ኤክቱስ ኅዳር 01/2019 ዓ.ም
የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ዲላ ማዕከል ጋር በመተባበር በመንፈሳዊ ትምህርት ላይ ለሚገኙ ለአንዲዳ የአዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት ደቀ መዛሙርት አጠቃላይ የጤና ምርመራ ተደረገ።
በመርሃግብሩ ላይ የሀገረ ስብከቱ የመንፈሳዊ ትምህርትና የካህናት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ፣ መምህራን እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ምርመራው የተከናወነው ማኅበረ ቅዱሳን ዲላ ማዕከል አባላት በሆኑት የጤና ባለሙያዎች አማካኝነት ሲሆን፤ የደቀ መዛሙርቱን ጤንነት አስቀድሞ በመጠበቅ ጤናማ የማስተማርና መማር ሂደት እንዲኖር ለማስቻል የተማሪዎችን አጠቃላይ የጤና ሁኔታ የሚመረምር ቡድን ተሰማርቷል። በዚህም መሰረት ለተማሪዎቹ አስፈላጊው የሕክምና ምርመራ ተደርጎላቸዋል።
