በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

“ዛሬም ልጆቻችንን እንደ ቅዱስ ቂርቆስ ዓይነት እንዲሆኑ ልንሠራባቸው ይገባል”ብፁዕ አቡነ ገሪማ

ኤክቱስ ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በጥንታዊውና በታሪካዊው በጪጩ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የሐምሌ ገብርኤል በዓል ላይ ለምዕመናን አባታዊ ቃለ ምዕዳን አስተላልፈዋል።

ብፁዕነታቸው በንግግራቸው የቅዱስ ቂርቆስን እና የቅድስት ኢየሉጣን ታሪክ በማንሳት የልጆች አስተዳደግ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል። እንዲሁም “ዛሬም ልጆቻችንን እንደ ቅዱስ ቂርቆስ ዓይነት እንዲሆኑ ልንሠራባቸው ይገባል” ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም በበጎ ሥነ-ምግባርና በሃይማኖት ኮትኩቶ በማሳደግ በዚህም ዘመን እንደ ቅዱስ ቂርቆስ ያሉ በሃይማኖታቸውና በበጎ ምግባር የጸኑ ልጆችን ማፍራት እንደሚቻል ገልጸዋል።

Scroll to Top