በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ለሚገኙ፦
#ለቡርጂ ወረዳ ቤተክህነት
#ለኮሬ ወረዳ ቤተክህነት
#ለቡሌና ረጴ ወረዳ ቤተክህነት
#ለይርጋጨፌ ወረዳ ቤተክህነት ለሚገኙ ገጠር አብያተክርስቲያናት የሚሆን የተለያዩ ንዋየ ቅድሳት መቀደሻ አልባሳት፣ ዣንጥላ፣ ዕጣን፣ ጧፍ ፣ቅዱሳት መጽሐፍት፣ መጎናጸፊያ ፣መጋረጃ፣ ጽና፣ መስቀል ፣ጽዋ ለአራቱም ወረዳ ቤተክህነት ኃላፊዎች ከሀገረ ስብከቱ የሰበካ ጉባኤና የሰ/ት/ቤት ማደራጃ ክፍል ኃላፊ ከመልአከ ብርሃን ዳንኤል ነቢዩ ተረክበዋል።
የየወረዳ ኃላፊዎችም የተረከቡትን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አብያተክርስቲያናት የሚያደርሱ ይሆናል።
በቀጣይም በሀገረ ስብከቱ ለሚገኙ ገጠር አብያተክርስቲያናት የሚያስፈልጉ ንዋየ ቅድሳትን ለማሟላት ድጋፋችሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንጠይቃለን ።


