ መዋላቸውንና መጠበቃቸውን ይቆጣጠራል ፣የሚመለሱትንም መርምሮ ይረከባል፡፡ ፪. ጥገና የሚያስፈልጋቸውን የሀገረ ስብከቱ ንብረቶችን  በሰዓቱ እንዲጠገኑ ያደርጋል፡፡ ፫. በየዓመቱ የንብረት ቆጠራ ያደርጋል፡፡

የሀገረ  ስብከቱ  የንብረት የንዋየ ቅድሳትና የቅርሳ ቅርስ ክፍል ሥራና ኀላፊነት Read More »

የሀገረ ስብከቱ  የካህናት አገልግሎት ክፍል ሥራና ኀላፊነት

የሀገረ ስብከቱ  የካህናት አገልግሎት ክፍል ሥራና ኀላፊነት ፩. በሀገረ ስብከቱ ሥር ባሉ አድባራትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መንፈሳዊ አገልግሎቶች ትክክለኛውን ሥነ ሥርዓት ይዘው መካሄዳቸውን ይከታታላል ይቆጣጠራል፡፡ ፪. ካህናት የንሰሐ ልጆቻቸን ለመጠበቅ እንዲችሉ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመቀናጀት  በትምህርተ ወንጌል እንዲሰለጥኑ ያደርጋል ፡፡ ፫.ለክህነት የሚያበቃውን ሙያ ያወቀና ግብረ ገብነቱና መንፈሳዊ ዝንባሌው በካህናትና በምዕመናን የተመሰከረለትን እንዲሁም ወንጌልን ማስተማር የሚችል እንደ የማዕረጋቱ የዲቁናና የቅስና ማዕረግ እንዲቀበል ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ያቀርባል፡፡ ፬. ክህነታቸው ያልታወቀና ካህን መነኩሴ ነኝ በሚሉ ላይ ቁጥጥር ያደርጋል፡፡

የሀገረ ስብከቱ  የካህናት አገልግሎት ክፍል ሥራና ኀላፊነት Read More »

የሀገረ  ስብከቱ  የህግ አገልግሎት ክፍል ሥራና ኀላፊነት

የሀገረ  ስብከቱ  የህግ አገልግሎት ክፍል ሥራና ኀላፊነት ፩. ከበላይ አካል የሚወጡ ህጎች ደንቦች ድንጋጌዎች ውሳኔዎችና መመሪያዎች ለካህናትና ለምዕመናን እንዲያውቁትና እንዲያጠኑት ያደርጋል፡፡ ፪. የሀገረ ስብከቱን ህግና ሥርዓት ተከትሎ በክብረ በዓል ቀን ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ከመንግስትና ህዝባዊ ድርጅቶ ጋር በመተባበር የበዓሉን ሥነ ሥርዓት ያስከብራል፡፡ ፫. ማንኛውንም መንፈሳዊና ሥጋዊ ህግ ነክ ጉዳዮችን ይከታተላል ለሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ የምክር አገልግሎት ይሰጣል እንዲሁም ሀገረ ስብከቱን ወክሎ በማናቸውም የህግ አካል ዘንድ ይከራከራል ፡፡

የሀገረ  ስብከቱ  የህግ አገልግሎት ክፍል ሥራና ኀላፊነት Read More »

የሀገረ ስብከቱ የአኃዛዊ መረጃ (ስታትስቲክስ) ክፍል ሥራና ኀላፊነት

የሀገረ ስብከቱ የአኃዛዊ መረጃ (ስታትስቲክስ) ክፍል ሥራና ኀላፊነት  ፩. በሀገረ ስብከቱ ያሉ የምዕመናን መረጃ፣መዝገበ ልደትና ጥምቀት፣መዝገበ ህያዋን፣መዝገበ ሙታን እንዲሰራባቸው ያደርጋል፡፡ ፪.በሀገረ ስብከቱ ያሉ አድባራትና አጥቢያ አብያተክርስቲያናት ማንኛውንም መረጃ ተመዝግቦ እንዲያዝ ያደርጋል፡፡ ፫. በየዓመቱ መጨረሻ በህይወት ያሉቱን የሞቱን፣ አዳዲስ የተጠመቁትን እና ወደ ሌላ ቤተ እምነት የፈለሱትን  መረጃን ፣ለአስተዳደር ጉባኤ ያቀርባል፡፡

የሀገረ ስብከቱ የአኃዛዊ መረጃ (ስታትስቲክስ) ክፍል ሥራና ኀላፊነት Read More »

የሰንበት ት/ቤት ታሪክ

የሰንበት ት/ቤት – ታሪክ በኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተክርስተያን ታሪክ የወጣቶች ሰንበት ት/ቤት ማቋቋም የተጀመረው ከ1936 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡ የኸውም ከብዙ ዓመታት በፊት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሃይማኖት ትምህርት ይከታተሉ የነበሩ ወጣቶች “የሥላሴ ማህበር” ተብሎ የሚጠራ አንድ ማህበር መሠረቱ፣ ይህ ማህበር ለወንዶች ብቻ የተቋቋመ ነበር ይሁንና ከጥቂት ዓመታት በኋላ የካቴድራሉ አስተዳደር ወጣት ልጃገረዶችም የራሳቸውን ማህበር መመሥረት እንዳለባቸው አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘው ለጸሎትና ለአምልኮ ወደ ካቴድራሉ የሚመጡ ልጃገረዶችን ሰብስቦ እነርሱም የራሳቸውን ማህበር እንዲያቋቁሙ አበረታታቸው በመሆኑም “ማህበረ ክርስቶስ” በሚል መጠሪያ የሚታወቅ ማህበር መሠረቱ፡፡ የእነዚህ ማህበር አባላት የተሻለ የሃይማኖትና የሥነ ምግባር ትምህርት ማግኘት ሲጀምሩ የቤተክርስቲያንን ትምህርት እየተማሩና እያወቁ በመምጣታቸው በተለይም ልጃገረዶች የቤተክርስቲያንን ዜማ በማጥናት በቤ/ክ ውስጥ ከቁርባን በኋላ መዘመር ጀመሩ፡፡ ይህም እንደ አዲስ ክስተት ታይቶ በካህናቱና በምእመናኑ ዘንድ የሚወደድ ሆኖ ተገኘ የእነዚህ ማህበራት ዓላማቸውም የሚከተሉት ነበሩ፡- ከላይ እንደተጠቀሰው በቅዳሴ ጊዜ የወጣት ልጃገረዶች ተሰጥዎ መቀበልና ከቅዳሴም በኋላ ልዩ ልዩ ጣዕመ ዜማዎችን ማስማታቸው እንደ አዲስ ነገር በመታየቱ ተግባሩ በሌሎችም አብያተ ክርስቲያናት ወጣቶች ቀጥሎ ተስፋፍቷል፡፡ የምስካየ ኅዙናን ቤተክርስቲያን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በሚሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት የተፈሪ መኮንን እና የእቴጌ መነን ት/ቤት ተማሪዎችን በብዛት መሳብ በመቻሉ በየሳምንቱ እሑድ ተማሪዎች በብዛት ወደ ቤ/ክ እየመጡ በመንፈሳዊ አገልግሎት ተሳታፊ ከሆኑ በኋላ ብዙዎች በቤ/ክ እንዳንድ ሥራዎች በፈቃደኝነት መሳተፍ ጀመሩ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተማሪዎችና በገዳሙ መካከል አንድነትን መፍጠር የሚችልና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የሚሰጥበት ሰንበት ት/ቤት እንዲቋቋም ወጣቶቹ በመጠየቃቸው  “ተምሮ ማሰተማር” የተባለው ታዋቂው ሰንበት ት/ቤት በ1939 ዓ.ም ተመሠረተ፡፡ የተምሮ ማሰተማር ማህበር ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ለማህበሩ አባላትና ለህብረተሰቡ አስፈላጊ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፡፡ ከዚያ በመቀጠል በ1942 ዓ.ም የተቋቋመው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሲሆን የወንጌል መልዕክተኞችና የእሑድ ት/ቤት ማህበር ተመሠረተ፣ በዚሁ ጊዜም ነበር የአሥመራው ማህበረ ሐዋርያት ፍሬ ሃይማኖት ማህበር የተቋቋመው፡፡ ቀጥሎም ወደ ታዕካ ነገስት በዓታ ለማርያምና መንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል፣ ወደ ገነተ ጽጌ መናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስና ወደ ሌሎች የአዲስ አበባ ታላላቅ ገዳማትና አድባራት ተስፋፋ ከዚያም አልፎ ወደ ዋና ዋና (በጊዜው አጠራር ጠቅላይ ግዛት) ከተሞችና ታላላቅ አውራጃዎች የተቋቋሙበት የደብሩን መለያ ስም በመያዝ በልዩ ልዩ የቅጽል ስም የወጣቶች መንፈሳዊያን ማህበራት እየተባሉ እስከ 1974 ዓ.ም ድረስ ተጓዙ፡፡ የአሁኑ ሰንበት ት/ቤት የወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር የቀድሞ አመሠራረቱ ከላይ እንደተጠቀሰው በወጣቶችና ልጃገረዶች ግላዊ ተነሳሽነት ፤በብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአንዳንድ ዓላማው በገባቸው የአድባራት አለቆችና ሰባክያነ ወንጌል በጎ ፈቃድና ድጋፍ ነበር፡፡  በተለይም በ1936 ዓ.ም በወቅቱ የመንበረ ጸባኦት ቅዱስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳዳሪ የመጀመሪው ሊቀሥልጣናት ሆነው የተሾሙት ሊቀ ሥልናናት አባ መልዕክቱ በኋላም ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የኢትዮጵያ ፓትርያሪክ ተብለው የተሸሙት ማህበሩ እንዲመሰረት ከፍተኛ ጥረት ከማድረጋቸውም በላይ ማህበሩ በአገልግሎቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ትልቅ ስራ ሰርተዋል፡፡ ይሁንና እነዚህ ማህበራት በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ቀስ በቀስ በሁሉም ገዳማትና አድባራት ተቋቁሞ ስለነበር ከቤተ ክህነቱ ጋር የሚያገኛኘው መስመር የግድ ስለነበር በጊዜው በስብከተ ወንጌልና ማስታወቂያ መምሪያ ስር የወጣቶች መንፈሳዊ ማህበራት አንድነት ማእከላዊ ጽ/ቤት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተቋቁሞለት እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ ይህ ማዕካላዊ ጽ/ቤት እስከ 1965 ዓ.ም ድረስ በመጠኑም ቢሆን የወጣቶች መንፈሳዊያን ማህበራትን ሲያስተባብር ቆይቷል፡፡ ከ1965 ዓ.ም ጀምሮ ግን ወደ ወጣቶች ጉዳይ መምሪያነት አደገ፡፡ ይህ በዚህ እንዳለም በ1966 ዓ.ም  በመላው አዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የተቋቋሙት የወጣቶች መንፈሳውያን ማህበራት የለውጡን ሂደት ተጠቅመው በራሳቸው ውሳኔ አጠቃላይ ጉባኤን መሰረቱ ይህ የወጣቶች መንፈሳውን ማህበራት አጠቃላይ ጉባኤ በዚያ ክፉ የደርግ ዘመን በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ እጅግ ብዙ ቁም ነገሮችን ለቤተ ክርስቲያኒቷ በቆረጥነት አበርክቷል መምሪያውንም ያጠናከረው አጠቃላይ ጉባኤው ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ ጉባኤውና በመምሪያው የተጠናከረ ትብብር የአሁኑ ሰንበት ት/ቤት እንደቀድሞው የወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር እየተባለ በ1970 ዓ.ም ተሻሽሎ በወጣው ቃለ ዓዋዲ የቤተ ክርስቲያኒቱ ህጋዊ አካልነቱ ተረጋግጦ ሙሉ በሙሉ ዐውቅና አገኘ እስከ 1974 ዓ.ም ድረስ ስያሜው ቀጥሎ በመላ ኢትዮጵያ በስፋት ተስፋፋ፡፡ ይሁን እንጂ ከ1974 ዓ.ም ካቲት ወር ጀምሮ የደርግ  መንግስት “ከአኢወማ” ጋር በስም ይሞካሻል፣ ይመሳሰላል ብሎ በውስጥ በደረገው ተጽዕኖ ምክንያት ሁሉም የወጣቶች መንፈሳውያን ማህበራት በቅዱሳት ቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ብልህነት የተመላው ውሳኔ ነበሩ ስማቸው ተለውጦ ይኸውና ከዕለቱ በመነሳት የሰንበት ት/ቤት ተብሎ እስከ አሁን ሊደርስ ችሏል፡፡ መምሪያውም የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የተባለው ከዚያን ወዲህ ጀምሮ ነው፡፡

የሰንበት ት/ቤት ታሪክ Read More »

የምዕመናን አገልግሎት

የምእመናን አገልግሎት ምእመናን በሃይማኖት የጸኑ፣ በምግባር የቀኑ ይሆኑ ዘንድ በሞራል ሊገነቡ ይገባል፡፡ እንደዚህ ሲባል ግን  በእውነት ላይ የተመሰረተ ምስጋና፤ ሞራላቸውን ይገነባል ለማለት እንጂ ባልሰሩት ይመስገኑ ማለት አይሆንም፡፡ የማይገባ ምስጋና ስድብ ነው፡፡ የሚገባ ምስጋና ግን ትልቅ ሽልማት ነው፡፡ ስለሆነም ቅዱስ ጳውሎስ በሚገባ ተጠቅሞታል፡፡ ‹‹ርቱዕ ናእኩቶ ለእግዚአብሔር በኵሉ በእንቲአክሙ አኃዊነ በከመ ይደልዎ፤ እስመ ዐብየት ሃይማኖትክሙ ወፈድፈደት ተፋቅሮትክሙ ምስለ ኵሉ ቢጽክሙ ከመንሕነኒ ንትመካሕ ብክሙ በቤተክርስቲያኑ ለእግዚአብሔር በእንተ ሃይማኖትክሙ፣ ወትዕግሥትክሙ፣ በሕማምክሙ፣ ወምንዳቤክሙ፣ ዘትትኤገሡ፡፡ ወንድሞቻችን ስለ እናንተ ዘወትር እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባል፤ እንደሚገባው ሃይማኖታችሁ ሰፍታለችና፤ ከባልንጀራችሁ ሁሉ ጋር ፍቅራችሁም በዝታለች፡፡ እኛም በእናንተ እንመካ ዘንድ በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለ ሃይማኖታችሁ፣ ስለ ትዕግስታችሁ፣ ታግሳችሁ፣ በምትቀበሉት መከራ፡፡›› 2ኛ፡ተሰ፡1፡3-4፡፡ ‹‹ወንድሞቻችን እኛስ ዘወትር እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባል፤ እግዚአብሔር ስለወደዳችሁ ስለ እናንተ የሕይወት ባለቤት እግዚአብሔር ይቅር ብሎ መርጦአችኋልና፤ በመንፈስ በመቀደስና በእውነተኛ ሃይማኖት፡፡›› 2ኛ፡ ተሰ፡1347፡፡ ‹‹ሙኑ ተስፋነ ወፍሥሐነ ወአክሊለ ምክሕነ አኮኑ አንትሙ በቅድመ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በምጽአቱ፡፡ እስመ አንትሙ ክብርነ ወፍሥሐነ፡፡ አለኝታችን ማነው? ደስታችንስ? የመመኪያችን ዘውድስ እናንተ አደደላችሁምን? በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት በሚመጣበት ጊዜ፣ ክብራችን ደስታችን እናንተ ናችሁና፡፡››1ኛ፡ተሰ፡2፡19-20፡፡ ወዘተ… ሲሆኑ ይህን መነሻ በማድረግ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አገልግሎትን በተመለከተ ለሁሉም ገዳማትና አድባራት በሕጉና በደንቡ እንዲያገለግሉ መመሪያ በማስተላለፍ የአድባራትና ገዳማት ካህናት የአጥቢያው ምእመናን በአቅራቢያቸው ዘመኑ የሚፈቅደውን ሙሉ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ብዙ ሥራዎች ተሰርተዋል በመሰራትመ ላይ ይገኛሉ፡፡

የምዕመናን አገልግሎት Read More »

የካህናት አገልግሎት፣ ኃላፊነትና ተግባር

የካህናት አገልግሎት፣ ኃላፊነትና ተግባር የካህናት ኃላፊነትና ተግባር ቀድሞ መጻህፍተ ህግጋት ሳይጻፉ በብሉይ ሆነ በሐዲስ ኪዳን ከዘመነ አበው ጀምሮ እንደየዘመኑ አፈጻጸሙ ይለያይ እንጂ ሰፊ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በመሠረቱ ክህነት፣ ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ፣ ማስተማር፣ በአጠቃላይ የእግዚአብሔር እንደራሴ መሆን ሕዝብን ለማገልግልና ለመጠበቅ፣ ሕዝባውያን ወይም ምዕመናን ሊፈጽሙዋቸው የማይችሉትን አገልግሎቶች ለማበርከት ከእግዚአብሔር ለተጠሩና ለተመረጡ ሰዎች የሚሰጥ መንፈሳዊ ኃይል እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ክህነት ከምንጩ ከመሰረቱና ከመገኛው፣ ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ሆኖ ሰማያዊና ምድራዊ መግቦትን ያካተተ ሐላፊነት ነው፡፡ ግብረ 6፡1-7፡፡ 20፡28፡፡ 1ኛ ጢሞ/4፡16፡፡ ጴጥ፡ 5፡2-4፡፡ ክህነት ለዚህ ታላቅ ሐለፊነት ለተዘጋጀና ለተጠራ ሰው የተሰጠ ሥልጣን ከሆነ፣ ካህንም የእግዚአብሔርን ሕዝብ ይጠብቅና ያገለግል ዘንድ ከእግዚአብሔር የተጠራ እንጂ በሰው ልዩ ፍላጎትና ኃይል የሚሾም አለመሆኑን ማወቅና መረዳት ለአገልግሎቱም መዘጋጀት ግዴታ ነው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ወአንትሙኒ ጽንዑ ከመእብን መንፈሳዊ ወኩኑ ታቦተ መንፈሳዌ ለክህነት ቅድስት ወንጽሕት ከመታቅርቡ ወታዕርጉ መሥዋዕተ መንፈሳዌ ዘይሰጠወክሙ እግዚአብሔር በእደዊሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ፡፡›› ….ማለት፣ ‹‹እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መስዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ፡፡›› ያለው፣ 1ኛ ጴጥ፣ 2፡5-6፡፡ እንግዲህ ረዘም ያለ ታሪክ ያለውን ክህነታዊ የትምህርት አገልግሎት፣ በዘመነ አበው፣ በዘመነ ኦሪትና በዘመነ ሐዲስ በሚል ርእስ ለይተን አጠር ባለ መልኩ እንደሚከተው ለመመልከት እንሞክራለን፡፡ 1.    የክህነት አገልግሎት በዘመነ አበውና በዘመነ ኦሪት፡፡ በዘመነ አበው የክህነት አገልግሎት በቤተሰብ ሐላፊ አማካይንነት ይከናወን ነበር ማለትም አንድ ሰው የቤተሰብ ሐላፊ በመሆኑ ብቻ መስዋትን የማቅረብ ሥልጣን ሲኖረው በዘመነ ኦሪት ግን የክህነት አገልግሎት፣ በተለዩና ለዚህ አገልግሎት በተጠሩ ሰዎች ብቻ የሚከናወን ሆነ፡፡ ከኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 14 ላይ እንደምንረዳው፣ የሰላሙ ንጉሥ መልከ ጼዴቅ ስለ አሻሿሙ ምሥጢርና በዘመኑ ይፈጸም ስለነበረው የክህናት አገልግሎት ሥርዓት በመጽሐፍ ቅዱስ በስፋት የተጻፈ መረጃ ባይኖርም፣ የልዑል እግዚአብሔር ካህን፣ የሰያሜ ካህናት የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ እንደቀረበ ግን እንረዳለን፡፡ ዘፍ፡ 14፡17-20፣ መዝ፡109/110፡4፡፡፣ ዕብ፡5፡6፡6፡20፡7፡1-22፡፡ መልከ ጼዴቅ ለአብርሃም የሰጠውን በረከት ስንመለከት ዛሬ ካህናት ለምዕመናን ለሕፃናት ለእናቶች የሚሰጡት በረከት ምን መሆን እንዳለበት እንድናስብ ይጋብዘናል፣ ከጦርነት ማግስት በረከት ያገኘው አብርሃምን ስናስብ ዛሬ ሰላም አጥተው ዕድገታቸው በሚቀጭ ሕፃናት፣ ደህንነታቸው ለማይጠብቅ እናቶች የምናቀርበው በረከት ምን እንደሚሆን እንድናጤን ያስገድደናል፡፡ከላይ በተገለጸው መልኩ ያገለግል በነበረው በሥርዓተ አበው ምትክ ሥርዓተ ኦሪት በተሰራ ጊዜም ለክህነት አገልግሎት የሚመረጡ፣ ነውረ ሥራ የሌለባቸው (ያልተገኘባቸው) የአሮን ልጆችና የልጅ ልጆች ሆኑ፡፡ ዘሌ፡21፡16-24፡፡ የካህናተ ኦሪት፣ መደበኛ ሐላፊነት ተግባር፣ መስዋዕትን ማቅረብ ሆኖ፣ የበዓላት አከባበር ሥርዓትን መጠበቅና ማስጠበቅ፣ መጻሕፍተ ኦሪትንና ነቢያትን ማንበብና መተርጎም ቋሚ ሥራቸው ነበር፡፡ካህናተ ኦሪት፣ የሕዝቡን ንጽሕናና ጤንነት ማስጠበቅም ከአገልግሎታቸው ዘርፍ አንዱ ነበር፡፡1ኛ. ዘዳ፣ 28፡1-5፡፡            2ኛ. ዘኁ፡15፡40፡፡3ኛ. ዘኁ፡18፡5             4ኛ. ዕዝ፡2፡63፡፡5ኛ. 2ኛ፡ዜና፡መ፡15፡3፡፡        6ኛ. ኤር፡18፡18፡፡7ኛ. ሕዝ፣ 7፡26፡፡            8ኛ. ሚክ፡3፡11፡፡ ካህናተ ኦሪት ሊቃነ ካህናትና ሌዋውያን በሚሉ ዐበይት መደቦች የሚከፈሉ ሲሆን፣ የሥራ መደባቸውም እንደየምድባቸው የሚከፋፈል ይሆናል፡፡ካህናተ ኦሪት ሓላፊነታቸውና ተግባራቸው ከሁሉ የከበደ እንደሆነ ቢታወቅም ከጊዜ በኋላ ግን ዓላማቸውን ለውጠው በሰማያዊ ክብር ፋንታ ምድራዊ ክብርን ሽተው (ታይታ) ለተርእዮ ብቻ የሚንቀሳቀሱ ሆነው ተገኝተው ስለነበር መድሐኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ዓለም በይቅርታ በጎበኘበት ወቅት የጸሐፍትንና የፈሪሣውያንን ከንቱነትና ግብዝነት ተመልክቶ በስምንት ዓበይት ነጥቦች መስሎ ወቅሶአቸዋል፡፡ ማቴ 23፡13-36፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ክህነታዊ ግዴታቸውን ወይንም የኖላዊነት ሓላፊነታቸውን ባልተወጡ ፈሪሣውያን ተግሣፁን በዚህ ሥእላዊ መግለጫ አሳየ እንጂ፣ ቀደም ሲል ሥርዓተ ኖሎት ሲጓደል፣ ሕዝቡ በመንፈሳዊም ሆነ በማኅበራዊ ሕይወቱ ሲበድል እግዚአብሔር በተለያዩ ወቅቶች ካህናቱን ገሥጾአል፡፡ በነቢዩ በሕዝቅኤል የተነገረውን ቃል ስንመለከት ‹‹የማሠማርያዬን በጎች ለሚያጠፋና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው ይላል እግዚአብሔር፡፡ ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለማይጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፡፡ በጎቼን በትናችኋል አባራችኋልም፣ አልጎበኛችኋቸውምም፡፡ እነሆ የሥራችሁን ክፋት እጎበኝባችኋለሁ ይላል እግዚአብሔር፡፡›› የሚል ሆኖ ስናገኘው፣ በሕዝቡና በካህናቱ መካከል ያለውን የመግቦትና የኖላዊነት ሥራ ሲጓድል የእግዚአብሔር ተግሣጽ ምን ያህል እንደሚበረታ እንረዳለን፡፡ ሕዝ፡34፡1-16፡፡ የካህናት ሓላፊነትና ተግባር በአዲስ ኪዳን ከዚህ በላይ የተመለትነው የካህናተ ኦሪትን የክህነታዊ አገልግሎት አፈጻጸምን በአጭሩ ነበረ፡፡ ቀጥሎም የካህናተ ወንጌልን ጥሪ፣ የሥራ ሓላፊነትንና ተግባርን እንመለከታለን፡፡የካህናተ ሐዲስ ሥልጣን እንደ ካህናተ ኦሪት በዘር የሚወረስ፣ በይገባኛል የሚገኝ መብት ሳይሆን አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ከማይሰፈር ብዕሉ ለሰው ልጅ በሰጠው ጸጋ መሰረት ጥሪውን ተቀብለው ለሐዋርያዊ አገልግሎት ለሚሰለፉ ሰዎች የተሰጠና የሚሰጥ፣ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ እናውቃለን እናምናለን፡፡ ሢመተ ክህነት ከሊቀ ካህናት ከኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የተሰጠ ጸጋና ሰማያዊ በረከት በመሆኑ፣ ድኅነተ ነፍስን ማስገኘት ካልተቻለው ከካህናተ ኦሪት የተለየ፣ ለካህናተ ኦሪት ያልተሰጠ ኃይልና ሥልጣን የተገኘበት ሰማያዊ ሐብት ነው፡፡ ካህን፣ ጠባቂ፣ መምህር፣ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም የእግዚአብሔር አገልጋይ፣ የሕዝብ መሪ አስተማሪ ኖላዊ መንፈሳዊ አባት ሆኖ የዓለምን ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመጥራት የተሰለፈ የእግዚአብሔር ሕግ አስፈጻሚ በመሆኑ ሓላፊነቱ ነፍስን የመጠበቅ ሓላፊነት ብቻ አይሆንም፣ በደዌ ሥጋ የሚፈርሰውን የእግዚአብሔርን ሕንፃ መጠበቅም ሓላፊነቱ ነው፡፡ካህናት፣ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኳችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀመዛሙርት አድርጓቸው እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፡፡ የሚለውን አምላካዊ አዋጅ ለመፈጸም ሥልጣን የተሰጣቸው የእግዚአብሔርን መንጋ ለመጠበቅ እንዲሰለፉ፣ ደዌ ሥጋንና ደዌ ነፍስን እንዲፈውሱ፣ ሙታነ ሥጋንና ሙታነ ነፍስን እንዲያስነሱ፣ አጋንንትን እንዲገዙ ኃይልና ሥልጣን የተሰጣቸው የክርስቶስ እንደራሴዎች፣ ይሕይወት ጎዳና መሪዎችና የመንግስተ እግዚአብሔር በረኞች ናቸው፡፡ ማቴ፡19፡19፡፡ 18፡18፡፡ 28፡19፡፡ ዛሬ የዚህ ሥልጣን በረከት ባለቤቶች የሆኑ፣ በዚህ ጸጋ የበለጸጉ ካህናት መንፈሳዊ ኃይላቸውን በሰው ሕይወት ላይ በሰለጠኑት ደዌያት ላይ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፣ ዛሬ በሰው ልጅ ድኅነት ላይ ማነቆ ሆኖ የሚታየው የኋላ ቀርነት ቀንበር ፈቺዎች እንዲሆኑ በተስፋ የሚጠበቁ የእግዚአብሔር መንጋዎች (የምእመናን) በረከት ናቸው፡፡ መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ዓሥራ ሁለቱን ሐዋርያት ወደ እርሱ ጠርቶ በአጋንንት ሁሉ ላይ፣ ደዌንም ይፈውሱ ዘንድ ኃይልንና ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡ የእግዚአብሔርንም መንግስት እንዲሰብኩና ደዌዎችንም እንዲፈውሱ ላካቸው፡፡ ተብሎ መጻፉን እናውቃለንና ነው፡፡ ሉቃ፡ 9፡1-2፡፡ ካህናተ እግዚአብሔር ሰይፈ መንፈስ ቅዱስን አንግበው ቃለ ወንጌልን ተጫምተው ዲያብሎስንና ሠራዊቱን ሊወጉ የተሰለፉ የእግዚአብሔር ሠራዊት ናቸው፡፡ ካህናት፣ በእግዚአብሔር ጥበብ የሠለጠኑ ሆነው ደዌ ሥጋንና ደዌ ነፍስን የሚፈውሱ የምዕመናን ሐኪሞች ናቸው፡፡  ወደ ዓለም የሚላኩት ካህናት ዓላማቸውን ለማስፈጸም ክህነታዊ አገልግሎታቸውን የተሟላ እንዲሆን ለማድረግ ጥበብና የውሃትን ገንዘብ ማድረግ እንዳለባቸው ተነግሮአቸዋል፡፡ ‹‹ወናሁ አነ እፌንወክሙ ከመአባግዕ ማእከለ ተኩላት፣ ኩኑ እንከ ጠቢባነ ከመአርዌ ምድር ወየዋሃነ ከመርግብ ተብሎ ተጽፏል፡፡ መቴ፡10፡1፡፡ ሉቃ 10፡3፡፡ ይህን ታላቅና ከባድ ኃላፊነት የተሸከመ ካህን፣ በተኩላዎች መካከል ገብቶ፣ በጥበብና በየዋህነት እየተመራ፣ ካህን የወገኖቹን ችግር ችግሩ ኃዘናቸውንም  ኃዘኑ አድርጎ ሲያዝኑ አዝኖ ሲያለቅሱ አልቅሶ ሲደሰቱ ተደስቶ በማጽናናቱ፣ በምክሩና በትምህርቱ የሻከረውን ልብ የሚያለዝብ ያዘነውንም የሚያጽናና የሥነ ልቡና መምህር ወይም ሳይኮሌጂስት ነው፡፡ ሮሜ፡12፡15፡፡ መዝ፡34፡13-14፡፡ካህን መምህረ ሕግ ወሥርዓት ከመሆኑም ሌላ ለሚጠብቀው መንጋ ራሱን አሳልፎ የሰጠ በመሆኑም የሚያስበውና የሚጨነቀው ስለሰው ልጅ መንፈሳዊ ሕይወት ብቻ አይደለም፡፡ ዘእንበለ ሥጋ ኢትቀውም ነፍስ መባሉ ለእንዲያው አይደለምና ሰው ነፍስና ሥጋውን ማኖር የሚስችለውን ጥረት ልማት እንዲያደርግ ሥጋዊና መንፈሳዊ መግባባቱን ለማረጋገጥ ማስተማር ሓላፊነቱና ግዴታው ነው፡፡ ዘፍ፡2፡15፡፡ 3፡19፡፡ ኩፉ፡4፡9፡፡ 5፡7፡፡ ማቴ፡5፡13-16፡፡ የእውነተኛ ዕረና መመዘኛ ነጥቦች የክህነት አገልግሎት ሰማያዊና ምድራዊ መግቦት ከሆነ ለዚህ ከባድ ኃላፊነት ብቁ ሆኖ ቸር ጠባቂና ታማኝ የክርስቶስ አምባሳደር እኔ ነኝ ብሎ በልበ ሙሉነት የሚቀርቡ ሰው እሱ ማነው ቢባል ሁኔታው ከባድ ሆኖ ሊታይ ይችላል፡፡ ነገር ግን ቅ/ጳውሎስ በዚህ ሐዋርያዊ አገልግሎት ለመሰለፍ መመኘት ከሁሉ የበለጠ መልካሙን ሥራ መመኘት መሆኑን ስለ አንቀጸ ካህናት በጻፈው መልእክቱ፣ ‹‹እሙን ነገር ዘይፈቅድ ይሠየም ጳጳስ ሠናየ ግብረ ፈተወ፡፡›› ካለ በኋላ ለክህነት አገልግሎት የሚሰለፍ ሰው፡-

የካህናት አገልግሎት፣ ኃላፊነትና ተግባር Read More »

Scroll to Top