በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የሀገረ ስብከቱ  የካህናት አገልግሎት ክፍል ሥራና ኀላፊነት

፩. በሀገረ ስብከቱ ሥር ባሉ አድባራትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መንፈሳዊ አገልግሎቶች ትክክለኛውን ሥነ ሥርዓት ይዘው መካሄዳቸውን ይከታታላል ይቆጣጠራል፡፡

፪. ካህናት የንሰሐ ልጆቻቸን ለመጠበቅ እንዲችሉ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመቀናጀት  በትምህርተ ወንጌል እንዲሰለጥኑ ያደርጋል ፡፡

፫.ለክህነት የሚያበቃውን ሙያ ያወቀና ግብረ ገብነቱና መንፈሳዊ ዝንባሌው በካህናትና በምዕመናን የተመሰከረለትን እንዲሁም ወንጌልን ማስተማር የሚችል እንደ የማዕረጋቱ የዲቁናና የቅስና ማዕረግ እንዲቀበል ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ያቀርባል፡፡

፬. ክህነታቸው ያልታወቀና ካህን መነኩሴ ነኝ በሚሉ ላይ ቁጥጥር ያደርጋል፡፡

Scroll to Top
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት