በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት

ብፁዕ አቡነ ገሪማ ለ፭ ዲያቆናት ማዕረገ ቅስና ሰጡ!

ኤክቱስ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም

ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዛሬው ዕለት በዲላ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለቅስና የሚያበቃ መንፈሳዊ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ ለ፭ ዲያቆናት የቅስና ማዕረግ ሰጥተዋል።

በዛሬው ዕለት ማዕረገ ቅስናን ከተቀበሉት ፭ ዲያቆናት መካከል ፬ቱ በአንዲዳ የአዳሪ የአብነት ትምህርት ቤት መንፈሳዊ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው።

ብፁዕነታቸው በመጨረሻም የተቀበሉትን አደራ በሥነ-ምግባር ጠብቀው እንዲኖሩ እና ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ አባታዊ ምክራቸውን ለግሰዋል።

Scroll to Top