በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ስብከት

<<ምልእዎንኬ ለእላ መሣብክት ማየ -ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው >>  ዮሐ 2:7

➠ በወርኃ ጥር ከሚከበሩ ዐበይት በዓላት መካከል ጥር 12 ቀን  የሚከበረው  የገሊላ ክፍል በሆነችው በቃና ሰርግ ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገው ታላቅ ተአምር አንዱ ነው ።<<ነገርን ከስሩ ውኃን ከጥሩ >> እንዲሉ  አበው ነገሩም እንዳህ ነበር  ። አካል ከህልውና ተገልጾለት  የሥላሴን አንድነት ሦስትነት በስፋትና በጥልቀት የተናገረው ነባቤ መለኮት በመባል የሚታወቀው  ባለ ራእዩ ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ   <<በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ >>  በማለት ሙሉ ታሪኩን ይጽፋል  ።➠ ይህም ሰርግ የተደረገው የካቲት 23 /30 ዓ ም ሲሆን የውኃን በዓል ከውኃ በዓል ( የጥምቀትን በዓል የውኃው  ወደ ጠጅነት መለወጥ በዓል ) ጋር እንዲከብር አባቶቻችን ስለ ወሰኑልን  የጥምቀት ማግስት ጥር 12  በቃና ዘገሊላ ኢየሱስ ክርስቶስ በእመቤታችን አማላጅነት ያደረገው ታላቅ ተአምር በደማቅ ሁኔታ ይከበራል  ። አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዕዳ ደብዳቤያችንን ይደመስስልን  ዘንድ ( ቆላ 2:4) ጥር  11 ቀን ዕለተ እሑድ  በእደ ዮሐንስ በማየ ዮርዳኖስ ተጠምቆ ( ማቴ 3:17) ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ ልጅነቱን አስመስክሮ ሳይውል ሳያድር ገዳመ ቆሮንቶስ ሄደ ( ማቴ 4:1) ። በገዳመ ቆሮንቶስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ በሦስቱ አርእስተ ኃጣውእ የመጣውን ሰይጣን ድል ነስቶ የካቲት 20 ቀን በዕለተ ቀዳም ከገዳመ ቆሮንቶስ ወጥቶ ቅዳሜ ለእሑድ  ገሊላ ገብቶ አድሯል ።   የገሊላ ክፍል በሆነችው በቃና  የተደረገውም ሰርግ ጌታ ከገዳም ከወጣ በሦስተኛው ቀን ማለትም  ማክሰኞ   ነበር ።  የዚህ ሰርግ ባለቤት ዶኪማስ ሲሆን በሰርጉ ላይ ይታደሙ ዘንድ ከወንድ እስከ ሴት ከመምህር እስከ ደቀ መዝሙር ያልጠራው አካል ከቶ አልነበረም ። ➠ የሚደንቅ ሰርግ ! ታዋቂ ስዎች ከላይ  ምስኪኖች  ከታች ፤ መምህሩ ከቤት ውጥ ደቀ መዛሙርቱ ከቤት ውጭ ያልታደሙበት ፤ሁሉም አብረው ያከበሩት ሰርግ ነበር ። በአምላካችን የተባረከ ፣  እመቤታችንና ሐዋርያት የተገኙበት ሰርግ ! የሙሽራው የዶኪማስ ልብ እንዴ በደስታ ይመላ ይሆን  ? ትዳሩስ እንዴት ያምር  ? ምንኛ  መመረጥ ምንኛስ መታደል ነው ! የጋብቻን ቅዱስነትና ክቡርነት የተማርነውም በሰርግ ቤት ተገኝቶ   ሰርግን ከባረከው  የቤተ ክርስቲያን ሙሽራዋ ከሆነላት ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።ብዙዎች  ግን ጋብቻን የሚረዱበትና የሚኖሩበት ሕይወት የተስተካከለ ባለመሆኑ መሰላቸትና መናቆር የበዛበት ይሆናል ። በየፍርድ ቤቱ ሳይቀር በስፋት ያለውም ጉዳይ የፍች ጉዳይ ነው ።➠ ### ጋብቻ በባልና ሚስት ፈቃድ ብቻ የሚመሠረት አይደለም ፤ በእግዘብሔር ፈቃድ ጭምር እንጂ ። ጋብቻ ስንፈልግ የምንገባበት ሳንፈልግ ደግሞ የምንወጣበትም አይደለሞ ፤ እስከ መጨረሻ የምንኖርበት እንጂ ። ጋብቻ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የሚፈጸም ፣ ሁለቱም አካላት አንድ የሚሆኑበት ምሥጢርም ነው  ( ሜቴ  19:6) ።   ጋብቻ የተበረከ ስለሆነ  የተበረኩ ልጆችም የሚገኙበት ነው (ዕብ 13:4)  ። የሚገርመው  ሰዎች ራሳቸው ያልፈለጉትን ግን በልጆቻቸው እንዲፈጸሙ የሚፈልጓቸው ሁለት ነገሮች አሉ ።1, የሰርጋቸው ቀን ከቤተ ክርስቲያን ጋር ሳይተዋወቁ የክርስትና  ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጡ ሰዎች ሲሆኑ2, ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ በሆነ ጋብቻ የተጋቡ ሰዎች ልጆቻቸው ሥርዓት ባለመያዛቸው የሚያዝኑ ሰዎች ናቸው ።  ### ልጆች ሥርዓትን ከማን  ይማሩ  ? ማንንስ ይከተሉ ? ተጠያቂውስ ማን ነው ?አሁን በአለንበት ዘመን  በዓለም ላይ ሥርዓት አልባነት ከተስፋፋባቸው መንገዶች መካከል የጋብቻ ሥርዓት መረሳቱና ክቡር በሆነው ጋብቻ የሚወለዱ ልጆች አለመኖራቸው አንዱ ይመስለኛል ። ➠ የእመቤታችን አማለጅነት የሰርጉም ታዳሚዎች ወደ መጡበት ሳይመለሱ ለሰርጉ ይበቃል ተብሎ የታሰበው የወይን ጠጅ ድንገት አለቀ፣ አገልጋዮች የሚያደርጉት አጥተው በጭንቀት ተውጠው ሰማይ ምድሩን ማየት ጀመሩ ፣የአገልጋዮች ፊት ጠቆረ ፣ አንገታቸውንም ደፉ ፤  ማጣት  ክፉ ነውና ያውም በሰርግ ቀን ሰው በተሰበሰበበት  !ነገር ግን ይህን ጭንቀታቸውን ያየችው እመቤታችን ማንም ሳይነግራት  << የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም >>  ስትል ነበር  ወደ ልጇ  የማማለድ ስራዋን ያቀረበችው ።  አምላካችንም የእመቤታችንን ምልጃ ከሰማ በኋላ << አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም >>  አላት ፤ ማለትም አንቺ ያልሽኝን ላለማድረግ ምን ጠብ  አለኝ አደርግልሻለሁ ማለት ነው ። ይህም ሊታወቅ << የሚላችሁን አድርጉ >> ነበር ያለችው ፤ ምልጃዋን እንደ ተቀበላት ታውቅ ነበርና ። የእናት ልመና ፊት አያስመልስ አንገት አያስቀልስ ነውና ነገሩ ።➠  ስለ ምልጃዋ ስለ ርኅራኄዋ  <<ፈጣን ደመና >>  ( ኢሳ 19:1) ብሎ ነቢዩ ኢሳይያስ የገለጣት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዛሬም  ቢሆን በአማላጅነቷ  ትረዳናለች ታግዘናለች ። እኛም  << ወበእንተዝ ንስአል ኀቤሃ  ኵሎ ጊዜ ከመ ታስተሥሪ በእንቲኣነ ኀበ ፍቁር ወለዳ ሔርት ይእቲ በኀበ ኵሎሙ ቅዱሳን – ስለዚህ ሁልጊዜ ወደ እርሷ እንለምን ከተወደደ ልጇ ዘንድ ስለእኛ ይቅር ታስብለን  (ታማልደን) ዘንድ በቅዱሳን ዘንድ ቸር ናት >> እያልን እንደ ቅዱስ ኤፍሬም እንማጸናታለን ።➠ ሌላው አሳብ << ጊዜዬ ገና ነው >> የሚለው ነው ።  ይህም ማለት ብዙ ትርጓሜ ቢኖረውም ዋናው አሳብ ግን ምሳሌው  ወይን የሆነለት ክቡር ደሙን  የዓለምን ኃጢአት ለማስተስረይ በመስቀል የሚያፈስበት ጊዜው  ዕለተ ዐርብ ገና ነው ማለቱ ነበር ። ይህውም አልቀረ ጊዜው ዕለተ ዐርብ ሲደር የዓለም ኃጢአት የሚሰረይበትን ክቡር ደሙን እንኩ ጠጡ ብሎ ሰጠን (ማቴ 26:28) ። በዚህ ክቡር ደም የዓለም ኃጢአት ተወገደ (ዮሐ 1:29) ፣ አነጻን ቀደሰን  << በውኂዘ ደሙ ቅዱስ አንጽሖሙ ለመሀይምናን ወለሕዝብ ንጹሓን >> እንዳለ  ቅዱስ ኤፍሬም  የዶኪማስን ሰርግ የፋሲካ ፤ የወይን ጠጁንም የክቡር ደሙ ምሳሌ አደረገው ።ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ብሉ ጠጡ የሚል ለጋስ ያለ እርሱ ማን አለ ?➠ ይህን ድንቅና ረቂቅ የሆነ ቃል በመናገር ዕለተ ሞቱን ከአስተማረ በኋላ የአገልጋዮቹን ጉድለት ይመላ ዘንድ በሰርግ ቤት የተገኘው አምላካችን  << ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው>> ብሎ አዘዘ ። የእመቤታችንን ምልጃ መቀበሉን የምንረዳውም ጋኖች በውኃ እንዲመሉ በማዘዙና ውኃውን ወደ ጠጅነት  በመለወጡ ነው፤ እመቤታችንም  የሚላችሁን አድርጉ ነበርና ያለችው ።ባዶ የነበሩት  ስድስቱም የድንጋይ ጋኖች በውኃ ከተሞሉ በኋላ በአምላካዊ ሥራው በእመቤታችን አማላጅነት ውኃውን ወደ ወይን ጠጅነት ለወጠው ፤ እግዚአብሔር ሲል ሁሉ ይለወጣልና ። ➠ የሰው ልጅ ጉድለት የሚሞላው በምን  ይሆን  ?የእኛስ ሕይወት የሚለወጠው መቼ ነው ? ከላይ ነጭ ነጠላ ለብሰን እንመላለሳለን ውስጣችን ግን በብዙ ነገሮች ጠቁሯል ፣ ሰብከን ስንጨርስ ቃለ ሕይወት ያሰማልን እንባላለን ሕይወት ግን ከሁላችንም ጠፍቷል ፣ ዘምረን ስንጨርስ ከጣዕሙ ብዛት የተነሣ አጥንትን የሚያለመልም የመላእክትን ዝማሬ ያሰማልን እንላለን  ነገር ግን የለመለመና ጣዕም ያለው ሕይወት የለንም ። ➠ በአምላካዊ ትእዛዝ የተለወጠው የወይን ጠጅ ቀድሞ ከነበረው  እጅጉን ጣፈጭ  መሆኑን የቀመሰው አሳዳሪውም   ሙሽራውን  ጠርቶ   << ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል ከሰከሩም በኋላ መናኛውን ፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል >> በማለት በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የተለወጠውን ወይን  ማድነቅ ጀመረ  ። በእርግጥ እግዚአብሔር ያደረገው ነገር በሙሉ ከሁሉ በላይ ነውና   መርምረንና ተናግረን ስለማንጨርሰው  << ናርምም እስመ ኢንክል ፈጽሞ ጥንቁቀ ነጊረ በእንተ ዕበዩ  >>   እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም ሁሉን ቻይ መሆኑን  አድንቀን ዝም እንላለን ። ➠ ይህም ሰርግ የሰርግ ሥርዓት ብቻ የተፈጸመበት አልነበረም ውኃውን ከውኃነት ወደ ወይን ጠጅነት በመለወጡ ምሥጢረ ሥጋዌን በሥራ ገልጦ ያሳየበት ዕለትም ጭምር  እንጂ ፤ በኋላም በኬልቄዶን ጉባኤ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ  የልዮናውያንን አስተምህሮ ማለትም ሁለት ባሕርይ የሚለውን ትምህርት ሲቃወም መልስ የሰጠበት ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነበር ።<< ወደ ሰርግ ቤት የተጠራ  ውኃውን ጠጅ ያደረገ  ማን ነው  ?>>  ብሎ ጠየቀ ። ሥጋ ካላችሁ የሥጋ ወደ ሠርግ ቤት መጠራት አያስደንቅም ፤ ብቻውንም ሥጋ ውኃውን ጠጅ ማድረግ አይችልም ፣ መለኮት ካላችሁ ውኃውን ጠጅ መድረግ ቢችልም ወደ ሰርግ ቤት መጠራት ግን አይችልም ብሎ እረቶበታል

<>  ዮሐ 2:7 Read More »

“ወነሥኡ ካህናት  ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር ወሖሩ ቅድመ ሕዝብ” (የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዘው በሕዝቡ ፊት አለፉ) ኢያ 3፥6‎

‎ታቦቱ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን  ታቦት በመባል ይጠራል፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ታቦት አሁን ካለው የተለየ ነው፡፡ የብሉይ ኪዳኑን ታቦት የሚሸከሙት አራት ሰዎች ሆነው ነው፡፡ የአሁኑ ታቦት ምሥዋዕ በመባል ይጠራል፡፡ ለሥጋ ወደሙ መፈተቻነት የሚያገለግል ነው፡፡‎‎እስራኤላውያን ከግብፅ ወጥተው ወደ አገራቸው በሚያደርጉት ጉዞ የዮርዳኖስ ወንዝ ፊታቸው ተደንቅሮ አላሳልፍ አላቸው፡፡ ታቦቱ በአንድ ሰው ብቻ ሊሸከሙት የማይቻል ነበርና ታቦቱን  የተሸከሙ ካህናት እግር ጫማ በዮርዳኖስ ወንዝ ውኃ ውስጥ ሲቆም እንደ ክምር ሆኖ ቆመ፡፡  ለእነርሱ ሲል ውኃው ሲቆም ሲያዩ ምንኛ ይደነቁ! ቆሞ አሳለፋቸው ፡፡ ሕዝቡ ተሻግረው ሲያበቁ ካህናቱ ከውኃው ወጥተው እግራቸው ደረቅ መሬት መርገጥ ሲጀምር ውኃው መልሶ መፍሰስ ጀመረ፡፡ ውኃው ቆሞ እንዳሳለፋቸው ፣ ከወጡ በኋላ ደግሞ መፍሰስ ሲጀምር መልሰው እንዴት ነው የማይደነቁት ትላላችሁ?‎‎ከወንዙም ውስጥ ያወጡአቸውን 12 ድንጋዮች ካህናቱ እግራቸው ቆሞ በነበረበት በወንዙ ውስጥም እንዲሁም ከወንዙ ውጭም ተተከሉ፡፡ የሚመጣ ትውልድ እግዚእብሔር ያደረገውን ተአምር እንዲሰማ ታስቦ ነው፡፡‎‎እግዚእብሔር ከግብፅ ያወጣውን ሕዝብ ሊያውም እጅግ ባለመታዘዝ ያስቸገሩትን በእንዲህ መልኩ ነበር ደንቅን እያሳያቸው የመራቸው፡፡ ቸርነቱ እንዴት ብዙ ነው!‎‎በዚህ ክፍል ግን የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት ወደ ጥምቀተ ባሕር የሚወርድበትን የከተራ በዓል ታሪክና ምሥጢር ነው የምንመለከተው ።‎‎”ከተራ”‎ተራ ምንድን ነው?‎   “ከተራ” በመባል የሚታወቀው “የጥምቀት ዋዜማው” ነው፡፡ “ከተራ” የሚለው ቃል “ከተረ ከበበ ካለው የግዕዝ ግስ የወጣ ነው፡፡ ከተራ ፍቺውም ውኃ መከተር፣ ወይም መገደብ ማለት ነው፡፡” ደስታ ተከለ ወልድ /1962፣ 694/ ደግሞ  የጥምቀት ዋዜማ፣ ጥር ፲ የጠራ ወራጅ ውኃ የሚከተርበት ታቦትና ሰው ወደ ዠማ ወንዝ የሚወርዱበት ጊዜ” ነው በማለት ይፈቱታል፡፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም /1948፣ 555/ ከተረ የሚለውን ቃል በቁሙ፣ “ዘጋ፣ አቆመ፣ አገደ፣ ከለከለ” ማለት ነው ብለው ይፈቱታል፡፡ በየዓመቱ ጥር ፲ ቀን የምእመናኑ አብዛኛው ሥራ ውኃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላል፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥል ይውላል፡፡ የምንጮች ውኃ ደካማ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከተራል ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሔድ ይገደባል፡፡ ውኃው የሚከተረው በማግሥቱ ጥር ፲፩ ቀን የጥምቀት በዓል ስለሚከበር ለሕዝቡ መጠመቂያ እንዲሆን ነው፡፡‎   ‎ ባሕረ ጥምቀት፣ የታቦት ማደሪያ‎በየሰበካው ቦታ ተለይቶና ተከልሎ ታቦታቱ በዳስ ወይም በድንኳን የሚያድሩበት፣ የተለያዩ የውኃ አካላት ተጠርገው የሚከተሩበት ወይም ሰው ሠራሽ የግድብ ውኃ የሚበጅበት ስፍራ “ባሕረ ጥምቀት”፣ “የታቦት ማደርያ” እየተባለ ይጠራል፡፡‎‎የከተራ በዓል በኢትዮጵያ‎‎ከዐፄ ገብረ መስቀል ጀምሮ የአደባባይ በዓል የሆነው የጥምቀት በዓል በ፲፭ኛው ክ/ዘመን በኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ /1426-1460 ዓ.ም/ አማካኝነት ታቦታቱ ወደ ወንዝ ወርደው ዕለቱን እንዳይመለሱ፣ በዚያ ፈንታ በጥምቀት ዋዜማ ጥር ፲ ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርደው እንዲያድሩ፣ አገሩን በኪደተ እግር ይባርኩም ዘንድ በሔዱበት መንገድ እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ፡፡ ይህን ታሪክ በመከተል ዐፄ ናዖድ /1486-1500 ዓ.ም/ ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመን ታቦተ ሕጉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በሚወርድበት እና ከባሕረ ጥምቀቱ ወደ ቤተ መቅደሱ በሚመለስበት ጊዜ አጅቦ አውርዶ፣ አጅቦ መመለስ እንዳለበት በዐዋጅ አስነግረው ነበር፡፡ ሕዝቡም ታቦታተ ሕጉን በሆታና በእልልታ ከቤተ መቅደስ አጅቦ ከአወጣ በኋላ በባሕረ ጥምቀት ከትሞ ማደር ጀመረ። /ሐመር ጥር/የካቲት 1998 ዓ.ም/‎‎ከቤተመቅደስ ወደ ባሕረ ጥምቀት‎     የከተራ ዕለት ጥር ፲ ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ የሔደበትን ለማዘከር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ኃዳፌ ነፍስ ለጻድቃን የሚለውን ዋዜማ ይቆማሉ፡፡  የዋዜማው ቀለም  ከቀኑ በአራት ሰዓት በመላው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ይጀመራል ከዚያም የዋዜማው ሥርዐት ቅዱስ ተብሎ እስከ ሰላም ያለው ቀለም ይደርሳል፡፡ በዕለቱም ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ ታቦተ ሕጉን የሚያነሡት ሰሞነኛ ካህን ከምግበ ሥጋ ተከልክለው ለዕለቱ የሚገባውን ጸሎት ያደርሳሉ፡፡ በከተራው ዕለት ድንኳን ተተክሎ፣ ዳሱ ተጥሎና ውኃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ ታቦተ ሕጉ የሚንቀሳቀስበት ሰዓት ሲደርስ የየቤተ መቅደሱ ታቦታት  በወርቅና በብር መጎናጸፊያ እየተሸፈኑ በተለያየ ኅብር በተሸለሙ የክህነት አልባሳት በደመቁ ካህናትና የመጾር መስቀል በያዙ ዲያቆናት ከብረው፣ ከቤተ መቅደስ ወደ አብሕርት /ምጥማቃት/ ለመሔድ ሲነሡ መላው አብያተ ክርስቲያናት የደወል ድምፅ ያሰማሉ፡፡ ምእመናን ከልጅ እስከ ዐዋቂ በዐጸደ ቤተ ክርስቲንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች “ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ …’’ እንደሚባለው ያማረ ልብሳቸውን ለብሰው በዓሉን ያደምቃሉ፡፡‎        ታቦቱ ከመንበረ ክብሩ ሲነሡ “ዮም ፍስሀ ኮነ” ተብሎ ከተጸነጸለ በኋላ ታቦቱ ወጥቶ ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት የሚለው ሰላም በሊቃውንቱ  ይዘመራል፣ ይጸነጸላል፣ ይመላለሳል፡፡ የወርቅ ካባና ላንቃ የለበሱ ቀሳውስት፣ መነኮሳት ጥላ የያዙት ከታቦቱ ጎን መስቀልና ጽና የያዙት ከታቦቱ ፊት ይሔዳሉ፡፡ እንደ ቀሳውስቱ ተመሳሳይ ልብሰ ተክህኖ የለበሱት ዲያቆናት ጥላ፣ መስቀልና ቃጭል ይዘው እያቃጨሉ ከቀሳውስቱ ፊት በመሆን ያጅቧቸዋል፡፡ ከነዚህም ሌላ ካባ፣ ላንቃ ጥንግ ድርብ የለበሱ መዘምራን የብር፣ የነሐስ መቋሚያና ጸናጽል ይዘው “ወረደ ወልድ”  የሚለውን አመላለስ እያሸበሸቡ ዲያቆናቱን ቀድመው ይሄዳሉ፡፡ የደብር አለቆችና አበው ካህናት ታቦቱን ተከትለው ይጓዛሉ፡፡ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎችም በተለያዩ ቀለማት ባሸበረቁ አልባሳት ተውበው ትርዒት እያሳዩ “ወረደ ወልድ፣ እግዚኡ መርሐ፣ ሆረ ኢየሱስ” እና ሌሎችንም የአማርኛ መዝሙራትን እየዘመሩ፣ እናቶች “ነይ ነይ እምዬ ማርያም” እያሉ ሌሎችም ምስጋናዎችም እየቀረቡ ጉዞ በዝግታ ወደ ጥምቀተ ባሕር ይሆናል፡፡‎‎የከተራ በዓል ማክበሪያ ቦታ እንደደረሱ ታቦታቱ በድንኳኑ አጠገብ ቆመው “ወረደ ወልድ”  የሚለው ሰላም ተመርቶ በአግባቡ ከተለዘበ በኋላ ጸሎት ተደርጎ የዕለቱ ትምህርተ ወንጌልና ዝማሬ  ከቀረበ በኋላ ውዳሴ ማርያም፣መልክዐ ኢየሱስ ተደግሞ  ታቦቱ ሕጉ  ወደ ተዘጋጀላቸው ድንኳን ይገባሉ /ሥርግው፤1981፣9/፡፡ በሁለተኛ የአገልግሎት ክፍል  ካህናቱ ስብሐተ እግዚአብሔር ሲያደርሱ ያድራሉ፡፡ በመንፈቀ ሌሊትም ሥርዐተ ቅዳሴው ተጀምሮ ከሌሊቱ በ9፡00 ሠርሆተ ሕዝብ ይሆናል፡፡‎የከተራ ምሳሌነት ‎‎በበዓለ ጥምቀት ዋዜማ የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድና የባሕረ ጥምቀቱ መዘጋጀት  ሃይማኖታዊ ታሪክና ምሳሌ አለው፡፡ እስራኤል ዘሥጋ ወደ ምድረ ርስት ለመግባት የዮርዳኖስን ወንዝ ሲሻገሩ፡- ድንኳን ጥለው የቃል ኪዳኑን ታቦት በድንኳን ውስጥ አድርገው ሌዋውያኑ በዙሪያው፣ ካህናቱ ደግሞ በውስጥ ኾነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አድረው በማለዳ ተሻግረዋል /ኢያሱ.፫፥፰-፱/፡፡  ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት አክብረው  የወንዙን ዳርቻ በረገጡት ጊዜ እንደ ክረምት ማዕበል ይወርድ የነበረው ውኃ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ወደ ላይ ቆሟል፡፡ ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ታቦተ ጽዮንን ያከበሩት  ካህናት ከወንዙ መሀል ይቆሙ ነበር፡፡ በዚህ መሠረት  “የካህናት እግሮቻቸው የዮርዳኖስን ውኃ በመርገጣቸው እንደ ጥምቀት ሆናቸው” በሐዲስ ኪዳነ ጌታችን ለመሠረተው ሥርዐተ ጥምቀት ምሳሌ ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የጥምቀትን ዋዜማ ከተራ ብላ የጠራችው ከዚህ በመነሣት ነው፡፡‎‎ጌታችን በተጠመቀ  ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ የላይኛው ሸሽቶ ወደ ላይ ተመልሶ ሽቅብ ፈሷል፡፡ የታቹም ወደ ታች ሸሽቷል፡፡ የላይኛው ፈሳሽ ተቋርጦ እንደ ክምር ተቆልሎ ቀርቷል። ቅዱስ ዳዊት የተመለከተውም ይህንኑ ነው። ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ቤዛነት ተቋርጦ፤ የታቹም ፈጽሞ መድረቁ ኃጢአተ አዳም የመጥፋቱ ምሳሌ ነው፡፡ እስራኤል ፈለገ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ኢያሪኮ  መሔዳቸው ምእመናን በጥምቀት ከኃጢአት ቍራኝነት ተላቀው እግራቸውን ወደ ልምላሜ ገነት ወደ ዕረፍት መንግሥተ ሰማያት አቅንተው ለመሔዳቸው ምሳሌ ነው፡፡  ኢያሱ የጌታ፣ እስራኤል  የምእመናን፣ ዮርዳኖስ የጥምቀት፣ ምድረ ርስት የገነት መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው፡፡‎       ታቦቱን አክብሮ  የሚሔደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ፣ ታቦቱ የጌታችን፣ ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ፣ ታቦታቱን አጅበው የሚሔዱትና በዓሉን የሚያከብሩት ምእመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩት ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ታቦታቱ በጥምቀት ዋዜማ ከመንበራቸው ወደ ጥምቀተ ባሕር መውረዳቸውና በዚያ ማደራቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከማታው ጀምሮ መውረዱንና ተሰልፎ ተራውን ሲጠብቅ ማደሩን ያጠይቃል፡፡  በመኾኑም ከዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ሁሉ በዮርዳኖስ ዙሪያ ድንኳናቸውን ተክለው ያርፉ ነበር፡፡ በዚህ አንጻር ዛሬም በባሕረ ጥምቀት ዙሪያ ድንኳኖች ዳሶች ይጣላሉ፡፡ የከተራ በዓል ታሪካዊ፣

“ወነሥኡ ካህናት  ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር ወሖሩ ቅድመ ሕዝብ” (የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዘው በሕዝቡ ፊት አለፉ) ኢያ 3፥6‎ Read More »

“ሰፍሐ እደዊሁ ለሕማም – እጆቹን ለሕማም ዘረጋ”  ቅዳሴ ሐዋርያት

እንኳን ለመድኃኔዓለም ጥንተ ስቅለት በዓል አደረሰን አደረሳችሁ! Your Attractive Heading Your Attractive Heading የዛሬው በዓላችንን የምናከብርበት ምክንያት እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለውን ጥልቅ ፍቅር የገለጠው አንድያ ልጁን ወደ ምድር ልኮ በተቀበላቸው ጸዋትወ መከራን በማሰብ ነው። የመጨረሻ ፍቅሩንም ያሳየው በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞቶ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን መከራን ተቀበለ? እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ከመፍጠሩ በፊት ለሰው የሚያስፈልገውን እንዳይቸገር ሁሉን አመቻችቶ (አዘጋጅቶ) በስድስተኛው ቀን ዐርብ ዕለት በእርሱ መልክና አርአያ ፈጠረው በምድርም ላይ ለሚኖሩ ፍጥረታት ገዢ አድርጎ ከጎኑም አጥንትን ወስዶ ሔዋንን ፈጠረለት። አዳምና ሔዋን በገነት መካከል ያሉትን ፍሬዎች እንዲበሉ ፈቀደላቸው ነገር ግን ዕፀ በለስ የተባለችውን ፍሬ እንዳይበሉ አዘዛቸው ከዚህች ፍሬ ብትበሉ የሞት ሞትን እንደሚሞቱ አስጠነቀቃቸው። አዳምና ሔዋን ግን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ አክብረው መኖር የቻሉት ለሰባት ዓመታት ብቻ ነበር ሰይጣን ዲያብሎስ በእባብ ገላ አድሮ ወደሔዋን በመሄድ ከንቱ የሆነ ውዳሴን ለሔዋን በማቅረብ “ዕፀ በለሱን አትብሉ ያላችሁ እግዚአብሔር አምላክ እንዳትሆኑ ብሎ ነው ስለዚህ ከዕፀ በለሱ ብትበሉ አምላክ ትሆናላችሁ” ብሎ ሔዋንን ዕፀ በለሱን እንድትበላ የሐሰት ስብከትን ሰበካት ሔዋንም ቀጥፋ የዲያብሎስን ምክር ሰምታ ከአዳም ጋር በሉ። በበሉም ጊዜ ጸጋቸው ተገፈፈ ፍርሃትም ወደቀባቸው እግዚአብሔርም ከእነርሱ ተለየአዳምና ሔዋንም በእግረ አጋንት በኃጢአት ወድቀው ከክብር ተዋርደው በለስን በልተው ሞትን ሸምተው ለብዙ ዘመናት በጨለማ፣በፍርሃት፣የብርሃን ጸጋቸው ተገፎ በሐዘን ውስጥ ስንሰቃዩ እግዚአብሔርም ተመልክቶ   ተገለጠላቸውና አምስት ቀን ተኩል ሲፈጸም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለው ብሎ ቃል ኪዳን ለአዳም ገባለት።በዚህም ጌታችን ሞታችንን ወስዶ ሕይወት ሊሰጠን መድኃኒት ልጁን ላከልን። “ፈነወ ለነ መዝራእቶ ልዑለ – ልዑል ክንዱን ሰደደልን” እንዳለ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምበተጨማሪም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ “እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደላከው እንመሰክራለን” 1ኛ ዮሐ 4፥14 በዚሁ መሠረት ከሦስቱ አካል አንዱ ወልድ በተለየ አካሉ ከሰማየ ሰማያት ወረደ ተወለደ ይኸውም ለአዳም ልጆች በሙሉ ለበደልነው፣ ለወንጀለኞች፣ ሕጉን ለጣስነው፣ በጨለማ ውስጥ ላለነው ፣ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ በርደተ መቃብር ርደተ ሲዖል እንድንወርድ ተፈርዶብን ለነበረው ፣ በእግረ ዲያብሎስ ስንረገጥ ለነበርነው እና ምንም የሚወደድ ማንነት የሌለን ስንሆን “እግዚአብሔር አንዲያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።ዮሐ 3፥16   ለኛ ሲል ምን ምን መከራን ተቀበለ? “የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምን አንደበት ነው? የፍቁር የጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያያል ሕሊናም ይመታል ነፍስም ትንቀጠቀጣለች ሥጋም ይደክማል” 1ኛ ከሊቶስትራ እስከ ቀራንዮ ከጲላጦስ አደባባይ እስከ ቀያፋ ጊቢ በአይሁድ በሊቃነ ካሕናት እጅ ተሰቃየ፣ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ጊዜ በጅራፍ ተገረፈ፣ አንድ መቶ ሃያ ጊዜ በጥፊ ተመታ፣ ሰማንያ ጊዜ ጺሙን ነጩት፣ ሰባ ሁለት ጊዜ አፉን በጡጫ መቱት፣ ሦስት መቶ የሚሆኑ ረዣዥም የእሾህ አክሊል በራሱ ደፉበት፣ ምራቅ ተፉበት፣ መስቀል ተሸክሞ እየወደቀ እየተነሳ ተሰቃየ።“እርሱ ግን ስለመተላለፋችን ቆሰለ ስለበደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን።” ኢሳ 53 ፥7 እንዲሁም ጌታችን ስድስት ሰዓት ሲሆን አዳምና ሔዋን አትብሉ የተባሉትን ዕፀ በለስ የበሉት በዚህ ሰዓት ነበረና ይህንን ለመካስ በስድስት ሰዓት ተሰቀለ። ጌታችን በመስቀል እያለ ተአምራት ተፈጽመዋል በሰማይና በምድር 1ኛ ጸሐይ ጨለመ2ኛ ጨረቃ ደም ለበሰች3ኛ ከዋክብት ረገፉ         # በምድር1ኛ መቃብራት ተከፍተው ከ500 በላይ የሚሆኑ ሙታን ተነሱ2ኛ ድንጋዮች ተሰነጣጠቁ3ኛ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለ2 ተከፈለ4ኛ ዓለም ሁሉ ጨለማ ሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ እያለ 13ቱን ህማማተ መስቀል ተቀብሏል። ጌታችን በመስቀል ላይ እያለ “ተጠማሁ “ሲል አንጀት የሚበጥስ ሀሞትና ከርቤ ቀላቅለው አጠጡት ሁሉን የሚያጠግበውን አጠጥቶ የሚያረካውን ተጠማሁ አለ። 40 ቀንና 40ሌሊት በጌቴሴማኒ  የጾመ ጌታ በአይሁድ እጅ 18 ሰዓታት ሳይሞላ ተጠማሁ ያላቸው ለምን ይሆን? ፍቅርን ሲገልጽ ነው አይሁድ ከታላቁ እስከ ታናሹ ድረስ በጠላትነት ተነስተውበታልና ለዚህም ነው ተጠማሁ ፍቅር ተራብኩ ሲል ነው።      ይህን ፍቅር የሆነውን ጌታ እስከመስቀሉ ያልተለዩ ሁለቱ ብቻ ነበሩ 1ኛ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የሚደርስበትን መከራ እስከ ቀራንዮ እየተከተለ መከራውን ፣ስቃዩን፣ መንገላታቱን ግርፋቱን አይሁድን ሳይፈራ ያይ ነበር ወንጌላዊው ቅ/ዮሐንስ ጌታ ይወደው የተባለው ቁጽረ ገጽ (ፊቱ በሐዘን) የሞላ የተባለው ለዚህም ነው በመጨረሻም በመስቀል እያለ እናቱን እነኋት እናትህ ብሎ በአደራነት የሰጠው2ኛ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት እርሷም የአይሁድን ዛቻ ዱላ ሳትፈራ እስከ ቀራንዮ የተከተለች በውስጧ እያለቀሰች ያ ሁሉ ስቃይ ሲደርስበት መጨረሻውን ሳላይ የትም አልሄድም ብላ መስቀሉ ስር የተገኘች ለመዳናችን ምክንያት የሆነች ንጽሕት፣ቅድስት፣ድንግል ለሁላችን የተሰጠች እናት ናት።    ስለዚህ የተከፈለልንን ውለታ በማሰብ በሕይወት ልንኖር ይገባል። 1ኛ በፍቅር ልንመላለስ ይገባል።         እኔ እንደወደድኳችሁ እርስ በእርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትዕዛዜ ይህች ናት    ዮሐ 15፥12ጠላቶቹ ሳለን ከወደደን     1ኛ 4፥16 እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል እግዚአብሔር ፍቅር ነው በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።2ኛ በትህትና ሕይወት ልንኖር ይገባልእርሱን ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት በትህትና ያያቸው ነበር።    ሉቃ 23፥34    አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለእኛም ሰዎች ሲንቁን ሲታበዩብን በዝምታ በፍቅር ልናሳልፍ ይገባል። 3ኛ በትዕግስት ፦ እርሱ ሲሰድቡት  አልተሳደበም፣ በፈጠራቸው ፍጥረታት ምራቅ ተተፋበት ምንም መልስ አይሰጣቸውም ነበር በትዕግስት ይመለከታቸው ነበር እንጂ           2ጴጥ 3፥15 የጌታችንም ትዕግስት መዳናችሁ እንደሆነ ቁጠሩ4ኛ ሮሜ6፥5       ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ  ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን                     ጌታችን ከቤተልሔም ጀምሮ ብርዱ፣ የግብጽ ስደቱ፣ረሃቡ ጥማቱ ከሐሙስ ማታ 3፡00 እስከ ዐርብ 9፡00 የተቀበላቸው መከራዎች ለሰው ልጅ ነውእኛም የእርሱ እውነተኛ ደቀ መዝሙር ስንሆን የሚደርስብን ልዩ ልዩ መከራ አለ ነገር ግን የኛ አምላክ በመስቀል ተሰቅሎ በአዲስ መቃብር ተቀብሮ መቃብር ሊይዘው ሳይችል መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በራሱ ኃይልና ሥልጣን ሞትን ድል አድርጎ አሸንፎ ተነስቷል እኛም በእምነት ጸንተን ንስሐ ገብተን በመስቀል ላይ የቆረሰውን ቅዱስ ሥጋውን በልተን ደሙን ጠጥተን መንግስቱን እንድንወርስ ከእርሱ ጋር ለዘለዓለም እንድንኖር አምላካችን ይርዳን።       ስብሐት ለእግዚአብሔር! መምህር በየነ ክፍሌየጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከትቁጥጥርና የምግባረ ሰናይ ክፍል ኃላፊ

“ሰፍሐ እደዊሁ ለሕማም – እጆቹን ለሕማም ዘረጋ”  ቅዳሴ ሐዋርያት Read More »

“የተወደደው ባለ መድኃኒቱ ሉቃስ…ወንጌላዊ ።”ቆላስይስ 4፥14

ሉቃስ ማለት በላቲኑ ትርጓሜ ብርሃናማ፣ ብርሃን የያዘ ማለት ነው፡፡ በትርጓሜ ወንጌል የተሰጠው ትርጉም ደግሞ ሉቃስ ማለት ዓቃቤ ሥራይ (ባለ መድኃኒት) ማለት ነው፣ ቀድሞ ዓቃቤ ሥራይ ዘሥጋ (ሥጋዊ ሐኪም) ነበር በኋላ ግን ዓቃቤ ሥራይ ዘነፍስ ( መንፈሳዊ ሐኪም) ሆኗልና፡፡ አንድም ተንሣኢ (ፈጣን) ማለት ነው ለስብከተ ወንጌል ይፋጠናልና፣ አንድም መበሥር (ብሥራት ነጋሪ) ማለት ነው ብሥራተ መልአክን ይጽፋልና በማለት ይተረጉመዋል፡፡የተወለደው በሶርያ አንጾኪያ ነው፡፡አስቀድሞ ከ72ቱ አርድእት ወገን የተቆጠረ ሲሆን ከበዓለ ሃምሳ በኋላ ወደ አንጾኪያ ወርዶ ወንጌልን ሰብኳል ከሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎሰ ጋር የተገናኘውም በዚሁ ነው፡፡ ቅዱስ ሉቃስ የሕክምና ሙያ የነበረው ሲሆን ያጠናውም ከአቴናና እስክንድርያ ሊቃውንት መሆኑ ታውቋል፡፡ ከዚህ ሙያው በተጨማሪ የሥነ ሥዕል ችሎታም እንደነበረው ይነገራል፡፡ ይህንን ችሎታውንም በወንጌሉና በሐዋርያት ሥራ መጽሐፉ ላይ ባለው ሥዕላዊ አገላለጥ ከማንጸባረቁም ሌላ በእጁ የተሳሉ ሥዕሎች በተለያዩ ሀገሮች ይገኛሉ፡፡የቅዱስ ሉቃስ ስዕሎች እመቤታችን ልጇን አቅፋ ( ምስለ ፍቁር ወልዳ) የሳላቸው ሲሆኑ በኢትዮጵያ በተድባበ ማርያም ፤ በደብረ ዘመዶ ፤ በዋሸራ ፤በጅበላ ሲገኙ ተመሳሳዩም በስፔን ቅድስት ማርያም ካቴድራል እንደሚገኝ ይነገራል ፡፡ የቅዱስ ሉቃስ ወንጌልየቅዱስ ሉቃስ ወንጌል የተጻፈው በሀገር አኪይያ (ሮም) በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ ነው፤ የሉቃስ ወንጌል ‹የአሕዛብ ወንጌል›፣ ‹ሰባኬ መንፈስ ቅዱስ›፣ ‹ሰባኬ ጸሎት›፣ ወንጌለ አንስት ተብሎም ይጠራል፡፡፩. ‹የአሕዛብ ወንጌል› እየተባለ የሚጠራው ወንጌሉ የተጻፈው ለአሕዛብ በመሆኑ ነው፡፡፪. ሰባኬ መንፈስ ቅዱስ የሚባለው ስለ መንፈስ ቅዱስ ደጋግሞ ስለሚናገር ነው፡፡፫. ሰባኬ ጸሎት የተባለው ከሌሎች ወንጌላት የበለጠ ደጋግሞ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ጸሎት ጽፏልና ነው፡፡፬. ወንጌለ አንስት የሚባለው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ስለ ቅድስት ኤልሳቤጥ፣ ስለ ማርያም እንተ እፍረት፣ ስለ ናይን እና ወዘተ በስፋት ስለሚናገር ነው፡፡ወንጌሉን ከመጻፉ አስቀድሞም ቅዱስ ሉቃስ የቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር ከመሆኑ በፊት የቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር እንደነበረ ትርጓሜ ወንጌል ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ በአንጾኪያ ሀገር ቅዱስ ጳውሎስን ካገኘው በኋላም ሊቀ ሐዋርያው ሰማዕት እስከሆነበት ድረስ አገልግሎታል፡፡ ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ጋርም በነበረበት ጊዜም መቄዶንያ የምትባል ሀገር ከፍሎ እንዲስተምር እንደሰጠው በወንጌል ትርጓሜ ተገልጿል፡፡ ቅዱስ ሉቃስም በዚያ ሀገር ከጌታችን ኢየሱስ መፀነስ ጀምሮ፣ መዋዕለ ስብከቱን፣ የሠራውን ትሩፋትና ገቢረ ተአምሩን በሙሉ ለአሕዛቡ በነገራቸው ጊዜ ከኃጢያት ወደ ጽድቅ፣ ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር ተመለሰው በማመን የክርስትና ጥምቀት ተጠምቀዋል፡፡ ለስብከት በሚጓዝበትም ወቅት ትምህርት ባልተዳረሰባቸው ስፍራ ሲያስተምር አንድ ታዖፊላ የተባለ የእስክንድርያ መኮንን ስብከቱን አድምጦ በማመን ‹ዜና ሐዋርያትን› (ገድለ ሐዋርያትን) እንዲጽፍለት በጠየቀው መሠረት ጽፎለታል፡፡ በዚህም ቅዱስ ሉቃስ የጻፋቸው መጻሕፍት ከወንጌሉና ከሐዋርያት ሥራ ጋር ሦስት ናቸው፡፡ የሐዋርያት ሥራየሐዋርያት ሥራን የጻፈው ቅዱስ ሉቃስ ነው፡፡ ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ከ1-34 ዓ.ም. ያለውን የክርስትና ታሪክ ካሰፈረ በኋላ ቀጣዩንና ከ34-58 ዓ.ም. ያለውን ደግሞ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፉ ላይ ጽፏል፡፡ከምዕራፍ 1-8 ያለው የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ በኢየሩሳሌም የሚያሳይ ሲሆን ከምዕራፍ 9-12 ያለው ታሪክ ደግሞ በእስጢፋኖስ ሰማኝትነት በተነሣው ስደት የተበተኑት የኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን ልጆች በአካባቢው ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ የሚያሳይ ነው፡፡ ከምዕራፍ 13 ጀምሮ እስከ ፍጻሜው ደግሞ የቅዱስ ጳውሎስን ጉዞዎች ተከትሎ የጻፈውና ክርስተና በታናሿ እኪያር በአውሮፓ እንዴት እንደተሰበከ የሚያሳየው ክፍል ነው፡፡የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመጀመሪያው የሮም እሥራቱ በቁም እሥር ላይ ሆኖ ወንጌልን እንዲሰብክ ተፈቅዶለት በነበረ ሰዓት በሮም ከሚኖሩ አይሁድ ጋር በ58 ዓ.ም ስለሃይማኖት ያደረገውን ውይይት ተርኮ ያጠናቅቃል፡፡ ወንጌላዊው ሉቃስ የሐዋርያት ሥራን የጻፈው በ58/በ59 ዓ.ም/ ነው፡፡ ምክንያቱም ከዚህ ዓመተ ምሕረት በኋላ የተከናወኑትን ለምሳሌ በ60 ዓ.ም የቅዱስ ጳውሎስን መፈታት ዘግይቶም በ64 ዓ.ም. የደረሰውን የሮማ መቃጠልና የአይሁድን ዓመፅ በመጽሐፉ ስላልገለጠው ነው፡፡ቅዱስ ሉቃሰ ሐዋርያው ጳውሎስን ተከትሎ ታሪኩን ሲያሰባስብ ከኖረ በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ ሲታሠር ዕረፍት በማግኘቱ አጠናቅሮ በመጽሐፍ መልክ በማዘጋጀት ለቴዎፍሎስ ልኮለታል፡፡ሉቃሰ ዘላሕም፡- አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ቅዱስ ሉቃስ ለምን በላም እንሚመሰል ሲናገር፣ የመድኃኒታችንን መሥዋዕትነት ሐዲስዋ እምቦሳ በወለደች በንጹሕ ላም ፍሪዳ መስሎ ይናገራልና ይለዋል፡፡ እንዲሁም በከብቶች በረት መወለዱን ስለሚናገርና ታረኩም የላም ወተት ለሕፃን ልጅ ቀላል ምግብ እንደሆነ ሁሉ ለአዲሰ አማኝ ቀለል በሎ የቀረበ መሆኑን ያስገነዝባል ።ቅዱስ ሉቃሰ የድንግልና ሕይወት የነበረው ወንጌላዊ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሰማዕትነት እስካረፈበት ጊዜ ድረስ ደቀ መዝሙር በመሆን አገልግሎታል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በ67 ዓ.ም. በሮማ በሰማዕትነት ሲያርፍ ሉቃስ ወደ ድልማጥያ መጣ በዚያም በሽምግልና ዘመኑ ወንጌልን በመስበክ ላይ እያለ አይሁድና ካህናተ ጣዖት ተባብረው ትምህርቱን በመቃወም ተነሡበት መስከረም 20 ቀን 68 ዓ.ም. አይሁድና አረማውያን ጉባዔ አድርገው ነገር በመሥራት ለሮም ንጉሥ ከሰሱት፡፡ በዚያን ዘመን ኔሮን እብደቱ ያየለበት ጊዜ በመሆኑ የቅዱስ ሉቃስን ከሮሜ ማምለጥና ወደ ድልማጥያ መምጣት ሲሰማ 200 ወታደሮችን ላከበት ቅዱስ ሉቃስም የሰዎችን መምጣት በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ ያሰተምራቸው የነበሩትን ምእመናን ወደየቤታቸው ላከና በድልማጥያ አጠገብ ወደሚገኘው ባሕር ተጠጋ በባሕሩ አጠገብ አንድ ዓሣ አስጋሪ ቆሟል፡፡ ቅዱስ ሉቃስ ወደ ዓሣ አስጋሪው ቀረበና ጨዋታ ጀመሩ ቀስ በቀስም ወንጌል ይሰብክለት ጀመር፡፡ ዓሣ አስጋሪውም ቅዱስ ሉቃሰ የሚነግረውን ሁሉ ሥራውን አቁሞ በደስታ ያዳምጠው ነበር በመጨረሻ እንካ እነዚህ የሕይወትን መገንድ ይመሩሃል አለና የያዛቸውን መጻሕፍት ሁሉ ሰጠው ያም ዓሣ አስጋሪ እጅግ ተደስቶ ዕቃ በሚያስቀምጥበት ቦታ በክብር አኖራቸው ቅዱስ ሉቃስ መጽሐፉን ሰጥቶት ዘወር ሲል የኔሮን ወታደሮች ተረባረቡና ያዙት ከዚያም ወደሮም ተወሰደና የኔሮን ፍርድ ቤት ቀረበ ።ንጉሡ ‹‹በሥራይህ ሕዝቡን የምታስት እስከ መቼ ነው?›› ብሎ ጠየቀው፤ ቅዱስ ሉቃስም ‹‹እኔ ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ነኝ እንጂ ሥራየኛ አይደለሁም›› ብሎ መለሰለት፡፡ ንጉሥ ኔሮንም ሁለተኛ እንዲህ አለው፤ ‹‹እየጻፈች ሰዎችን የምታስት ይህች እጅህን እኔ እቆርጣታለሁ፤›› ይህንንም ብሎ የቀኝ እጁን እንዲቆርጡት አዘዘ፡፡ በቆረጡትም ጊዜ ‹‹ንጉሥ ሆይ እኛ የዚህን ዓለም ሞት እንደማንፈራ ዕወቅ፤ ነገር ግን የጌታዬና የፈጣሪዬን ኃይሉን ታውቅ ዘንድ አሳይሃለሁ፤›ይህንንም ብሎ የተቆረጠች የቀኝ እጁን በግራ እጁ አንሥቶ ከተቆረጠችበት ቦታዋ ላይ አገናኝቶ እንደ ቀድሞዋ ደኅነኛ አደረጋት፤ ከዚህም በኋላ ለያት፤ በዚያም የነበሩ አደነቁ፤ የሠራዊቱም አለቃና ሚስቱ ብዙዎችም ሰዎች ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ፤ ቁጥራቸውም ዐራት መቶ ሰባ ሰባት ነፍስ ሆነ፡፡ ንጉሡም ከቅዱስ ሉቃስ ጋር ራሶቻቸውን እንዲቆርጡ በማዘዙ ቆረጡአቸው፤ የምስክርነት አክሊልም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ፡፡ ቅዱስ ሉቃስ ያረፈው በ፹፬ ዓመቱ ነው፡፡ከዚህም በኋላ ሥጋውን በማቅ አይበት ውስጥ አድርገው ወደ ባሕር ጣሉት፡፡ በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ አንድ ደሴት ደረሰ ምእመናንም አግኝተው ወስደው ገነዙት፤ በአማረ ቦታም አኖሩት፡፡ የወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ አማላጅነት፣ ተረዳኢነትና በረከት አይለየን፤ አሜን! መልአከ ብርሃን ዳንኤል ነቢዩበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የሰበካ ጉባኤና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ክፍል ኃላፊ፣ የዳግማዊት ጌቴሴማኒ በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ

“የተወደደው ባለ መድኃኒቱ ሉቃስ…ወንጌላዊ ።”ቆላስይስ 4፥14 Read More »

“ወኀረዩ እስጢፋኖስሀ ብእሴ ዘምሉእ ሃይማኖተ ወመንፈሰ ቅዱሰ – በእምነትና በመንፈስቅዱስ የተሞላውን እስጢፋኖስን መረጡ” ሐዋ 6፥5

እስጢፋኖስ ማለት አክሊል (ዘውድ)ማለት ነው።በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሀገረ እስራኤል ተወልዷል።አባቱ ስምዖን እናቱ ሐና ይባላሉ። መጀመሪያ ከመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በኋላም ከቅዱሳን ሐዋርያት ተምሯል። የመልካም ዛፍ መልካም ፍሬ ለመሆን የበቃ መንፈሳዊ ወጣት ነበር። ማቴ7፥17 በምእመናን ዘንድ መታመንንና መወደድን ያተረፈ፣ በወጣትነት ጊዜው በመንፈሳዊ ዕውቀትና በመንፈሳዊ ጥበብ ያደገ ፣በሃይማኖት የጸና፣መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሰው ነበር። በአንደኛው መቶ ከፍለ ዘመን ማለትም ከ34-41 ዓ/ም ባለው ጊዜ አይሁድና አሕዛብ ክርስትናን ከተቀበሉ በኋላ በመካከላቸው መነቃቀፍ ፣መተማማትና አለመግባባት ተፈጥሮ ጉዳዩ ከሐዋርያት ሲደርስ “ኢይደልወነ ከመንኅድግ ቃለ እግዚአብሔር ወንፀመድ ማዕዳተ – የእግዚአብሔርን ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ አይገባንም” ሐዋ 6፥2 ብለው ችግሩን የሚፈቱ፣ በመልካምነታቸው የታወቁ፣ መንፈስቅዱስ የሞላባቸው፣ ጥበበኞች የሆኑ ሰባት ሰዎች እንዲመረጡ በማዘዛቸው ችግሩን እንዲፈቱ በሕዝቡ ተመርጠው በሐዋርያት ከተሾሙት 7 ዲያቆናት አንዱና ዋናው ነበር። በመሆኑም ሊቀ ዲያቆናት (የዲያቆናት አለቃ) ይባላል። የሐሥ 6፥6 ይሄ ምን ይነግረናል? ሐዋርያት መርጠው እንሹባችሁ አላሉም ።ሕዝቡን ራሳችሁ ምረጡ አሏቸው እንጂ። ይህ ነገርም ሕዝቡን ደስ አሰኝቷል። የአመራረጡ መስፈርት መልካምነት፣ ጸጋ መንፈስ ቅዱስና ጥበብ እንጂ ዝምድና አልነበረም ቀረቤታ አልነበረም ብሔር አልነበረም ቋንቋም አልነበረም እጅ መንሻሞ አልነበረም ጆሮ ጠቢነትም አልነበረም አማላጅም አልነበረም ጮሌነትም አልነበረም። በዚህ ሁሉ የመጣ(የተሾመ)ችግር ከማባባስ ባለፈ ችግር ፈቺ መሆን አይችልም ሰው ያለ ቦታው ተቀምጦ እንዴት ችግር ሊፈታ ይችላል? ለመንፈሳዊ ሹመት መንፈሳዊ ሰው ነው የሚገባው የዛሬዋ ቤተክርስቲያን ከዚህ ምን መማር አለባት ? በሊቀ ዲያቆንነቱ ጊዜ 8000 ማኅበረ ክርስቲያንን መርቷል። በአገልግሎቱ ኦሪት እጠፋ እጠፋ ፣ወንጌል እሰፋ እሰፋ ብላለች። በእኛ የአገልግሎት ጊዜ ክርስቲያንነት እሰፋ እሰፋ፣ ኢክርስቲያንነት እጠፋ እጠፋ ብሎ ይሆን?? በእስጢፋኖስ የአገልግሎት ጊዜ ናዖስ የሚባል መሠርይ (ጠንቅዋይ) (ጠንቋይ) በምትሐታዊ ተአምራት ሕዝቡን ሲያስት እውነተኛ ተአምራትን በማድረግ የናዖስን የምትሐት ሐሰትነትና ከንቱነት ለሕዝብ በማሳየት በእምነቱ እንዲጸና፣በምትሐታዊ ተአምር ከመታለል ራሱን እንዲጠብቅ በማስተማር የዕቅበተ እምነት ተልእኮውን በሚገባ ተወጥቷል። መሠርዩ ናዖስ በምስሐበ አጋንንትወደሰማይ ዐርጋለሁ ሲል በስመ እግዚአብሔር አውርዶ መሬት ላይ የጣለገባሬ ተአምራትም ነው ይባላል።የሐሥ6፥8የሄኖክን የትውልድ ሱባኤ፣የዳንኤልን የሰንበት ሱባኤየኤርምያስን የዕለት ሰባኤ አውጥቶኦሪትን ከወንጌል፣ዘመኑን ከዘመን ፣ትንቢቱን ከመድኅን አስማምቶ ዘመነ ሥጋዌ እንደደረሰ፣እግዚአብሔር ወልድ ሥጋ እንደለበሰ ሲያስተምር”ወሰእኑ ተቃውሞቶ”እንዲል እስጢፋኖስ የሚናገርበትን ጥበብ መቃወም ቢሳናቸው ተበሳጭተው ወደ ዐደባባይ አውጥተው በደንጊያ ወግረው ገድለውታል።እርሱም ሰማዕትነትን ተቀብሏል።ቀዳሜ ሰማዕት ይባላል።የሐዲስ ኪዳን ሰማዕታት መጀመሪያ ማለት ነው።”በእስጢፋኖስ አዕባን እመየኀልቁ፣ወገረኒ ኢያሱ በወርቁ”እንዳለ ባለቅኔው።ኦሪትን በሥርዓተ መላእክት ተቀብያለሁ ብሎ የሚመጻደው፣ነገር ግን ኦሪት የማይጠብቀው የአይሁድ ጉባኤ”ኦሪት ከወንጌል፣ዘመን ከዘመን፣ትንቢቱ ከመድኅን”እንደማይገጥም ለማሳየት ሲሉዓመተ አበውን ለመቀነስ፣ኦሪተ ሌዋውያንን ወደ ኦሪተ አይሁድ ብጡል ለመለወጥ ተገዷል ። “ከሸንጎ ቢረታ ሚስቱን ከቤት መታ” እንደሚባለው ማለት ነው።”እሙንቱሰ እምከንቱ ውስተ ከንቱ”እንዲል አካሔዱም ከጥፋት ወደፋት ሆኖበታል። እስጢፋኖስን እንጂ የእስጢፋኖስን እምነት መግደል አልቻለም “ዛሬም ክርስታያኑን እንጂ ክርስትናን መግደል አይቻልም።ማጥፋት አይቻልም ።መከራ ሊኖር ይችላል።ስደት ሊኖር ይችላል ፣ጫና ሊኖር ይችላል ነገር ግን ክርስቲያንነት ድል ያደርጋል እንጂ ድል አይሆንም።አይሸነፍም። ቅዱስ እስጢፋኖስ ግን “እግዚኦ ስረይ ሎሙ ዘንተ ኀጢአቶሙ ወኢትረሲ ቦሙ ጌጋየ” አቤቱ ይሄን በደል አታድርግባቸው” የሐሥ7፥60 በማለት ከክርስቶስ የተማረውን ይቅር ባይነትን ሉቃ 23፥34 ገዳዮቹን ይቅር በማለትና “ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመጠዋ ለነፍስየ” ጌታየ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል” የሐሥ 7፥59ከርስቶስን መስሎታል ሉቃ23፥46 1ኛ ቆሮ 11፥1“በዚያን ጊዜም በቤተክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ” የሐሥ 8፥1 ማኅበረ እስጢፋኖስ ወደ እስያ ወቢታንያ ወደ ቀጰዶቅያ ተበትኗል።ይህም ውስጡ ጥበበእግዚአቦሔር ነበር በኢየሩሳሌም በኖሩ ሃይማኖት ይጸናል እንጂ አይሰፋም ነበር አሁን ግን ወንጌልንበደረሱበት ሥፍራ ሁሉ ስለሰብኩ የሃይማኖት መጽናት ብቻ ሳይሆን መስፋትም ሆነ። “እግዚአብሔርን ለሚወዱት እንደ ዐሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን” ሮሜ 8፥28 ጥቅምት 17 ሢመቱ ጥር 1 ዕረፍቱ የሰማዕቱ ረድኤትና በረከት አይለየን። ሊቀ ማእምራን ሰሎሞን ፈጠነ

“ወኀረዩ እስጢፋኖስሀ ብእሴ ዘምሉእ ሃይማኖተ ወመንፈሰ ቅዱሰ – በእምነትና በመንፈስቅዱስ የተሞላውን እስጢፋኖስን መረጡ” ሐዋ 6፥5 Read More »

‎”በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ” (ሐዋ 6:3)‎በዚህ የአባቶቻችን የሐዋርያት መመሪያ መሠረት ከተመረጡ አገልጋዮች መካከል አንዱ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ ነው።

በመጋቤ ምሥጢር ጥበቡ አናጋው ‎ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ እግዚአብሔር ልኮት ኢትዮጵያዊውን ጃንረባ ባኮስን ያጠመቀው ነው።‎‎የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ታረክ፣ ምስረታ እና ልደት የሚያወሳ የታሪክም ሆነ የቤተክርስቲያን ምሁር ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስን እና ቅዱስ ባኮስን ሳያነሳ ማለፍ አይቻለውም፡፡‎‎ምክንያቱም በኢትዮጵያ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንዲሰበክ መነሻ የሆኑ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የወንጌል አባታቶቻችን ስለሆኑ ነው፡፡‎‎ከሰባቱ ሊቃነ-ዲያቆናት አንዱ ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ፊልጶስ ትውልዱ ኢሲዶር ከምትባል የቄሳሪያ የወደብ ከተማ ሲሆን በቅዱስ እስጢፋኖስ ሞት ምክንያት ደቀመዛሙርት ከኢየሩሳሌም እስከተበተኑ ድረስ በኢየሩሳሌም ከሐዋርያት እግር ስር ሆኖ ተምሯል፡፡‎‎ከመንፈስ ቅዱስ መገለጥ በኋላ ሐዋርያት በኢየሩሳሌም ባደረጉት የመጀመሪያ የስብከት አገልግሎት በርካታ ምዕመናን አምነው ተጠመቁ፤ የምዕመናኑ ቁጥር እጅግ በመጨመሩ እና የአገልግሎቱ ዘርፉም እየበዛ በመሄዱ አገልጋዮችን መጨመር አስፈላጊ መሆኑን ባመኑ ጊዜ ሐዋርያት ቀደም ሲል በአርድትነት ሲያገለገሉ ከነበሩት መካከል ሰባቱን ሊቃነ-ዲያቆናት ለመጋቢነት መረጡ፡፡‎‎ምዕመኑን በመጋቢነት እንዲያገለግሉ ከተመረጡት ሰባቱ ሊቀ-ዲያቆናት መካካል አንዱ ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ ዘሰማርያ ወኢትዮጵያ ነው፡፡‎‎በ35ዓ.ም. ቅዱስ እስጢፋኖስ በአይሁድ እጅ በሰማዕትነት ማለፉ ተከትሎ በኢየሩሳሌም የነበሩት ማኅበረ ምዕመናን ተበተኑ፤ ቅዱስ ፊልጶስም ጊቶን ወደ ምትባል የስሞን መሠርይ የትውልድ ስፍራ ወደሆነች የሰማርያ ከተማ ሄደ፡፡‎‎በዚያም ሐዋርያዊ አገልግሎቱን በማጠናከር በርካታ ምዕመናን በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት አምነው እንዲጠመቁ አስችሏል፡፡ በተለይ በጥንቆላ ግብሩ የሚታወቀውን ሲሞን መሠርይን በማሳመን ማጥመቁን ቅዱስ መጽሐፍ ዘግቦለታል፡፡ ሐዋ 8፡13።‎‎በሰማርያ ሳለ የጌታም መልአክ ፊልጶስን ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ አለው፡፡ እርሱም ተነሥቶ ሂደ፡፡ እነሆ የኢትዮጵያ ንግሥት የህንደኬ ባላሟል እና የሀብት ንብረቷ ሁሉ አዛዥ የሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ አገኘ፡፡‎‎ይህም ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፡፡ ሲመለስም በሠረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር፡፡ መንፈስም ፊልጶስን “ሂድ ወደዚህ ሠረገላ ቅረብ” አለው፡፡ ፊልጶስም ፈጥኖ ወደ ሠረገላው ሂደ፤ ጃንደረባውም የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰምቶ “ለመሆኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን?” አለው፡፡ ጃንደረባውም “የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት አድርጌ አስተውለዋለሁ” አለው፤ ቅዱስ ፊልጶስም ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሰበከለት፡፡ በመጓዝ ላይ ሳሉም ውሃ ካለበት ስፍራ ደረሱ ጃንደረባውም “እነሆ ውሃ እዚህ አለ ታዲያ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምን ነገር አለ?” አለው፡፡ ፊልጶስም “በፍጹም ልብህ ካመንህ መጠመቅ ትችላለህ” አለው፡፡ ጃንደረባውም ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምናለሁ›› ሲል መለሰለት፤ ሠረገላውም እንዲቆም አዘዘ፡፡‎‎ከዚያም ሁለቱም አብረው ወደ ውሃው ወረዱ፤ ፊልጶስም ጃንደረባውን አጠመቀው፡፡ ከውሃውም በወጡ ጊዜ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ነጥቆ ወደ አዛጦን ወሰደው። ሐዋ 8፣ 26-39። ወደ ቂሣርያ እስኪመጣ ድረስም በእየከተሞቹ ሁሉ እየተዘዋወረ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ በቂሳርያ ሳለ ሚስት አግብቶ 4 ሴቶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ሀብተ ትንቢት የተሰጣቸው ደናግናል ነበሩ፡፡ ሐዋ 21፣8። በረጅም የወንጌል አገልግሎቱ ብዙ አይሁድን እና ሳምራዊያንን ወደ ክርስትና መልሶ ጥቅምት 14 ቀን በሰላም ማረፉን የታረክ መዛግብት ይናገራሉ፡፡‎‎የሐዋርያው የቅዱስ ፊሊጶስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን! መጋቤ ምሥጢር ጥበቡ አናጋው ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም

‎”በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ” (ሐዋ 6:3)‎በዚህ የአባቶቻችን የሐዋርያት መመሪያ መሠረት ከተመረጡ አገልጋዮች መካከል አንዱ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ ነው። Read More »

ጾመ ፍልሰታ/ጾመ ማርያም/

ፍልሰታ ማለት ፈለሰ፤ተሰደደ፤ተጓዘ፤ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ «ፈለሰት ማርያም እምዘይበሊ ኀበኢይበሊ፤ ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት፣ ተሻገረች» በማለት ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጓሜ አመሥጥሮ ገልጾታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የዕረፍት ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እመቤታችን በዚህ ዓለም ፷፬ ዓመታትን በሕይወተ ሥጋ ከቆየች በኋላ ጌታችን የእናቱን ተድላ ነፍሷን እንጂ ተድላ ሥጋዋን አይወድምና ጥር ፳፩ ቀን ፵፱ ዓመተ ምሕርት አረፈች፡፡ ዕረፍቷም እንደሌላው ሰው በሕማምና በድካም አይደለም፡፡ በገነት ዕፀዋት መዓዛ ተመስጣ ቅድስት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታለች፡፡ ታሪኩ በነገረ ማርያም እንደተጻፈው ሐዋርያት እመቤታችንን በአጎበር አድርገው አክብረው ወደጌቴሴማኒ መካነ መቃብር ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉም ነበርና ቀድሞ ልጇን ተነሣ ዐረገ እያሉ ሲያውኩ ኖረዋል፤ እርሷን ደግሞ ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነውና «ኑ የማርያምን ሥጋ በእሳት እናቃጥለው» ብለው በምቀኝነት ተነሱ፡፡ ከመካከላቸው አንድ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ ዘሎ ሄዶ የአልጋውን ሸንኮር ሲይዝ የታዘዘ መልአክ በረቂቅ ሰይፉ እጆቹን ቆረጠው፡፡ እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ የምሕረት እናት የሆነችው ድንግል ማርያም ቅዱስ ጴጥሮስ ጸልዮ እጆቹን እንዲመልስለት ነግራው እንደነበረ አድርጎለታል፡፡ የእመቤታችን ሥጋዋን መላእክት ከዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ወስደው አስቀምጠውታል፡፡ ሥጋዋ ያለበትን ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እነርሱ ባለማየታቸው እመቤታችን ባረፈች በ፮ኛው ወር ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ፲፬ ቀን ድረስ ከጾሙ በኋላ በ፲፬ኛው ቀን ሥጋዋን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በጌቴሴማኒ ባለው መቃብር ቀብረውታል፡፡ ከዚህ በኋላ እንደ ልጇ በ፫ኛው ቀን ተነሥታ መላእክት እየዘመሩላት ወደሰማያት ስታርግ፤ ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሰ ዕርገቷን በማየቱ መላእክት «እመቤትህ እርሷ ናት፤ስገድላት» አሉት፤ እርሱም «ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይላል፤ከደመናው ሊወድቅ ወደደ» ምክንያቱም ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ፤ዛሬ ደግሞ የእርሷን ትንሣኤ ለማየት ብሎ ነው፡፡ እመቤታችንም «ትንሣኤየን ያየህ አንተ ነህ ሌሎቹ አላዩም» ብላ ሐዋርያት ገንዘው የቀበሩበትን የሐር ግምጃ ሰጥታ አጽናንታ ሰደደችው፡፡ ቅዱስ ቶማስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ ብሎ ጠየቃቸው፤እነርሱም አግኝተው እንደቀበሯት ነገሩት፤ እርሱም ያየውን ምሥጢር በልቡ ይዞ «ሞት በጥር፤ በነሐሴ መቃብር፤ ለሰሚውም አያምር፤ይህ እንዴት ይሆናል?»፤ ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ «ድሮም አንተ ተጠራጣሪ ነህ፤ማን ያርዳ የቀበረ፤ ማን ይናገር የነበረ እንዲሉ፤ ገንዘን የቀበረን እኛ እያለን እንዴት ትጠራጠራለህ» ብለው ወደ መቃብሯ ሄደው መቃብሯን ቢከፍቱት ባዶ ሆኖ አገኙት፡፡ በዚህ ተደናግጠው ተያዩ፤ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቶማስ «አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነሣች፤ዐረገች፤ ይኸው ምልክቱ» ብሎ ገንዘው የቀበሩበትን ሰበን አሳያቸው፤እነርሱም አምነው ሰበኗን ለበረከት ተካፈሉት፡፡ በዓመቱ ነሐሴ ፩ ቀን ሐዋርያት በመንፈሰዊ ቅናት ተነሳስተው «ቶማስ ትንሣኤዋን አይቶ እኛ ሳናይ እንዴት ይቀርብናል» በማለት ነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ ጀምረው በ፲፮ኛው ቀን የሐዋርያትን ሱባኤ ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር ጴጥሮስን ተራዳኢ፣ ካህን እስጢፋኖስን ሠራዔ ዲያቆን አድርጉ ቀድሶ አቅርቧቸዋል፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላም ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፭ ቀን ጾመ ፍልሰታ ተብሎ ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ይጾመዋል፡፡ የጾሙና የትንሣኤዋ በረከት ተካፋይ ያድረገን፤አሜን።

ጾመ ፍልሰታ/ጾመ ማርያም/ Read More »

የአቋም መግለጫ

“ዝክረ ወንጌል ወዝክረ ሊቃውንት”በሚል መሪ ቃል በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ከትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ ጋር በመሆን ያዘጋጀው የሁለት ቀናት የምክክር ጉባኤ የአቋም መግለጫ አውጥቷል የአቋም መግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል፦ “ዘአዘዞሙ ለአበዊነ፡፡ ከመ ይንግሩ ለደቂቆሙ፡፡ ወከመ ያእምር ካልእ ትውልድ፡፡ ደቂቅ እለ ይትወለዱ ወይትነሥኡ፡፡ ወይዜንው ለደቂቆሙ፡፡” ለልጆቻቸው ያስታወቁ ዘንድ ለአባቶቻችን ያዘዘውን….የሚመጣ ትውልድ የሚወለዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ ተነሥተው ለልጆቻቸው ይነግራሉ” መዝ 77 ቁ 5-6 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊት ታሪካዊትና ሐዋርያዊት እንደመሆንዋ የዕለት ከዕለት ሥራዋንና አስተዳደርዋን የምታራምደው ቅዱሳን አበው ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በወሰኑት ፍትሕ መንፈሳዊ ነው፡፡ እምነትዋን የምታስፋፋበት፣የምታስተምርበትና የምታጸናበትን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜ ተሰብስቦ በመምከር የጠመመውን በማቅናት የቀናውን በማጽናት በሚሰጠው ውሳኔና በሚያወጣው የሥራ መመሪያ መሠረት ነው፡፡ ይህን ውሳኔና መመሪያ አስፈጻሚው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሥሩ በሚመራቸው መምሪያዎችና የሥራ ክፍሎች አማካኝነት፡- የቤተ ክርስቲያኒቱ ልዕልና በሁሉም ዘንድ እንዲታወቅና እንዲከበር ያደርጋል፣ ቤተ ክርስቲያን ባላት መብት መሠረት ሕልውናዋን ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ይሠራል፣ ሕጓና ሥርዓትዋ እንዲከበር፣በአንድነትዋና በአላማዋ ጸንታ እምነቷ እንዲስፋፋ የሥራ ዕድገቷ ተፋጥኖ ግቡን ይመታ ዘንድ ዕለት በዕለት ይሠራል፣ ሕዝበ ክርስቲያኑ ማግኘት የሚገባውን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለማሟላት በሚቻልበት ጉዳይ በማተኮር ጉዳዮችን እየመረመረ በሥራ የሚተረጎሙበትን የሥራ አፈጻጸም መመሪያ ከሚሰጥባቸው መምሪያዎች መካከል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያና የትምህርት ማሰልጠኛ መምሪያ በጋራ “ዝክረ ወንጌል ወዝክረ ሊቃውንት” በሚል ርዕስ መምሪያዎቹ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሥራ መዋቅር የተጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ያልተቆጠበ ጥረት በማድረግ የጉባኤውን ተሳታፊዎች በሙሉ ደስ ያሰኘ ትልቅ ሥራ ከሰኔ 24 ቀን እስከ ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ዕለታት ሠርተዋል፡፡ የመርሐ ግብሩም አፈጻጸም በሚገባ ከዋናው መ/ቤት ከየአህረ ሰብከቱ ተመርጠው ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ በማድረግ፣ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዩኒቨርሲቲዎች፣ኮሌጆች፣ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፤ከአዲስ አበባ ክፍላተ ከተሞች ከገዳማትና አድባራት የተመደቡ ሊቃውንት የአብነት ትምህርት መምህራን፣ሰባክያነ ወንጌል (ላዕካነ ወንጌል) በአጠቃላይ በምክክር ጉባኤው የተሳተፉ ምሁራን የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት የሚያስገነዝብ ትምህርታዊ ጥናትና መወያያ ርእሶች ተቀርጸው የቤተ ክርስቲያናችንን ሁለንተናዊ ተልዕኮ ከሥልጠና እስከ ተልዕኮ ማስፈጸም ድረስ ያለውን ሐዋርያዊ ግልጋሎት ውስጣዊውን ገጽታ በዳሰሰ መልኩ በቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ መስክ በቂ ግንዛቤ ዕውቀትና ችሎታ ባላቸው ሊቃውተ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት የቆየውን ልምዳቸውና ዕውቀታቸውን አሁን ላይ ካለው አካሄዳችንና አገልግሎታችን አንጻር የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ለሆነው ሁሉ እኔ ማነኝ ብሎ መጠየቅ እስኪያስችል ድረስ በጥናታዊ ጽሑፍ የተደገፈ ትምህርት ተሰጥቷል፤በችግሩም ዙሪያ ያተኮሩ መጠይቆች ተነስተዋል፤ በመምህራኑም በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶናል፡፡ ውይይቱም ሰፊና ጠቃሚ ሐሳብ ማሰባሰብ ያስቻለ ስለሆነና የምክክር ጉባኤው ተካፋዮችም በቅዱስነታቸው የተሰጠንን መመሪያና ቃለ ምእዳን ከብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ የተላለፈውን የሥራ አፈጻጸማዊ መመሪያ የጉባኤውን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ሲመሩት ከነበሩት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ሊቀ ጳጳስ የጉባኤ አመራርና ማብራሪያዎች ጥናታዊ ጽሁፍ አቅራቢዎች ከሆኑት ምሁራነ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠንን መመሪያና ከምክክር ጉባኤው ባገኘነው ጠቃሚ ትምህርት መሠረት የሚከተለውን ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡ ጉባኤያችን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተ/ሃይማኖት የተላለፈውን የመክፈቻ ቃለ ምዕዳን፣ከብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ የተሰጠውን የሥራ መመሪያና ጥናት አቅራቢዎች ያቀረቡትን ጥናታዊ ጽሑፎች በሥራ ለማዋል ቃል እንገባለን፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ከቅዱስ ፓትርያርኩና ከዋናው መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሚወጡት ሕጎችና መመሪያዎች፣እንዲሁም ስለ ስብከተ ወንጌልና ትምህርትና ሥልጠና የሚተላለፉትን ትዕዛዞች በየአህጉረ ስብከቱና በቤተ ክርስቲያኗ ተቅዋማት ሁሉ በተግባር እንዲውሉ ቃል እንገባለን፣ እነዚህ መምሪያዎች የቤተ ክርስቲያኗን ሁለንተናዊ ተልዕኮ ለማሟላት የወሰዱትን የሥራ ተነሳሽነትና ኃላፊነትን በጋራ የመወጣት ልምዳቸው የሚበረታታ ስለሆነ በዚሁ መልኩ ተቀራራቢ የሆኑ የቤተ ክርስቲያኗ የሥራ መዋቅር ክፍሎች በጥምር የሚያስፈጽሙበት አሠራር መዘርጋት የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ ተልዕኮ ስለሚያማክልና የጉባኤው ተሳታፊዎችም የምንደግፈው ስለሆነ በአፈጻጸም ረገድ የሚጠበቅብንን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁነታችንን እንገልጻለን፡፡ የአብነት ት/ቤቶች እየተስፋፉ መሆናቸው ግልጽ ነው፤እነሱን ያግዙ ዘንድ የተቋቋሙት ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆችም በንባብ፣በቅዳሴ፣በዜማና በመጻሕፍት የትምህርት ዘርፍ እያደጉ የሚገኝበት ወቅት ስለሆነ ተመርቀው የወጡት ደቀ መዛሙርትም ከዋናው ማእከል ጀምሮ በየአህጉረ ስብከቱና ከተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቅዋማት በአገልግሎትና በኃላፊነት የሚገኙበት ወቅት ላይ መድረሳችን የቤተ ክርስቲያናችንን ሁለንተናዊ ዕድገቷን የሚያሳይ በመሆኑ አሁንም በየጊዜው በጥናት የተደገፈ ሥልጠና በመስጠት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላችን አስተዋጽኦ ለመወጣት ዝግጁነታችንን እንገልጻለን፡፡ ቋሚ የቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ ትምህርት ለማጠናከር፤የመምህራንና የደቀ መዛሙርትን ኑሮ ለመደገፍ በየአካባቢው በየአህጉረ ስብከቱ በቂ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ዘገባዎች ቢያመለክቱም በውስጣዊ የአመራርና ውጫዊ ሁኔታዎች አንዳንድ ችግሮች የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መምህራንን ለፍልሰት እያደረጉ ስላሉ ለወደፊቱ መምህራኑ በየአካቢያቸው ወንበራቸውን አጽንተው ደቀ መዛሙርቶቻቸውን በሁለንተናዊ ስብእና ክብር አስታጥቀው እንዲያወጡ በመሥራት የበኩላችንን አደራና ኃላፊነት እንወጣለን፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን መሠረታዊ ትምህርት ዜማ፣ቅዳሴና ቅኔና ትርጓሜ መጻሕፍት የሚማሩ ደቀ መዛሙርት ለትምህርተ ወንጌልበአርያነት ለሚጠቀስ ለመንፈሳዊ አስተዳደር ለቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና ለቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች ጊዜውን የዋጀ መምህራን ለማግኘት የሥርዓተ ትምህርት ዳሰሳዊ ጥናት የቤተ ክርስቲያኗን ባለሙያዎችና ሌሎች አጋዥ ኃይሎች በማሳተፍ እንዲቀርብ በተደጋጋሚ በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነ ስለሆነ እነዚህ ሁለቱም መምሪያዎች ሆኑ ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ተባብረውበት ማኅደረ ጉዳዮች ታይተው የቀሩትን ተግባራት ወደ ሥራ ለማስገባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝና ለመወጣት ቃል እንገባለን፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ምንጊዜም ሐዋርያዊ አገልግሎቷን ያላቋረጠች መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቷም በውጭው ዓለም በሚገኙ ክፍላተ ዓለማት ጭምር መስፋፋቷ በእግዚአብሔር ረድኤት እየቀጠለ ስለሆነ የቤተ ክርስቲያኗ ወገኖች የሆን ውሉደ ክህነትና ውሉደ ክርስቲያን ለሐዋርያዊ ተልዕኮዋ መፋጠን የእምነት ተከታዮቿንም ምእመናን ለመጠበቅ የጋራ አሠራር በያዘ መልኩ በውስጣዊና ውጫዊ አሠራራችንና ግንኙነታችን ሁሉ ከመምሪያዎቹም የሚተላለፉ የሥራ መርሐ ግብሮችን ለማስፈጸም ቃል እንገባለን፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያት የሰጠውን ታላቁን ሐዋርያዊ ተልእኮ ተቀብላ በሐዋርያት አሠረ ፍኖት ተገብታ በባለቤትነት ታስፈጽማለች። ነገር ግን ከእኛ ከአገልጋዮች የእውቀት እና የቁርጠኝነት ማነስ እንዲሁም ከአንዳንዶቻችን ጥቅም ተኮር እንቅስቃሴ የተነሳ ይህንን ታላቅ ተልእኮ ለመፈጸም የተቸገርን ቢሆንም ከዚህ በኋላ በተቻለን መጠን ለመማር፣የተማርነውን ለማስተማር ፣ለማሳመን፣ ከመንጋው ለመቀላቀልና ለመንከባከብ በሚደረገው ማንኛውም ጥረት ከቤተክርስቲያን ጎን ለመቆም ቃል እንገባለን። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ለሀገራችን ለዘመናት ሃይማኖትንና ታሪክን ስታስተምርና ስትዘግብ ብራና ዳምጣ፣ቀለም በጥብጣ፣የራሷን ፊደል ቀርጻ፣ የራሷን ቀመር ቀምራ ለቁጥር የሚያዳግቱ መጻሕፍትን ጽፋለች፤ እየጻፈችም ነው። ነገር ግን አባቶቻችን የጻፏቸው መጻሕፍት በየገዳማቱ ግምጃ ቤት ሆነው ለጉብኝት አገልግሎት ከመዋል ባሻገር ለጥናትና ምርምር ክፍት ተደርገው ለማኅበረሰቡ መድረስ ባለመቻላቻው በዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ በሚገኙ አንዳንድ ወገኖች ቤተክርስቲያንን መጻሕፍት አልባ ከማስመሰሉም በላይ የትምህርት ተቋማቶቻችን የአባቶቻችን ወዝ ባልካቸው መጻሕፍትና ታሪክ አልባ ተሞልተዋል የሚል ስሞታ እንዳለ ተገልጿል፤በመሆኑም ይህንን ችግር ለመቅረፍ ቤተ ክርስቲያን ለምታደርገው ጥረት ጥናትና ምርምር በመሥራት በሁሉም ዘርፍ ከቤተክርስቲያን ጎን ለመቆም ቃል እንገባለን። ቅድስት ቤተክርስቲያን የሁሉ እናት እንደመሆኗ መጠን ዘር ቀለም ጎሳ ሳትለይ እናቴ ብሎ የመጣውን ሁሉ አቅፋ የያዘች፣ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያን ከመሆኗ ባሻገር የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን የምታቀብል መሆኗ የሚታወቅ ነው፤ነገር ግን ከላይ እስከታች የምንገኝ የቤተክርስቲያን ኃላፊዎች በጠረፋማ ሥፍራ የሚኖሩ ሰዎችን ወንጌል ለማስተማር የምናደርገው ጥረት ጅምሩ የሚበረታታ ቢሆንም ፍጹም ሥራ መሥራትን፣ ለሌሎች ዓለማትም መትረፍን የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን በጉባኤው ከተሰጠው ዐውደ ጥናት ተረድተናል፤ በመሆኑም እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የሁሉ እናትነት መላልሶ ለማስተማርና ለመላላክ የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ቃል እንገባለን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ

የአቋም መግለጫ Read More »

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜዎች

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜዎች ከትንሣኤ ሌሊት ፩ ሰዓት ጀምሮ እስከ ዳግም ትንሣኤ ያለው ሳምንት የፉሲካ ምሥጢር የተገለጠበት፤ ከግብፅ ወደ ምድረርስት ከሲኦል ወደ ገነት መሻገርን የሚያመላክት ሳምንት ነው። ለፉሲካ የሚታረደውም በግ ፉሲካ ይባላል (ዘዳ. ፲፮÷፪:፭÷፮)፤ ፉሲካ ማለት ደግሞ ማለፍ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትም ሳምንት የፉሲካ ሳምንት ነበር፤ (ሉቃ. ፳፪፥፲፬-፲፮፤ ዮሐ. ፲፰፥፴፰-፵)። እርሱም ንጹሕ የእግዚአብሔር በግ ሆኖ ደሙን ስላፈሰሰልን ፉሲካችን ክርስቶስ ተባለ፤ ብሉይ ደግሞ የሐዲስ አምሳል ነው። ይኸውም ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ ባሕረ ኤርትራን ካሻገራቸው በኋላ ወደ ምድረ ርስት፤ ነፍሳት ደግሞ በክርስቶስ መሪነት ከሲኦል ወደ ገነት መግባታቸውን የሚገልጽ ነው፡፡ ዕለቱም ሙሴ የወልደ እግዚአብሔር፤ በትረ ሙሴ የመስቀል ምሳሌ፤ግብፅ የሲኦል፤ የገሃነመ እሳት፤ የፈርዖን የዲያብሎስ፤ ሠራዊቱ የሠራዊተ ዲያብሎስ፤ እስራኤል የምእመናንና ባሕረ ኤርትራ የባሕረ ሲኦል ምሳሌ ነው፡፡ ሰኞ– ማዕዶት (ፀአተ ሲኦል) ማዕዶት የቃሉ ትርጓሜ መሻገር ሲሆን፤ በዚህ ቀን ቤተ ክርስቲያን ነፍሳት በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ከሞት ወደ ሕይወት፤ ከሐሳር ወደ ክብር፤ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሲኦል ወደ ገነት መሻገራቸውንና ፉሲካችን ክርስቶስ መሆኑን ታስባለች። ማክሰኞ– ቶማስ ቅዱስ ቶማስ በጦር የተወጋ ጎኑን፤ በቀኖት የተቸነከረው እጁንና እግሩን ካላየሁ አላምንም በማለቱ ክርስቶስም «ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤እጅህንም አምጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን» ብሎታል። ቶማስም «ጌታዬ አምላኬም»፤ ብሎ በመለሰ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስም «ስለ አየኸኝ አመንህን? ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓንስ ናቸው» አለው (ዮሐ ፳፥፳፯-፳፱)፤ ቶማስ የጌታን ፍቅር ተገንዝቦ ትንሣኤውን ስላመነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዕለቱን ቶማስ ብላ ታስበዋለች። ዲዲሞስ የተባለ ከአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙር አንዱ ቶማስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዝግ ቤት ገብቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ባላቸው ጊዜ ከእርሳቸው ጋራ አልነበረም»። ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ (ማቴ. ፲፥፪-፫) ቶማስ በአራማይክ ዲዲሞስ በግሪክ መንታ ማለት ነው፤ (ዮሐ. ፳፥፳፬)፡፡ ቶማስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በፋርስና በሕንድ ወንጌልን እንዳስተማረ ይነገራል። ለቶማስ ጎኑን እንዲዳስስ የፈቀደው ለሌሎችም ቅዱሳን ሐዋርያት የተቸነከረውን እጅና እግሩን ያሳየው ካህናት ሥጋውና ደሙን እንዲፈትቱ ነው፤ ዮሐንስም በእጃችን ዳሰስነው ብሏል፤ (ሉቃ. ፳፬፥፴፱)፡፡ ለማርያም መግደላዊት ግን የተነሣ ዕለት አትንኪኝ ማለቱ ለሴቶች ሥጋውን ደሙን መፈተት አልተፈቀደም ሲል ነው ብለው ሊቃውንት ያትታሉ፤ «አትንኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሂጅና፡- ወደ አባቴ÷ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ÷ ወደ አምላካችሁም አርጋለሁ አለ ብለሽ ንገሪአቸው» አላት፤ (ዮሐ. ፳፥፲፯)። ገቦ መለኮቱን የዳሰሰች እጁ በሕይወት ትኖራለች፤ በሕንድ ሀገር ከታቦት ጋር በመንበር ላይ ትኖራለች። በየዓመቱ በእመቤታችን በዓል በአስተርእዮ ሊያጥኑ ሲገቡ የሚሾመውን ወጥታ ቀኝ እጁን ትይዘዋለች፤ ዓመት አገልግሎ ያርፋል። ረቡዕ –አልዓዛር አልዓዛር ክርስቶስ ያስነሣው የማርያምና የማርታ ወንድም ነው፤ የስሙም ትርጓሜ እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው፤ (ዮሐ. ፲፩፥፯-፵፰)፤ አልዓዛር የሞተው መጋቢት ፲፯ ነበር፡፡ እህቶቹም ክርስቶስ እንዲመጣ መልእክት ልከውበት ነበር፤ ክርስቶስ ግን በ፬ኛው ቀን ማለትም መጋቢት ፳ መጥቶ ከሞት አስነሥቶታል፤(ዮሐ.፲፩፥፵፬)፡፡ ፋሲካውንም በወዳጁ በአልዓዛር ቤት ያከብር ዘንድ ከቀደ መዛሙርቱ ጴጥሮስንና ዮሐንስን አስቀድሞ ላከ፤ ከዚያም በአልዓዛር ቤት ሆኖ የሐዲስ ኪዳንን ሥርዓት ምሥጢረ ቁርባንን ሰርቶ ለደቀ መዛሙርቱ አሳያቸው፤ አልዓዛር ከተነሣ በኋላ በሐዋርያት ኤጲስ ቆጶስነት ተሸሞ ፵ ዓመት አገልግሎ ግንቦት ፳፯ ቀን ዐርፏል (ስንክሳር ግንቦት ፳፯)፡፡ አዳም ሐሙስ አዳም የመጀመሪያ ሰውና የሰው ሁሉ አባት ነው፤ በ፮ኛው ቀን የተፈጠረ የሰው ሁሉ ምንጭ ስለሆነ የሰው ዘር ሁሉ ከእርሱ ተገኝቷል፡፡ በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው የተስፋ ቃል ስለመፈጸሙ፤ (ዘፍ. ፫÷፲፭) አዳም ከነልጆቹ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻ ስለመውጣቱ ይታሰብበታል፡፡ ክርስቶስ በተነሳበት በአምስተኛው ቀን ሐሙስ አዳም ይባላል፤ ጌታችን አዳምን ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ብሎ ቃል ገብቶለት እንደነበር በቀሌምንጦስ ተጽፏል፡፡ አዳምና ሔዋን በገነት ፯ ዓመት ከቆዩ በኋላ ትእዛዙን በመተላለፋቸው ከኤደን ገነት አስወጣቸው (ኩፋ.፬፥፲፮፤ዘፍ.፫፥፳፫) «ብዙ ተባዙ» ያለው ቃል እንዳይቀር በምድር ላይ ወርደው ልጆችን ወለዱ ይላል፡፡ የተወለዱትም ልጆችም በቁጥር ፷ እንደሆኑ (፩መቃ. ፳፰፥፮) የተወለዱት ልጆች ደጎችና ክፉዎች እንደ ነበሩ በአቤልና በቃየል ታውቋል፤ (ዘፍ. ፬፥፰)፤ አዳም በዚህ ዓለም ፱፻፴ ዓመት ኑሮ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ፵፻፭፻፸ ሚያዚያ ፮ ዐርፏል፡፡ ዐርብ– ቤተ ክርስቲያን ዐርብ የእግዚአብሔር ቅድስት ማደሪያ በሆነችው ቤተ ክርስቲያን ተሰይማለች፤ ይህም ሁሉም ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመባት ዕለት በመሆኗ ነው፤ ዕለተ ዐርብ፤ የሥራ መከተቻ፤ ምዕራብና መግቢያ በሚሉት ስያሜዎችም ትጠራለች፡፡ በዕለቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ያደረገውን ተአምር በመስቀሉ ድኅነትን እንዳሳየ፤ በቀራንዮ የሕንጻዋ መሠረት እንደተተከለላትና ሥጋ መለኮት እንደተቆረሰላት፤ ልጆቿን ከማሕፀነ ዮርዳኖስና ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ የምትወልድበት ማየ ገቦ እንደፈሰሰላት ተገልጾባታል፤(ኤፍ.፪፥፲፱፤ራዕ.፩፥፮-፰)፡፡ ቅዳሜ– ቅዱሳት አንስት ቅዳሜ ቅዱሳት አንስት ተብሎ ይጠራል፤ ይህም ስያሜ በስቅለት ዕለት በልቅሶና በዋይታ የሸኙትን፤(ሉቃ. ፳፫፥፳፯) በዕለተ ትንሣኤ ሽቱና አበባ ይዘው ወደ መቃብር የገሰገሱትን፤ ከሁሉም ቀድሞ ጌታችን በዕለተ ሰንበት ተነሥቶ ለተገለጸላቸው ማርያም መግደላዊት፤ የታናሹ ያዕቆብ እና የዮሳ እናት ማርያም፤ የዘብዴዎስም የልጆቹ እናት ሰሎሜንም መታሰቢያ ለማድረግ ነው፤«ከሳንምንቱ በመጀመሪያዩቱ ቀን ያዘጋጁትን ሽቶ ይዘው እጅግ ማልደው ወደ መቃብሩ ሄዱ፤ሌሎች ሴቶችም አብረዋቸው ነበሩ (ሉቃ. ፳፬ ፥ ፩ )፡፡ እሑድ– ዳግም ትንሣኤ «ያም ከሳምንቱ የመጀመሪያው ቀን በመሸ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን ስለ ፈሩ ተሰብስበው የነበሩት ቤት ደጁ ተቆልፎ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ መጥቶ በመካከላቸው ቆመና÷«ሰላም ለእናንተ ይሁን» አላቸው፤ ማቴ.፳፥፲፱፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ተሰውሮ ከሰነበተ በኋላ በዕለተ እሑድ በዝግ ቤት እንዳሉ ዳግም ተገለጸላቸው፤ስለዚህም ዳግም ትንሣኤ ተባለ፡፡ (ምንጭ:-መዝሙረ ማኅሌት ወቅዳሴ፤ ሥርዓተ አምልኮ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፤ የዮሐንስ ወንጌል አንድምታ፤ ምዕ. ፳፥፳፬)

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜዎች Read More »

“ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አታሸነፍ” (ሮሜ ፲፪፥፳፩)

“ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አታሸነፍ” (ሮሜ ፲፪፥፳፩) መምህር ሳምሶን ወርቁጥር ፲፯፤ ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት ክፉና በጎ የሰው ልጆች ባሕርያት ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር ለመልካም ነበረ፡፡ (ዘፍ.፩፥፲፪) ምንም እንኳን የፍጥረት አክሊል የሆነው ሰው ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ ከብርሃን ጨለማን፣ ከሕይወት ሞትን፣ ከመታዘዝ አለመታዘዝን ቢመርጥም እግዚአብሔር አምላክ የፈጠረው ስሙን እንዲቀድስ ክብሩን እንዲወርስ ነበረ፡፡ ለዚህም ክፉና ደጉን መለየት ይችል ዘንድ አስቀድሞ የሚያስተውል አእምሮ ሰጥቶት ነበር፡፡ በኅሊናው መመራት ተስኖት የሰው ልጅ ከወደቀ በኋላ ዳግመኛ የተጻፈ ሕግ ሰጥቶታል፡፡ ሰዎች ራሳቸው ላይ የክፉ ብድራት እንዳይደርስባቸው አስበው በባልንጀራቸው ላይ ክፉ እንዳያደርጉ ክፉ ላደረጉ የክፉ ብድራት እንዲከፈላቸው ሙሴ ሕግን ጻፈላቸው፡፡ ክፉ የሚያደርጉ ሁሉ ቅጣት ነበረባቸው፤ “ሕይወት በሕይወት፥ ዓይን በዓይን፥ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር፥መቃጠል በመቃጠል፥ቍስል በቍስል፥ ግርፋት በግርፋት ይከፈል” እንዲል። (ዘፀ.፳፩፥፳፬) በተመሳሳይ ሙሴ ለእስራኤል ሲናገር “ሰውም ባልንጀራውን ቢጐዳ፥እርሱ እንዳደረገ እንዲሁ ይደረግበት። ስብራት በስብራት ፋንታ፥ዓይን በዓይን ፋንታ፥ጥርስ በጥርስ ፋንታ፥ሰውን እንደ ጐዳ እንዲሁ ይደረግበት። እንስሳውንም የሚገድል ካሳ ይተካ፤ ሰውንም የሚገድል ይገደል” በማለት ሕግን አስተምሯል፡፡ (ዘሌ.፳፬፥፲፱) የሕግ መምህር ሐጋጌ ሕግ የሆነው አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመንግሥቱን ወንጌል በመዋዕለ ሥጋዌው ሲያስተምር አስቀድሞ የነበረው በሙሴ የተነገረው እንዳለፈ ሲናገር “ዓይን ለዓይን ጥርስ ለጥርስ እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ እኔ ግን እላችኋለሁ ክፉን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጨህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤ እንዲከስህም እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት፤ ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ፡፡” (ማቴ.፭፥፴፰) ክፉን በክፉ ሳይሆን በበጎነት ማሸነፍ እንደሚገባ ያስተምረናል፡፡ ክፉን በክፉ መመለስ ምን ያስከትላል? ዛሬ ላይ በቤተሰባዊ ሕይወታችን ባል በሚስት፣ ሚስት በባል፣ ወላጆች በወላጆች፣ ልጆች በወላጆች ላይ በክፋት ተነሣስተው አንዱ ሌላው ላይ “እንዲህ አደረጉ ሲባል እንሰማለን፡፡ ለጥፋታቸው እንዲህ አድርጋኝ ነው፤ እንዲህ አድረጎኝ ነው” የሚሉ ምክንያቶችን ሲደረድሩም እንሰማለን፡፡ ክፉን በክፉ መቃወም ሰዎችን የበለጠ እልኸኛ ያደርግ ይሆናል እንጂ ክፉ አድራጊዎችን ከክፋት ለመመለስ አይችልም፡፡ ክፉን በክፉ በመመለስ ሰዎች በመካከላቸው ያለውን ግንኙነትን ማቋረጥ፣ ከዚያም ባለፈ ትልቁን ተቋም ቤተሰብ እስከማፍረስና ልጆች እስከመበተን ያደርሳቸዋል፡፡ ክፉን በክፉ መመለስ ለጊዜው የአሸናፊነት ስሜት በመፍጠር ደስ የሚያሰኝ ቢመስልም ፍጻሜው ጸጸት ነው፡፡ አንዳንዶች ደረሰብኝ ለሚሉት ክፉ ነገር በክፉ መልሰው ከጸጸት ለመሸሽ ሲሉ አደንዛዥ ዕፅንና መጠጥን መደበቂያ የሚያደርጉት ለዚህ ነው፡፡ እንደሀገርም ከገባንበት የፖለቲካ አዙሪት መውጣት የተሳነን ክፉን በክፉ የመመለስ ደዌ ስለተጠናወተን ነው፡፡ ይህ ደግሞ እንደ ሀገር ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን አሳጥቶ ሁለንተናዊ ቀውስ እያስከተለብን ይገኛል፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ ግለሰቦችና ቡድኖች “ደረሰብን ቆመንለታል” በሚሉት ማኅበረሰብ ላይ ደረሰ ለሚሉት ክፉ ነገር አማራጭ መፍትሔ አድርገው የሚያስቡት መልሶ ክፉን በክፉ መመለስ የሆነው ለዚህ ነው፡፡ ክፉን በክፉ መመለስ ለተጠቃው አካል ምን ይጨምርለታል? መቼስ ይህንን ለመረዳት የተለየ ዕውቀት አይጠይቅም፤ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው፡፡ ክርስቲያን መሆን ደግሞ ተጨማሪ ኃላፊነት ነው፡፡ የደረሰብን ክፉ ነገርን በክፉ እንዳንመልስ የወንጌል ሕግ ግድ ይለናል፡፡ “ተወዳጆች ሆይ፥ራሳችሁ አትበቀሉ፥ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፏልና።” (ሮሜ ፲፪፥፲፱) ክፉን በመልካም መመለስ ለጠላት ጊዜያዊ ድል ሊያስገኝ ይችላል! ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ አንጻራዊ ሰላም አግኝታ ይሆናል እንጂ ከክፉዎች ፍላጻ ዕረፍት ያገኘችበት ዘመን አለ ማለት ይቸግራል፡፡ በተለይ አሁን ባለንበት ዘመን የክፉዎች ጥቃት ተቋማዊ ሆኖ አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠል፣ የምእመናን ደም ማፍሰስና ማሳደድ በስፋት እየተመለከትን ነው፡፡ ምንም እንኳ ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ መሥዋዕትነት ሀገርን አጽንታ ብታቆይም መብቷን በድርድር በቸሮታ እንድትቀበል ለማድረግ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ከመሀል ሀገር እስከ ጠረፍ እየተመለከትን ነው፡፡ በጌታችን ሞት እንደተባበሩት እዚህም እዛም ከኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖት በአፍአ ያሉ የእምነት ቡድኖች ተባብረው ቀድሞ የነበረውን ስውር ጦር በግልጽ መወርወር ጀምረዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን በዓላትን በዐደባባይ የምታከብራቸውን ቦታዎች ላይ የይገባኛል ጥያቄ ማንሳት፣ በበዓላት ላይ እንዲህ ዓይነት ቀለም ለበሳችሁ በማለት ምእመናንን ማንገላታት ማስቆጣት፣ ምክንያት እየፈለጉ በኦርቶዶክሳዊ ማንነት ማሸማቀቅ፣ መደብደብ ፣ ማቁሰልና መግደል የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡፡ ይህ ሁሉ ጠላት ለጊዜው ድል ያገኘ እንዲመስለው ያደርግ ይሆናል እንጂ ፍጻሜው ጥፋት ውድቀት ነው፡፡ “የፍጹም ሰው ጽድቁ መንገዱን ያቀናለታል፤ ኃጥእ ግን በኃጥአቱ ይወድቃል” እንዲል፤ (ምሳ.፲፩፥፭) ለጊዜው ከፍ ከፍ ብሎ መታየቱ የውድቀቱ መጀመሪያ እንደሆነ ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡ “ኃጥእን ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት፡፡ ብመለስ ግን አጣሁት ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም” እንዲል፡፡ (መዝ.፴፯፥፴፭) ክፉን በመልካም መመለስ ትዕግሥታችንን ይፈትናል! ባለንበት ዘመን አብያተ ክርስቲያናት እንደ ጣፍ ሲነዱ፣ ንዋየ ቅድሳት እንደ ደረቅ እንጨት ሲማገዱ፣ አገልጋይ ካህናትና ምእመናን እንደ መጻተኛ ሲሳደዱ፣ ይባስ ብሎ እንደ በግ ሲታረዱ፣ ደማቸው ክረምት ከበጋ እንደማይደርቅ ጅረት ሲፈስ እየተመለከተ የማይቀና ኦርቶዶክሳዊ አለ ማለት አይቻልም፡፡ ነገር ግን ቅናታችን እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሊሆን አይገባም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ክፉን በክፉ በመለሰ ጊዜ ጌታችን ገሥጾታል፤ “ስምዖን ጴጥሮስም ሰይፍ ስለ ነበረው መዘዘው፥የሊቀ ካህናቱንም ባሪያ፡መቶ፟ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠ፤ የባሪያውም ስም ማልኮስ ነበረ። ኢየሱስም ጴጥሮስን፦ ሰይፍህን ወደ ሰገባው ክተተው፤ አብ የሰጠኝን ጽዋ አልጠጣትምን አለው።” (ዮሐ. ፲፰፥፲) ክፉን መታገሥ ስሜታችንን የሚፈታተነን ቢሆንም ራሳችንን ገዝተን ክፉን በመልካም በመመለስ ክፉን ማሸነፍ ይገባል እንጂ ክፉን በክፉ በመመለስ በክፉ መሸነፍ አይገባም፡፡ በሰውኛ አስተሳሰብ ክፉን በመልካም መመለስ ከባድ ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን እኛ ፈቃደኝነቱ ካለን እግዚአብሔር ኃይል ብርታት ሆኖ ያስችለናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ በማለት ተናግሯል፤ “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ፡፡” (ፊል.፬፥፲፫) ክፉን በመልካም መመለስ በጠላት ላይ ድል ያስገኛል! ከሰዎች ጋር በሚኖረን ማንኛውም ግንኙነት የሚያጋጥሙንን ክፉ ሐሳቦችን፣ ክፉ ንግግሮችንና ክፉ ድርጊቶችን በበጎ በመመለስ ክፉ አሳቢዎችን፣ ክፉ ተናጋሪዎችንና ክፉ አድራጊዎችን ማስተማርና ወደ መልካም መንገድ መመለስ ከክርስቲያኖች ይጠበቃል፡፡ ምክንያቱም “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ” ተብለናልና ክፉዎች የሠለጠኑበት አልጫው ዓለም የሚጣፍጠው እኛ ጨው ሆነን ስንገኝ እንደሆነ ልንረዳ ይገባል፡፡ (ማቴ.፭፥፲፫) እንዲሁም ክፋት የበረታበት ጨለማው ዓለም በብርሃን የሚመላለሰው በእኛ ክርስቲያኖች ብርሃንነት ነው፡፡ “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፡፡” ስለዚህ ክፉን በመልካም በመመለስ ለአልጫው ዓለም ጨው፤ ለጨለማው ዓለም ብርሃን መሆን የእኛ ድርሻ ነው፡፡ (ማቴ.፭፥፲፬) ክፉን በመልካም መመለስ በጠላት ላይ ድል ያስገኛል፤ ምክንያቱም እኛ ክርስቲያኖች ነን፡፡ ክፉን በመልካም ማሸነፍ የሚቻለው እንዴት ነው? በወንጌል ትርጓሜ ክፉን በበጎ ማሸነፍ እንደሚቻል የሚያስረምር ታሪክ አለ፡፡ ታሪኩ የአንድ ባሕታዊ ሲሆን እርሱ በበዓቱ ሳለ ወንበዴዎች እንግዶች መስለው መጡበት፤ እግራቸውን አጥቦ አብልቶ አሳደራቸው፤ ሌሊት ተነሥተው እርሱን አሥረው መብራት አብርተው ያለ ገንዘቡን ይዘው ሄዱ፡፡ ከሄዱ በኋላ መብራት አብርቶ ቢያይ ሁለት ድሪም የምታወጣ ፀምር አገኘ፡፡ “ይህችም ለአንድ ጉዳይ ትሆናችኋለች” ብሎ ተከትሎ ወስዶ ሰጣቸው፡፡ ይህ ሰው እንዲህ ማድረጉ ከዚህ የበለጠ ዋጋ እንዳለ ቢያውቅ እንጂ ነው ብለው ተመልሰው ንስሓ ገብተው የሚኖሩ ሁነዋል፡፡ ሰዎች የቱንም ያህል ለክፋት ቢሠለጥኑ እግዚአብሔር ኅሊናን የሚያህል ዳኛን ሰጥቷልና የጊዜ የሁኔታ ጉዳይ ይሆናል እንጂ መመለሳቸው አይቀርም፡፡ ክፉ አድራጊዎች ላይ እንኳን ብድር መመለስ ይቅርና መጥላት እንደማይገባ ሲያስተምር እንዲህ ብሏል፡፡ “ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህን ጥላ እንደተባለ ሰምታችኋል፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ በሰማይ ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግማችሁን መርቁ፤ ለሚጠሏችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞች ላይ ዝናብን ያዘንባልና፡፡ የሚወዷችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ፤ ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን፡፡” (ማቴ.፭፥፵፫) ክርስቲያኖች ሰዎች በጠላትነት ተነሥተውባቸው ሲረግሟቸውና ሲያሳድዷቸው ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን ምረረ ገሃነምን ባያውቅ ባታውቅ ነው ብለው መታገሥ እንደሚገባ፣ የሚወዱንን ብቻ ሳይሆን የማይወዱንን በመውደድ ለማያምኑ ሃይማኖታችንን በተግባር በመግለጥ የድኅነት ምክንያት መሆን ከእኛ ከክርስቲያኖች ይጠበቃል፡፡ ክፉን በመልካም ማሸነፍ ማለት ክፉ ግብር ይዘው

“ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አታሸነፍ” (ሮሜ ፲፪፥፳፩) Read More »

Scroll to Top