ኤክቱስ ሐምሌ 7/2018 ዓ.ም
በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በኮቾሬ፣ ገደብና ጮርሶ ወረዳዎች የሚገኙ በጨለለቅቱ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አስራ ስድስት አዳዲስ አማንያን በብፁዕ አቡነ ገሪማ ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል።
ከተጠማቅያኑ መካከል አስራ ሁለቱ በጨለለቅቱ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አማካኝነት፣ ቀሪዎቹ አራት አዳዲስ አማንያን ደግሞ በማኅበረ ቅዱሳን ጨለለቅቱ ማዕከል አማካኝነት የቅድመ ጥምቀት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።
ይህ መንፈሳዊ አገልግሎት በብፁዕነታቸው መመሪያ ሰጪነት በሀገረ ስብከቱ ሥር በሚገኙ አድባራት የሚከናወነውን የክርስቶስን የመንግሥቱን ወንጌል የማስፋፋት ሥራ ውጤት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን መሰል የማስተማርና የማጥመቅ አገልግሎቶች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመልክቷል።
