በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

​ብፁዕ አቡነ ገሪማ የሀገረ ስብከቱን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ገለጻ አቀረቡ!

ኤክቱስ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለተዘጋጀው ጉባኤ ከአዲስ አበባ ለመጡት መምህራንና ዘማርያን ስለ ሀገረ ስብከቱ አሁናዊ ሁኔታ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የሀገረ ስብከቱ ታሪካዊ ዳራ፣ አጠቃላይ መዋቅራዊ መረጃዎች እንዲሁም በአሁኑ ወቅት እየተሠሩ ያሉ መንፈሳዊና ተቋማዊ ሥራዎች ለእንግዶቹ ቀርበዋል።

​ብፁዕነታቸው ባቀረቡት ገለጻ ሀገረ ስብከቱ በአገልግሎት እንቅስቃሴው ላይ እያጋጠሙት ያሉትን ወቅታዊ ተግዳሮቶች በጥናት ላይ ተመስርተው ያመለከቱ ሲሆን፤ ከችግሮቹ ጎን ለጎንም መፍትሔ ሊሆኑ የሚችሉ ስልታዊ የሃሳብ አማራጮችንና የቀጣይ የተግባር አቅጣጫዎችን በፕረዘንቴሽኑ አካተው አብራርተዋል።

​በተያያዘ ተጋባዥ እንግዶቹ በሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት በሥራ ላይ የሚገኘውን የዶሮ ልማት ፕሮጀክት፣ አዲሱን የመንበረ ጵጵስና ሕንፃ ግንባታ ሂደት እንዲሁም በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እየተከናወኑ ያሉ የግብርና የልማት ሥራዎችን ተገኝተው ጎብኝተዋል። የተደረገው የመስክ ምልከታ የሀገረ ስብከቱን ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ በተግባር ያሳየ እንደነበር ተመልክቷል።

Scroll to Top