በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የጨለለቅቱ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ እና የሐምሌ ሥላሴ ዓመታዊ በዓል ብፁዕነታቸው በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ!

ኤክቱስ ሐምሌ 7/2018 ዓ.ም

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በኮቾሬ፣ ገደብና ጮርሶ ወረዳዎች ቤተ ክህነት በጨለለቅቱ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት ተከብሯል።

ታቦቱ ከመንበሩ ከወጣ በኋላ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያሬዳዊ ዝማሬ ያቀረቡ ሲሆን የደብሩ የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያንም ዝማሬ አቅርበዋል።

የዕለቱን ትምህርት ያስተማሩት መምህር እስራኤል ሲሆን በዓሉ የሚከበርበትን ምክንያት በሚገባ በመዘርዘር ወደ ሕይወት እየቀየሩ በሚገባ አስተምረዋል።

በደብሩ ለሚሠሩ የልማት ሥራዎች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ያከናወኑት መልአከ ሰላም እኔምአየሁ ዓለሙ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው።

በመቀጠል በደብሩ አስተዳዳሪ በበኩረ ትጉሃን አእምሮ ሙሉ አቅራቢነት ለሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ አስተዋጽዖ ላደረጉ አካላት በብፁዕነታቸው የምስጋና የምስክር ወረቀትና ሽልማት ተበርክቷል።

በመጨረሻም በመልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ የሀገረ ስብከቱ የመንፈሳዊ ትምህርትና የካህናት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ ጋባዥነት ብፁዕነታቸው በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በጌዴኡፋ ቋንቋዎች መዝሙር የዘመሩ ሲሆን አክለውም ስለቤተ ክርስቲያን ምንነት በማንሳት ካስረዱ በኋላ የሰው ልጅ ሰውነት የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደመሆኑ ራሱን እንዴት ከእርኩሰት መጠበቅ እንዳለበት አባታዊ መመሪያ ሰጥተው በጸሎት ፈጽመዋል።

Scroll to Top