በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

Uncategorized

ስለ ሥራ ማስታወቂያው የተሰጠ ማብራሪያ

​በሀገረ ስብከታችን በወጣው የሥራ ማስታወቂያ ላይ “ሙሉ ጤነኛ” ለሚለው መስፈርት ለተፈጠረው ጥያቄና ስለምዝገባው ሁኔታ የሚከተለውን ማብራሪያ እንሰጣለን። ​በመጀመሪያ ደረጃ “ሙሉ ጤነኛ” የሚለው አገላለጽ የተፈለገው አመልካቾች የተሰጣቸውን የሥራ ኃላፊነት ያለ ጤና እክል በብቃት መወጣት የሚችሉ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው። በመሆኑም አንድ አመልካች ለሂሳብ ሥራ መደቡ የሚያስፈልጉትን መሠረታዊ ተግባራት (ለምሳሌ የሰነዶችን ትክክለኛነት በጥንቃቄ ማረጋገጥ እና የኮምፒውተር ላይ የሂሳብ ሥራዎችን ማከናወን) በብቃት ለመወጣት የሚያስችል አቅም እስካለው ድረስ፣ ማንኛውም አካላዊ ሁኔታ እንደ መከልከያ መስፈርት አይቆጠርም። ​በተጨማሪም የሚጠየቀው የሕክምና ማስረጃ ዓላማው አመልካቹ የተመደበበትን የሥራ ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችልና ለሥራው አስፈላጊ የሆነው የተሟላ የጤና ቁመና ላይ መሆኑን ለማረጋገጥ እንጂ ማንኛውንም ዓይነት መድልዎ ለመፈጸም እንዳልሆነ እንገልጻለን። ​በመጨረሻም በርቀት የምትገኙና በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የማትችሉ አመልካቾች በማስታወቂያው ላይ የተጠቀሱትን አስፈላጊና የተሟሉ ማስረጃዎች በሙሉ በሀገረ ስብከቱ ይፋዊ የኢሜል አድራሻ Office@eotc-gkb.org በመላክ በኦንላይን መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። ​የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል​

ስለ ሥራ ማስታወቂያው የተሰጠ ማብራሪያ Read More »

ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተ ክህነት በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መሪነት አዲስ ወደሚገነባው ወደ ጨልባ ቅዱስ መርቆርዮስ ቤተ ክርስቲያን የካቲት 29/2018 ዓ.ም ጉዞ ስለተዘጋጀ ሁላችሁም እንድትሳተፉ መልእክታችንን እናስተላልፋለን!

ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ Read More »

​🔔 የዕጣ ማውጫ ቀን ማሳሰቢያ!

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ​የመንበረ ጵጵስና ሕንጻ ግንባታ ዕጣ የካቲት 16 በይርጋጨፌ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በሕዝብ ፊት በይፋ ይወጣል። በዕለቱ ዕጣ የማውጣት ሥነ ሥርዓቱን በገጻችን በቀጥታ ሥርጭት (Live) የምናስተላልፍ መሆኑን እየገለጽን ሁላችሁም እንድትከታተሉን እናሳውቃለን።

​🔔 የዕጣ ማውጫ ቀን ማሳሰቢያ! Read More »

ልዩ መንፈሳዊ የእግር ጉዞ ጥቂት ምዕመናን ብቻ ወደሚገኙበት ወደ ኦቲልቾ የስብከተ ወንጌል ኬላ

በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መሪነት በቀን 15/6/2018 ዓ/ም በዕለተ እሁድ የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ ስለሚካሄድ ሁላችሁም በዕለቱ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን! የጉዞ መነሻ አንዲዳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን

ልዩ መንፈሳዊ የእግር ጉዞ ጥቂት ምዕመናን ብቻ ወደሚገኙበት ወደ ኦቲልቾ የስብከተ ወንጌል ኬላ Read More »

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ለጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ቋሚ ፀሐፊ ከዚህ በታች ባለው ክፍት የሥራ መደብ መስፈርቱን የሚያሟላ ሠራተኛ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል!

ኤክቱስ የካቲት 9/2018 ዓ.ም

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ለጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ቋሚ ፀሐፊ ከዚህ በታች ባለው ክፍት የሥራ መደብ መስፈርቱን የሚያሟላ ሠራተኛ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል! Read More »

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ከዚህ በታች ባለው ክፍት የሥራ መደብ መስፈርቱን የሚያሟላ ሠራተኛ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል!

ኤክቱስ የካቲት 9/2018 ዓ.ም

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ከዚህ በታች ባለው ክፍት የሥራ መደብ መስፈርቱን የሚያሟላ ሠራተኛ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል! Read More »

ለሦስት ወራት መጠነኛ ዕድሳት ሲደረግለት የቆየው የሻራ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ገሪማ ቡራኬ ተከናወነ!

ኤክቱስ የካቲት 08/2018 ዓ.ም በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በዲላና ወናጎ ወረዳ ቤተ ክህነት የሻራ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ለሦስት ወራት ያኽል መጠነኛ ዕድሳት ሲደረግለት ቆይቶ በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ቡራኬ ተከናውኗል። በዕለቱ ብፁዕነታቸውን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ መንፈሳዊ ትምህርትና የካህናት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀ ስዩማን ቀሲስ ምሕረት፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናትና ዲያቆናት ተገኝተዋል።

ለሦስት ወራት መጠነኛ ዕድሳት ሲደረግለት የቆየው የሻራ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ገሪማ ቡራኬ ተከናወነ! Read More »

Patriarchate Delegation Conducts Extensive Field Visit Led by His Grace Abune Gerima

​Ichthus Dilla, February 12, 2026 (Yekatit 5, 2018 EC) ​A high-level delegation from the Patriarchate General Secretariat of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, led by His Grace Abune Gerima, Bishop of the Diocese of Gedeo, Kore, and Burji and member of the Holy Synod, conducted an extensive field visit to various development projects across the diocese. ​The tour commenced at the Andida Traditional School of Excellence (Abnet School), where the delegation observed the teaching-learning process of the residential students. They also inspected the poultry and beekeeping projects, the students’ and teachers’ dormitories, the dining facilities, classrooms, and the administrative office. Following this, the delegation visited the beekeeping initiatives and the Enset and coffee plantations at the Dilla Dama St. George Church. ​The visit continued with an inspection of the current construction progress of the Diocesan Residence (Menbere Ppizna). Additionally, the delegation toured the water and poultry projects, as well as the school located at the Dilla Debre Ghenet St. Michael Church. ​Furthermore, the delegation visited the newly constructed administrative office and the parish school at the Dilla Second Gethsemane Ba’ata Le-Mariam Church, including the specific site designated for the Diocese’s upcoming new project. The field visit concluded at the Diocesan Headquarters. ​During the visit, Memhir Daniel Seifemichael, Head of the Research and Development Department at the Patriarchate and Communications Head of the Holy Synod Office, expressed his admiration for the Diocese’s exceptional efforts in fulfilling the mission of the Holy Church. He pledged continued support from the Patriarchate to sustain and enhance these services. ​In his closing remarks, His Grace Abune Gerima extended his gratitude to the delegation for their active participation throughout the training program and for their dedication in visiting the various Diocesan development activities.

Patriarchate Delegation Conducts Extensive Field Visit Led by His Grace Abune Gerima Read More »

ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የመጡ ልዑካን በብፁዕነታቸው መሪነት የመስክ ጉብኝት አደረጉ!

ኤክቱስ የካቲት 4/2018 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመጡ ልዑካን በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መሪነት በሀገረ ስብከቱ የሠሩ በርካታ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። በመጀመርያ በአንዲዳ የሚገኘው የአዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት የመማር ማስተማር ሂደት፣ የዶሮና የንብ ፕሮጀክቶች፣ የደቀ መዛሙርትና የመምህራን የማደርያ የመመገቢያ እና የመማርያ ክፍሎች እንዲሁም ጽሕፈት ቤት ከተጎበኘ በኋላ የዲላ ዳማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኘው የንብ ማነብ ሥራ እንዲሁም የእንሰትና የቡና ልማቶች ተጎብኝተዋል። በመቀጠል ሀገረ ስብከቱ የሚያስገነባው መንበረ ጵጵስና አሁናዊ ሁኔታ፣ የዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሚገኘው የውኃና የዶሮ ፕሮጀክቶች እንዲሁም ትምህርት ቤት ተጎብኝቷል። እንዲሁም በዲላ ዳግማዊት ጌቴሴማኒ በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ጽሕፈት ቤት፣ የደብሩ ትምህርት ቤት እና ሀገረ ስብከቱ አዲስ ፕሮጀክት ለመሥራት ከደብሩ የወሰደው ቦታዎች ከተጎበኙ በኋላ የሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ተጎብኝቷል። መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የጥናትና ምርምር መምሪያ ኃላፊ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት የኮሚኒኬሽን ኃላፊ በበኩላቸው ሀገረ ስብከቱ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ለመፈጸም እያደረገ ያለውን ከፍተኛ ጥረት አድንቀው ይህንን አገልግሎት ለመደገፍ ከሀገረ ስብከቱ ጎን እንደሚቆሙ ቃል ገብተዋል። በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ልዑካኑ ከሥልጠናው ጀምሮ የነበራቸውን ቆይታ አንስተው እንዲሁም የሀገረ ስብከቱን ሥራዎች ዞረው ስለጎበኙ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የመጡ ልዑካን በብፁዕነታቸው መሪነት የመስክ ጉብኝት አደረጉ! Read More »

Scroll to Top