የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ከዚህ በታች ባለው ክፍ የሥራ መደብ መስፈርቱን የሚያሟላ ሠራተኛ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል!
ኤክቱስ ሰኔ 18/2018 ዓ.ም
የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ከዚህ በታች ባለው ክፍ የሥራ መደብ መስፈርቱን የሚያሟላ ሠራተኛ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል! Read More »
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት
ኤክቱስ ሰኔ 17/2018 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ የሕግ ክፍል ዐቢይ ኮሚቴ አማካኝነት የተዘጋጀ የሕግ ሥልጠና ተሰጥቷል። በዚሁ መርሃግብር ላይ የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች፣ የዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት ሠራተኞች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎችና መላው የአስተዳደር አካላት ተሳትፈዋል። ሥልጠናውን የሰጡት የዲላ ዩኒቨርሲቲ የነጻ ሕግ አገልግሎት ማዕከል አስተባባሪ ወይዘሪት የምስራች ያለው ሲሆኑ በጠዋቱ ክፍለ-ጊዜ ስለ ሕግ ምንነት፣ ስለ ሕጋዊ ሰውነት፣ መብቶችና ስለ ንብረት ሕግ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከሰዓት በኋላ በነበረው መርሃ-ግብር ደግሞ ስለ ግዴታዎች፣ ውሎች እንዲሁም ስለ አሠሪና ሠራተኛ ሕጎች ትኩረት ያደረገ ትምህርት ቀርቧል። ሥልጠናው በአጠቃላይ ተቋማዊ አሠራርን በሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ለመምራትና መብትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ የፍትሐብሔር እና የወንጀል ሕግ መሠረታዊ ነጥቦችን ያካተተ ነበር። በሥልጠናው ወቅት ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከአሰልጣኟ በተጨማሪ የሕግ ክፍል ዐቢይ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዲያቆን መስፍን ተስፋዬ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተውባቸዋል። በማጠቃለያው ላይ ብፁዕነታቸው በተሰጠው ሥልጠና የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው “የቤተ ክርስቲያን ሀብቷ ልጆቿ ናቸው” በማለት በበጎ ፈቃዳቸው አገልግሎት ለሰጡት ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል። አያይዘውም እንዲህ ያሉ ሥልጠናዎች ሁሉም አካል ስለ ሕግ በትክክል እንዲያውቅና ቤተ ክርስቲያንም መብቷን በሕግ አግባብ እንዴት ማስጠበቅ እንዳለባት ለማስገንዘብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ጠቁመው መርሐ-ግብሩን በጸሎት ፈጽመዋል።
በሀገረ ስብከቱ የሕግ ክፍል ዐቢይ ኮሚቴ ብፁዕነታቸው በተገኙበት ሥልጠና ተሰጠ! Read More »
ኤክቱስ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በተካሄደው ዐቢይ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ምዕመናን የምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ተካፋይ እንዲሆኑ ለማስቻል የንሥሐ አባት የሌላቸውን ምዕመናን የመመዝገብ ሥራ ተከናውኗል። ይህ ልዩ መርሃ ግብር የጉባኤውን ዋና ዓላማ መነሻ በማድረግ ምዕመናን በንሥሐ ሕይወት ታንጸው ወደ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ እንዲቀርቡ በተግባር ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በዚሁ መሠረት በጉባኤው በርካታ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን የንሥሐ አባት እንዲኖራቸው እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን ይህም የሕዝቡን መንፈሳዊ ሕይወት ለመለወጥና ምዕመናንን የምሥጢራት ተካፋይ ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት ይበልጥ እንደሚያጠናክር ተገልጿል።
በጉባኤው ለምዕመናን የንሥሐ አባት የማስያዝ መርሃግብር ተከናወነ! Read More »
ኤክቱስ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም የታላቁን መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን ዓመታዊ በዓል በማስመልከት በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ዐቢይ መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቋል። ይህ ታላቅ ጉባኤ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት የተዘጋጀ መሆኑ ነው። የዚህ መንፈሳዊ ጉባኤ ዋና ዓላማ ምዕመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጡ በውጪው ቅጥር ግቢ ብቻ ተመላልሰው የሚመለሱ ሳይሆን በቀጥታ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሥጢራት ተካፋይ መሆን የሚችሉበትን ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑ ተገልጿል። በዚህም መሠረት የሦስቱም ቀናት የትምህርት ትኩረት ምዕመናን በጊዜ መጥተው እንዲያስቀድሱ፣ ንሥሐ እንዲገቡና ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን እንዲቀበሉ (እንዲቆርቡ) ለማነቃቃትና ለማስተማር ያለመ ነበር። በጉባኤው ላይ የተገኙት ከአዲስ አበባ ድረስ የተጋበዙት መምህራን ቀሲስ ደረጀ እና መምህር ብርሃኑ አድማስ ይህንን የጉባኤውን ዓላማ መነሻ በማድረግ የምዕመናንን መንፈሳዊ ሕይወት የሚፈትሹ አስተማሪ ትምህርቶችን በጥልቀት አስተምረዋል። እንዲሁም በዝማሬ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ እና ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን አገልግለዋል። ብፁዕነታቸው በምዕመኑ መንፈሳዊ መነቃቃት እጅግ መርካታቸውን የገለጹ ሲሆን አክለውም ለጉባኤው መሳካት በተለያየ መልኩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ምዕመናንም በንሥሐ ታጥበው የቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ተካፋይ መሆን እንዳለባቸው ባሳሰቡበት አባታዊ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የጉባኤው ፍጻሜ ሆኗል።
በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀው ዐቢይ መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ Read More »
ኤክቱስ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለተዘጋጀው ጉባኤ ከአዲስ አበባ ለመጡት መምህራንና ዘማርያን ስለ ሀገረ ስብከቱ አሁናዊ ሁኔታ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የሀገረ ስብከቱ ታሪካዊ ዳራ፣ አጠቃላይ መዋቅራዊ መረጃዎች እንዲሁም በአሁኑ ወቅት እየተሠሩ ያሉ መንፈሳዊና ተቋማዊ ሥራዎች ለእንግዶቹ ቀርበዋል። ብፁዕነታቸው ባቀረቡት ገለጻ ሀገረ ስብከቱ በአገልግሎት እንቅስቃሴው ላይ እያጋጠሙት ያሉትን ወቅታዊ ተግዳሮቶች በጥናት ላይ ተመስርተው ያመለከቱ ሲሆን፤ ከችግሮቹ ጎን ለጎንም መፍትሔ ሊሆኑ የሚችሉ ስልታዊ የሃሳብ አማራጮችንና የቀጣይ የተግባር አቅጣጫዎችን በፕረዘንቴሽኑ አካተው አብራርተዋል። በተያያዘ ተጋባዥ እንግዶቹ በሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት በሥራ ላይ የሚገኘውን የዶሮ ልማት ፕሮጀክት፣ አዲሱን የመንበረ ጵጵስና ሕንፃ ግንባታ ሂደት እንዲሁም በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እየተከናወኑ ያሉ የግብርና የልማት ሥራዎችን ተገኝተው ጎብኝተዋል። የተደረገው የመስክ ምልከታ የሀገረ ስብከቱን ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ በተግባር ያሳየ እንደነበር ተመልክቷል።
ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ገለጻ አቀረቡ! Read More »
ኤክቱስ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም “የእግዚአብሔር ድምጽ ከተማይቱን ይጠራታል”ሚክ ፮፥፱
ኤክቱስ ሰኔ 13/2018 ዓ.ም በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በኮሬ ዞን ወረዳ ቤተ ክህነት በደርባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በትናንትናው በቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል ዕለት ሃያ ሁለት አዳዲስ አማንያን በጥምቀት የሥላሴ ልጅነትን አግኝተዋል። መረጃው የደብሩ ሕዝብ ግንኙነት ነው።
ሃያ ሁለት አዳዲስ አማንያን በጥምቀት የሥላሴን ልጅነት አገኙ! Read More »
ኤክቱስ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ተከበረ። በዕለቱ በደብሩ መሠረተ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያም ለዕለቱ የሚስማማ ያሬዳዊ ዝማሬ ያቀረቡ ሲሆን በደብሩ ለሚሠሩ የልማት ሥራዎች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር በሀገረ ስብከቱ የሰበካ ጉባኤና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ክፍል ኃላፊ በመልአከ ብርሃን ዳንኤል ነቢዩ ተከናውኗል። የዕለቱን ትምህርት ብፁዕነታቸው እጅግ በጥልቀት ያስተማሩ ሲሆን ታሪኩን በሰፊው በመዘርዘር ምዕመናን ራሳቸውን እንዴት ከፈተና መጠበቅ እንዳለባቸው እና መንፈሳዊነታቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው አስተምረዋል። በተጨማሪም ብፁዕነታቸው ምዕመናን በቅዳሴ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲሄዱ በአጽንዖት አሳስበው በጸሎት ፈጽመዋል። በመርሃግብሩ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ፣ የሀገረ የመንፈሳዊ ትምህርትና የካህናት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ፣ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጠበብት መሠረት ይልማ፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ካህናትና ምዕመናን ተገኝተዋል።
የሰኔ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል ብፁዕነታቸው በተገኙበት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተከበረ! Read More »
ኤክቱስ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዛሬው ዕለት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለቅስና የሚያበቃ መንፈሳዊ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ ለ፭ ዲያቆናት የቅስና ማዕረግ ሰጥተዋል። በዛሬው ዕለት ማዕረገ ቅስናን ከተቀበሉት ፭ ዲያቆናት መካከል ፬ቱ በአንዲዳ የአዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት መንፈሳዊ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው። ብፁዕነታቸው በመጨረሻም የተቀበሉትን አደራ በሥነ-ምግባር ጠብቀው እንዲኖሩ እና ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ አባታዊ ምክራቸውን ለግሰዋል።
ብፁዕ አቡነ ገሪማ ለ፭ ዲያቆናት ማዕረገ ቅስና ሰጡ! Read More »