በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

በጉባኤው ለምዕመናን የንሥሐ አባት የማስያዝ መርሃግብር ተከናወነ!

ኤክቱስ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም

​በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በተካሄደው ዐቢይ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ምዕመናን የምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ተካፋይ እንዲሆኑ ለማስቻል የንሥሐ አባት የሌላቸውን ምዕመናን የመመዝገብ ሥራ ተከናውኗል። ይህ ልዩ መርሃ ግብር የጉባኤውን ዋና ዓላማ መነሻ በማድረግ ምዕመናን በንሥሐ ሕይወት ታንጸው ወደ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ እንዲቀርቡ በተግባር ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

​በዚሁ መሠረት በጉባኤው በርካታ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን የንሥሐ አባት እንዲኖራቸው እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን ይህም የሕዝቡን መንፈሳዊ ሕይወት ለመለወጥና ምዕመናንን የምሥጢራት ተካፋይ ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት ይበልጥ እንደሚያጠናክር ተገልጿል።

Scroll to Top