በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት የወንጌል አገልግሎት የሚውል ሞንታርቦ ድጋፍ ተደረገ!

ኤክቱስ ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ለወንጌል ማስፋፊያ አገልግሎት የሚውሉ ስድስት ዘመናዊ የድምፅ መሣሪያዎች (ሞንታርቦ) ድጋፍ ተደረገ። የድጋፍ ቁሳቁሶቹ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኘው የሀገረ ስብከቱ መማክርት ጉባኤ የተበረከቱ መሆናቸው ተገልጿል።

የተበረከቱት እነዚህ የድምፅ ማጉያ፣ ስፒከር እና ሚክሰርን በአንድ ላይ አዋሕደው የያዙት ሞንታርቦዎች በቻርጅ የሚሠሩ፣ ለአጠቃቀም ቀላልና ከቦታ ወደ ቦታ ለማንቀሳቀስ አመች የሆኑ ናቸው። ይህም የኤሌክትሪክ መብራትና የመጓጓዣ መሠረተ ልማት ችግር ባለባቸው የገጠር አካባቢዎች ድምፅ ሳይበታተን ጥራት ባለው መልኩ እንዲሰማ በማድረግ ለሚካሄዱ የወንጌል አገልግሎቶች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንደገለጹት የተደረገው ቁሳቁስ በየገጠር አካባቢዎች በሀገር በቀል ቋንቋዎች ለማካሄድ ለታቀደው የወንጌል አገልግሎት እጅግ ከፍተኛ አቅም እንደሚሆን ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው የተረከቧቸውን ስድስት የድምፅ መሣሪያዎች ለስድስቱ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆችና ጸሐፍት በአንድነት ያስረከቡ ሲሆን
ቁሳቁሶቹ ለአገልግሎት የተለዩበትን ዓላማ ብቻ መሠረት አድርገው ጥቅም ላይ እንዲውሉ አሳስበዋል።

Scroll to Top