በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

በ አረጋዊዉ አባት ርዕሠ ደብር ለገሠ በለጠ አስተባባሪነት ለገጠር አብያተክርስቲያናት የንዋየ ቅድሳትና የቅዱሳት መጽሐፍት ድጋፍ ተደረገ !!

በጌዴኦ በኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላ ደብረ ገነት ለብዙ ዓመታት ያገለገሉትና አሁን በመንፈሳዊ አገልግሎት ላይ የሚገኙት ርዕሰ ደብር ለገሠ በለጠ የንሰሐ ልጆቻቸውን በማስተባበር በሀገረ ስብከቱ ለሚገኙ በንዋየ ቅድሳት አለመኖር ምክንያት አገልግሎት ለማይሰጡ አብያተክርስቲያን የሚሆን ንዋየ ቅድሳት ቅዱሳትና መጽሐፍትን ለብፁዕ አቡነ ገሪማ ለሀገረ ስብከቱ ጳጳስ አስረክበዋል ። በተለይ ርዕሰ ደብር ለገሰ በለጠ ድጋፍ የተደረጉትን መጽሐፍቱን በግል ገንዘባቸው እንዳስደጎሱ ታውቋል።

ድጋፍ የተደረጉ የንዋየ ቅድሳት አይነት፦

፩. የአምስት ሰሞነኛ ሙሉ ልብሰ ተክህኖ

፪. ወንጌል አዲስ ኪዳን በግዕዝ እና በአማርኛ-ተአምረ ማርያም-መጽሐፈ ቅዳሴ በግዕዝና በአማርኛ -መዝሙረ ዳዊት-መጽሐፈ ሰዓታት-ማህሌተ ጽጌ-ፀሎተ ዕጣን-መጽሐፈ ግጻዌ-መጽሐፈ ግንዘት-መጽሐፈ ክርስትና ሲሆን

ይህን የንዋየ ቅድሳትና የመጽሐፍት ስጦታ ያበረከቱት

ወልደ ሚካኤል፣ ኅይለ ገብርኤል፣ወልደ ገብርኤል ፣ ወልደ አረጋዊ፣ ፍቅረ አማኑኤል፣ ኃይለ ማሪያም ናቸው።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ የተበረከቱትን ንዋየ ቅድሳትና የመጽሐፍት ስጦታ ተረክበው መልዕክት ምስጋና አረጋዊ አባት ርዕሰ ደብር ለገሰ በለጠንና በገንዘባቸው የተባበሩትን ሁሉ አመስግነዋል ።

ኤክቱስ ሐምሌ 1/2017 ዓ.ም

Scroll to Top