በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ለ40 የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ካህናት የደመወዝ ድጋፍ ተደረገ!

ኤክቱስ መስከረም 29/2019 ዓ.ም

በጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙና ድጋፍ ለሚሹ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት የሚደረገው የአንድ ዓመት የካህናት ደመወዝ ድጋፍ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ መሆን እንደጀመረ ተገለጸ።

ይህ ድጋፍ ሊደረግ የቻለው በብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አባታዊ ጥሪ መሠረት ሲሆን ቀደም ሲል በመምህር ዘመድኩን አስተባባሪነት ለ56 አብያተ ክርስቲያናት ለደመወዝ ድጎማ፣ ለአብያተ ክርስቲያናቱም ደግሞ ጧፍ፣ ዕጣን እና ዘቢብ ከተገባው ቃል መካከል በአሁኑ ወቅት ገቢ ተደርጎ ለተጠናቀቁ ለ40 ለተቸገሩ እና ለተጎዱ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ለእያንዳንዳቸው ለአንድ ካህን ወርሃዊ ደመወዝ የሚሆን 4,000 (አራት ሺህ) ብር ድጋፍ የተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ የተመደበው በጀት አብያተ ክርስቲያናቱ ለአንድ ዓመት ያህል የካህናት እጥረት ሳይገጥማቸው አገልግሎታቸውን በጥንካሬ እንዲቀጥሉና መንፈሳዊ እንቅስቃሴያቸው እንዳይደናቀፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተገልጿል።

ሀገረ ስብከቱ ይህ ድጋፍ እውን እንዲሆን ላስተባበረው የቤተ ክርስቲያን ልጅ ለሆነው ለመምህር ዘመድኩን በቀለ እንዲሁም ጥሪውን ተቀብለው ለተባበሩት ምዕመናን በሙሉ የላቀ ምስጋናውን አቅርቧል። ድጋፉ ከጥቅምት ወር ጀምሮ እንዲከፈል በቀጥታ ለየአብያተ ክርስቲያናቱ ገቢ የተደረገ ሲሆን ሀገረ ስብከቱ አፈጻጸሙን በበላይነት እንደሚከታተል ታውቋል።

Scroll to Top