በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

የሰኔ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል ብፁዕነታቸው በተገኙበት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተከበረ!

ኤክቱስ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም

የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

በዕለቱ በደብሩ መሠረተ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያም ለዕለቱ የሚስማማ ያሬዳዊ ዝማሬ ያቀረቡ ሲሆን በደብሩ ለሚሠሩ የልማት ሥራዎች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር በሀገረ ስብከቱ የሰበካ ጉባኤና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ክፍል ኃላፊ በመልአከ ብርሃን ዳንኤል ነቢዩ ተከናውኗል።

የዕለቱን ትምህርት ብፁዕነታቸው እጅግ በጥልቀት ያስተማሩ ሲሆን ታሪኩን በሰፊው በመዘርዘር ምዕመናን ራሳቸውን እንዴት ከፈተና መጠበቅ እንዳለባቸው እና መንፈሳዊነታቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው አስተምረዋል።

በተጨማሪም ብፁዕነታቸው ምዕመናን በቅዳሴ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲሄዱ በአጽንዖት አሳስበው በጸሎት ፈጽመዋል።

በመርሃግብሩ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ብርሃኑ ክፍሌ፣ የሀገረ የመንፈሳዊ ትምህርትና የካህናት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ዮሐንስ ምሕረቱ፣ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጠበብት መሠረት ይልማ፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ካህናትና ምዕመናን ተገኝተዋል።

Scroll to Top