በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

፫ኛው ሀገረ ስብከት አቀፍ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቀቀ!

ኤክቱስ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም

በብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ርእሰ መንበርነት በዲላ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ሲካሄድ የዋለው ፫ኛው ሀገረ ስብከት አቀፍ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተጠናቋል።

በጉባኤው የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ የ2018 ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸም አጠቃላይ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በመቀጠልም ቀሲስ ጤናው እንዳላማው የሀገረ ስብከቱን የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ለጉባኤው አቅርበዋል።

በቀረቡት የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ከታዳሚዎች በርካታ ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና ጠቃሚ ሀሳቦች የቀረቡ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎች በቂና አጥጋቢ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

በተጨማሪም በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ ሀገረ ስብከቱን በበርካታ ነገሮች ሲያግዙና ሲደግፉ ለቆዩት “ማኅበረ አቡቀለምሲስ” ልዩ የእውቅና ምስክር ወረቀት የተሰጣቸው ሲሆን በ2018 ዓ.ም ከፍተኛ የሥራ አፈጻጸም ላመጡ የወረዳ ቤተ ክህነቶች የምሥጋና የምስክር ወረቀትና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በመጨረሻም ጉባኤው በ2019 ዓ.ም የተቀመጡትን አቅጣጫዎች ሙሉ በሙሉ በመቀበልና የጋራ አቋም በመያዝ በብፁዕነታቸው ቃለ በረከትና ጸሎት ፍጻሜ አግኝቷል።

Scroll to Top