በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ለስምንት ወራት የተማሩ ደቀመዛሙርት በብፁዕ አቡነ ገሪማ ጳጳስ ተመረቁ!!

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በሀገረ ስብከቱ በተቋቋመው በአንዲዳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የተማሩ የአብነት እና የተለያዩ መሠረታዊ ትምህርትና ሥልጠና የወሰዱ ከ5ት ወረዳ ቤተክህነት የተወጣጡ 5ት ደቀመዛሙርት በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተመረቁ።

በምርቃ መርሐ ግብር ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ደቀመዛሙርት የተሸለሙ ሲሆን የተለያዩ መጻሕፍት ከማህበረ ቅዱሳን ተሰጥቷቸዋል።በተጨማሪ ያለ ምንም ክፍያ ለስምንት ወራት ያስተማሩ መምህራን በብፁዕነታቸው ተመስግነዋል ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

የደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት መዘምራን መዝሙር ያቀረቡ ሲሆን ተመራቂ ደቀመዛሙርትም ያሬዳዊ ወረብና ግጥም አቅርበዋል ።

ስለ ተመራቂ ደቀመዛሙርት አጠቃላይ ቆይታ በቀሲስ ጤናው እንዳለማው ቀርቧል።

አጠቃላይ አጭር ስለ አብነት ት/ቤቱ ሪፖርት በመልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ የሀገረ ስብከቱ የትምህርትና የካህናት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ ገልጸዋል ።

በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ቃለምዕዳን ያስተላለፉ ሲሆን ደቀመዛሙርት የተሰጣቸውን ተልዕኮ መወጣት ማስተማር እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

Scroll to Top