በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

አሥራ ሰባት ኢ-አማንያን በብፁዕ አቡነ ገሪማ ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አገኙ!

ኤክቱስ ኅዳር 07/2019 ዓ.ም

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት በይርጋጨፌ ወረዳ ቤተ ክህነት በገርቦታ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል ላይ የቅድመ ጥምቀት ትምህርት ሲማሩ የነበሩ አሥራ ሰባት ኢ-አማንያን ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል።

አሥሩ አዳዲስ አማንያን ሲሆኑ ሰባቱ ደግሞ ከዚህ በፊት ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው የነበሩ በመሆናቸው ሥርዓተ ቄደር ተፈጽሞላቸዋል።

በሀገረ ስብከቱ ከሥሩ በሚገኙ በስድስቱም ወረዳ ቤተ ክህነት የክርስቶስን የመንግሥቱን ወንጌል ከማስፋፋትና ያላመኑትን ከማሳመን ረገድ በርካታ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

Scroll to Top