በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ዘመናዊውን የሀገረ ስብከት ዳታቤዝ ለማጠናቀቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያዩ!

ኤክቱስ ጥቅምት 04/2019 ዓ.ም

የሀገረ ስብከቱን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመንና መረጃዎችን በተደራጀ መንገድ ለመያዝ እየበለጸገ የሚገኘው የሀገረ ስብከቱ ዳታቤዝ (Database) ግንባታ ወደመጠናቀቅ መሄዱን ተከትሎ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ከቴክኖሎጂው አልሚ ከሆነው «AYO TECH» ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር እና በአዲስ አበባ ከሚገኘው የመማክርት ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት አደረጉ።

በዚሁ የምክክር መርሃግብር ላይ ለ፵፭ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የመጡ የሀገረ ስብከቱ ልዑካን እና በአዲስ አበባ የሚገኙት የሀገረ ስብከቱ መማክርት ጉባኤ አባላት ተገኝተውል።

በውይይቱ ወቅት የዳታቤዙ አጠቃላይ የመልማት ሂደትና የመጨረሻ ደረጃዎች የቀረቡ ሲሆን ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ ሥራ ሲጀምር የሀገረ ስብከቱን የመረጃ ልውውጥ፣ የአገልጋዮችና የምእመናን ምዝገባ እንዲሁም አስተዳደራዊ ተግባራት ይበልጥ የተቀላጠፉና ግልጽነት ያላቸው እንደሚያደርጋቸው ተገልጿል።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ለሥራው መሳካት ያለ ምንም ክፍያ አስተዋጽኦ ላደረጉት ለAYO TECH የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ለመማክርት ኮሚቴው አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አያይዘውም የቤተክርስቲያኗን አገልግሎት ከዘመኑ የቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር በማጣጣም ረገድ የዳታቤዙ መጠናቀቅ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖረው በመጠቆም በቀጣይም ከላይኛው መዋቅር በተናበበ፣ የመረጃ ደኅንነትንና አስተማማኝነትን ባረጋገጠ መልኩ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ እንዲገባ አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የመማክርት ኮሚቴውና የቴክኖሎጂ ድርጅቱ ተወካዮች የዳታቤዙን ሥራ የመጨረሻ ማስተካከያዎች በማጠናቀቅ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ለማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸው የጋራ ውይይቱ በብፁዕነታቸው ጸሎት ተጠናቋል።

Scroll to Top