ኤክቱስ ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም
ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሐምሌ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሚከበርበት በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ለ17 ደቀ መዛሙርት የዲቁና ለ1 ዲያቆን የቅስና በአጠቃላይ ለ18 ደቀመዛሙርት ሥልጣነ ክህነት ሰጥተዋል።
ደቀ መዛሙርቱ ለዲቁና እና ለቅስና የሚያበቃቸውን መንፈሳዊ ትምህርት ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆኑ ከመሾማቸው በፊትም ብቁ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ፈተና ተሰጥቷቸው ማለፋቸው ተገልጿል።
ብፁዕነታቸው በሰጡት አባታዊ ቃለ ምዕዳን የተቀበሉት እጅግ ትልቅ ኃላፊነት መሆኑን አሳስበው አገልጋዮቹ መንጋውን በንጽሕና፣ በትጋትና በቅድስና እንዲጠብቁ አደራ ብለዋል።
