ኤክቱስ መስከረም 30/2019 ዓ.ም
በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የሚገኘው የአንዲዳ የአዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሚያስተምራቸውን ከስድስቱም ወረዳ ቤተ ክህነት የተውጣጡ ተማሪዎችን ተቀብሏል።
በዕለቱ የሀገረ ስብከቱ የመንፈሳዊ ትምህርት እና የካህናት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤቱ የመጻሕፍት ትርጓሜ መምህር መልአክ መሠለ ተገኝተዋል።
የአንዲዳ የአዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት ለሀገረ ስብከቱ በርካታ አገልጋዮችን በማፍራት፣ በአገልጋይ እጥረት ምክንያት የተዘጉ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን ከመክፈት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
