በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

መሰረታዊ የሀይማኖት ትምህርት

የአቋም መግለጫ

“ዝክረ ወንጌል ወዝክረ ሊቃውንት”በሚል መሪ ቃል በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ከትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ ጋር በመሆን ያዘጋጀው የሁለት ቀናት የምክክር ጉባኤ የአቋም መግለጫ አውጥቷል የአቋም መግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል፦ “ዘአዘዞሙ ለአበዊነ፡፡ ከመ ይንግሩ ለደቂቆሙ፡፡ ወከመ ያእምር ካልእ ትውልድ፡፡ ደቂቅ እለ ይትወለዱ ወይትነሥኡ፡፡ ወይዜንው ለደቂቆሙ፡፡” ለልጆቻቸው ያስታወቁ ዘንድ ለአባቶቻችን ያዘዘውን….የሚመጣ ትውልድ የሚወለዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ ተነሥተው ለልጆቻቸው ይነግራሉ” መዝ 77 ቁ 5-6 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊት ታሪካዊትና ሐዋርያዊት እንደመሆንዋ የዕለት ከዕለት ሥራዋንና አስተዳደርዋን የምታራምደው ቅዱሳን አበው ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በወሰኑት ፍትሕ መንፈሳዊ ነው፡፡ እምነትዋን የምታስፋፋበት፣የምታስተምርበትና የምታጸናበትን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜ ተሰብስቦ በመምከር የጠመመውን በማቅናት የቀናውን በማጽናት በሚሰጠው ውሳኔና በሚያወጣው የሥራ መመሪያ መሠረት ነው፡፡ ይህን ውሳኔና መመሪያ አስፈጻሚው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሥሩ በሚመራቸው መምሪያዎችና የሥራ ክፍሎች አማካኝነት፡- የቤተ ክርስቲያኒቱ ልዕልና በሁሉም ዘንድ እንዲታወቅና እንዲከበር ያደርጋል፣ ቤተ ክርስቲያን ባላት መብት መሠረት ሕልውናዋን ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ይሠራል፣ ሕጓና ሥርዓትዋ እንዲከበር፣በአንድነትዋና በአላማዋ ጸንታ እምነቷ እንዲስፋፋ የሥራ ዕድገቷ ተፋጥኖ ግቡን ይመታ ዘንድ ዕለት በዕለት ይሠራል፣ ሕዝበ ክርስቲያኑ ማግኘት የሚገባውን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለማሟላት በሚቻልበት ጉዳይ በማተኮር ጉዳዮችን እየመረመረ በሥራ የሚተረጎሙበትን የሥራ አፈጻጸም መመሪያ ከሚሰጥባቸው መምሪያዎች መካከል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያና የትምህርት ማሰልጠኛ መምሪያ በጋራ “ዝክረ ወንጌል ወዝክረ ሊቃውንት” በሚል ርዕስ መምሪያዎቹ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሥራ መዋቅር የተጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ያልተቆጠበ ጥረት በማድረግ የጉባኤውን ተሳታፊዎች በሙሉ ደስ ያሰኘ ትልቅ ሥራ ከሰኔ 24 ቀን እስከ ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ዕለታት ሠርተዋል፡፡ የመርሐ ግብሩም አፈጻጸም በሚገባ ከዋናው መ/ቤት ከየአህረ ሰብከቱ ተመርጠው ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ በማድረግ፣ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዩኒቨርሲቲዎች፣ኮሌጆች፣ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፤ከአዲስ አበባ ክፍላተ ከተሞች ከገዳማትና አድባራት የተመደቡ ሊቃውንት የአብነት ትምህርት መምህራን፣ሰባክያነ ወንጌል (ላዕካነ ወንጌል) በአጠቃላይ በምክክር ጉባኤው የተሳተፉ ምሁራን የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት የሚያስገነዝብ ትምህርታዊ ጥናትና መወያያ ርእሶች ተቀርጸው የቤተ ክርስቲያናችንን ሁለንተናዊ ተልዕኮ ከሥልጠና እስከ ተልዕኮ ማስፈጸም ድረስ ያለውን ሐዋርያዊ ግልጋሎት ውስጣዊውን ገጽታ በዳሰሰ መልኩ በቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ መስክ በቂ ግንዛቤ ዕውቀትና ችሎታ ባላቸው ሊቃውተ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት የቆየውን ልምዳቸውና ዕውቀታቸውን አሁን ላይ ካለው አካሄዳችንና አገልግሎታችን አንጻር የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ለሆነው ሁሉ እኔ ማነኝ ብሎ መጠየቅ እስኪያስችል ድረስ በጥናታዊ ጽሑፍ የተደገፈ ትምህርት ተሰጥቷል፤በችግሩም ዙሪያ ያተኮሩ መጠይቆች ተነስተዋል፤ በመምህራኑም በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶናል፡፡ ውይይቱም ሰፊና ጠቃሚ ሐሳብ ማሰባሰብ ያስቻለ ስለሆነና የምክክር ጉባኤው ተካፋዮችም በቅዱስነታቸው የተሰጠንን መመሪያና ቃለ ምእዳን ከብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ የተላለፈውን የሥራ አፈጻጸማዊ መመሪያ የጉባኤውን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ሲመሩት ከነበሩት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ሊቀ ጳጳስ የጉባኤ አመራርና ማብራሪያዎች ጥናታዊ ጽሁፍ አቅራቢዎች ከሆኑት ምሁራነ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠንን መመሪያና ከምክክር ጉባኤው ባገኘነው ጠቃሚ ትምህርት መሠረት የሚከተለውን ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡ ጉባኤያችን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተ/ሃይማኖት የተላለፈውን የመክፈቻ ቃለ ምዕዳን፣ከብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ የተሰጠውን የሥራ መመሪያና ጥናት አቅራቢዎች ያቀረቡትን ጥናታዊ ጽሑፎች በሥራ ለማዋል ቃል እንገባለን፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ከቅዱስ ፓትርያርኩና ከዋናው መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሚወጡት ሕጎችና መመሪያዎች፣እንዲሁም ስለ ስብከተ ወንጌልና ትምህርትና ሥልጠና የሚተላለፉትን ትዕዛዞች በየአህጉረ ስብከቱና በቤተ ክርስቲያኗ ተቅዋማት ሁሉ በተግባር እንዲውሉ ቃል እንገባለን፣ እነዚህ መምሪያዎች የቤተ ክርስቲያኗን ሁለንተናዊ ተልዕኮ ለማሟላት የወሰዱትን የሥራ ተነሳሽነትና ኃላፊነትን በጋራ የመወጣት ልምዳቸው የሚበረታታ ስለሆነ በዚሁ መልኩ ተቀራራቢ የሆኑ የቤተ ክርስቲያኗ የሥራ መዋቅር ክፍሎች በጥምር የሚያስፈጽሙበት አሠራር መዘርጋት የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ ተልዕኮ ስለሚያማክልና የጉባኤው ተሳታፊዎችም የምንደግፈው ስለሆነ በአፈጻጸም ረገድ የሚጠበቅብንን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁነታችንን እንገልጻለን፡፡ የአብነት ት/ቤቶች እየተስፋፉ መሆናቸው ግልጽ ነው፤እነሱን ያግዙ ዘንድ የተቋቋሙት ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆችም በንባብ፣በቅዳሴ፣በዜማና በመጻሕፍት የትምህርት ዘርፍ እያደጉ የሚገኝበት ወቅት ስለሆነ ተመርቀው የወጡት ደቀ መዛሙርትም ከዋናው ማእከል ጀምሮ በየአህጉረ ስብከቱና ከተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቅዋማት በአገልግሎትና በኃላፊነት የሚገኙበት ወቅት ላይ መድረሳችን የቤተ ክርስቲያናችንን ሁለንተናዊ ዕድገቷን የሚያሳይ በመሆኑ አሁንም በየጊዜው በጥናት የተደገፈ ሥልጠና በመስጠት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላችን አስተዋጽኦ ለመወጣት ዝግጁነታችንን እንገልጻለን፡፡ ቋሚ የቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ ትምህርት ለማጠናከር፤የመምህራንና የደቀ መዛሙርትን ኑሮ ለመደገፍ በየአካባቢው በየአህጉረ ስብከቱ በቂ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ዘገባዎች ቢያመለክቱም በውስጣዊ የአመራርና ውጫዊ ሁኔታዎች አንዳንድ ችግሮች የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መምህራንን ለፍልሰት እያደረጉ ስላሉ ለወደፊቱ መምህራኑ በየአካቢያቸው ወንበራቸውን አጽንተው ደቀ መዛሙርቶቻቸውን በሁለንተናዊ ስብእና ክብር አስታጥቀው እንዲያወጡ በመሥራት የበኩላችንን አደራና ኃላፊነት እንወጣለን፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን መሠረታዊ ትምህርት ዜማ፣ቅዳሴና ቅኔና ትርጓሜ መጻሕፍት የሚማሩ ደቀ መዛሙርት ለትምህርተ ወንጌልበአርያነት ለሚጠቀስ ለመንፈሳዊ አስተዳደር ለቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና ለቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች ጊዜውን የዋጀ መምህራን ለማግኘት የሥርዓተ ትምህርት ዳሰሳዊ ጥናት የቤተ ክርስቲያኗን ባለሙያዎችና ሌሎች አጋዥ ኃይሎች በማሳተፍ እንዲቀርብ በተደጋጋሚ በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነ ስለሆነ እነዚህ ሁለቱም መምሪያዎች ሆኑ ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ተባብረውበት ማኅደረ ጉዳዮች ታይተው የቀሩትን ተግባራት ወደ ሥራ ለማስገባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝና ለመወጣት ቃል እንገባለን፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ምንጊዜም ሐዋርያዊ አገልግሎቷን ያላቋረጠች መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቷም በውጭው ዓለም በሚገኙ ክፍላተ ዓለማት ጭምር መስፋፋቷ በእግዚአብሔር ረድኤት እየቀጠለ ስለሆነ የቤተ ክርስቲያኗ ወገኖች የሆን ውሉደ ክህነትና ውሉደ ክርስቲያን ለሐዋርያዊ ተልዕኮዋ መፋጠን የእምነት ተከታዮቿንም ምእመናን ለመጠበቅ የጋራ አሠራር በያዘ መልኩ በውስጣዊና ውጫዊ አሠራራችንና ግንኙነታችን ሁሉ ከመምሪያዎቹም የሚተላለፉ የሥራ መርሐ ግብሮችን ለማስፈጸም ቃል እንገባለን፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያት የሰጠውን ታላቁን ሐዋርያዊ ተልእኮ ተቀብላ በሐዋርያት አሠረ ፍኖት ተገብታ በባለቤትነት ታስፈጽማለች። ነገር ግን ከእኛ ከአገልጋዮች የእውቀት እና የቁርጠኝነት ማነስ እንዲሁም ከአንዳንዶቻችን ጥቅም ተኮር እንቅስቃሴ የተነሳ ይህንን ታላቅ ተልእኮ ለመፈጸም የተቸገርን ቢሆንም ከዚህ በኋላ በተቻለን መጠን ለመማር፣የተማርነውን ለማስተማር ፣ለማሳመን፣ ከመንጋው ለመቀላቀልና ለመንከባከብ በሚደረገው ማንኛውም ጥረት ከቤተክርስቲያን ጎን ለመቆም ቃል እንገባለን። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ለሀገራችን ለዘመናት ሃይማኖትንና ታሪክን ስታስተምርና ስትዘግብ ብራና ዳምጣ፣ቀለም በጥብጣ፣የራሷን ፊደል ቀርጻ፣ የራሷን ቀመር ቀምራ ለቁጥር የሚያዳግቱ መጻሕፍትን ጽፋለች፤ እየጻፈችም ነው። ነገር ግን አባቶቻችን የጻፏቸው መጻሕፍት በየገዳማቱ ግምጃ ቤት ሆነው ለጉብኝት አገልግሎት ከመዋል ባሻገር ለጥናትና ምርምር ክፍት ተደርገው ለማኅበረሰቡ መድረስ ባለመቻላቻው በዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ በሚገኙ አንዳንድ ወገኖች ቤተክርስቲያንን መጻሕፍት አልባ ከማስመሰሉም በላይ የትምህርት ተቋማቶቻችን የአባቶቻችን ወዝ ባልካቸው መጻሕፍትና ታሪክ አልባ ተሞልተዋል የሚል ስሞታ እንዳለ ተገልጿል፤በመሆኑም ይህንን ችግር ለመቅረፍ ቤተ ክርስቲያን ለምታደርገው ጥረት ጥናትና ምርምር በመሥራት በሁሉም ዘርፍ ከቤተክርስቲያን ጎን ለመቆም ቃል እንገባለን። ቅድስት ቤተክርስቲያን የሁሉ እናት እንደመሆኗ መጠን ዘር ቀለም ጎሳ ሳትለይ እናቴ ብሎ የመጣውን ሁሉ አቅፋ የያዘች፣ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያን ከመሆኗ ባሻገር የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን የምታቀብል መሆኗ የሚታወቅ ነው፤ነገር ግን ከላይ እስከታች የምንገኝ የቤተክርስቲያን ኃላፊዎች በጠረፋማ ሥፍራ የሚኖሩ ሰዎችን ወንጌል ለማስተማር የምናደርገው ጥረት ጅምሩ የሚበረታታ ቢሆንም ፍጹም ሥራ መሥራትን፣ ለሌሎች ዓለማትም መትረፍን የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን በጉባኤው ከተሰጠው ዐውደ ጥናት ተረድተናል፤ በመሆኑም እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የሁሉ እናትነት መላልሶ ለማስተማርና ለመላላክ የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ቃል እንገባለን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ

የአቋም መግለጫ Read More »

ትምህርተ ሃይማኖት

በሊቀ ካህናት ኃይለሥላሴ ዓለማየሁ ወልድ ዋሕድ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና የሌሎች አኃት አብያተ ክርስቲያናት መሠረታዊ እምነት «ተዋሕዶ» ነው። ተዋሕዶን የሚተረጉም ኃይለ ቃልም ፣ «ወልድ ዋሕድ» የሚለው ነው። ወልድ ዋሕድ ለሚለው ሥያሜ መሠረቱ «ቃል ሥጋ ኮነ» የሚለው ቃለ ወንጌል ነው። ዮሐ ፩፥፲፬። ስለሆነም፣ የዚህ ዝግጅት ዐቢይ ርእስ /ዋና ርእስ/ ወልድ ዋሕድ እንዲባል ተመርጦአል።በዚህ ዝግጅት የሚቀርቡ ንኡሳን አርእስተ ትምህርት በየርእሳቸው እየታተቱ የሚቀርቡ ሆኖ ጥናቱ በማስረጃ የተደገፈ እንዲሆን ለማድረግ አዘጋጁ ተገቢውን ጥረት ያደርጋል። ለወጣቱ ግንዛቤ ይሰጣል ተብሎ የሚታመንበት ዝግጅት እንዲሆንም በቀላል አገላለጽ ለማቅረብ ይሞክራል። የትምህርተ ሃይማኖት ምሥጢራዊ ይዘት ከመጽሐፍ ቅዱስና ከአበው ሊቃውንት የትርጉም ዘይቤ እየተገናዘበ ይቀርባል። የዝግጁቱ ዋና ዓላማ፣ ወጣቶች የትምህርተ ሃይማኖት ግንዛቤያቸውን እንዲያሰፉ ማድርግ በመሆኑ፣ የቤተክርስቲያናችንን መሠረተ እምነት ሊያዛቡ ከሚችሉ አዳዲስ አስተሳሰቦችና የግል አስተያየቶች ፍጹም ነፃ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ሆኖ እንዲቀርብ ተገቢው ጥንቃቄ ይደረጋል። ከአንባቢያን ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ሁሉ አስፈላጊው ትኩረት እየተሰጣቸው ተገቢውን መልስ እንዲያገኙ ማድረግ የአዘጋጁ ተቀዳሚ ተግባርና ግዴታ ነው። ይህን ዝግጅት የሚከታተሉ አንባብያንም እያንዳንዱን ኃይለ ቃል፣ በማስተዋል መከታተል፣ ምሥጢሩንና ቁም ነገሩንም በጥንቃቄ መቅሰም ይጠበቅባቸዋል። ጥበብና ማስተዋል የሚገኘው ከእግዚአብሔር ነውና እግዚአብሔር ጥበቡንና ማስተዋሉን ይስጠን። ከእግዚአብሔር አጋዥነትና ረድኤት ውጪ ምንም ምን የሚሆን ነገር ስለሌለ፣ በተለይም ባሕረ ጥበባት የሆነውን ትምህርተ መለኮት ለማቅረብ መሞከር፣ ውቅያኖስን በእንቊላል ቅርፊት… ማለት በመሆኑ፣ የጥበባት አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ጥበቡንና ማስተዋሉን እንዲሰጠን እንለምነዋለን። ትምህርተ ሃይማኖት መለኮታዊ ምሥጢርን የሚያስረዳ እንደመሆኑ ትምህርቱ ጥልቅ፣ ረቂቅና ምጡቅ ነው። ይሁንና በዚህ ዝግጅት ግን እንደ ትምህርቱ ጥልቀትና ምጥቀት ሳይሆን፣ እንደ አዘጋጁ የዕውቀት ውሱንነትና እንደ ተቀባዩ የአእምሮ ስፋት መጠን፣ ግልጽ በሆነ አቀራረብ ባጭር ባጭሩ ይቀርባል። የሃይማኖት ትርጉም  ሃይማኖት ምንድን ነው? ሃይማኖት ወይም እምነት ማለት ማመን፤ መታመን፤ የፈጣሪን ሕልውና ማወቅ፤ ከሃሊነቱን፣ መግቦቱንና ቸርነቱን መረዳት፤ መለኮታዊ እውነታዎችን በትክክል መቀበል፤ በእግዚአብሔር መለኮታዊ ሥራ ፈጽሞ አለመጠራጠር፤ ጥርጥርን ከኅሊና ማስወገድ፤ ስለ ሰማያዊ ሕይወት ጽኑ ተስፋ ማድረግ በሚሉ አገላለጾች ይተረጐማል። ሃይማኖት በረቂቅ ሐሳብ፣ በልብ ሰሌዳነት፣ የሚጻፍ የአእምሮ መጽሔት ነው። ሃይማኖት የኅሊና መሰላል በመሆኑ የዓለምን አስቸጋሪ ዳገት ይወጡበታል። ሃይማኖት የሕይወት መርከብ በመሆኑ ገፊውን ማዕበል ተቋቁመው ባሕሩን ይሻገሩበታል። ንጉሠ ሰማይ ወምድር እግዚአብሔርን ደስ ያሰኙበታል። ዕብ ፲፩፥፮። ልክና መጠን፣ ወሰንና ዳርቻ የሌለው መለኮታዊ ባሕርይ የሚታየው፣ ሕልውናው ከሃሊነቱና መግቦቱ የሚታወቀው በሃይማኖት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ የሃይማኖትን ኃይል ሲተረጉም፦ «እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፣ የማናየውን ነገር የሚያስረዳ ነው።» ይልና በመቀጠልም «ነአምር ከመ ተፈጥረ ዓለም በቃለ እግዚአብሔር። ዓለም በእግዚአብሔር ቃል እንደተፈጠረ እናውቃለን።» ብሎአል። ዕብ ፲፩፥፩-፫። ሃይማኖት ፍጡርን ከፈጣሪው ጋር የሚያገናኝ የኅሊና መሰላል በመሆኑ ፍጡር የሃይማኖት መሰላሉና ድልድዩ ከተሰበረበት ወደ ፈጣሪው መድረስ ይሳነዋል፤ ሌላ መድረሻ ሌላ መንገድ ፈጽሞ የለውም። የሃይማኖት ኃይል ልዩና ዕፁብ ድንቅ የሚያሰኘው፣ ምድራዊ ባለሥልጣን የማይገዛውን የሚገዛ፣ በዓይነ ሥጋ የማይታየውን የሚያሳይ፣ በእጅ የማይዳሰሰውን የሚዳስስ፣ በሥጋዊ ጥበብ የማይመረመረውን የሚመረምር ምሥጢር መሆኑ ነው። ማቴ ፲፮፥፲፯። ልዕልና ነፍስ /የነፍስ ልዕልና/ ክብረ ነፍስ የሚገኘው በሃይማኖት ነው፤ ከሃይማኖት ውጪ የሚሆነው ሁሉ ኃጢአትና በደል ነው። «ወኲሉ ዘይከውን ዘእንበለ አሚን ኃጢአት ወጌጋይ ውእቱ። በእምነት ያልሆነ ሁሉ ኃጢአትም፣ በደልም ነው።» ሮሜ ፲፬፥፳፫። የሚታይና የማይታይ፣ ግዙፍና ረቂቅ፣ ሁሉ ከማይታይ እንደሆነ ማለትም በመለኮታዊ ሥልጣን የተገኘ መሆኑን ያሳውቃል። እግዚአብሔር ለፍጥረቱ ሁሉ መገኘት ምክንያት ሳይሻለት በከሃሊነቱ እምሀበአልቦ ፈጥሮታል። ይህን ማወቅ የሚያስችል ከሃይማኖት ውጪ ሌላ ጥበብ ፈጽሞ የለም። የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወራሽ የመሆን ዕድል የሚያገኘው በሃይማኖት ብቻ ነው። በዓለም ያለውን ሥርዓት በቀላሉ በምሳሌነት ማየት ይቻላል፤ ይኸውም የአንድን ሰው ሃብትና ንብረት ለመውረስ በቀላሉ ባለመብት መሆን የሚቻለው የባለጸጋው ወይም የባለሀብቱ ልጅ ሆኖ መገኘት ሲቻል ነው። በእግዚአብሔር መንግሥትም በሃይማኖት ልጅነትን ካላገኙ የመንግሥቱ ወራሽ መሆን አይቻልም። «እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።» እንዳለ ጌታ በቅዱስ ወንጌል። ዮሐ ፫፥፭። «… ስለዚህ ከእንግዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም። ልጅም ከሆንክ ደግሞ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።» ገላ ፬፥፬-፯።ሃይማኖት በአማኙ ዘንድ ሦስት ነገሮች ተሟልተው እንዲገኙ ግድ ይላል። እነዚህም፦ ፩. ትክክለኛ አረዳድ /እውነት/፪. የልብ ንጽሕና /ቅንነት/፫. መጥዎተ ርእስ፣ ማለትም ጥብዓት፣ ራስን መካድ፣ ራስን አሳልፎ ለሃይማኖት መገዛት ፈቃደ ሥጋን አሸንፎ መስቀልን መሸከም የሚሉ ናቸው። እነዚህ መሠረታዊ ነገሮች ያልተሟሉለት አማኝ ግብዝ ሃይማኖተኛ ይባላል። ማስረጃ «… እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ። አጋንንት ደግሞ ያምናሉ፤ ይንቀጠቀጡማል። …» ያዕ ፪፥፲፬-፳፪። ማር ፭፥፯። ጌታም በቅዱስ ወንጌል እንዲህ ይለናል። «በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።» ማቴ ፯፥፳፩። «ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ፣ እንዲህ አላቸው፤ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፣ ራሱን ይካድ። መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።» ማር ፰፥፴፬። ሉቃ ፱፥፳፫። ማቴ ፲፥፴፰፣ ፲፮፥፳፬። «ወኅሊናሁሰ ለነፍስትነ ሞተ ያመጽእ ላእሌነ፤ ወሕሊናሁሰ ለመንፈስ ሰላመ ወሕይወተ ይሁብነ። የሥጋችን ፈቃድ ሞትን ያመጣብናል /ያስፈርድብናል/ የነፍሳችን ፈቃዱ ግን ሰላምን ከእግዚአብሔር ጋር አንድነትን ድኅነትን ይሰጠናል። እስመ ኅሊናሁ ለነፍስትነ ፀሩ ለእግዚአብሔር ውእቱ። የሥጋችን ፈቃዱ የእግዚአብሔር ጠላቱ ነውና ሞትን ያመጣብናል።» ሮሜ ፰፥፭-፰።የሃይማኖት ዓላማውና ግቡ፣ ሀልዎተ እግዚአብሔርን ማሳወቅና ፍጡር በፈጣሪው ሕግና ትእዛዝ እየተመራ ዘለዓለማዊ ክብር እንዲያገኝ ማድረግ ነው። ማቴ ፳፭፥፴፬። ሀልዎተ እግዚአብሔርን ማወቅ ማለትም ቅድመ ዓለም የነበረ፣ በማዕከለ ዓለም ያለ፣ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር፣ ፈጣሪ፣ መጋቢ ሠራዒ፣ በመለኮታዊ ባሕርዩ ጸንቶ የሚኖር፣ ለመንግሥቱ ሽረት፣ ለሕልውናው ኅልፈት የሌለበት አንድ ፈጣሪ፣ አንድ አምላክ መኖሩን አውቆ ማመን ማለት ነው። «እስራኤል ሆይ ስማ፤ አምላክህ እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው።» ዘዳ ፭፥፬። የማይታይና የማይመረመር፣ የማይገሰስና የማይዳሰስ፣ ሕያወ ባሕርይ እግዚአብሔር በከሃሊነቱ ሁሉን የፈጠረ፣ በመግቦቱ ሁሉን የሚያስተዳድር፣ በቸርነቱ ሁሉን የሚጠብቅ አምላክ በመሆኑ ለፍጥረቱ የሚታወቅበት ገጽታ አንዱ ይኸው ነው። ሁሉን የሚገዛ፣ ሁሉን የሚያስተዳድር በመሆኑ ይቅርታውና መግቦቱ በሁሉም ላይ ነው። «እስመ ቅንየትከ ወምልክናከ ላዕለ ኲሉ፣ ይሬስየከ ትሣሃል ላዕለ ኲሉ። ማለት በሁሉ ላይ ያለ ሥልጣንህና አገዛዝህ ሁሉን ይቅር እንድትል ያደርግሃል።» እንዲል። «… እርሱ በክፉዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።» ማቴ ፭፥፵፭። በከሃሊነቱ ዓለምን የፈጠረ እግዚአብሔር የማይታይ፣ የማይመረመርና የማይዳሰስ፣ እንደሆነ ቢታወቅም፣ ባሕርዩ ከሚገለጽባቸው አያሌ መገለጫዎች ጥቂቶቹን በምሳሌነት መመልከት ይቻላል። እነሱም፦ ፩. ፈጣሪ፪. ከሃሊ፫. ምሉእ፬. ዘለዓለማዊ፭. ቅዱስ፮. ፍጹም፯. ማእምር /አዋቂ/ ጥበበኛ የሚሉ ናቸው። እነዚህን በዝርዝር እንመለከታለን። እግዚአብሔር ፈጣሪ ነው ፈጣሪ ስንል የሌለን ወይም ያልነበረን ነገር በሥልጣኑና በከሃሊነቱ ያስገኘ፣ ዓለምን እምሀበአልቦ /ካለመኖር ወደ መኖር/ የፈጠረ ማለታችን ነው። ዓለምን እምሀበአልቦ ያስገኘ፣ በመለኮታዊ  ሥልጣኑ የሚታየውንና የማይታየውን፣ ግዙፉንና ረቂቁን ፍጥረት ሁሉ የፈጠረ እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ዓለምን /ፍጥረቱን/ ለመፍጠር ምክንያት የሆነው መለኮታዊ ሥልጣኑ ብቻ ነው፤ የፍጥረታት ሁሉ አስገኝ እግዚአብሔር በመሆኑም የፍጥረታት ሁሉ ጌታና ባለቤት እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ዓለምን ፈጥሮ እንዲሁ አልተወውም፤ በመግቦቱ ይጠብቀዋል፤ ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ እግዚአብሔር ብቻ በመሆኑና በመለኮታዊ ሥልጣኑ መሳይ ተወዳዳሪ ስለሌለውም እግዚአብሔር አንድ አምላክ ይባላል። እግዚአብሔር ዓለሙን ሲፈጥር፣ ይሁን ብሎ በቃሉ፣ በመለኮታዊ ሥልጣኑና በከሃሊነቱ ፈጠረው እንጂ ፍጥረታትን ለማስገኘት ሌላ አፍአዊ ምክንያት አላስፈለገውም። እንደዚህ ያለ መለኮታዊ ሥልጣን በሰማይም በምድርም ስለሌለ፣ እግዚአብሔር ብቻ ፈጣሪ እንዲባል ያደርገዋል። «ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቊጥር የሚያወጣ እርሱ ነው። ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል። በኃይሉ ብዛትና በከሃሊነቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።» ይላል የእግዚአብሔር ቃል። ኢሳ ፵፥፳፮። በእግዚአብሔር ረቂቅ ሥልጣንና ከሃሊነት የተፈጠረ ፍጥረት ሁሉ ሥርዓት ተሠርቶለት፤ ወሰን ተበጅቶለት ይኖራል። ከተሠራለት ሥርዓት አይወጣም፤ ከተደነገገለት ወሰን አያልፍም። ለይኩን

ትምህርተ ሃይማኖት Read More »

Scroll to Top