ኤክቱስ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም
ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ እርስ በእርስ ተጣልተው የነበሩ ምዕመናን ወደ ዐውደ ምሕረት በመውጣት አስታረቁ።
ይህ የእርቅ ሥነ-ሥርዓት የተከናወነው የጻድቁ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን የእረፍት በዓል ምክንያት በማድረግ በኮቾሬ፣ ገደብና ጮርሶ ወረዳዎች ቤተ ክህነት በገደብ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ለሦስት ቀናት በተዘጋጀው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ነው።
በዕለቱ ምዕመናኑ በሙሉ ፈቃዳቸው ወደ ዐውደ ምሕረት በመውጣት የቆየ ቅሬታቸውን እና ጥላቸውን በመተው ይቅር ተባብለዋል። ይህም ክስተት የዕለቱ ትምህርተ ወንጌል ዋና ፍሬ ሆኖ መሆኑንም ገልጸዋል።
