በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የዲላ መዝገበ ምሕረት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የቤተልሔም ቡራኬ ተከናወነ!

ኤክቱስ ጥቅምት 25/2019 ዓ.ም

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት የዲላ መዝገበ ምሕረት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲስ የተገነባው ቤተልሔም ቡራኬ ተከናወነ።

ቡራኬው በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መልካም ፈቃድ ሲሆን፤ ቡራኬው በሀገረ ስብከቱ የመንፈሳዊ ትምህርትና የካህናት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ በመልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ ተከናውኗል።

በዚህ መርሃ-ግብር ላይ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ፣ መልአከ ምሕረት ሰናይ ሥርእጁ የደብሩ አስተዳዳሪ፣ ካህናትና ዲያቆናት ተገኝተዋል።

Scroll to Top