በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

July 2025

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ከአዲስአበባና ከሀዋሳ የመጡ የቤተክርስቲያን ልጆች ጋር በሀገረ ስብከቱ አጠቃላይ ጉዳዮች ጋር ውይይት አደረጉ !!

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ከአዲስአበባና ከሀዋሳ የመጡ የቤተክርስቲያን ልጆች ጋር በሀገረ ስብከቱ አጠቃላይ ጉዳዮች ጋር ውይይት አደረጉ ብፁዕነታቸዉ በሀገረ ስብከቱ ላለፉት ሁለት አመታት ታቅደው እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እንዲሁም በቀጣይ የሚተገበሩ ስራዎችን ለታዳሚዉ ገለፃ አድርገዋል ። ተሳታፊዎችም ከተደረገዉ ገለጻ በመነሳት በብፁዕ አቡነ ገሪማ ገለፃ በመደረጉ መገረማቸዉን እና አብሪዉ የሚችሉትን ሁሉ ለማገዝ እንደሚፈልጉ ቃል ገብተዋል። በመጨረሻም በግንባታ ላይ የሚገኝዉን መንበረ ጵጵስና የተጎበኝ ሲሆን በነበረው ቆይታ ደስተኛ እንደሆኑ በመግለጽ ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ብር በላይ (1,200.000…) ቃል ገብተዋል። #ብፁዕነታቸዉም ድጋፍ ያደረጉትን አመስግነዉ በቀጣይም ከሀገረ ስብከቱ ጎን በመቆም በሀሳብም በገንዘብም አቅም በፈቀደ ሁሉ አብረዉ እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዉ በፀሎት ተፈፅሟል።

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ከአዲስአበባና ከሀዋሳ የመጡ የቤተክርስቲያን ልጆች ጋር በሀገረ ስብከቱ አጠቃላይ ጉዳዮች ጋር ውይይት አደረጉ !! Read More »

በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ብፁዕ አቡነ ገሪማ በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከበረ!

በጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጵጵስ ዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተክህነት ሥር የሚገኘው በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ መልአከ ብርሃን አጥናፉ ማሞ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ፣ የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች ፣ የወረዳ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀጠበብት መሪጌታ መሠረት እና ዋና ጸሐፊ ሊቀ ኅሩያን እሸቱ ዋለ ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ኃይል መሪጌታ ሀብቴ ፣የየአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ሊቀውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤት አባላት፣ ቁጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የተገኙ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ክብር ተከብሯል ። #በዕለቱም በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ለድቁና የሚያበቃቸውን ትምህርት ለተማሩ ለ44 ደቀመዛሙርት ማዕረገ ድቁና የሰጡ ሲሆን ለቅስና የሚያበቃቸውን ትምህርት ለተማሩ ለ10ት ዲያቆናት ማዕረገ ቅስና ሰጥተዋል። #ታቦቱ ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ ዑደት ካደረገ በኋላ የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ያሬዳዊ መዝሙር አቅርበዋል። #በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ አስተዳደር የዲላ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር መስፍን ደምሴ በክብረ በዓሉ ላይ በመገኘት የመልካም ምኞትና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። #ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በክብር እንግድነት የተገኙትን የዲላ ከተማ ከንቲባንና የሥራ ባልደረቦቻቸውን አመስግነዋል። የዕለቱን ትምህርት ብፁዕ አቡነ ገሪማ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዓሉን የተ92መለከተ ስለ ቅዱሳን መላእክት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል በመላእክትና በሰው መካከል ያለውን ግንኙነት የቅዱስ ጳውሎስን መልዕክት መነሻ በማድረግ የመላእክት እርዳታ አስፈላጊነት ገልጸዋል። የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነትና ጥበቃ ቅድስት ኢየሉጣና ቅዱስ ቂርቆስ ቅዱስ ገብርኤል እንደረዳቸውን በሰፊው ትምህርት ሰጥተዋል። በመጨረሻም ጸሎት በመድረግ የበዓሉ ፍጻሜ ሲሆን ጸሎተ ቅዳሴው በብፁዓን አባቶች ተመርቷል።

በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ብፁዕ አቡነ ገሪማ በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከበረ! Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ለ54 ደቀመዛሙርት ሥልጣነ ክህነት ሰጡ!!

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ በሚከበረው በቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል ላይ በመገኘት በሀገረ ስብከቱ ለሚገኙ መንፈሳዊ ትምህርታቸው ሲከታተሉ ለነበሩ ለ44 ደቀመዛሙርት የዲቁና እንዲሁም ለ 10 ዲያቆናት የቅስና ሥልጣነ ክህነት ክህነት ሰጥተዋል። ብፁዕነታቸው መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግሉ በንጽህናና በቅድስና ማገልገል እንዳለባቸው፣ በማይመጥናቸው ቦታ መገኘት እንደሌለባቸው እና የተቀበሉትን ትልቅ ኃላፊነት በትጋት መጠበቅ እንዳለባቸው መልእክታቸውን ከአደራ ጭምር አስተላልፈዋል።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ለ54 ደቀመዛሙርት ሥልጣነ ክህነት ሰጡ!! Read More »

በቡርጂ ወረዳ ቤተክህነት ሀረወንጄ ቅ/ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን የንዋየ ቅድሳት ድጋፍ ተደረገ!!

ኤክቱስ ሐምሌ 17/2017 ዓ.ምበጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በቡርጃ ወረዳ ቤተክህነት ሥር ለምትገኘው ሀረወንጄ ቅ/ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ቅዱሳት መጽሐፍት ፣ንዋየ ቅድሳት ልብሰ ተክህኖ ጽና ፣መስቀል ፣አውድ እና ሌሎች ንዋየ ቅድሳትን ከብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የሲኖዶስ አባል እጅ የቤተክርስቲያኑ ተወካይ ተቀብለዋል።

በቡርጂ ወረዳ ቤተክህነት ሀረወንጄ ቅ/ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን የንዋየ ቅድሳት ድጋፍ ተደረገ!! Read More »

በጨለለቅቱ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከሐምሌ11-13/2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ !!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በኮቸሬ ገደብና ጮርሶ ወረዳ ቤተክህነት በጨለለቅቱ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከሐምሌ 11-13/2017 ዓ.ም ሲካሄድ የነበረው ጉባኤ በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ጸሎት ሰጥተው ምስጋና ለሚገባቸው ምስጋና አቅርበው ተጠናቋል ። በጉባኤው፦ #ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ደሳለኝ #መጋቤ ሠናያት መ/ር አብይ #መጋቤ ሀዲስ ግሩም #ዘማሪ መ/ሰ/እንግዳወርቅ በቀለ #ዘማሪት መቅደስ መኮንን #ዘማሪ ዕዝራ ኃ/ሚካኤል #የዜማ መሣሪያ ተጨዋቾች #ከጉባኤ መጀመሪያ እስከ ፍጻሜ ድረስ የወረዳ ቤተክህነት የሥራ ኃላፊዎች የደብሩ አስተዳደሪና ካህናት እና የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ በጉባኤው ተገኝተዋል። በጉባኤው የእግዚአብሔር ቃል የተሰበከበት ፣ልዩ ልዩ ጣዕመ ዝማሬ መንፈሳዊ ዝማሬ የቀረበበት እንዲሁም የምክረ አበው መርሐ ግብር የተከናወነበት ነው ።

በጨለለቅቱ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከሐምሌ11-13/2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ !! Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ከተለያዩ የቤተክርስቲያን ልጆች ጋር ተወያዩ !!

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በሀገረ ስብከቱ እየተከናወኑ ባሉ ስራዎችና በቀጣይ በሚተገበሩ ሥራዎች ዙሪያ ውይይት አደረጉ ። ውይይቱ ከተደረገ በኋላም በአንዲዳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የሚገኘውን አብነት ት/ቤት ፣አዲስ እየተገነባ የሚገኘዉን መንበረ ጵጵስናና በውስጡ እየለማ የሚገኘውን የጎሮ አትክልትና የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት ተጎብኝቷል።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ከተለያዩ የቤተክርስቲያን ልጆች ጋር ተወያዩ !! Read More »

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ከጌዴኦ የባህል አባቶች አባ ገዳ ቢፎም ዋቆ እና ካብኔዎቻቸው ጋር በጽ/ቤታቸዉ ተወያዩ ።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ከጌዴኦ የባህል አባቶች አባ ገዳ ቢፎም ዋቆ እና ካብኔዎቻቸው ጋር በጽ/ቤታቸዉ ተወያዩ ። Read More »

የጎላ ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን የጸበል ሥፍራ በብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ተባረከ!!

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በጎላ ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን በሚገኘው የጸበል ሥፍራ ላይ በመገኘት ጸሎተ ወንጌል፣ ኪዳን አድርሰው የጸበል ሥፍራውን ባርከዋል። በመርሃግብሩ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ መልአከ ብርሃን ቀሲስ አጥናፉ ማሞ ፣ የመንበረ ጵጵስናና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጠበብት መሪጌታ መሰረት፣ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ እሸቱ ዋለ፣ ቀሲስ ሄኖክ የቤተ ክርስቲያኑ የሰበካ ጉባኤ ሊቀ መንበር፣ የደብሩ ካህናትና ዲያቆናት፣ የደብሩ የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያንና ምዕመናን ተገኝተዋል። ብፁዕነታቸው በመርሃግብሩ ትምህርት የሰጡ ሲሆን በትምህርታቸው የእግዚአብሔር መልአክ በሚያናውጸው ውሃ ብዙዎች ከደዌ ሥጋ ይፈወሱ እንደነበር፣ ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌው ምራቁን በአፈር እንትፍ ብሎ ተአምራትን እንዳደረገ አንስተው ዛሬም በዘመናችን እግዚአብሔር የሰጠንን ይህንን ጸበል አክብረን ብንይዘው እና በእምነት ብንጠቀመው ብዙ ተአምራትን እንደሚያደርግ በሰፊው ገልጸው መርሃግብሩን በጸሎት ፈጽመዋል።

የጎላ ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን የጸበል ሥፍራ በብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ተባረከ!! Read More »

#ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንኳን ለ፪ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ በሰላምና በጤና አደረስዎ !!

ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን በሙሉ ለብፁዕ አባታችን አቡነ ገሪማ ጳጳስ የ፪ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በዓል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን። በኢትዮጵያ ኦርቶዶከክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የብፁዕ አቡነ ገሪማ የ፪ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም በታላቅ ድምቀት የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅና የየክፍል ኃላፊዎች የወረዳ ቤተክህነት ኃላፊዎች እና የአድባራት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት ይከበራል። ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በሀገረ ስብከት ከተመደቡበት ጊዜ ጀምሮ ሐዋርያዊ ጉዞ በማድረግ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ከ 70 በላይ አብያተክርስቲያናት የጎበኙ፣ አባታዊ ምክርና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት የሰጡና ከዚህ በፊት በጳጳሳት ያልተጎበኙና ያልተባረኩ ምዕመናን በመጎብኘታቸው ልዩ አባት ያደርጋቸዋል። ብፁዕ አቡነ ገሪማ የስብከተ ወንጌልን አገልግሎት እንዲስፋፋ፣ ለሰበካ ጉባኤ አባላት ስልጠና በመስጠት አዳዲስ አማኒያንን በማጥመቅ የሀገረ ስብከቱን የ፲ ዓመት መሪ ዕቅ እንዲዘጋጅ በማድረግ ፣የመንበረ ጵጵስና መኖሪያ ግንባታ እንዲጀመር በማድረግ ፣ አዲስ የተሠሩ አብያተክርስቲያናትን ባርከው ለአገልግሎት እንዲበቁ፣በሀገረ ስብከቱ ዘመናዊ አሠራርን በመዘርጋት፣ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት፣ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ሁሉም አብያተክርስቲያናት በይዞታቸው አቅደው ተገቢውን ልማት እንዲያለሙ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጥናት እንዲያደርግ መመሪያ በመስጠት የመጎብኘትና የማበረታታት ተግባርን አከናውነዋል። በገጠሪቱ አብያተክርስቲያናት የእግር ጉዞ በማድረግ ወንጌል ሰብከዋል። በታላላቅ በዓላት በመገኘት ቀድሶ በማቁረብ ወንጌልን በማስተማር በሀገረ ስብከቱ በሚነገሩ ቋንቋዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ያደረጉ እንዲገለገልበት መመሪያን የሰጡ ፣የገጠሪቷ ቤተክርስቲያን የጎበኙ ፤ ሀገረ ስብከቱ ዘመኑን ያማከለ ዘመናዊ አሰራርን እንዲያከናውን ያደረጉ፤ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ጥያቄዎች አፋጣኝ መልስ የሚሰጡ፤ወደ ገጠር ቤተክርስቲያን የእግር ጉዞ እንዲደረግ በማድረግ አብያተክርስቲያናት እንዲረዱና እንዲተዋወቁ አድርገዋል። በተለይ በቅርቡ አዲስ ቤተክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠለትን የቂሻ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ጉዞ እንዲደረግ በማድረግ ሕዝበ ክርስቲያኑ ለቤተክርስቲያን መታነጽ ከፍተኛ ገቢ እንዲገባ ተደርጓል ። በጸሎታቸው በመንፈሳዊ አገልግሎታቸው የመልካም አሰተዳደርና የልማት አባት መሆናቸውን በተግባር ያሳዩ ፤ሐዋርያዊ አባትነታቸው ዘወትር የሚነገርላቸው ፤ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ከሠራተኞች ጀምሮ ካህናት ዲያቆናት በሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በምዕመናን ከልብ የሚወደዱ አባት ናቸው። ለሀገራችንና ለሕዝቦቿ ፍቅር ፣ሰላም ፣አንድነት እንዲኖር አብዝተው የሚጸልዩ አባታችን፤ እንኳን ለ ፪ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ በሰላምና በጤና አደረስዎ ! ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ዲላ ኢትዮጵያ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ብፁዕነትዎ ለረጅም ዘመናት በሰላምና በጤና በሀገረ ስብከትዎ ያቆይልን !!!! #የብፁዕነታቸው_ቡራኬ_አይለየን!!

#ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬ ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንኳን ለ፪ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ በሰላምና በጤና አደረስዎ !! Read More »

ለገጠር አብያተክርስቲያናት የሚሆን የቅዱሳት መጽሐፍት ድጋፍ ተደረገ !!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት የማይሰጡ አብያተክርስቲያናት ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ለማድረግ አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ ይታወቃል ።ከዚህም በንዋየ ቅድሳት ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ ድጋፎች እየተደረጉ ይገኛል ። ከእነዚህም የቅዱሳት መጽሐፍት እጥረቱ ላለባቸው አብያተክርስቲያናት የሚሆን መጽሐፍትን መ/ርት አልማዝ ለብፁዕ አቡነ ገሪማ ለሀገረ ስብከቱ ጳጳስ አስረክበዋል። ብፁዕነታቸውም ስለተሰጠው ስጦታ ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም አብያተክርስቲያናቱ ተከፍተው መንፈሳዊ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ሁሉም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሀገር የሚገኙ የቤተክርስቲያን ልጆች የአቅማቸውን ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል። ንዋየቅዱሳት ፣ ቅዱስት መጽሐፍትን ፣ልብሰ ተክህኖ አልባሳትን የካህናት ደመወዝን በመቻል የተዘጉ አብያተክርስቲያናት ማስፈከትና በረከት መቀበል አለብን እያልን መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ለገጠር አብያተክርስቲያናት የሚሆን የቅዱሳት መጽሐፍት ድጋፍ ተደረገ !! Read More »

Scroll to Top