በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ለአንዲዳ የአዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት አዳዲስ ደቀ መዛሙርት መመሪያ ኦሪየንቴሽን ሰጡ!

ኤክቱስ ጥቅምት 1/2019 ዓ.ም

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የአንዲዳ የአዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከሀገረ ስብከቱ ሥር ከሚገኙት ስድስቱም ወረዳ ቤተ ክህነት የተውጣጡ አዳዲስ ደቀ መዛሙርትን ተቀብሏል።

በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአብነት ትምህርት ቤቱ ትምህርታቸውን ለመከታተል የመጡት እነዚህ ደቀ መዛሙርት ከስድስቱም ወረዳ ቤተ ክህነት የተመረጡ ናቸው። ትምህርት ቤቱ አዳዲስ ተማሪዎችን የመቀበልና ማደርያ የመሥጠት ሥራውን ሙሉ በሙሉ አጠናቋል።

ደቀ መዛሙርቱ መግባታቸውን ተከትሎ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ለተማሪዎቹ የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ብፁዕነታቸው ለደቀ መዛሙርቱ በሰጡት የመግቢያ ኦሪየንቴሽን በትምህርት ቆይታቸው ሊከተሏቸው ስለሚገቡ መንፈሳዊና ሥነ-ምግባራዊ መመሪያዎች፣ ስለ አብነት ትምህርት ታላቅነትና ቤተክርስቲያንን በታማኝነት የማገልገል ኃላፊነት ሰፊ ማብራሪያና አባታዊ ምክር ሰጥተዋል።

ትምህርት ቤቱ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሚያሠልጠናቸውን ደቀ መዛሙርት በጥራት ኮትኩቶ በማሳደግ ለቤተክርስቲያኗ የትምህርትና የአገልግሎት ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ አገልጋዮችን ለማፍራት አልሞ እየሰራ ይገኛል። ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱም ሀገረ ስብከቱ ለአብነት ትምህርት ቤቱና ለደቀ መዛሙርቱ የሚያደርገውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በመጨረሻም ብፁዕነታቸው የደቀመዛሙርቱን ማደርያ፣ መመገቢያ ክፍሎችን እንዲሁም አዲስ የሚገነባውን የአብነት ትምህርት ቤት አሁናዊ የግንባታ ሁኔታ ጎብኝተዋል።

በመርሃግብሩ ቀሲስ ጤናው እንዳላማው የሀገረ ስብከቱ የፕሮጀክት ማናጀር፣ መምህር መልአክ መሠለ የአብነት ትምህርት ቤቱ የቅኔና የመጻሕፍት ትርጓሜ መምህር፣ የአንዲዳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት፣ አዳዲስና ነባር ደቀ መዛሙርት ተገኝተዋል።

Scroll to Top