በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የሀገረ ስብከቱ ግብና ተግባራት

ሀገረ ስብከቱ የሚያከናውናቸው ተግባራት

ሀገረ ስብከቱ የሚያከናውናቸው ተግባራት የሀገረ ስብከቱን ዓላማ  ከግብ ለማድረስ በቀጣዩ አሥር ዓመት ሀገረ ስብከታችን የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡፡ ፩. የሀገረ ስብከቱን ሙሉ ስታስቲካዊ መረጃዎችን አስባስቦና  አጠናቅሮ ይይዛል ፪.ስብከተ ወንጌል በሁሉም የሀገረ ስብከቱ ወሰን እንዲስፋፋ ያደርጋል፡፡ ፫. ሁለ ገብ የአብነት  ት/ቤቶችን በቅደም ተከተል ያቋቁማል ያደራጅማል ፬. በሀገረ ስብከቱ ክልል ውስጥ ያሉት ገጠር አብያተክርስቲያናት በተለያየ ምክንያት የተዘጉ እንዲከፈቱ አገልጋይ እጥረት ያለባቸው እንዲሟላላቸው ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል፡፡ ፭. አድባራቱን በመንፈሳዊና በማህበራዊ ተግባር እንዲተባበሩ ያደርጋል፡፡ ፮.የሰንበት ት/ቤት ባልተቋቋመባቸው አብያተ ከርስቲያናት የማቋቋም ሥራ ይሰራል በተቋቋመበትም ቦታ የማጠናከር ሥራ በትጋት ይሰራል፡፡ ፯.በሀገረ ስብከታችን በሚነገሩ ሦስት ቋንቋዎች ማለትም በጌዴኡፋ፣ኮሬቲና ቡርጂ ቋንቋዎች  የትርጉም ሥራ ፣መንፈሳዊ መጻህፍትን ፣መዝሙራትንና ወዘተ የመተርጎም  ሥራ ይሰራል፡፡ ፷.በሀገረ ስብከቱ ወሰን ውስጥ ያሉት አብያተክርስቲያናት በሀብትና ንብረት ራሳቸውን እንዲችሉ በኢኮኖሚ  ያስተሳስራል፡፡ ፱.ሁሉም በሀገረ ስብከቱ ያሉ አብያተክርስቲያናት ይዞታ ማረጋገጫ እንዲኖራቸው ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል፡፡ ፲. የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን በመዘርጋትና በማዘመን ለውጥ ለማምጣት ይሠራል፡፡ ፲፩. በሀገረ ስብከታችን ከሀያና ከዚያ ዓመት በላይ ቤተክርስቲያን አገልግለው ሥጋዊ  አቅማቸው የደከመ ካህናት  በጡረታ ከማግለል ይልቅ እስከ እረፍተ ዘመናቸው በጸሎት እንዲያገለግሉ በእንክበብካቤ እንዲያዙ ይሰራል ፣በጣም አቅመ ደካማ ሆነው የሚረዳቸው ቤተሰብ ሳይኖራቸው ሲቀር ቤተክርስቲያን ልዩ የእንክብካቤ ማዕከል (Rest Home) በማዘጋጀት እስከ ዓረፍተ ዘመናቸው ድረስ በእንክብካቤ እንዲያዙ ለማድረግ ጥረት ያደርጋል፡፡ ፲፪.የቀብር ቦታዎችን በዘመናዊ መልኩ በማደራጀት በጽዳትና በክብር እንዲያዙ ያደርጋል፡፡

ሀገረ ስብከቱ የሚያከናውናቸው ተግባራት Read More »

የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ተግባርና ኃላፊነት

የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ተግባርና ኃላፊነት ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሆኖ፡- ፩. በዋናነት በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ክልል ውስጥ ያለችውን ቤተክርስቲያን በበላይነት ይመራል ይጠብቃል፡፡ ፪. በሀገረ ስብከት ውስጥ ለሚገኙ ካህናትና ምዕመናን መንፈሳዊ አባትና መሪ እንደመሆኑ መጠን ሃይማኖታቸውን ፣ሥርዓተ ቤተክርስቲያናቸውንና ኦርቶዶክሳዊ ትውፊታቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ ብርቱ ጥበቃ ያደርጋል ፣መመሪያና ቡራኬ ይሰጣል፡፡ ፫. በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ ስድስትና ሰባት ፣በህገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 54 ተራ ቁጥር አራት በተደነገገው መሠረት በሥነ ምግባራቸው የተመሰገኑትንና በትምህርት ደረጃቸው ብቁ የሆኑትን ቀሳውስትና ዲያቆናት በመሾም በሀገረ ስብከቱ ለሌላው አርአያ የሚሆኑ ካህናት ማፈፍራት፡፡ ፬. በሀገረ በስብከቱ ወሰን ውስጥ ማንኛውም መዋቅራዊ ደረጃውን ጠብቆና አጠናቆ የቀረበን የቤተክርስቲያን ጉዳይ በተመለከተ ከሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ጋር  በይግባኝ ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ  ይሰጣል እንደ ጉዳዩ ክብደት  ለቅዱስ ሲኖዶስ አስተላልፎ የመጨረሻውን ውሳኔ እንዲያገኝ ያደርጋል፡፡ እንደ አስፈላጊነቱም ምህረትና ይቅርታ ያደርጋል፡፡ ፭. በመንበረ ጵጵስናው ዋና ከተማ መርሐ ግብር በማውጣት እንደ ዕድሜአቸውና ዕውቀታቸው በመከፋፈል እንደ ሁኔታው  ሰብስቦ ያስተምራል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ተግባርና ኃላፊነት Read More »

የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር

የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር ፩. የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ተጠሪነቱ ለሊቀ ጳጳሱ ይሆናል ፪. ከበላይ የሚመጡ ውሳኔዎች፣መመሪያዎችን እና የሀገረ ስብከቱ የአስተዳደር ጉባኤ ውሳኔዎችን በየደረጃው ለሚገኙት ለበታች ላሉ መዋቅሮች በወቅቱ እንዲደርሱ ያደርጋል አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡ ጥፋት ሲፈጸምም ከሊቀጳጳሱ መመሪያ እየተቀበለ እንደጥፋቱ መጠን የቃልና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፡፡ ፫. የሀገረ ስብከቱን አኃዛዊ መረጃዎች/ስታትስቲክስ/ የበጀት ዓመቱን የሥራ ክንውን እና የፋይናንስ ሪፖርት ለመንበረ ጵጵስናው ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ በወቅቱ ያቀርባል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር Read More »

የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ ሥልጣንና ተግባር

የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ ሥልጣንና ተግባር ፩. የሀገረ ስብከቱን ጠቅላላ የጽህፈት ፣የሂሳብና የንብረት አጠባበቅ ሥራዎችን እንደዚሁም የልዩ ልዩ ክፍሎችን የሥራ ሂደት በቅርቡ እየተከታተለ በመቆጣጠር ይሠራል ያሠራል፡፡ ፪. የወረዳ ቤተክህነቶች ለሀገረ ስብከቱ ገቢ የሚያደርጉትን ክፍያ በወቅቱ ገቢ መሆኑን ይከታተላል፡፡ ፫. በሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኙ የምዕመናን አኃዛዊ መረጃዎች እንዲያዙ ያደርጋል፡፡ ፬. የሀገረ ስብከቱን የሥራ አፈጻጸምና የሒሳብ ይዘት መግለጫ ለመጭው ዓመት ከሚፈቅደው ዓመታዊ የገንዘብ ድልድል (በጀት) ጋር አዘጋጅቶ በሥራ አስኪያጁ አማካኝነት ለአስተዳደር ጉባኤ ያቀርባል፡፡ ፭.የሀገረ ስብከቱን የልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች የሚቀርብለትን የሥራ ክንውን እንዲሁም አኃዛዊ መረጃዎችን በማጠቃለል በየሦስት ወሩ ለአስተዳዳር ጉባኤ ሪፖርት ያቀርባል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ ሥልጣንና ተግባር Read More »

የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ሥራና ኀላፊነት

የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ሥራና ኀላፊነት ፩. የእግዚአብሔርን ወንጌለ መንግስት መስበክና ትምህርቱንም ማስፋፋት ፪. ምዕመናን በሚረዱት እና በሚያውቁት ቋንቋ ትምህርተ ወንጌል እንዲሰጥ ተከታዮች እንዲበዙና በሰበካ ጉባኤም እንዲመዘገቡ  በማድረግ ሐዋርያዊ ተልእኮውን ይፈጽማል ፫. የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በቅዳሴ ዕለት በክብረ በዓላት በመንፈሳዊ ጉባኤያት በሀዘንና በደስታ ስፍራዎች እንዲሰጥ ያደርጋል ተፈጻሚነቱን ይከታተላል ፬. ያለ ፈቃድ እንሰብካለን እናስተምራለን የሚሉ ግለሰቦችን መቆጣጠር ወደ ህጋዊ መስመር እንዲመጡ ማድረግ ፭. በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ሰባኪያነ ወንጌልን ማብቃት ማሰልጠን ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ እና  በበጎ ፈቃድ የሚያገለግሉ ሰባኪያነ ወንጌልን ማስልጠን ህጋዊ ፈቃድ እንዲያገኙ ማድረግና መከታተል ፮.የስብከት ኬላዎችን በማቋቋም የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ምዕመናን በሚሰሙት ቋንቋ እንዲሰበክ ያደርጋል፡፡ ፯. ለምዕመናን፣ለሰንበት ት/ቤት አባላትና ለካህናት ምቹ ሁኔታዎችን በማመቻቸት የትምህርተ ሃይማኖት ኮርሶችን ይሰጣል እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡ ፰. ከቤተክርስቲያን እውቅና ውጪ የሆኑ የህትመት የድምጽና የምስል ውጤቶችን  እንዳይሰራጩ  ይቆጣጠራል  ተፈጻሚነቱን  ይከታተላል፡፡ እንዲሁም የተፈቀደላቸው  ለምዕመናን እንዲሰራጩ ያደርጋል፡፡

የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ሥራና ኀላፊነት Read More »

የሀገረ ስብከቱ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ክፍል ተግባራና ኀላፊነት

የሀገረ ስብከቱ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ክፍል ተግባራና ኀላፊነት ፩. በሀገረ ስብከቱ ስር ባሉት አብያተ ክርስቲያናት  በቃለ ዓዋዲው መሰረት የተመረጡ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤያት  የአገልግሎት  ጊዜያቸው  ሲያበቃ  አዳዲስ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤያት እንዲመረጡ ማድረግ፤ ፪. አዲስ ለሚመረጡ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር  ጉባኤ አባላት ስለ ቃለ ዓዋዲው ስልጠና መስጠት፤ ፫. አዳዲስ በሚሰሩ አቢያተክርስቲያናት የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ማቋቋም ፤ ፬. በሀገረ ስብከቱ ስር ባሉ አብያተ ክርስቲያናት  በቃለ ዓዋዲው መሰረት የተመረጡ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤያት የሚጠበቅባቸውን ተግባራት እንዲፈጽሙ ማገዝ እና መከታተል፤ ፭. ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃ በአጥቢያ፤በወረዳ ቤተክህነት እና በሀገረ ስብከት  እንዲመዘገብ እና እንዲደራጅ ማድረግ፤

የሀገረ ስብከቱ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ክፍል ተግባራና ኀላፊነት Read More »

የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ክፍል ተግባራትና ኀላፊነት

የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ክፍል ተግባራትና ኀላፊነት ፩.ስለ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የሚወጡ ደንቦችን እና መመሪያዎችን  እየተከታተለ ለየአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ያስተላልፋል አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል፤ ፪.የሰንበት ትምሀርት ቤት ባልተቋቋመባቸው አድባራት እና አጥቢያ አብያተክርስቲያናት  ያቋቁማል፤ይከታተላል፤ ፫. በተቋቋመባቸው አድባራት እና አጥቢያ አብያተክርስቲያናት ያሉ የሰንበት ትምህርት ቤቶች በቃለ ዐዋዲው መሰረት መደራጀታቸውን፤በማእከል ደረጃ የወጣውን ስርዓተ ትምህርት መተግበራቸውን ይከታተላል ድጋፍም ያደርጋል፤ ፬. ከሀገረ ስብከቱ ሌሎች ክፍላት  ጋር በመተባበር በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ተምረው የማስተማር ብቃት ያላቸውን ተተኪ የሰንበት ትምህርት ቤት መምህራንን ያሰለጥናል ፤ ፭. በየደረጃው የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት እንዲቋቋም በተወሰነው መሠረት በሀገረ ስብከት እና በወረዳ ደረጃ እንዲቋቋም ያደርጋል፤ይከታተላል፤ ፮.የቤተክርስቲያኒቱን ደንብና ሥርዓት የጠበቁ መዝሙሮችን እንዲያጠኑ ያደርጋል ፤ያስደርጋል፤

የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ክፍል ተግባራትና ኀላፊነት Read More »

የሀገረ ስብከቱ ዕቅድና ልማት ክፍል ሥራና ኃላፊነት

    የሀገረ ስብከቱ ዕቅድና ልማት ክፍል ሥራና ኃላፊነት ፩.የሀገረ ስብከቱን የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ያወጣል አፈጻጸሙንም ለአስተዳደር ጉባኤ ያቀርባል ፪. በሀገረ ስብከቱ ሥራ የአብያተ ክርስቲያናት የይዞታ ቦታዎች ከመመሪያ ወጪ የበላይ አካል ሳይፈቅድ ለሦስተኛ ወገን እንዳይሰጡ ይቆጣጠራል ይከታተላል ፫.የሥራውን ውጤት በሚመለከት በየሦስት ወር ለአስተዳር ጉባኤ ሪፖርት ያቀርባል

የሀገረ ስብከቱ ዕቅድና ልማት ክፍል ሥራና ኃላፊነት Read More »

የሀገረ ስብከቱ የሒሳብ ክፍል ሥራና ኃላፊነት

የሀገረ ስብከቱ የሒሳብ ክፍል ሥራና ኃላፊነት ፩.የሂሳብ መዛግብትን አሟልቶ ገቢ ወጪ በህጋዊ ደረሰኝ እየሰራ በየወሩ ከወጪ ቀሪ ያለውን ያረጋግጣል በየወሩ ለጽ/ቤት መጨረሻ ሪፖርት ያቀርባል፡፡ ፪.የተበጀተውን በጀት ለታሰበለት ዓላማ መዋሉን ይከታተላል፡፡ ፫.የሒሳብ ሰነዶችንና ቼኮችን  በጥንቃቄ በመያዝ በተፈለገ ጊዜ ለኦዲት ያቀርባል፡፡ ፬.ከወረዳ እስከ አጥቢያ አብያተክርስቲያናት ድረስ በህጋዊ ደረሰኝ የሚሠራ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ፭. በጀት በሚደለደልበት ጊዜ ለሚደለደለው በጀት በቂ ገንዘብ መኖሩን ያረጋግጣል፡፡ ፮.የበጀት ዓመቱ ከማለቁ ከሁለት ወራት በፊት የየወሩን ገቢ ገምግሞ የተከታዩን ዓመት በጀት በመሥራት ዝርዝርሩን ለአስተዳደር ጉባኤ ያቀርባል፡፡

የሀገረ ስብከቱ የሒሳብ ክፍል ሥራና ኃላፊነት Read More »

የሀገረ  ስብከቱ  የገንዘብ  ቤት  ሥራና  ኃላፊነት

    የሀገረ  ስብከቱ  የገንዘብ  ቤት  ሥራና  ኃላፊነት ፩.ገንዘብን በህጋዊ ደረሰኝ (ካርኒ) ይቀበላል፡፡ ፪.ለማንኛውም የገንዘብ ወጪ ህጋዊ ትዕዛዝ ሲደርሰው ብቻ ክፍያ ይፈጽማል፡፡ ፫.ገቢና ወጪውን በተለየ በተዘጋጀ የገቢና የወጪ መዛግብት ላይ ይመዘግባል እንዲሁም ሂሳቡን በጥንቃቄ መዝግቦ ይይዛል፡፡ ፬.በየወሩ መጨረሻ በጠቅላላ የገባውና የወጣውን ገንዘብ ልክ ከወጪ ቀሪውን ከሂሳብ ክፍሉ መዛግባት ጋር ያመሳክራል፡፡

የሀገረ  ስብከቱ  የገንዘብ  ቤት  ሥራና  ኃላፊነት Read More »

Scroll to Top