በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

በሀገረ ስብከቱ ሥር ለሚገኙ አቅመ ደካማ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ!

ኤክቱስ ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም

ማኅበረ አቡቀለምሲስ በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ አቅመ ደካማ ተማሪዎች የሚሆን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አበርክቷል።

ማኅበሩ ይህንን ድጋፍ ያደረገው በተለያዩ ምክንያቶች የመማሪያ ቁሳቁስ ለማሟላት ለተቸገሩ ተማሪዎች ድጋፍ ለማድረግና የመማር እድላቸውን ለማመቻቸት በማሰብ እንደሆነ ተገልጿል።

ለዚሁ የበጎ አድራጎት ተግባር ከአራት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን የተደረገው የቁሳቁስ ድጋፍም 608 ደርዘን ደብተር፣ 50 ደርዘን እርሳስ፣ 50 ደርዘን ላጲስ፣ 50 ደርዘን መቅረጫ እንዲሁም 50 ደርዘን እስክሪብቶ ያካተተ ነው።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ድጋፉን ከተረከቡ በኋላ ለማኅበሩ አባላት እንዲሁም ለተወካዮቹ ለላዕከ ወንጌል ያሬድ አደመ እና ለሰላም አያሌው ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

አያይዘውም የተበረከተው ቁሳቁስ ለተያዘለት በጎ ዓላማ ብቻ እንዲውል መመሪያ በመስጠት ድጋፉን ለስድስቱም ወረዳ ቤተ ክህነት አከፋፍለዋል።

Scroll to Top