በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

በጨለለቅቱ ከተማ የመጀመርያ ዙር የወጣቶች መርሃግብር ተካሄደ!

ኤክቱስ ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም

በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አባታዊ መመሪያ መሠረት በኮቾሬ ገደብና ጮርሶ ወረዳዎች ቤተ ክህነት በጨለለቅቱ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ወጣቶች በሥነ ምግባር ታንጸው በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲያግዛቸው የሚረዳቸው ወርኃዊ የወጣቶች መርሃግብር ተከናውኗል።

በዕለቱ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት እና አገልግሎት በሚል ርእስ ሥልጠና ተሰጥቷል።

በመርሃግብሩ የአድባራቱ አስተዳዳሪ በኩረ ትጉሃን አእምሮ ሙሉ፣ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስተዳደር አካላት፣ ካህናትና ምዕመናን ተገኝተዋል።

Scroll to Top